የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
2.58K subscribers
6.1K photos
67 videos
60 files
1.7K links
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
Download Telegram
#ጥር 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

1.ቅዱስ እስጢፋኖስ ቀዳሜ ሰማዕት (ሊቀ ዲያቆናት)
2.ቅዱሳን ሰማዕታተ አክሚም
3.ቅዱሳን ዲዮስቆሮስ ወሰከላብዮስ
4.ቅዱስ ለውንድዮስ ሰማዕት
5.አባ መቃርስ ሊቀ ዻዻሳት

#ወርኀዊ በዓላት

1.ልደታ ለማርያም ድንግል እግዝእትነ
2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
3.ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
4.ቅዱስ ሚልኪ ትሩፈ ምግባር
5.ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላእክት
​​እንኳን ለቀዳሚ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሰን።

#ጥር_1

💠የቅዱስ እስጢፋኖስ የልደቱም የዕረፍቱም ቀን ነው።

#የስሙ_ትርጉም

💠 ወደብ፣ ጸጥታ ማለት ነው።

#ለምን_ሊቀ_ዲያቆናት_ተባለ?

💠 በሐዋርያት እጅ ከተሾሙት 7 ዲያቆናት ውስጥ የሁሉም አለቃ ስለሆነ።

#ለምን_ቀዳሚ_ሰማዕት_ተባለ ?

💠 ከጌታችን ዕርገት በኋላ ስለ ጌታችን መውረድ መወለድ መስክሮ ስለሞተ።

#ሰማዕትነት_እንዴት_ተቀበለ ?

💠 ሐዋ ም 6 ቁ 8 ጀምሮ እንዲህ ይላል

እስጢፋኖስም ጸጋንና ኃይልን ተሞልቶ በሕዝቡ መካከል ድንቅንና ታላቅ ምልክትን ያደርግ ነበር። የነፃ ወጪዎች ከተባለችው ምኵራብም ከቀሬናና ከእስክንድርያም ሰዎች ከኪልቅያና ከእስያም ከነበሩት አንዳንዶቹ ተነሥተው እስጢፋኖስን ይከራከሩት ነበር፤ ይናገርበት የነበረውንም ጥበብና መንፈስ ይቃወሙ ዘንድ አልቻሉም። በዚያን ጊዜ በሙሴ ላይ በእግዚአብሔርም ላይ የስድብን ነገር ሲናገር ሰምተነዋል የሚሉ ሰዎችን አስነሡ። ሕዝቡንና ሽማግሌዎችንም ጻፎችንም አናደዱ፥ ቀርበውም ያዙት ወደ ሸንጎም አመጡትና። ይህ ሰው በዚህ በተቀደሰው ስፍራ በሕግም ላይ የስድብን ነገር ለመናገር አይተውም፤ ይህ የናዝሬቱ ኢየሱስ ይህን ስፍራ ያፈርሰዋል ሙሴም ያስተላለፈልንን ሥርዓት ይለውጣል ሲል ሰምተነዋልና የሚሉ የሐሰት ምስክሮችን አቆሙ። በሸንጎም የተቀመጡት ሁሉ ትኵር ብለው ሲመለከቱት እንደ መልአክ ፊት ሆኖ ፊቱን አዩት።

ይልና ወረድ ብሎ ም 7 ቁ 51 ላይ እንዲህ ይላል

እናንተ አንገተ ደንዳኖች ልባችሁና ጆሮአችሁም ያልተገረዘ፥ እናንተ ሁልጊዜ መንፈስ ቅዱስን ትቃወማላችሁ፤ አባቶቻችሁ እንደ ተቃወሙት እናንተ ደግሞ። ከነቢያትስ አባቶቻችሁ ያላሳደዱት ማን ነው? የጻድቁንም መምጣት አስቀድሞ የተናገሩትን ገደሉአቸው፤ በመላእክት ሥርዓት ሕግን ተቀብላችሁ ያልጠበቃችሁት እናንተም አሁን እርሱን አሳልፋችሁ ሰጣችሁት ገደላችሁትም። ይህንም በሰሙ ጊዜ በልባቸው በጣም ተቈጡ ጥርሳቸውንም አፋጩበት። መንፈስ ቅዱስንም ተሞልቶ ወደ ሰማይ ትኵር ብሎ ሲመለከት የእግዚአብሔርን ክብር ኢየሱስንም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አየና። እነሆ፥ ሰማያት ተከፍተው የሰው ልጅም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አያለሁ አለ። በታላቅ ድምፅም እየጮኹ ጆሮአቸውን ደፈኑ፥ በአንድ ልብ ሆነውም ወደ እርሱ ሮጡ፥ ከከተማም ወደ ውጭ አውጥተው ወገሩት። ምስክሮችም ልብሳቸውን ሳውል በሚሉት በአንድ ጎበዝ እግር አጠገብ አኖሩ። እስጢፋኖስም ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ነፍሴን ተቀበል ብሎ ሲጠራ ይወግሩት ነበር። ተንበርክኮም ጌታ ሆይ፥ ይህን ኃጢአት አትቍጠርባቸው ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህንም ብሎ አንቀላፋ። ሳውልም በእርሱ መገደል ተስማምቶ ነበር።

በረከቱ ይደርብን!!
#ጥር 2 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

1.ቅዱስ አቤል ጻድቅ
2.ቅዱስ ቴዎናስ ሊቀ ዻዻሳት
3.ቅዱስ አላኒቆስ ሰማዕት
4.ቅድስት ሳቤላ ነቢዪት
5.ቅዳሴ ቤታ ለድንግል (በደብረ አባ ሲኖዳ)

#ወርኀዊ በዓላት

1.ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ
2.ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ ተአጋሲ
3.ቅዱስ አባ ዻውሊ ገዳማዊ (ታላቁ)
4.ቅዱስ ዮሐንስ ነቢይ (መጥምቀ መለኮት)
5.ሊቁ አባ ሕርያቆስ
6.ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ
#ጥር 4 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

1.ቅዱስ ዮሐንስ ሐዋርያ
(ፍቁረ እግዚእ)
2.አባ ናርዶስ ጻድቅ (ዘደብረ ቢዘን)
3.ቅዱስ ጊዮርጊስ
4.ቅዱስ ማርቴና

#ወርኀዊ በዓላት

1.ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ
2.ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ
3.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
4.ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ (ሰማዕት)
#ጥር 5 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

1.ቅዱስ አባ ማቴዎስ
2.ቅዱስ አውስግንዮስ አረጋዊ (ሰማዕት)
3.ቅድስት እስክንድርያ
4.ቅድስት አውስያ ሰማዕት

#ወርሐዊ በዓላት

1.ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
2.ቅዱስ ዻውሎስ ብርሃነ ዓለም
3.አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
4.ቅዱስ ዮሐኒ ኢትዮዽያዊ
5.ቅዱስ አሞኒ ዘናሒሶ
6.ቅድስት አውጋንያ (ሰማዕትና ጻድቅ)
⬆️
የተክለሃይማኖት አደባባይ ለጥምቀት በኖኅ መርከብ አምሳያ ተውቧል።
የሰ/ት/ቤታችን ልማት ክፍል ለጥምቀት በዓል የተለያዩ ቲሸርቶችን፣ ባጆችን፣ ኮፍያዎችን፣ ለስላሳ መጠጦችን፣ ችፕስ፣ ውሃ በተመጣጣኝ ዋጋ አቅርቦላችኋል።
#ጥር 9 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

1.አባ አብርሃም ገዳማዊ
2.አባ ገዐርጊ ጻድቅ
3.ቅዱስ ዲዮስቅርስ ዘሮሜ
4.አባ ኪናፎርያ

#ወርሐዊ በዓላት

1.ቅዱሳን 318ቱ ሊቃውንት
2.አባ በርሱማ ሶርያዊ (ለሶርያ መነኮሳት ኁሉ አባት)
3.አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ
4.የብሔረ ብፁዐን ጻድቃን
5.አባ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ
6.ቅዱስ ዞሲማስ ጻድቅ
​​ልማት ክፍላችን ያሰራው ቲሸርት ይህን ይመስላል። ከነገ ጀምሮ ለሽያጭ ይቀርባል።
​​የሰ/ት/ቤታችን ልማት ክፍል ለጥምቀት በዓል የተለያዩ ቲሸርቶችን፣ ባጆችን፣ ኮፍያዎችን፣ ለስላሳ መጠጦችን፣ ችፕስ፣ ውሃ በተመጣጣኝ ዋጋ አቅርቦላችኋል።