የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
2.58K subscribers
6.1K photos
67 videos
60 files
1.7K links
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
Download Telegram
እናመሰግናለን!
የሰንበት ት/ቤታችን Youtube Channel በእናንተ ድጋፍ እዚህ ደርሷል በቀጣይም እንበረታ ዘንድ ሰብስክራይብ አድርጋችሁ ጠብቁን አዝናኝ እና ትምህርታዊ ዝግጅቶች በቅርቡ ይለቀቃል
👇👇👇Click and Subscribe👇👇👇
https://m.youtube.com/channel/UCXMG9oO5j1M-lRbAn0OdVdQ
#መስከረም_9 በዚህች የመላእክት አለቃ #ቅዱስ_ሚካኤል በሮም አገር ፍሩምያ በምትባል ከተማ ላደረገው ተአምር መታሰቢያ ነው

#ሊቀ_መላእክት_ቅዱስ_ሚካኤል

በዚህች ቀን በሮም አገር ፍሩምያ በምትባል ከተማ ለሆነው ተአምር መታሰቢያ ሆነ። ይህም እንዲህ ነው የሰማይ ሠራዊት አለቃ በሆነ በከበረ መልአክ በሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሚታዩ ድንቆችና ተአምራቶች ምክንያት ዮናናውያን ሰዎች ሰይጣናዊ ቅናትን እንደ ቀኑ ከመቅናታቸውም ብዛት የተነሣ በዚያ አካባቢ የሚወርደውን የወንዝ ውኃ በዚያች ቤተ ክርስቲያን ላይ ሊመልሱትና ከሚጠብቃት መጋቢዋ ጋር በውኃ ስጥመት ሊአጠፉአት ፈልገው መለሱት።

የሰማያውያን ሠራዊት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ለቤተ ክርስቲያኑ መጋቢ ለናርጢኖስ ተገለጠለት ወደርሱም ቀርቦ ጽና አትፍራ አለው ይህንን ብሎ በእጁ ውስጥ ባለ በትር አለቱን መታው አለቱም ተደንጥቆ እንደ በር ሆነ የዚያ ወንዝ ውኃም በውስጡ አልፎ ሔደ።

ይህንንም ያዩ ምስጉን እግዚአብሔርን አመሰገኑት የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልንም አከበሩት። ከዚያች ቀን እስከ ዛሬ የወንዙን ውኃ በዚያች በተሠነጠቀች አለት ውስጥ አልፎ ሲሔድ ያዩታል ወደ መላእክት አለቃ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ከቶ አይቀርብም።

ስንክሳር ዘወርኀ መስከረም
መልካም ዕለተ ሰንበት
በቅርብ ቀን
መጋቤ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ በማህበራዊ ኑሮ ላይ ከምዕመናን ለተነሱላቸው ጥያቄ በጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ መልስ ሰጥተዋል youtube ቻናላችን ላይ ይለቀቃል በቅርብ ቀን ሰብስክራይብ አድርገው ይጠብቁን Share
👇👇👇 Click ሰብስክራይብ አድርገው ይጠብቁን 👇👇
https://m.youtube.com/channel/UCXMG9oO5j1M-lRbAn0OdVdQ
#መስከረም_10
#ጼዴንያ_ማርያም እና #ተቀጸል_ጽጌ / አጼ መስቀል
#ጼዴንያ_ማርያም
በዚህች ቀን ቅዱስ ሉቃስ የሳላትና ሥጋን የለበሰችው: ከፊቷም ወዝ የሚወጣትና ድውያንን የምታድነው የድንግል ማርያም ስዕለ አድኅኖ ወደ ጼዴንያ ከወዳጇ ከብጽዕት ማርታ ዘንድ ገብታለች:: ቅድስት ማርታ ሃብት ንብረቷን በአብርሃማዊ ተግባር (በምጽዋትና እንግዳን በመቀበል) ላይ ያዋለች ክብርት ሴት ናት::
ለእመ ብርሃን ካላት ፍቅር የተነሳ እንቅልፍ አልነበራትም ተግታ ታገለግላትም ነበር ስዕሏን እንዲያመጣላት የላከችው ኢትዮዽያዊው መነኩሴ አባ ቴዎድሮስ የስዕሏን ተአምራት ባየ ጊዜ ለራሱ ለመውሰድ ሞክሮ ነበር::
ነገር ግን ከሁሉም በተሻለ የምትወዳት ቅድስት ማርታ ነበረችና በድንቅ ተአምር: በዚህች ቀን ወደ ጼዴንያ ገብታለች:: ቅድስት ማርታም ያለ ዕረፍት ስታገለግላት ኑራ ዐርፋለች::
#ተቀጸል_ጽጌ / አጼ መስቀል
ከ1500 ዓመት በፊት አበባን ተቀዳጅ የሚል ትርጉም ያለው የ‹‹ተቀጸል ጽጌ›› ክብረ በዓል መከበር የተጀመረው በአፄ ገብረ መስቀል ዘመን ሲሆን፣ ዝማሬውን ያዘጋጀው ደግሞ ቅዱስ ያሬድ ነበር ክረምት በሚወጣበት መስከረም 25 ቀን የአበባው በዓል ሲከበር ቅዱስ ያሬድ ንጉሠ ነገሥቱን ‹‹ተቀጸል ጽጌ ገብረ መስቀል ሐፀጌ›› - አፄ ገብረ መስቀል ክረምቱ አልፎልሃልና አበባን ተቀዳጅ፣ አበባን ተላበስ እያለ ያወድሰው የነበረው በዓላዊ ትውፊት እየተቀባበለ እስከ 15ኛው መ, ክ,ዘ ደርሶ ነበር፡፡
በአፄ ዳዊት ዘመን የጌታችን ግማደ መስቀሉ መስከረም 10 ቀን ከግብፃውያን እጅ በመቀበላቸው ግማዱም በንጉሡ ምክንያት በመምጣቱ ‹‹አፄ መስቀል›› እየተባለ መከበር ሲጀምር፣ የ25ኛው ቀን የአበባው
በዓልም በ15 ቀን ወደኋላ በማፈግፈግ ከርሱ ጋር ባንድነት እንዲከበር በመወሰኑ እስካሁን በመከበር ላይ ይገኛል፡፡ በቀድሞ ግዜ እስከ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመን (1923-1967) የ1966ቱ መስከረም 10 ድረስ በዓሉ በንጉሡ ፊት በገነተ ልዑል ቤተ መንግሥት፣ በኋላም በኢዮቤልዩ ቤተ መንግሥት ይከበር ነበር፡፡
በዘመነ ደርግ ተቋርጦ የነበረው የአበባው በዓል ተቀጸል ጽጌ ከ1980ዎቹ አጋማሽ ጀምሮ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አማካይነት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ዐውደ ምሕረት በመንፈሳዊ ሥነ ሥርዓትና ለምእመኑ አበባ እየታደለ መከበር ጀምሮ እንደቀጠለ ነው፡፡ ‹‹የክረምቱ ወራት አልፎ መጸዉ ብሎም በጋው ሲተካ፣ ምድር በልምላሜ ፀጋ ተውባ አረንጓዴ ልብስ ተጎናጽፋ፣ በዕፀዋት አበባ ደምቃ፣ የመንፈስ ደስታ የምታድልበት፣ ሰማይ በከዋክብት አጊጦና አሸብርቆ የሚታይበት በመሆኑ የአበባ በዓል ስም ከግብር የተስማማለት ነው፡፡›
አምላካችን እግዚአብሔር ከዚህ ወቅት መልካሙን ነገር እንድናገኝና ከእናታችንም ረድኤት በረከቷን ምልጃ ጸሎቷን እንዲያካፍለን መልካም ፈቃዱ ይሁን።
#ፍኖተ_ብርሃን_ሰንበት_ት/ቤት
👉የ2013 ዓ.ም በሰንበት ት/ቤታችን በሕጻናት እና በወጣት ክፍል ለ2ወር የክረምት መንፈሳዊ ኮርስ ሲማሩ ቆይተው እሁድ መስከረም 09/2014 ዓ.ም ተመርቀዋል፡፡
የጥበብ መገኛ የሠላም ንጉስ
ጥበብ ግለጽልን ቸሩ ክርስቶስ
መልካም አገልግሎት ግዜ
መስከረም 11/2014 ዓ.ም ወርሐዊ የቅዱስ ሚካኤል ጸሎት ተደረገ።

#ሚካኤል ብሂል /የቃሉ ትርጉም/ መኑ ከመ አምላክ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማነው ማለት ነው ።
#ቅዱስ ሚካኤል የሰማይ ሰራዊት አለቃ ነው ኢያሱ 5 ÷ 14
#በዘመነ ብሉይ እስራኤላውያንን በበረሃ በስደት ጊዜ የተራዳ መልአክ ነው በዚህም (መጋቤ ብሉይ በመባል ይጠራል) ዘፀአት 23
#ለሰው ልጆች አዛኝ ተራዳኢ መልአክ በመሆኑም ሩሁሩህ መልዐክ ይባላል ።
#ዛሬም ምልጃውና ተራዳኢነቱ ለሐገራችን ለኢትዮጵያና ለህዝቦቿ ጋሻ መከታ ጥላ ከለላ ይሁንልን ጦርነቱን ረሐብ ስደቱንም ከአምላክ በተሰጠው ቃል ኪዳን እየተራዳ ያስታግስልን አሜን
#መስከረም_13

#ቅዱስ_ባስልዮስ_ዘቂሣርያ

መስከረም ዐሥራ ሦስት በዚህች ቀን ታላቅና ቅዱስ የሆነ የቂሣርያ ሊቀ ጳጳሳት ባስልዮስ ላደረገው ተአምር መታሰቢያ ሆነ።

ይህም እንዲህ ነው አንድ ጐልማሳ አገልጋይ የጌታውን ልጅ ስለወደዳት ልቡ እርሷን ወዶ እንደ እሳት እስከ ነደደ ድረስ እርሷንም ከመውደዱ ብዛት የተነሣ ወደ አንድ ከሀዲ ሥራየኛ ሔደ። ሥራየኛውም የክህደት ደብዳቤ ጽፎ ሰጠው። ወደ አረሚ መቃብርም ሒዶ በመንፈቀ ሌሊት ደብዳቤዋን ይዞ ወደላይ እጁን አንሥቶ በዚያ እንዲቆም አዘዘው።

ይህም አገልጋይ ይህን ነገር ተቀብሎ ያ መሠርይ እንዳዘዘው አደረገ። በዚያንም ጊዜ ከሰይጣናት አንዱ መጥቶ ወደ አለቃቸው ወስዶ አደረሰው ያቺንም የክህደት ደብዳቤ ከእጁ ወሰደ። እንዲህም ብሎ ጠየቀው "ንጉሥህ ክርስቶስን ትክደዋለህን? ፈቃድህን ከፈጸምኩልህ በኋላ ወደእርሱ አትመለስምን?" ይህም ጐስቋላ ባሪያ "አዎን ጌታዬ ያዘዝከኝን ሁሉ አደርጋለሁ" አለው። መስሐቲ ዲያብሎስም ይህን ልታደርግ በእጅህ ደብዳቤ ጻፍልኝ አለው። እርሱም በከበረ ደሙ የዋጀውን የክብር ባለቤት ክርስቶስን ክዶ በደብዳቤ ውስጥ የክህደቱን ቃል ጻፈለት።

በዚያንም ጊዜ ሰይጣን በጌታው ልጅ ልብ ውስጥ የፍትወት እሳትን አነደደ ይህንንም ባሪያ እጅግ ወደደችው ከእርሱም መታገሥ አልተቻላትም። ወደ አባቷ በመጮህ በግልጥ ከዕገሌ ባሪያህ ጋር ካላጋባኸኝ አለዚያ ራሴን እገድላለሁ ትለዋለች እንጂ መታገሥ አልተቻላትም። አባትና እናቷም ፈጽሞ አዘኑ በምንም በምን ሊያስታግሥዋት አልቻሉም። የዚያም አገልጋይ ፍቅሩ በየዕለቱ በልቧ ይጨመር ነበር እንጂ። ስለዚህም ራሷን እንዳትገድል አባቷ ፈራ ለዚያ ባሪያ ሰጠው። እርሱም የጌታውን ልጅ ተቀብሎ ወደቤቱ አስገባት። ከርሷ ጋር ያለውን ፍላጎቱንም ፈጸመ። ከእርሱም ጋር ረጅም ጊዜ ከኖረች በኋላ አባትና እናቷም ይቅር ብሎ ኀዘናቸውን ከላያቸው ያርቅላቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ኀዘንንና ልቅሶን አብዝተው ነበር።

ከዚህም በኋላ ክብር ይግባውና ጌታችን ክርስቶስ ጩኸታቸውን ሰማ ልመናቸውንም ተቀብሎ ይህ የወደደችው አገልጋይ ጐልማሳ ክርስቲያን እንዳልሆነ አስገነዘባት ከእርሷ ጋር በነበረበት በዚህ በረጅም ዘመን አንዲት ቀን እንኳ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲሔድ ሥጋውንና ደሙንም ሲቀበል ወይም አዳኝ በሆነ በመስቀል ምልክት ራሱን ሲአማትብ እርሷ አላየችውም።

ስለእምነቱም ጠየቀችው ግን አልገለጠላትም እርሷም እንዲህ አለችው "አንተ ክርስቲያን ከሆንክ ና በአንድነት ወደ ቤተ ክርስቲያን እንሒድና በፊቴ ቅዱስ ቊርባንን ተቀበል።" እንዲህም በአስገደደችው ጊዜ ስለርሷ ያደረገውን ሁሉ ወደ ሥራየኛ እንደሔደም በሰይጣንም አምኖ እምነቱንም በክርታስ ጽፎ ያንን ክርታስ ለሰይጣን እንደ ሰጠው ነገራት።

ይህንንም ነገር ከእርሱ በሰማች ጊዜ ደነገጠች መሪር ልቅሶንም አለቀሰች ራሷንም በማወዛወዝ እጅግ ተጸጽታ አዘነች። ያን ጊዜም ፈጥና ተነሣች የቤተ ክርስቲያን ምሰሶ ወደሆነው ወደ ሀገርዋ ሊቀ ጳጳሳት ወደ ቅዱስ ባስልዮስ ሔደች ከእግሩ በታችም ወድቃ ሰገደችለት በላይዋ የደረሰውን ሁሉ አስረዳችው ለሰው ልጆች ጠላት ከሆነ ከሠይጣን እጅ ፈጽሞ ያድናት ዘንድ ብዙ በማልቀስ ለመነችው።

ቅዱስ ባስልዮስም ባሏ የሆነውን ባርያ ወደርሱ ልኮ አስመጣውና ጠየቀው እርሱም የሠራውን ሁሉ አስረዳው ቅዱስ ባስልዮስም "ተመልሰህ ክርስቲያን ልትሆን ከሰይጣንም እጅ ልትድን ትወዳለህን?" አለው ያም ባርያ "ጌታዬ ይሆንልኛልን?" አለ ይህ ቅዱስ አባትም የፈጣሪህን ስም እየጠራህ ልብህን አጽና አለው።

ከዚህም በኋላ ከእርሱ ዘንድ በአንድ ቦታ ዘጋበት በመስቀል ምልከትም አማተበበት እንዲጸልይም አዘዘው ራሱ ቅዱስ ባስልዮስም ስለርሱ ጸለየ። ከሦስት ቀኖች በኋላም ጎበኘው እንዲህም አለው በእሊህ በሦስት ቀኖች የደረሰብህ ምንድን ነው እርሱም በላዩ በመጮህ ሠይጣናት ሲያስፈራሩት ያንንም ደብዳቤ ሲአሳዩትና በእርሱ ላይ ሲቆጡ በመከራ ውስጥ እንደኖረ ነገረው ቅዱስ ባስልዮስም ከእሳቸው ቁጣ የተነሣ አትፍራ እግዚአብሔር ይረዳሃልና አጽንቶም ይጠብቅሃል አለው።

ከዚህም በኋላ ጥቂት እንጀራና ውኃ ሰጥቶ ወደ ቦታው መለሰው ቅዱስ ባስልዮስም ስለዚያ አገልጋይ ሒዶ ይጸልይ ጀመረ። ዳግመኛም ከሦስት ቀኖች በኋላ ጐበኘውና በእርሱ ላይ ምን እንደ ደረሰበት ጠየቀው ያ አገልጋይም ጩኸታቸውን እሰማለሁ ግን አላያቸውም ብሎ መለሰለት። እንጀራና ውኃም ሰጠውና መከረው ወደ ቦታውም መለሰውና ስለርሱ ሊጸልይ ቅዱስ ባስልዮስ ሔደ። እስከ አርባ ቀኖች ፍጻሜ ድረስ እንዲህ አደረገ። በአርባውም ቀን ፍጻሜ ከእርሱ ስለ ሆነው ጠየቀው ያ አገልጋይም እንዲህ አለው ቅዱስ አባቴ ሆይ ስለ እኔ ሰይጣንን ስትጣላውና ድል አድርገህ ጥለህ ስትረግጠው በዛሬዋ ሌሊት አየሁ አለው።

ቅዱስ ባስልዮስም ይህን ነገር ከእርሱ በሰማ ጊዜ እጅግ ደስ አለው የገዳማቱን መነኰሳትና ካህናቱንም ጠርቶ ስለዚያ ሰው ያቺን ሌሊት መላዋን እንዲጸልዩባት አዘዛቸ። በነጋ ጊዜም ያንን አገልጋይ ወደ ቤተክርስቲያን እንዲአመጡት የዚያችንም አገር ሕዝብ ሁሉንም ሰብስቦ እጆቻቸውን ወደ ሰማይ አንሥተው አቤቱ ክርስቶስ ማረን ይቅር በለን እያሉ ወደ እግዚአብሔር ፈጽሞ እንዲማልዱ አዘዛቸው እንዳዘዛቸውም አደረጉ።

እንዲህም እያሉ ሲማልዱ ያ ሰው ጽፎ ለሰይጣን የሰጠው የክህደት ደብዳቤ ከሰይጣን እጅ በሕዝቡ ሁሉ ፊት ወደቀ ሁሉም ደስ ብሏቸው ምስጉን እግዚአብሔርን አመሰገኑት የከበረ አባት ባስልዮስም ባረካቸው ሥጋውንና ደሙንም አቀብሎ ወደ ቤቶቻቸው በሰላም በፍቅር አሰናበታቸው ። እነርሱም ስለ ኃጢአታቸው ስርየትና ስለ ድኅነታቸው ፈጽሞ ደስ እያላቸው እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ይህንን ቅዱስ አባት ባስልዮስን እያከበሩ ወደ ቤታቸው ገቡ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_መስከረም)
አቡነ አረጋዊ ማለት የልጅ አዋቂ ማለት ሲሆን አባታቸው ይስሐቅ እናታቸው እጅና ይባላሉ ሀገራቸው ቆስጥንጥንያ ሲሆን በጥር 14 ቀን በ400 ዓ.ም ተወለዱ በ14አመታቸው ወደ ገዳም ገቡ ከአባ ጳጉሚስ ምንኩስናቸውን ተቀበሉ።

በጥቅምት 14 ቀን በ470ዓ.ም ወደ ታላቂቷ ሀገር ኢትየጵያ መጡ ደብረ ዳሞ የቀድሞ ቦታ ሃሌሉያ ይባል ነበር ከዚያ ተራራ ስር ሆነው ማን ያውጣኝ እያሉ ሲፀልዩ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ዘንዶውን ላከላቸው።

ዘንዶውም ቁመቱ 60ክንድ ነበር በወገባቸው ላይ ተጠምጥሞ ጥቅምት 12 ቀን መልአኩ ዘንዶውን እያዘዘው ተራራውን ወጥተዋል አባታችን በተወለዱ በ158 አመታቸው በሞት ፈንታ በጥቅምት 14 ቀን በ558 ዓ.ም ተሰውረዋል።

በረከታቸው ሁላችንን ይጠብቀን
👇የሰንበት ት/ቤታችንን Youtube ገጻችንን ሰብስክራይብ በማድረግ አገልግሎታችንን ይደግፉ 👇 https://m.youtube.com/channel/UCXMG9oO5j1M-lRbAn0OdVdQ
#መስከረም_15 በዚህች ቀን የዲያቆናት አለቃ የሰማዕታት መጀመሪያ ለሆነ #ቅዱስ_እስጢፋኖስ የሥጋው ፍልሰት ሆነ።

ይህም እንዲህ ነው ከአረፈበት ጊዜ ብዙ ዓመቶች ከአለፉ በኋላ ሦስት መቶ ዓመት ያህል ከዚያም የሚበዛ ጻድቁ ቈስጠንጢኖስ ሲነግሥ የቀናች ሃይማኖትም ተገልጣ የሕያው እግዚአብሔር አምልኮት በሁሉ ሲዘረጋ ያን ጊዜ የቅዱስ እስጢፉኖስ ሥጋ በአለበት አቅራቢያ የገማልያል ቦታ በትምባል በኢየሩሳሌም በአንዲት ቦታ አንድ ሰው ይኖር ነበር። የዚያም ሰው ስም ሉክያኖስ ነው ተጋዳይ የሆነ እስጢፋኖስም ብዙ ጊዜ በሕልም ተገለጠለት እንዲህም ብሎ አስረዳዉ እኔ እስጢፋኖስ ነኝ ሥጋዬ በዚህ ቦታ ተቀብሮ አለ።

ያም ሉክያኖስ የሚባል ሰው የኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ ወደ ሆነው መጥቶ በራእይ ያየውን ይህን ነገር ነገረው ኤጲስቆጶሱም ሰምቶ እጅግ ደስ አለው ያን ጊዜም ሁለት ኤጲስቆጶሳትን፣ ካህናትንና፣ የቤተ ክርስቲያንን ሰዎች ሁሉ ከእርሱ ጋራ ይዞ ተነሣ የቅዱስ እስጢፋኖስ ሥጋ በውስጡ ወዳለበት ወደዚያ ቦታ ደርሰው ሊቆፍሩ ጀመሩ ታላቅ ንውጽውጽታም ሆነ የቅዱስ እስጢፋኖስ ሥጋ በውስጡ ያለበት ሣጥን ተገለጠ ከእርሱ እጅግ በጎ የሆነው የሽቱ መዓዛ ሸተተ።

በሰማያት ለእግዚአብሔር ምስገና ሆነ በምድርም ሰላም ለሰው ነፃነቱ ይሰጠው ዘንድ በጎ ፍቃድ እያሉ ሲያመሰግኑ የመላእክትን ቃሎች ሰሙ። እንዲህም መላልሰው ሦስት ጊዜ አመሰገኑ ኤጲስቆጶሳቱና ካህናቱም የቅዱስ እስጢፋኖስን ሥጋ በያዘ ሣጥን ፊት ለጌታ ሰገዱ ከዚያም በኋላ ወደ ጽርሐ ጽዮን እስኪያደርሱት ብዙ መብራቶችን አብርተው በመያዝ በማኀሌት ምስጋና እየዘመሩ ተሸከሙት።

ከዚህም በኋላ እንዲህ ሆነ በኢየሩሳሌም ነዋሪ የሆነ የቊስጥንጥንያ ተወላጅ ስሙ እለእስክንድሮስ የሚባል ሰው ነበር ለቅዱስ እስጢፋኖስም ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያንን ሠርቶለት ሥጋውን አፍልሰው ወደርሷ ወስደው አኖሩት ከአምስት ዓመት በኋላም እለእስክንድሮስ አረፈ ሚስቱም በቅዱስ እስጢፋኖስ አስከሬን ጕን ቀበረችው። ከሌሎች አምስት ዓመቶችም በኋላ የእለእስክንድሮስ ሚስት የቧላን አስከሬን ወደ ቊስጥንጥንያ አገር ይዛ ልትሔድ አሰበች ባሏንም ወደ ቀበረችው እርሱ ባሏ ወደ ሠራት ቤተ ክርስቲያን ሔደች የባሏ ሥጋ ሣጥን ግን የቅዱስ እስጢፋኖስን ሥጋ በያዘ ሣጥን አምሳል ነበር በእግዚአብሔር ፈቃድ የቅዱስ እስጢፋኖስን ሣጥን ወስዳ እስከ አስቃላን ከተማ ተሸከመችው ከዚያም ወደ ቊስጥንጥንያ ልትጓዝ በመርከብ ተሳፈረች።

በመርከብ ስትጓዝ ከሣጥኑ ጣዕም ያለው ምስጋናን የምትሰማ ሆነች እጅግም አድንቃ ያን ሣጥን ልታየው ተነሣች በውስጥ የቅዱስ እስጢፋኖስ ሥጋ ያለበት ሣጥን እንደሆነ ተረዳች ይህም የሆነው ክብር ይግባውና በእግዚአብሔር ፈቃድ እንደሆነም አወቀች ወደ ኢየሩሳሌም ትመለስ ዘንድ አልተቻላትም ይህንንም ታላቅ ጸጋ ስለሰጣት ልዑል እግዚአብሔርን አመሰገነች።

ወደ ቍስጥንጥንያ አገርም በደረሰች ጊዜ ያቺ ሴት ወደ ንጉሡ ሒዳ የቅዱስ እስጢፋኖስን ዜና ከእርሱ የሆኑትን ተአምራት ወደ ቍስጥንጥንያ አገር ወደብም እንደ ደረሰ ነገረችው ሰምቶም እጅግ ደስ አለው ንጉሡም ከሊቀ ጳጳሳቱና ከካህናቱ ከብዙ ሕዝቦችም ጋር ወጣ ከወደቡም በክብር አንሥተው ወደ መንግሥት አዳራሽ እስከ አስገቡት ድረስ በፍጹም ደስታ እየዘመሩና እያመሰገኑ ተሸክመውት ተጓዙ።

ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ከእርሱ ተአምራትን ገለጠ በሠረገላ ሥጋውን ጭነው በሁለት በቅሎዎች በሚስቡት ጊዜ ቍስጣንጢንዮስ ከሚሉት ቦታም ሲደርሱ የቅዱስ እስጢፋኖስንም ሥጋ በዚያ እንዲያኖሩ ስለ ፈቀደ የሚስቡት በቅሎዎች ቆሙ። አልተንቀሳቀሱም በቅሎዎችንም ይመቷቸው ጀመሩ የቅዱስ እስጡፋኖስን ሥጋ በዚህ ሊያኖሩ ይገባል የሚል ቃል ከአንዱ በቅሎ ሰሙ ይህንንም ያዩና የሰሙ ሁሉም አደነቁ።

እግዚአብሔርንም አመሰገኑት የበለዓምንም አህያ ያናገራት እርሱ እነዚህን የቅዱስ እስጢፋኖስን ሥጋ የተሸከሙትን በቅሎዎች ያናገራቸው እርሱ እንደሆነ አወቁ። ንጉሡም በዚያ መልካም የሆነች ቤተ ክርስቲያን ሠርተው ይህን የከበረና ንጹሕ የሆነ ዕንቈ ባሕርይ በውስጧ እንዲያኖሩ አዘዘ። ይኸውም ለተመሰገነና ለተባረከ ሐዋርያ የዲያቆናት አለቃና የሰማዕታት መጀመሪያ ለሆነ እስጢፋኖስ ሥጋው ነው።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን ።
#ፍኖተ_ብርሃን_ሰንበት_ት/ቤት

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_መስከረም እና #ከገድላት_አንደበት)
#ፍኖተ_ብርሃን_ሰንበት_ት/ቤት
https://t.me/finotebirhan12
https://t.me/finotebirhan12
https://t.me/finotebirhan12