የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
2.58K subscribers
6.1K photos
67 videos
60 files
1.7K links
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
Download Telegram
☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️
የሰንበት ት/ቤታችን አዲሱ የሕንጻ ግንባታ
የመሠረቱ ሥራ እንዲህ ተጠናቋል
👉 በጸሎት በጉልበት በገንዘብ በሀሳብ በተለያየ ነገር አብራችን ስላላችሁ እናመሰግናለን
👉 ጀምርነዋል ከእናንተ ጋር ሆነን እንጨርሰዋለን ልትረዱን የምትፈልጉ በአካልም በስልክም አግኙን አግዙን አበርቱን

መልካሙን ሁሉ የምንሰማበት እለት ተመኝን
የሰንበት ት/ቤታችን የ2014 ዓ.ም የአዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት
መስከረም 2-መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ በሰማዕትነት ዐረፈ፡፡

በዚህችም ቀን የሰማዕት ዲዲሞስና የቅድስት መሪና መታሰቢያቸው መሆኑን ስንክሳሩ በስም ይጠቅሳቸዋል።
+በዚችም ቀን በግብጽ ውስጥ ታዕዳ ከሚባል አገር ዳስያ ሰማዕት ሆነ። ይህንንም ቅዱስ የእንዴናው አገረ ገዥ አርያኖስ አሠቃየው ጽኑ ሥቃይንም ከአሠቃየው በኋላ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለ። በረከቱም ከእኛ ጋር ለዘላለሙ ትኑር አሜን፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ ነቢይ (መጥምቀ መለኮት)፦ዮሐንስ ማለት ‹‹ፍሥሐ ወሐሴት፣ ርኅራኄ›› ማለት ነው፡፡ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መንገድ ጠራጊ የሆነው ቅዱስ ዮሐንስ የብሉይ ኪዳን የመጨረሻው የሐዲስ ኪዳን ደግሞ የመጀመሪያው ነቢይ ነው፡፡

ይህም እንዲህ ነው በፊልጶስ ሚስት በሄሮድያዳ ምክንያት ነቢዩ ዮሐንስ በገሠጸው ጊዜ ፊልጶስ ወንድሙ ስለሆነ ቅዱስ ዮሐንስም የወንድምህን ሚስት ልታገባ አይገባህም ይለው ነበርና። ቅዱስ ዮሐንስም ሄሮድስን የወንድሙን የፊልጶስን ሚስት ሄሮድያዳን ስለማግባቱና ሌላም ያደርገው ስለነበረ ክፉ ሥራ ሁሉ ይገሥጸው ነበር። ደግሞም በተግሣጽ ላይ ተግሣጽን ጨመረ ስለዚህም ዮሐንስን ተቀየመውና በግዞት ቤት አኖረው።

ሄሮድስም ዮሐንስን ይፈራው ነበር ጻድቅ ቅዱስ ሰው እንደሆነ ያውቅ ነበርና ብዙ ይጠባበቀውም ነበር። ሄሮድስ የተወለደባትን ቀን በዓል የሚያከብርባት ዕለት ነበረች መኳንንቱን አለቆቹን መሣፍንቱን ሹሞቹን በገሊላ አገር ያሉትን ታላላቅ ሰዎች ግብር አገባ።

የሄሮድያዳ ልጅም ወደ አዳራሹ ገብታ ዘፈነች ሄሮድስንም ደስ አሰኘችው ከእርሱ ጋር በማዕድ የነበሩትንም ንጉሡም ያቺን ብላቴና የምትሺውን ለምኚኝ እሰጥሻለሁ አላት። እስከ መንግሥቱ እኩሌታ ድረስም ቢሆን የለመነችውን ሊሰጣት ማለላት ወጥታም እናቷን ምን ልለምነው አለቻት እናቷም የመጥምቁ ዮሐንስን ራስ አለቻት ያን ጊዜም እየሮጠች ወደ ንጉሡ ገብታ የመጥምቁ ዮሐንስን ራስ በወጭት አሁን እንድትሰጠኝ እሻለሁ ብላ ለመነችው ንጉሡም ስለ መሐላው አብረውት ስለ ነበሩትም ሰዎች አዘነ እምቢ ሊላት ግን አልወደደም።

ያን ጊዜም ባለወጎችን ላከ በእሥር ቤትም ሳለ የዮሐንስን ራስ ቆረጡ ራሱንም በወጭት አምጥተው ለዚያች ብላቴና ሰጡአት እርሷም ወስዳ ለእናቷ ሰጠች በዚያችም ቀን የቅዱስ ዮሐንስ ራስ ከሄሮድያዳ ከእጆቿ ላይ ወደ አየር ስለ በረረች ታላቅ ድንጋፄ ሆነ። ደግሞም ሄሮድስ ሆይ የወንድምህን ሚስት ልታገባ አይገባህም እያለች በመጮኽ ዘልፋዋለችና። ደቀ መዛሙርቱም በሰሙ ጊዜ መጥተው በድኑን ወስደው ቀበሩት።

የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን፡፡
ምንጭ፦ስንክሳር ዘወርኀ መስከረም
እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሠላም አደረሳችሁ እያልን 👉 የሰንበት ት/ቤታችን አባላት ጉዳይ በያዝነው በአዲሱ 2014 ዓ.ም
👉 የአባላትን ፎርም በአዲስ መልኩ መሙላት ስላሰበ ሁላችሁም ነባር አባላት የአገልግሎት ፎርም እስከ መስከረም 30 ድረስ እየመጣችሁ እንድትሞሉ ይሁን
👉 በዚህ ፎርም ላይ ለአገልግሎት የምትመጡበት እና የማይመቻችሁን ግዜ ማሳወቅ መሙላት ይጠበቅባቹሃል
👉 ይህን መረጃ ለሰንበት ት/ቤታችን በቅርቡ ልናሰራው ባሰብነው Database (ዳታቤዝ) ልማት አስፈላጊ ሆኖም ተገኝቷል

ይህ ማስታወቂያ ሁላችንም የሰንበት ት/ቤት አባላትን ይመለከታል የምዝገባ የመጨረሻ ቀን መስከረም 30 ነው ላልሰሙት እናሰማ
👉 በወርኃ መስከረም በዓራተኛው ቀን ከ12ቱ ሐዋርያትና ከ4ቱ ወንጌላውያን አንዱ ፍቁረ እግዚእ የተባለ አባታችን ቅዱስ ዮሐንስ ልደቱ እንደሚታሰብ አበው መምህራን ይናገራሉ።

#ፍኖተ_ብርሃን_ሰ/ት/ቤት
#አቡነ_አሮን_መንክራዊ

ዳግመኛም በዚህች ቀን የዚህ ታላቅ አባት የእረፍት ቀን ነው፡፡

ኢትዮዽያዊው ጻድቅ አቡነ አሮን በ14ኛው መቶ ክ/ዘ የነበሩ ኢትዮዽያዊ ሲሆኑ በገዳማዊ ሕይወታቸው በሐዋርያዊ አገልግሎታቸውና ነገሥታቱን ሳይፈሩ በመገሰጻቸው ይታወቃሉ፡፡

በተለይም ሕይወታቸው በተአምር የተሞላ ስለነበር 'አሮን መንክራዊ' (ድንቅ አባት) ተብለው ይጠራሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜም 'አሮን ዘመቄት /ዘደብረ ዳሬት/' በሚልም ይጠራሉ፡፡
የአቡነ አሮን ወላጆች ገብረ መስቀልና ዓመተ ማርያም የሚባሉ ሲሆን ከልጅነታቸው ጀምረው በቅዱስ ቃሉ የታነጹ ነበሩ፡፡ ምናኔን በደብረ ጐል ከአቡነ በጸሎተ ሚካኤል
ጀምረው ብዙ ገዳማትን መሥርተዋል፡፡ በርካታ ደቀ መዛሙርትንም አፍርተዋል::

ለወንጌል አገልግሎት በወጡበት ጸሐይን አቁመው ሕዝቡን ድንቅ አሰኝተዋል፡፡ እንኩዋን ሰዉ ይቅርና አጋንንትም ያደንቁዋቸው ነበር፡፡ ነገሥታቱንም ስለ ኃጢአታቸው በገሰጹ ጊዜ ራቁትነት እሥራት ግርፋትና ስደት ደርሶባቸዋል ከብዙ ተጋድሎ በኋላ መስከረም 5 ቀን አርፈዋል፡፡

በረከታቸው ሁላችንንም ይጠብቀን

ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት
👉https://t.me/finotebirhan12👈
👉https://t.me/finotebirhan12👈
👉https://t.me/finotebirhan12👈
መስከረም ፮ (6) ቀን።

✍️ እንኳን ለኢትዮጵያዊው ጻድቅ ለታላቁ አባት ለአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ ዐፅማቸው ከዋልድባ አብረንታንት ወደ ደብረ ዓባይ ለፈለሰበት ቀን መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን።

+ + +
#የአቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ_የሥጋ_ፍልሰት
=========================
✍️ ከዋልድባ አብረንታንት ወደ ደብረ ዓባይ፤ አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ ትውልዳቸው ከካህናቱ ወገን አክሱም ነው አባታቸው እስጢፋኖስ እናታቸው አመተ ማርያም ይባላሉ። ለመምህር ሰጥተዋቸው ሲማሩ አድገው በኋላም ወላጆቻቸው በሞት ሲለዩአቸው ደብረ በንኰል ገዳም ገብተው ሥርዓተ ምንኩስናን ከአበው እያጠኑ ለትልቁም ለትንሹም በትሕትና እየታዘዙ ውሃ እየቀዱ እንጨት እየሰበሩ በትኅርምት በጽሞና በጸሎት ይኖሩ ነበር።

✍️ ሰይጣን በውዳሴ ከንቱ ጾር ቢመጣባቸው ከማሕበረ መነኰሳቱ ተለይተው በተባሕትዎ ለመኖር ሽተው ወጥተው ሲሔዱ ተከዜ ደረሱ። ወንዙ ሞልቶ የማያሻግራቸው ቢሆን ውሃውን በትምህርተ መስቀል ባርከው በአንድ እጃቸው መጽሐፍ በአንድ እጃቸው መብራት እንደያዙ ገብተው መብራቱ ሳይጠፋ መጽሐፉ ሳይበላሽ ተሻግረዋል። ዋልድባ ሲደርሱ ጌታ እዚህ ተቀመጥ ስላላቸው ገዳም መሥርተው ሥርዓተ ምንኩስናን እያስተማሩ ተቀመጡ። ዛሬ በዋልድባ የሚያመሰግኑበት ውዳሴ ማርያም ቅዳሴ ማርያምን ከተከዜ ወዲህ ያመጡ እሳቸው ናቸው። ይህንን እየጸለዩ ሲሔዱ ክንድ ከስንዝር መሬት ለቀው ይታዩ ነበር።

✍️ አንድ ቀንም ይህንን ጸሎት ደግመው ውኃውን ቢባርኩት ኅብስተ ሕይወት ሆነላቸው ከነደቀ መዛሙርቶቻቸው ተመግበውታል። እመቤታችንም የፍቅር መግለጫ ዕጣን፣ ወርቅ፣ እንቁ ሰጥታቸዋለች። "ውዳሴዬን ከቅዳሴዬ አንድ አድርጎ የደገመውን አንተ ከገባህበት መካነ ሕይወት አስገባዋለሁ" ብላ ቃልኪዳን ሰጥታቸዋለች። ጊዜ ዕረፍታቸው ሲደርስ ጌታን በስብሐተ መላእክት ተገልጦ "በስምህ የተማጸነውን በጎ የሰራውን፣ ዜና ገድልህን የጻፈውን፣ ያስጻፈውን፣ ያነበበ፣ የተማረ፣ ያስተማረ፣ እስከ አሥር ትውልድ ድረስ ምሬልሃለሁ። በዚህ ቦታ በዋልድባ የሚሰበሰቡ ልጆችህን ከእዳ ከፍዳ እሰውርልሃለሁ" አላቸው። እንኪያስ ቦታዋን ባርክልኝ ብለው እንደ መሶብ አንስተው አስባርከዋታል ጌታችንም "እህል አይብቀልብሽ ኃጢአት አይሻገርብሽ" ብሎ ቃል ኪዳን ገባላት ለገዳመ ዋሊ። አባታችን አቡነ ሳሙኤል በበዓታቸው ውስጥ ጸንተው ሲኖሩ ታህሣሥ 12 ቀን ያረፉ ሲሆን ዛሬ መስከረም 6 ግን ፍልሰተ አጽማቸው የተከናወነበት ዕለት ነው። ከአባታቸው ከአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸውም ይማረን።
✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥
#ፍኖተ_ብርሃን_ሰንበት_ት/ቤት
👉https://t.me/finotebirhan12👈
👉https://t.me/finotebirhan12👈
👉https://t.me/finotebirhan12👈
#መስከረም_7

መስከረም ሰባት በዚህች ቀን ....
1- አምላክን የወለደች የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እናት #የቅድስት_ሐና ልደቷ ነው፣
2- የመጥምቁ ዮሐንስ እናት የከበረች #ቅድስት_ኤልሳቤጥ አረፈች፣
3- #የእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት #ቅዱስ_ዲዮስቆሮስ አረፈ፣
4- የከበረ አባት #ቅዱስ_ሳዊርያኖስ አረፈ፣
5- የከበሩ #አጋቶንና_ጴጥሮስ_ዮሀንስና_አሞን እናታቸውም ራፈቃ በሰማእትነት አረፉ።

የቅዱሳኑ በረከታቸው አማላጅነታቸው ይጠብቀን
#ፍኖተ_ብርሃን_ሰንበት_ት/ቤት ቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉን
👉https://t.me/finotebirhan12👈
👉https://t.me/finotebirhan12👈
👉https://t.me/finotebirhan12👈
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_መስከረም እና #ከገድላት_አንደበት)
እናመሰግናለን!
የሰንበት ት/ቤታችን Youtube Channel በእናንተ ድጋፍ እዚህ ደርሷል በቀጣይም እንበረታ ዘንድ ሰብስክራይብ አድርጋችሁ ጠብቁን አዝናኝ እና ትምህርታዊ ዝግጅቶች በቅርቡ ይለቀቃል
👇👇👇Click and Subscribe👇👇👇
https://m.youtube.com/channel/UCXMG9oO5j1M-lRbAn0OdVdQ