የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
2.62K subscribers
6.23K photos
67 videos
79 files
1.72K links
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
Download Telegram
እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ!

"ዮም ሰማያዊ በጎል ሰከበ ለዘተወልደ እምቅድስት ድንግል ርእይዎ ኖሎት አእኰትዎ መላእክት፤
እነሆ ዛሬ ሰማያዊውን በበረት የተኛውንና ከቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደውን እረኞች አዩት መላእክትም አመሰገኑት።"

እነሆ አራቱም ክፍላት
   📌ሕፃናት ክፍል
   📌ማዕከላውያን ክፍል
   📌ወጣት ክፍል
   📌ባለ ትዳር ክፍል የሚገኙበት
     ልዩ የዝማሬ ቀን
      በልደተ ክርስቶስ
ታኅሣሥ 29/2017 ዓ.ም

ቦታ፦ በስብከተ ወንጌል አዳራሽ
ሰዓት፦ ከ 10-12 ሰዓት

ይህንንም የመዳኛችን መጀመሪያ ቀን ሁላችንም በበዓሉ ቀን በቤተክርስትያን በመገኘት አምላካችንን በማመስገን እናክብረው።

ሲመጡ 2 ጧፍ አንዱ መባችን ይሆንና ሌላኛውን እናበራው ዘንድ ይዛችሁ ተገኙ።

ማስታወሻ፦ ከርቀት ቦታ የሚመጡ አባላት ስለሚኖሩና ሲመለሱ ትራንስፖርት ሊቸገሩ ስለሚችሉ በተባለው ሰዓት እንጀምር ዘንድ ሰዓት አክብረን እንምጣ።

     የመዝሙር አገልግሎት እና የዜማ     
          ትምህርቶች ሥልጠና ክፍል

ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12

የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12

የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1

የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com
ውድ የጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚ/ቤ/ክ የፍኖተ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት አባላት እና ወዳጆች 

የ2017 ዓ.ም. የገና(የልደት) በዓል ሥጦታን ለምታሰሩት ህንጻ ማጠናቀቂያ የሚሳተፉበት ዘመቻን እስከ ገና ድረስ እናደርጋለን። እነሆ  ለሰንበት ትምህርት ቤታችን  ፍቅራችንን ለመግለጽ ጊዜው አሁን ነው። ሰብአ ሰገል ለተወለደው ንጉስ አምሐን(ሥጦታን) እንዳበረከቱለት እናንተም የጌታችንን ልደት ምክንያት በማድረግ ለሰ/ት/ቤታችን ሕንጻ ማስፈጸሚያ የሚሆን ሥጦታችሁን

የወርቅ ሥጦታ - 1500- 2000 ና ከዚያ በላይ
የዕጣን ሥጦታ - ከ1000- 1500 ብር
የከርቤ ሥጦታ - ከ500-1000 ብር

እንድታስገቡ (እንድትለግሱ)በተወለደው አምላክ  ስም ጥሪያችንን እናቀርባለን::

አምሐ ብላችሁ በመጻፍ

1000375969533
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
51281930205011
      ዳሽን ባንክ

የፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት ሕንጻ አሰሪ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን::
    
         ስለ መጽሐፉ አጭር ገለፃ

    ይህ የሥልጠና መጽሐፍ በዉስጡ አራት እጅግ ጠቃሚ ሥልጠናዎችን በዉስጡ የያዘ ነዉ፡፡   እነርሱም:-

- ምክር በእንተ ጥናት (የጥናት ዘዴ)
- የጊዜ አጠቃቀም
- ለዛ ያለዉ ንግግር አቀራረብ
- ዉጤታማ ስብሰባ

           * ስለ መጽሐፉ ርእስ

"መጽሔት" የሚለው ቃል ግእዝ ሲሆን ፍቺው የጠራ መስታወት ነው፡፡ "ብልኀት" የሚለው ቃልም ግእዝ ሲሆን በቁሙ ሲፈታም መስላት፣ መፍጠን ሲሆን ብልኅነትን እና የሰላ አእምሮን የሚገልጽ ነው::

ይህም መጽሐፍ የሚያተኩርባቸው አራት አርእስተ ጉዳዮችን እንደ መስታወት በጠራ አማርኛ ገልጾ አንባቢውን በእነዚህ ጉዳዮች ላይ የሰላ መረዳት እንዲኖረው ስለሚያደርግ ስያሜው መጽሔተ ብልኀት ሊሆን ችሏል፡፡

    የመጽሔቱ የሽያጭ ዋጋ-100 ብር ስለሆነ
ሁላችሁም በመግዛት ልጆቻችን እንዲጠቀሙበት እናድርግ።

"የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።"
                       2ኛ.  ጢሞ. 3 ፥16-17

ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12

የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12

የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1

የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com
የሰንበት ት/ቤታችን ሕጻናት ክፍል የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል ምክንያት በማድረግ በጎጆ የሕሙማን ማረፊያ በመገኘት የእንኳን አደረሳችሁ መርሐግብር አካሂደዋል።

  እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ።

ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12

የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12

የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1

የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com
እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ!

"ዮም ሰማያዊ በጎል ሰከበ ለዘተወልደ እምቅድስት ድንግል ርእይዎ ኖሎት አእኰትዎ መላእክት፤
እነሆ ዛሬ ሰማያዊውን በበረት የተኛውንና ከቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደውን እረኞች አዩት መላእክትም አመሰገኑት።"

እነሆ አራቱም ክፍላት
   📌ሕፃናት ክፍል
   📌ማዕከላውያን ክፍል
   📌ወጣት ክፍል
   📌ባለ ትዳር ክፍል የሚገኙበት
     ልዩ የዝማሬ ቀን
      በልደተ ክርስቶስ
ታኅሣሥ 29/2017 ዓ.ም

ቦታ፦ በስብከተ ወንጌል አዳራሽ
ሰዓት፦ ከ 10-12 ሰዓት

ይህንንም የመዳኛችን መጀመሪያ ቀን ሁላችንም በበዓሉ ቀን በቤተክርስትያን በመገኘት አምላካችንን በማመስገን እናክብረው።

ሲመጡ 2 ጧፍ አንዱ መባችን ይሆንና ሌላኛውን እናበራው ዘንድ ይዛችሁ ተገኙ።

ማስታወሻ፦ ከርቀት ቦታ የሚመጡ አባላት ስለሚኖሩና ሲመለሱ ትራንስፖርት ሊቸገሩ ስለሚችሉ በተባለው ሰዓት እንጀምር ዘንድ ሰዓት አክብረን እንምጣ።

     የመዝሙር አገልግሎት እና የዜማ     
          ትምህርቶች ሥልጠና ክፍል

ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12

የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12

የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1

የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com
ውድ የጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚ/ቤ/ክ የፍኖተ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት አባላት እና ወዳጆች 

የ2017 ዓ.ም. የገና(የልደት) በዓል ሥጦታን ለምታሰሩት ህንጻ ማጠናቀቂያ የሚሳተፉበት ዘመቻን እስከ ገና ድረስ እናደርጋለን። እነሆ  ለሰንበት ትምህርት ቤታችን  ፍቅራችንን ለመግለጽ ጊዜው አሁን ነው። ሰብአ ሰገል ለተወለደው ንጉስ አምሐን(ሥጦታን) እንዳበረከቱለት እናንተም የጌታችንን ልደት ምክንያት በማድረግ ለሰ/ት/ቤታችን ሕንጻ ማስፈጸሚያ የሚሆን ሥጦታችሁን

የወርቅ ሥጦታ - 1500- 2000 ና ከዚያ በላይ
የዕጣን ሥጦታ - ከ1000- 1500 ብር
የከርቤ ሥጦታ - ከ500-1000 ብር

እንድታስገቡ (እንድትለግሱ)በተወለደው አምላክ  ስም ጥሪያችንን እናቀርባለን::

አምሐ ብላችሁ በመጻፍ

1000375969533
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
51281930205011
      ዳሽን ባንክ

የፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት ሕንጻ አሰሪ

ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12

የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12

የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1

የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com
ልደተ  ክርስቶስ

ታኅሣሥ ሃያ ዘጠኝ በዚህች ቀን የከበረና የተመሰገነ ታላቅ የልደት በዓል ሆነ የጌታችንና የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደባት ዕለት  ናት።

የቤተ ክርስቲያን መምህራን አባቶቻችን የከበረ የልደትን በዓል በሁለት ቀኖች ያከብሩ ዘንድ በምክራቸው ተስማሙ ከወደኋላ ባለ በሃያ ስምንት ሌሊቱ የልደት በዓል ነው በሃያ ዘጠኝ መዓልቱ ጳጉሜን ስድስት በሆነ ጊዜ በዚያች ዓመት የልደት በዓል በሃያ ስምንት በመዓልት ይከበራል። ጳጉሜን አምስት ከሆነ ግን በሃያ ዘጠኝ ይሆናል ስለዚህ የበዓላት ሁሉ ራስ የሆነ የከበረ የልደት በዓል በሁለቱ ቀኖች እንዲከበር አዘዙ ወሠኑ።

የበዓላት ራስ ስለሆነ ስለ ከበረ የልደት በዓል የከበረ ወንጌል እንዲህ አለ። በንጉሡ በኄሮድስ ዘመን በይሁዳ ዕፃ በቤተልሔም ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደ ጊዜ እነሆ የፍልስፍና ሰዎች ከምሥራቅ መጥተው ወደ ኢየሩሳሌም ደረሱ። ኮከቡን በምሥራቅ አይተን እንሰግድለት ዘንድ መጥተናልና የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው እያሉ።

እሊህ ፈላስፎች ከበለዓም ወገን ናቸው እነርሱም በከዋክብት የሚፈላሰፉ ናቸው በመጽሐፋቸው በበለዓም መጽሐፍም የአይሁድ ንጉሥ ሊወለድ እንዳለው ተጽፎአል እርሱ በለዓም ከያዕቆብ ኮከብ ይወጣል ከእስራኤልም ንጉሥ ብሎ ነበርና።

ይቅር ባይ እግዚአብሔርም በረቀቀ ጥበቡ  በሚያምኑበትም ሳባቸው እነርሱ ከዋክብትን በመጠባበቅ የሚፈላሰፉ ናቸውና ይህንንም ኮከብ ገለጠላቸው በአዩትም ጊዜ ደስ አላቸው መልኩ በብዙ አይነት ልውጥ ነውና። ሕፃን የታቀፈች ድንግል ብላቴናን ይመስላል እርሱም በቀን ይጓዛል በሌሊትም ይሠወራል ከሰውም ሲገናኙ ይሠወርና ሲቆሙ በሌላ አንጻር ይገለጥላቸዋል።

እነርሱም ወደ ኢየሩሳሌም ሲደርሱ ያ ኮከብ ተሠወራቸው እጅግ አዘኑ የሚያደርጉትንም አላወቁም ከዚህም በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ ገብተው ስለተወለደው ንጉሥ ጠየቁ።

ንጉሡ ኄሮድስም በሰማ ጊዜ ደነገጠ ኢየሩሳሌምም በመላዋ ከእርሱ ጋር ደነገጠች። የካህናት አለቆችና የሕዝቡን ጸሐፊዎች ሁሉ ሰብስቦ ክርስቶስ በየት ይወለዳል ብሎ ጠየቃቸው። በይሁዳ ዕፃ በቤተልሔም ነው አሉት በነቢይ እንዲህ ተብሎ ተጽፏልና።

የኤፍራታ ዕፃ ቤተልሔም አንቺም ከይሁዳ ነገሥታት አታንሺም ወገኖቼ እስራኤልን የሚጠብቅ ንጉሥ ካንቺ ይወለዳልና። ከዚህም በኋላ ኄሮድስ ሰብአ ሰገልን በጭልታ ጠርቶ ኮከቡ የታየበትን ዘመን ከነሱ ተረዳ።
ሒዳችሁ የዚያን ሕፃን ነገር እርግጡን መርምሩ ያገኛችሁትም እንደሆነ እኔም መጥቼ እሰግድለት ዘንድ በኔ በኩል ተመልሳችሁ ንገሩኝ ብሎ ወደ ቤተልሔም ሰደዳቸው። የነገራቸውንም ሰምተው ከንጉሡ ሔዱ እነሆ በምሥራቅ ያዩት ከከብ ወደ ቤተልሔም እስኪያደርሳቸው ይመራቸው ነበር ሕፃኑ ካለበትም ዋሻ ላይ ደርሶ ቆመ።

ኮከቡንም ባዩ ጊዜ እጅግ ደስ አላቸው ወደ ቤትም በገቡ ጊዜ ሕፃኑን ከእናቱ ከድንግል ማርያም ጋር አገኙት ወድቀውም ሰገዱለት ሣጥናቸውንም ከፍተው ወርቅ ከርቤ ዕጣን እጅ መንሻ አቀረቡለት።

በእግዚአብሔርም ፈቃድ ዮሴፍ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሕፃኑ ጌታ ኢየሱስም በዚያች ዕለት ወደ ቤተልሔም መጡ ስለዚህም ሰብአ ሰገል አገኙአቸው የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያለ ናዝሬት በሌላ ቦታ አላደገምና ከተወለደም ዕድሜው ሁለት ዓመት ሆኖት ነበር።

አምላክ ነውና ስለ መንግሥቱ ወርቅን ገበሩለት ክህነትም ገንዘቡ ነውና ዕጣንን ገብሩለት ማሕየዊ ለሆነ ሞቱ ምልክትም ከርቤን ገበሩለት። ወደ ኄሮድስም እንዳይመለሱ በሕልም ነገራቸው በሌላ መንገድም ወደ አገራቸው ተመልሰው ገቡ። አምላክ በሥጋ ስለመገለጡ ዓዋጅ ነጋሪዎችና ሰባኪዎች ሆኑ።

ይችም ዕለት ነቢዩ ኢሳይያስ ትንቢት ስለርሷ የተናገረላት ናት እንዲህ ብሎ እነሆ ድንግል ፀንሳ ወንድ ልጅን ትወልዳለች ስሙንም ዐማኑኤል ትለዋለች ትርጓሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ነው።

ዳግመኛም ኢሳይያስ እግዚአብሔር እንደ እኔ የሥጋ መጋረጃ በመጋረድ ተገለጸልኝ አለ። አሁንም ደግሞ አዲስ ሰማይ አዲስ ምድር እሠራ ዘንድ አለኝ አለ ሁለተኛም ከዕሴይ ሥር በትር ትወጣለች ከእርሷም ጽጌ አበባ ይወጣል አለ። ዳግመኛም ሕፃን ተወልዶልናልና ወንድ ልጅም ተሰጥቶልናልና ይኸውም ሥልጣን በጫንቃው የሆነ ክርስቶስ ነው። ስሙም ድንቅ መካር የዘላዓለም አባት የሰላም አለቃ ይባላል አለ።

ዳዊትም በመዝሙሩ እንዲህ አለ እግዚአብሔር አንተ ልጄ ነህ ዛሬም በተዋሕዶ ወለድኩህ አለኝ። ለምነኝ አሕዛብን ርስት አድርጌ እሰጥሃለሁ ግዛትህም በመላው ዓለም ነው። ዳግመኛም አብ አለ ቀዳማዊ ወልድ በኃይል ቀን ካንተ ጋራ ሳለሁ ከአጥቢያ ኮከብ በፊት ከሆድ ወለድኩህ እንደ መልከጼዴቅ ሥርዓት አንተ የዓለሙ አገልጋይ ካህን ነህ ብሎ እግዚአብሔር ማለ ከማለም አይጸጸትም።
ቤዛ ይስሐቅ በግዕ ከኅቱም ዕፀ ሳቤቅ እንደተገኘ ለእስራኤልም በበረሀ ውስጥ ከኅቱም አለት ውኃ እንደ ፈለቀ የደነቀች የአሮን በትርም እንደለመለመችና እንደ አፈራች። በሶምሶንም እጅ ውስጥ ከአህያ መንጋጋ አጥንት ውኃ እንደ ፈሰሰ።

እንዲሁ የጌታችን ልደት በኅቱም ድንግልና ሆነ። በዕፀ ጳጦስ ውስጥ እሳት እንደ ነደደች ዕፂቱም እንዳልተቃጠለች እንዲሁ የመለኮቱ እሳት ድንግልን አላቃጠላትም።