የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
2.62K subscribers
6.23K photos
67 videos
79 files
1.72K links
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
Download Telegram
እንኳን ለጾመ ነቢያት አደረሳችሁ

. ጾመ ነቢያት :- ከጌታ ልደት አስቀድሞ የሚጾም ጾም  ሲሆን  ከኅዳር 15 ቀን ጀምሮ  የሚጾም ሲሆን ፋሲካው ፍቺው በልደት በዓል ነው፡፡ ይህም ጾም በዘመነ ብሉይና በዘመነ ሐዲስ ቅዱሳንና ምዕመናን ጾመውታል፡፡

. ጾመ ነቢያት:- ስያሜውን ያገኘው ነቢያት የተናገሩት ትንቢት ስለተፈጸመበት ነው፡፡ በየዘመናቱ የተነሡ ነቢያት እግዚአብሔር ወደፊት ሊያደርግ ያሰበውን በእምነት ዓይን እያዩ ምስጢር ተገልጦላቸው የራቀው ቀርቦ ፣ የረቀቀው ገዝፎ ጎልቶ እየተመለከቱ ትንቢት ተናገሩ ፤ ያዩትም መልካም ነገር እንዲደርስላቸው ጾሙ ጸለዩ፡፡

. ነቢያት ጌታችን ከእመቤታችን ስለ መወለዱ ፥ ወደ ግብፅ ስለ መሰደዱ ፥ በባሕረ ዮርዳኖስ ስለ መጠመቁ ፥ ብርሃን በሆነው ትምህርተ ወንጌል ጨለማውን ዓለም ስለ ማብራቱ ፥ ለሰው ልጆች ድኅነት ጸዋትወ መከራ ስለመቀበሉና ስለ መሰቀሉ ፥ ስለ ትንሣኤው ፥ ስለ ዕርገቱና ስለ ዳግም ምጽአቱ ትንቢት ተናግረው አላቆሙም፡፡ ለአዳም የተሠጠው ተስፋ ተገልጦላቸው ለተናገሩት ትንቢት ፍፃሜ እንዲያደርሳቸው ፈጣሪያቸውን ተማፀኑትም እንጂ፡፡ በየዘመናቸው ፦ "አንሥእ ኃይልከ ፣ ፈኑ እዴከ" እያሉ ጮኹ፡፡ በጾምና በጸሎት ተወስነውም እግዚአብሔር ሰው የሚሆንበትን ጊዜ በቀናት ፣ በሳምንታት ፣ በወራትና በዓመታት ቆጠሩ፡፡  ነቢዩ ኤርምያስ ስለ ሥጋዌው ትንቢት በተናገረ በ446 ዓመት ጌታችን ከእመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሰው ሆኗል፡፡

ነቢያት ተስፋው በዘመናቸው ተፈጽሞ በዓይነ ሥጋ ለማየት ባይችሉም እግዚአብሔር ፦ "አያደርገውን አይናገር የተናገረውን አያስቀር" ብለው አምነው ከወዲሁ ተደሰቱ፡፡ ለዘመነ ሥጋዌ ቅርብ የነበሩ እነ ነቢዩ ኢሳይያስ ጾሙ እንዴት መፈጸም እንዳለበት ተናግረዋልም፡፡  ኢሳ.58÷3
  በመሆኑም በጌታ ልደት ትንቢተ ነቢያት ስለተፈጸመበት ይህ ጾም "የነቢያት ጾም" ይባላል፡፡ የወልደ እግዚአብሔርን ሰው መሆን ያስተማሩበት ስለሆነም "ጾመ ስብከት" ይባላል፡፡

ይህ ጾም ሌሎች የተለያዩ ስያሜዎችም አሉት።

.  ጾመ ማርያም ይባላል :- እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሰማይና ምድር የማይወስኑትን አምላክ ጸንሻለሁ  ምን ሰርቼ እወልደዋለሁ ብላ ጾማለችና ጾመ ማርያም ይባላል።

.  ጾመ ፊሊጶስ  ይባላል :- የአፍራቅያ ሰዎች ሐዋርያው ፊሊጶስን ገደሉት የሐዋርያው ደቀ መዛሙርቱ ሊቀብሩት በፈለጉ ጊዜ ተሰወረባቸው ሱባኤ ያዙ በሶስተኛው ቀን ተገለጸላቸውና ቀበሩት እርሱን ቀብረው ጾሙን እስከ በዓለ ልደት ጾመውታልና ጾመ ፊሊጶስ ይባላል።

ምንጭ:- ፍትሃነገስት አንቀጽ 15

ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12

የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12

የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1

የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com
የማቴዎስ ወንጌልን ንባብ በተሰጠው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት እንዳነበቡ  እናምናለን ።አሁን ደግሞ የማርቆስ ወንጌልን ማንበብ ጀምረናል መልካም የንባብ ጊዜ
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12

የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12

የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1

የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com