የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
2.58K subscribers
6.08K photos
67 videos
60 files
1.7K links
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
Download Telegram
🌑 ሀዘን ዜና
እህታችን እፁብድንቅ አየለ በሰንበት ት/ቤታችን በሕጻናት ክፍል ስታገለግል ቆይታ ባደረባት የልብ ሕመም በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ስትረዳ ቆይታ በትላንትናው ዕለት አርፋለች

👉 ዛሬ ነሐሴ 11 ቀብር ደብረ ኢሚን አቡነ ተክለሃይማኖት በ8:30 ይፈጸማል
👉 ለቤተሰቧቿ መጽናናትን ይስጥልን የምንችል አባላት በቦታው እንገኝ
#ደብረ_ታቦር

ነሐሴ ዐሥራ ሦስት በዚች ቀን ክብር ይግባውና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታላቅና ክቡር በዓል ነው።

በዚች ቀን መድኃኒታችን ሦስቱን ደቀ መዛሙርቶቹን ጴጥሮስን፣ ያዕቆብንና ዮሐንስን ይዞ ወደ ታቦር ተራራ ላይ አወጣቸው። መልኩም በፊታቸው ተለወጠ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ሆነ። ስለ እነርሱም ጌታችን የሰው ልጅ በጌትነቱ ሲመጣ እስከሚያዩት ድረስ በዚህ ከቆሙት መካከል ሞትን የማይቀምሱት አሉ አለ።

ሰዎች ሁሉ እርሱ ለሙሴ ጌታውና ከሞት ያስነሣው እንደሆነ ለኤልያስም ፈጣሪው እንደሆነና ካሳረገበትም ያወረደው እርሱ እንደሆነ ያውቁ ዘንድ እነሆ ከጌታ ከኢየሱስ ጋራ እየተነጋገሩ ሙሴና ኤልያስ ወደርሱ መጡ።

ስለዚህም ጴጥሮስ ጌታችንን እንዲህ አለው አቤቱ በዚህ ትኖር ዘንድ ትወዳለህን ሦስት ሰቀላዎችንም አንድ ላንተ፣ አንድ ለሙሴ፣ አንድ ለኤልያስ እንሠራ ዘንድ።

እንኳን አደረሳችሁ
የወጣት ጉዞ የመጨረሻ ቀን ክፍያ ነሐሴ 23 ነው
ክፍያውን በጽ/ቤት እንዲሁም የሰንበት ት/ቤታችን ልማት ሱቅ ያገኛሉ
👉 ባለትዳር አባላት እፀገነት ጋር ትኬቱ ይገኛል
የዚህ አመት የፍልሰታ ጾም ትርጓሜ በዚህ አበቃ የአመት ሰው ይበለን።

#ፍኖተ_ብርሃን_ሰንበት_ት/ቤት
የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
የዚህ አመት የፍልሰታ ጾም ትርጓሜ በዚህ አበቃ የአመት ሰው ይበለን። #ፍኖተ_ብርሃን_ሰንበት_ት/ቤት
ሱባኤው ከተጀመረበት እስከ ተጠናቀቀበት እስከዛሬዋ እለት ድረስ ደከመኝ፣ ሰለቸኝ ሳትሉ እንደ መተርጉማኑ ሊቃውንት የዓመት ልምዳችንን ለመስማት የራቀብንን አቅርባችሁ እንድንሳተፍ ላደረጋችሁን የICT ክፍል አባላት እግዚአብሔር ድካማችሁን ያስብላችሁ። ቃለ ሕይወት ያሰማችሁ። የሊቃውነወቱን ዋጋ፣ ጸጋ ይስጣችሁ።