የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
2.58K subscribers
6.08K photos
67 videos
60 files
1.7K links
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
Download Telegram
ነሐሴ ፯ (7)
#ጽንሰታ_ለእግዝእትነ_ቅድስት_ድንግል_ማርያም_ወላዲተ_አምላክ

ከጥንት ጀምሮ በአዳም ባሕርይ ውስጥ እንደ ነጭ ዕንቁ የምታበራ የብርሃን እናቱ እግዝእትነ ማርያም በቅዱስ ገብርኤል ብሥራት ነሐሴ ፯ ተፀነሰች፡፡

እንኳን ለባህሪያችን መመኪያ፤ ለቊስላችን የመድኃኒት ሙዳይ፤ ለድኅነታችን መጀመሪያ፤ ለንጽሕናችን መሠረት ለመላእክት እህት ለነቢያት ትንቢት፣ ለሐዋርያት ሞገስ፣ ለሰማዕታት አክሊል፣ ለደናግል መመኪያ፣ ለእኛ ለኃጥአን መመኪያ፣ ለነፍሳችን ነፍስ ለሆነችው፣ ስሟን ጠርተን ከማንጠግባት ክብሯን ስንናገር ያሳነስን መስሎን ለምንሳቀቅላት ከቅድስት ሥላሴ ዘንድ ባለማል ለሆነችን ለቅድስተ ቅዱሳን ለንጽሕተ ንጹሐን ለቅድስት ድንግል ማርያም የጽንሰት በዓል እንኳን አደረሳችሁ፡፡

ዓለም ሳይፈጠር አስቀድሞ በሕሊና አምላክ ታስባ ትኖር የነበረች እመቤታችን የተነገረላት ትንቢት ሊፈጸም የአባት የእናቷ የቅድመ አያቶቿ ራእይ ሊተረጐም ጌታ የፈቀደበት ጊዜ ሲደርስ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል መጥቶ ኢያቄምን ሚስትህ ሐና ትፀንሳለች ደግ ልጅም ትወልዳለች አለው፡፡

ክብርት እናቱን እናት አድርጎ ለሰጠን ለመድኀኔዓለም ክርስቶስ ክብርና ምስጋና ይግባው!
በቃልኪዳኗ በምልጃዋ ይማረን።
👉 በዚህ ሳምንት የቅዳሴ ማርያምን ትርጓሜ በPDF እናቀርብሎታለን መልካም ንባብ
🌑 ሀዘን ዜና
እህታችን እፁብድንቅ አየለ በሰንበት ት/ቤታችን በሕጻናት ክፍል ስታገለግል ቆይታ ባደረባት የልብ ሕመም በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ስትረዳ ቆይታ በትላንትናው ዕለት አርፋለች

👉 ዛሬ ነሐሴ 11 ቀብር ደብረ ኢሚን አቡነ ተክለሃይማኖት በ8:30 ይፈጸማል
👉 ለቤተሰቧቿ መጽናናትን ይስጥልን የምንችል አባላት በቦታው እንገኝ