የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
2.58K subscribers
6.08K photos
67 videos
60 files
1.7K links
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
Download Telegram
🔴 ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳ የነፍስ አርነት መጽሐፍ
👑👑👑👑👑👑👑👑👑
ሰው ሆይ! በእግዚአብሔር አርአያና ምሳሌ የተፈጠርህ መሆንህን አስታውስ። ስለዚህ ስለ ራስህ በተጠየቅህ ጊዜ በሙሉ እምነት "እኔ የእግዚአብሔር አምሳል ነኝ" በማለት ተናገር። አንተ በምድር ላይና ውስጥ ካሉት ሁሉ በላይ ዕውቀትና አንደበት የተሰጠህ የመለኮት ፍጡር ነህ። ከዚህ በተጨማሪ እግዚአብሔርን የማወቅ የማምለክና ደስ የሚያሰኘውን ሁሉ የመረዳት ችሎታ ያለህ ፍጥረት ነህ።

እስቲ ከፍ ካለው ተራራ፤ከታላቁ ባህር፤ከምታበራው ፀሐይና ከምታንጸባርቀው ጨረቃ የምትበልጥ መሆንህን አስብ! አንተ እኮ ስፋት ካለው ምድረ በዳና ከተንጣለለው ሜዳ እንዲሁም በምድር ላይ ያለውን ኃይል ሁሉ ከሚያጠፋው አቶም ትበልጣለህ። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን እነዚህ ሁሉ ያልፋሉ። "ሰማይና ምድር ያልፋሉ" (ማቴ 20፥35)። አንተ የእግዚአብሔር አምሳያ ግን አታልፍም። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማያልፈው ቃሉ የዘለዓለም ሕይወት እንዳለህ ቃል ገብቶልሃልና። ለአንተ በእግዚአብሔር አምሳል ለተፈጠርከው ሰው።
(ዮሐ 4፥4)

ሰው ሆይ! አሁንስ የነፍስህን ዋጋና በእግዚአብሔር ፊት ያላትን ታላቅነት ተመለከትህ? ምንም እንኳ እግዚአብሔር በርኩሳን መናፍስት ሁሉ ላይ ሥልጣን ቢሰጥህም ዲያብሎስ በዚህ ክብርህና ታላቅነትህ ላይ እንደወደደ እንዲቀልድ ትተወዋለህን? አይመስለኝም።

👇👇👇ይጫኑ👇👇👇👇👇
👉https://t.me/finotebirhan12👈
👉https://t.me/finotebirhan12👈
👉https://t.me/finotebirhan12👈
☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️
ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት
🔴የፊታችን እሁድ በ29/2013 ልዩ መርሐግብር ተዘጋጅቶዋል ከ11ሰዓት ጀምሮ
🌑 የሀዘን ዜና
የሰ/ት/ቤታችን አባል የሆነው ወንድማችን ፍቅሬ ወልደጻዲቅ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቶናል።
👉 ቀድሞ በሒሳብ ክፍልና በልዩ ልዩ አገልግሎቶች ተመድቦ ያገለግል የነበረ ነው
👉 ቀብር ዛሬ 9:00 ሰዓት በቅዱስ ዮሴፍ ቤ/ክ

ወንድማችንን ነፍስ በሰላም ያሳርፍልን
ዛሬ 6:30 በሰንበት ት/ቤታችን ንብረት ክፍል ዩኒፎርም በመውሰድ በሀዘኑ ቦታ በመገኝት ወንድማችንን እንቀብራለን
🌑 ሀዘን
የአባላችን የሙሉጌታ ሰማን አባቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል ቀብራቸውም ዛሬ ሰኔ 24 ቀን በ9:00 ሰዓት ቀራንዮ ገብርኤል ስለሆነ የምንችል ሰዎች እንገኝ።
ለወንድማችን መጽናናቱን ይስጥልን
🌑ዜና እረፍት
የወንድማችን መስፍን ታደሰ የባለቤቱ እናት ዛሬ ጠዋት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተውናል።
ቀብር ነገ ማክሰኞ በደብረአሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን ከቀኑ 5:30 ሰዓት የሚፈጸም ይሆናል።
#ሰኔ_30
ሰኔ ሠላሳ በዚች ዕለት ነቢይ ሰማዕትና ሐዋርያ የሆነ #መጥምቁ_ዮሐንስ ተወለደ።

➡️መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ
➭የቅዱሳኑ ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ልጅ
➭በማሕጸን ሳለ መንፈስ ቅዱስ የሞላበት
➭በበርኀ ያደገና በገዳማዊ ቅድስና ያጌጠ
➭እሥራኤልን ለንስሃ ያጠመቀ
➭የጌታችንን መንገድ የጠረገ
➭ጌታውን ያጠመቀና
➭ስለ እውነት አንገቱን የተቆረጠ ታላቅ ሰው ነው::
➡️ስለዚህም ቤተ ክርስቲያን
➫ነቢይ
➫ሐዋርያ
➫ሰማዕት
➫ጻድቅ
➫ገዳማዊ
➫መጥምቀ መለኮት
➫ጸያሔ ፍኖት ብላ ትጠራዋለች
የቅዱስ ዮሐንስ በረከቱ ይደርብን።
መልካሙን ሁሉ የምንሰማበት ዕለት ይሁንልን
#ፍኖተ_ብርሃን_ሰንበት_ት/ቤት
Channel name was changed to «የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)»
9 የሰንበት ትምህርት ቤታችን አባላት ከደብሩ አባቶች እግር ስር ቁጭ ብለው ተምረው ቆይተው የሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁእ አቡነ ቀውስጦስ ሱሉልታ ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን በመሄድ የዲቁና ሥልጣንን ተቀበሉ

በጸሎት አስቡዋቸው
"በጎውን ማን ያሳየናል የሚሉ ብዙ ናቸው" መዝ 4፥6
==============
ዛሬ የሰንበት ት/ቤታችንን ዩኒፎርምና ጥንድ ድርብ በማጠብ የበረከት ስራን ሲሳተፉ የዋሉ ወንድምና እህቶቻችን...

እግዚአብሔር ጉልበታችሁን ይባርክ
በአባቶቻችን ጸሎት ሕንጻ ግንባታው ተጀመረ
==================
በጸሎት፣ በጉልበት፣ በሙያችሁና በሃሳባችሁ አብራችሁን ሁኑ
እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን