🕯🕯🕯የሀዘን መግለጫ🕯🕯🕯
የሰንበት ት/ቤታችን አባል የሆነው የወንድማችን ዲ/ን ፈቃዱ (ትንሹ) እናት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩ በመሆኑ ወንድማችንን በመኖሪያ ቤቱ በመገኘት እንድናጽናና ይሁን።
አድራሻው ጎላ በኤክስትሪም ሆቴል መውጫ

ማስታወቂያ፦
የገድላት እና የድርሳናት ንባብ ከመነበቡ በፊት እና ከተነበበ በኋላ የሚዜም ሲሆን ጸሎት ላይ በቋሚነት አጥንተን የምንሞክረው ይሆናል ዜማዉን ለመያዝ ይረዳ ዘንድ ሰምታችሁ እድትመጡ እናሳስባለን ። የዚህ ዜማ ጥናት ተጀምሯል።
መዝሙር ክፍል

የሰንበት ት/ቤታችን አባል የሆነው የወንድማችን አብረሃም አስራት እናት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። የቀብር ሥነ ሥርዓቱም በአራብሳ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን በ 6:00 ሰዓት የሚፈጸም በመሆኑ የቻልን አባላት ቀብር ላይ በመገኘት ወንድማችንን እንድናጽናና ስንል እንጠይቃልን። ካልቻልን ደግሞ የካ አባዶ በሚገኘው የወንድማችን መኖሪያ ቤት በመገኘት ማጽናናት እንችላለን።
ነፍስ ይማር!

⚫️ ሀዘን..
10/09/2013 ዓ.ም
የወንድማችን የወንድምዬ አዋሽ አባት ያረፉ ስለሆነ ቀብር 9:00 ሰዓት ለቡ በሚገኘው ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ገብርኤል መሆኑ ከወዳጅ ዘመዶቹ ስለደረሰን በተጠቀሰው ሰዓት እና ቦታ እንገናኝ
ለወንድማችን መጽናናቱን ይስጥልን
አሜን

🔵🔴 እንኳን ለታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።
††† ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ †††
ሊቀ ሊቃውንት እዝራ ሐዲስ እንደሚሉት:- "ቅዱስ ያሬድ ለኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከራስ ጸጉሯ እስከ እግር ጥፍሯ : ሙሉ አካሏ ነው::"
††† የሊቁ ዜና ሕይወት በጥቂቱ †††
††† ቅዱስ ያሬድ የተወለደው በ505 ዓ/ም አክሱም አካባቢ ሲሆን እናቱ ክርስቲና (ታኡክልያ) አባቱ ደግሞ ይስሐቅ (አብድዩ) ይባላሉ:: ሊቁ በሕጻንነቱ ምሥጢር (ትምሕርት) አልገባው ብሎ ይቸገር ነበር:: ትምህርት እንቢ ያለው ሰነፍ ስለ ነበር አይደለም በጥበበ እግዚአብሔር እንጂ::
ምን ትምህርት ባይገባው ጾምና ጸሎትን ያዘወትር ነበር:: ልቡናው ደግሞ በእመቤታችንና በልጇ ፍቅር የታሠረ ነበር አንድ ቀን ግን መምሕሩ የነገሩት ቀለም አልያዝሕ አለው ሲፈትኑትም ባለመመለሱ ተገረፈ::
ዱላው በጣም ስለ ተሰማው ቅዱሱ ከመምህሩ ኮብልሎ ማይ ኪራሕ አካባቢ ሲደርስ ደክሞት አርፎ እግዚአብሔር ትጋትንና ተስፋ አለመቁረጥን ከትል አስተማረው ትሏ ስድስት ጊዜ ወድቃ በሰባተኛው ፍሬዋን ስትበላት ተመልክቷልና::
ከዚህ በኋላ ቅዱስ ያሬድ ወደ መምሕሩ ተመልሶ ይቅርታ ጠይቆ ትምሕርት ጀመረ ሊቁም ትጋትንና ጸሎትን ከሰጊድ ጋር አበዛ እግዚአብሔር ደግሞ በድንግል እናቱ አማካኝነት የምሥጢር ጽዋን አጠጣው::
ካህኑ ያሬድ እንዲያ አልገባህ ያለው ምስጢር ተገልጦለት በጥቂት ጊዜ ብሉይን ከሐዲስ በምሥጢር ባሕርም ይዋኝ ጀመር::
ያን ጊዜ ሰማያዊ ዜማ አልተገለጠም ነበርና በጸሎት ላይ ሳለ ተደሞ መጣበት ሦስት መላእክት በሦስት ወፎች አምሳል መጥተው አነጋገሩት ድንገትም ነጥቀው ወደ ሰማያት ወደ ልዑላኑ መላእክት ዘንድ አደረሱት ሊቁ በሰማያት ልዩ ምሥጢር ልዩ ምስጋናና ልዩ ዜማን አዳመጠ ይሕንን ምስጋና ብዙ ቅዱሳን ቢሰሙትም ቅዱስ ያሬድ ግን ይዞት እንዲወርድ ተፈቀደለት::
ሊቁ ወደ ምድር ተመልሶ በታላቅ ተመስጦ አክሱም ጽዮን ውስጥ በሃሌታ አመሰገነ ሕዝቡና ንጉሡም ከጣዕሙ የተነሳ አደነቁ:: ቅዱስ ያሬድ ለተወሰነ ጊዜ በአክሱምና ደብረ ዳሞ ሲያገለግል ቆይቶ ከመሬት ክንድ ከስንዝር ከፍ ብሎ ለእመቤታችን አንቀጸ ብርሃንን ደርሶላት ከሃገሩ ወጣ::
††† ቅዱስ ያሬድ በቀሪ የሕይወቱ ዘመናት:-
1. አምስት ያሕል መጻሕፍትን ጽፏል::
2. በጣና ቂርቆስ : በዙር አባና በሌሎችም ቦታዎች ወንበር ዘርግቶ ብዙ ደቀ መዛሙርትን አፍርቷል::
3.በሰሜን ተራሮች አካባቢ በትጋሃ መላእክትና በተባሕትዎ ኑሯል::
††† በ576 (571) ዓ/ም በተወለደ በ71 ዓመቱ በዚህች ቀን ተሰውሯል::
🔵🔴 ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት

✞ 💚 💛 ❤️ ግንቦት 12 የሚከበሩ በዓላት
✞ 🔴ግንቦት 12 ፍልሰተ አፅሙ ለተክለሀይማኖት
የአባታቸንና የኢትዮጵያ ፀሀይ የፃድቁ የተክለሀይማኖት የዐፅሙ ፍልሰት ክብረ በዓል ግንቦት ፲፪ ከደብረ አሰቦ ወደ ደብረ ሊባኖስ አጽማቸው የፈለሰበት(ፍልሰተ አጽም) በዓለ ንግስናቸው ይከበራል።
የፃድቁ የአባታችን የተክለሀይማኖት በረከት በሁላችን ላይ ይደር፤ አገራችን ኢትዮጵያን ደግሞ ከክፉ ይጠብቃት፤ አሜን!!
✞ 🔴ግንቦት 12 በዚህች ቀን ደገኛው አባት ዮሐንስ አፈወርቅ አረፈ፡፡
“ዮሐንስ” የእብራይስጥ ቋንቋ ሲሆን ትርጓሜውም ፍስሐ ወ ሐሴት ርህራሄ ወሳህል :-: ፍፁም ደስታ ደግነት ይቅርታ ማለት ነው፡፡
✞ 🔴የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ወርሃዊ መታሰቢያ
✞ 🔴ግንቦት 12 ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ የልደቷ መታሰቢያ በዓል ነው
✞ 💚 💛 ❤️ ✞
@finotebirhan12
@finotebirhan12
@finotebirhan12
ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት

13/09/2013 ዓ.ም
የወንድማችን የነቢዩ ኤልያስ አያት ያረፉ ስለሆነ ቀብር ከ5:00 - 6:00 ሰዓት በደብረ አሚን ቅዱስ ተክለሃይማኖት መሆኑ ከወዳጅ ዘመዶቹ ስለደረሰን በተጠቀሰው ሰዓት እና ቦታ ተገኝተን ወንድማችንን እንድናጽናና ይሁን።
ለወንድማችን እና ለቤተሰቡ መጽናናቱን ይስጥልን
አሜን።

🔴 ይህንን ያውቃሉ...
የመንፈስ ቅዱስና የ12ቱ ሐዋርያት ጽላት
በጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን እንዳለ ያውቃሉ ??
የቤተ ክርስቲያን የልደት ቀን
በዓለ ጰራቅሊጦስ
በበዓለ ጰራቅሊጦስ ሙሉው የትንሳኤ ቀለም ሳይጓደል ይደርሳል ነፍስን የሚያስደስተው ሌሊቱ እንደ ደቂቃ ሳይታሰብ የሚያልፈው በዚህ ቀን ነው ስለዚህ ይህ ለሐዋርያት የወረደ የመንፈስ ቅዱስ በረከት ተካፋይ ለመሆን በአዲስ አበባ ያላችሁ በጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን በመገኘት የበዓሉ በረከት ተካፋይ ሁኑ ላልሰሙትም ሁሉ በማሰማት ቀጠሯችሁን በዚያ አድርጉ በዓሉ የሚከበረው ሰኔ 13 ቀን 2013 ዓ.ም ነውና መልእክቱን ሼር ያድርጉ ተያይዞም ሰኔ 12 የቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል ነው
የደብሩ ስብከተ ወንጌል
ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት
በደብሩ የሚገኙ መንፈሳዊ ማህበራት ጋር በመሆን ከሰኔ 11 - 13 የሚጀምር ልዩ የአውደ ምህረት መርሐግብር ተዘጋጅቷል
ላልሰሙትም ሁሉ በማሰማት ቀጠሯችሁን በዚያ አድርጉ

ግንቦት 21 እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በግብፅ ደብረ ምጥማቅ በተባለች ቦታ ለክርስቲያኑም ለአህዛቡም ቅዱሳን መላእክትን፣ ጻድቃንንና ሰማዕታትን አስከትላ በወርቅ ወንበር ላይ ተቀምጣ በክብር ለ5 ተከታታይ ቀናት የተገለጠችበት ታላቅ እለት ነው።
ይህች ቦታ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር በሄሮድስ ምክንያት በተሰደደ ጊዜ ያረፉባት ቦታ ነበረች ቦታውን ባርኮ ለዘለዓለም የአንቺ መገለጫ ይሁን ብሎ ቃል ኪዳን ገብቶላታል።
በእውነት በዚህ ክፉ ጊዜም የእመቤታችን መገለጥ ከምን ጊዜውም በላይ ያስፈልገናልና እመ ብርሃን በክብር ተገልጣ አይዟችሁ ትበለን ጣዕመ ስሟን በአንደበታችን፣ ጣዕመ ፍቅሯን በልቡናችን ታሳድርብን። አሜን

🔴በዚህች ዕለት ግንቦት 26 ቀንም የአቡነ ሀብተ ማርያም ልደቱ ነው፡፡ አቡነ ሀብተ ማርያም ነሐሴ 26 ተጸነሶ ከአባታቸው ፍሬ ቡሩክና ከእናታቸው ቅድስት ዮስቴና ግንቦት 26 ተወለዱ፡፡
ጻድቁ አባታችን፤
#በማዕጠንቱ የታወቀ፤
#በጽድቅ ሥራው የተደነቀ፤
#አምስት መቅሰፍቶችን ቃል ኪዳን ተገብቶላቸዋል
፩ኛ. #መብረቅ፣
፪ኛ. #ቸነፈር፣
፫ኛ. #ረሃብ፣
፬ኛ. #ወረርሽኝ፣
፭ኛ. #የእሳት ቃጠሎ የማስወገድ ቃል ኪዳን የተሰጠው ነው፡፡
እኛንም በጻድቁ አቡነ ሀብተ ማርያም ጸሎትና አማልጅነት ይማረን አሜን፡፡
መልካሙን ሁሉ የምንሰማበትና የምናይበት ቀን ይሁንልን
#ፍኖተ_ብርሃን ሰንበት ት/ቤት
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/finotebirhan12

🔴 ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳ የነፍስ አርነት መጽሐፍ
👑👑👑👑👑👑👑👑👑
ሰው ሆይ! በእግዚአብሔር አርአያና ምሳሌ የተፈጠርህ መሆንህን አስታውስ። ስለዚህ ስለ ራስህ በተጠየቅህ ጊዜ በሙሉ እምነት "እኔ የእግዚአብሔር አምሳል ነኝ" በማለት ተናገር። አንተ በምድር ላይና ውስጥ ካሉት ሁሉ በላይ ዕውቀትና አንደበት የተሰጠህ የመለኮት ፍጡር ነህ። ከዚህ በተጨማሪ እግዚአብሔርን የማወቅ የማምለክና ደስ የሚያሰኘውን ሁሉ የመረዳት ችሎታ ያለህ ፍጥረት ነህ።
እስቲ ከፍ ካለው ተራራ፤ከታላቁ ባህር፤ከምታበራው ፀሐይና ከምታንጸባርቀው ጨረቃ የምትበልጥ መሆንህን አስብ! አንተ እኮ ስፋት ካለው ምድረ በዳና ከተንጣለለው ሜዳ እንዲሁም በምድር ላይ ያለውን ኃይል ሁሉ ከሚያጠፋው አቶም ትበልጣለህ። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን እነዚህ ሁሉ ያልፋሉ። "ሰማይና ምድር ያልፋሉ" (ማቴ 20፥35)። አንተ የእግዚአብሔር አምሳያ ግን አታልፍም። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማያልፈው ቃሉ የዘለዓለም ሕይወት እንዳለህ ቃል ገብቶልሃልና። ለአንተ በእግዚአብሔር አምሳል ለተፈጠርከው ሰው።
(ዮሐ 4፥4)
ሰው ሆይ! አሁንስ የነፍስህን ዋጋና በእግዚአብሔር ፊት ያላትን ታላቅነት ተመለከትህ? ምንም እንኳ እግዚአብሔር በርኩሳን መናፍስት ሁሉ ላይ ሥልጣን ቢሰጥህም ዲያብሎስ በዚህ ክብርህና ታላቅነትህ ላይ እንደወደደ እንዲቀልድ ትተወዋለህን? አይመስለኝም።
👇👇👇ይጫኑ👇👇👇👇👇
👉https://t.me/finotebirhan12👈
👉https://t.me/finotebirhan12👈
👉https://t.me/finotebirhan12👈
☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️