የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
2.58K subscribers
6.1K photos
67 videos
60 files
1.7K links
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
Download Telegram
​​የሰ/ት/ቤታችን ልማት ክፍል እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት በሰላም አደረሳችሁ እያለ ለበዓሉ ማክበሪያ ይሆን ዘንድ ኃይማኖቱን እና ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ የጌታችንን ግርግም በተመጣጣኝ ዋጋ አቅርቦላችኋል።
ውድ የቻናላችን ተከታታዮች ቻናላችንን ለወዳጆቻችሁ በማጋራት እንዲቀላቀሉ አግዙን።

እናመሰግናለን!!!!


@finotebirhan12
​​🙏🙏🙏🙏🙏
የማደርገውን አላውቅምና፤ የምጠላውን ያን አደርጋለሁና ዳሩ ግን የምወደውን እርሱን አላደርገውም።የማልወደውን ግን የማደርግ ከሆንሁ ሕግ መልካም እንደ ሆነ እመሰክራለሁ። እንደዚህ ከሆነ ያን የማደርገው አሁን እኔ አይደለሁም፥ በእኔ የሚያድር ኃጢአት ነው እንጂ።

♦️♦️ #ሮሜ 7 : 15 -17
ዜና ዕረፍት

የወንድማችን ሚሊዮን ሽርጋ አባት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ቀብር ቀጨኔ መድኃኔዓለም ቤ/ክ 9፡00 ላይ ነው። ቀብር መድረስ ያልቻልን ቤታቸው ፍልውሃ አካባቢ ስለሆነ ሄደን እንድናጽና ይሁን።

የአባታችንን ነፍስ ይማርልን።
ለቤተሰቦቻቸውም መጽናናቱን ያድልልን።
የሰንበት ት/ቤቱ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት።
⬇️
#ታሕሳስ 28 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=

1.አማኑኤል አምላካችን
2.በዓለ ጌና ስቡሕ
3.ዕለተ ማርያም ድንግል
4."174" ሰማዕታት (የቅዱስ ዻውሎስ ማሕበር)

#ወርኀዊ በዓላት

1.ቅዱሳን (አብርሃም: ይስሐቅና ያዕቆብ)
2.ቅዱስ እንድራኒቆስና ሚስቱ ቅድስት አትናስያ
3.ቅድስት ዓመተ ክክርስቶስ
4.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ
5.ቅዱስ አባዲርና ቅድስት ኢራኢ
​​እንኳን ለጌታችን ለአምላካችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት በሰላም አደረሰን።
⬆️
የሰ/ት/ቤታችን የእንኳን አደረሰን መልዕክት
​​💠 ነፍስ የሌለው ሥጋ የሞተ እንደሆነ እንዲሁ ፀሎትን የማደታደርግ ነፍስ ሕይወት የላትም፡፡
/ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
#ጥር 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

1.ቅዱስ እስጢፋኖስ ቀዳሜ ሰማዕት (ሊቀ ዲያቆናት)
2.ቅዱሳን ሰማዕታተ አክሚም
3.ቅዱሳን ዲዮስቆሮስ ወሰከላብዮስ
4.ቅዱስ ለውንድዮስ ሰማዕት
5.አባ መቃርስ ሊቀ ዻዻሳት

#ወርኀዊ በዓላት

1.ልደታ ለማርያም ድንግል እግዝእትነ
2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
3.ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
4.ቅዱስ ሚልኪ ትሩፈ ምግባር
5.ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላእክት
​​እንኳን ለቀዳሚ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሰን።

#ጥር_1

💠የቅዱስ እስጢፋኖስ የልደቱም የዕረፍቱም ቀን ነው።

#የስሙ_ትርጉም

💠 ወደብ፣ ጸጥታ ማለት ነው።

#ለምን_ሊቀ_ዲያቆናት_ተባለ?

💠 በሐዋርያት እጅ ከተሾሙት 7 ዲያቆናት ውስጥ የሁሉም አለቃ ስለሆነ።

#ለምን_ቀዳሚ_ሰማዕት_ተባለ ?

💠 ከጌታችን ዕርገት በኋላ ስለ ጌታችን መውረድ መወለድ መስክሮ ስለሞተ።

#ሰማዕትነት_እንዴት_ተቀበለ ?

💠 ሐዋ ም 6 ቁ 8 ጀምሮ እንዲህ ይላል

እስጢፋኖስም ጸጋንና ኃይልን ተሞልቶ በሕዝቡ መካከል ድንቅንና ታላቅ ምልክትን ያደርግ ነበር። የነፃ ወጪዎች ከተባለችው ምኵራብም ከቀሬናና ከእስክንድርያም ሰዎች ከኪልቅያና ከእስያም ከነበሩት አንዳንዶቹ ተነሥተው እስጢፋኖስን ይከራከሩት ነበር፤ ይናገርበት የነበረውንም ጥበብና መንፈስ ይቃወሙ ዘንድ አልቻሉም። በዚያን ጊዜ በሙሴ ላይ በእግዚአብሔርም ላይ የስድብን ነገር ሲናገር ሰምተነዋል የሚሉ ሰዎችን አስነሡ። ሕዝቡንና ሽማግሌዎችንም ጻፎችንም አናደዱ፥ ቀርበውም ያዙት ወደ ሸንጎም አመጡትና። ይህ ሰው በዚህ በተቀደሰው ስፍራ በሕግም ላይ የስድብን ነገር ለመናገር አይተውም፤ ይህ የናዝሬቱ ኢየሱስ ይህን ስፍራ ያፈርሰዋል ሙሴም ያስተላለፈልንን ሥርዓት ይለውጣል ሲል ሰምተነዋልና የሚሉ የሐሰት ምስክሮችን አቆሙ። በሸንጎም የተቀመጡት ሁሉ ትኵር ብለው ሲመለከቱት እንደ መልአክ ፊት ሆኖ ፊቱን አዩት።

ይልና ወረድ ብሎ ም 7 ቁ 51 ላይ እንዲህ ይላል

እናንተ አንገተ ደንዳኖች ልባችሁና ጆሮአችሁም ያልተገረዘ፥ እናንተ ሁልጊዜ መንፈስ ቅዱስን ትቃወማላችሁ፤ አባቶቻችሁ እንደ ተቃወሙት እናንተ ደግሞ። ከነቢያትስ አባቶቻችሁ ያላሳደዱት ማን ነው? የጻድቁንም መምጣት አስቀድሞ የተናገሩትን ገደሉአቸው፤ በመላእክት ሥርዓት ሕግን ተቀብላችሁ ያልጠበቃችሁት እናንተም አሁን እርሱን አሳልፋችሁ ሰጣችሁት ገደላችሁትም። ይህንም በሰሙ ጊዜ በልባቸው በጣም ተቈጡ ጥርሳቸውንም አፋጩበት። መንፈስ ቅዱስንም ተሞልቶ ወደ ሰማይ ትኵር ብሎ ሲመለከት የእግዚአብሔርን ክብር ኢየሱስንም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አየና። እነሆ፥ ሰማያት ተከፍተው የሰው ልጅም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አያለሁ አለ። በታላቅ ድምፅም እየጮኹ ጆሮአቸውን ደፈኑ፥ በአንድ ልብ ሆነውም ወደ እርሱ ሮጡ፥ ከከተማም ወደ ውጭ አውጥተው ወገሩት። ምስክሮችም ልብሳቸውን ሳውል በሚሉት በአንድ ጎበዝ እግር አጠገብ አኖሩ። እስጢፋኖስም ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ነፍሴን ተቀበል ብሎ ሲጠራ ይወግሩት ነበር። ተንበርክኮም ጌታ ሆይ፥ ይህን ኃጢአት አትቍጠርባቸው ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህንም ብሎ አንቀላፋ። ሳውልም በእርሱ መገደል ተስማምቶ ነበር።

በረከቱ ይደርብን!!
#ጥር 2 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

1.ቅዱስ አቤል ጻድቅ
2.ቅዱስ ቴዎናስ ሊቀ ዻዻሳት
3.ቅዱስ አላኒቆስ ሰማዕት
4.ቅድስት ሳቤላ ነቢዪት
5.ቅዳሴ ቤታ ለድንግል (በደብረ አባ ሲኖዳ)

#ወርኀዊ በዓላት

1.ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ
2.ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ ተአጋሲ
3.ቅዱስ አባ ዻውሊ ገዳማዊ (ታላቁ)
4.ቅዱስ ዮሐንስ ነቢይ (መጥምቀ መለኮት)
5.ሊቁ አባ ሕርያቆስ
6.ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ