ለፍኖተ ብርሃን አባላት በሙሉ
የጠቅላላ ጉባኤ አባላት ስብሰባን ይመለከታል።
ታህሳስ 18 እና 24 በተደረጉ ስብሰባዎች መተዳደሪያ ደንባችን ላይ ውይይት ማድረጋችን ይታወሳል።
ሆኖም በነበሩት የመርሐግብር መጨናነቆች ስብሰባውና ውይይቱን ለማራዘም ተገደን ነበረ።
ስለሆነም የፊታችን ቅዳሜ የካቲት 13 እና እሑድ የካቲት 21 ቀን 2013 ዓ·ም ከ11:30 እስከ 1:00 ሰዓት ድረስ ተመሳሳይ መርሐግብር የሚኖር በመሆኑ እንድትገኙ እናሳስባለን።
የፍኖተ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ጽ/ቤት

የሀዘን መግለጫ 😭😭😭
የሰንበት ት/ቤታችን አባል የሆነችው ወጣት አየሉ ወንድሟ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። ቀብር ቀጨኔ መድኃኔዓለም በ9:00 ሰዓት የሚፈጸም ይሆናል። ወነድማችንን ነፍሱን ይማርልን። ለቤተሰቦቹም መጽናናትን ያድልልን።

🕯🕯🕯የሀዘን መግለጫ🕯🕯🕯
የሰንበት ት/ቤታችን አባል የሆነው የወንድማችን ሱራፌል ተክሌ አያት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። የቀብር ሥነ ሥርዓቱም በዓለም ባንክ ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን በ 5:00 ሰዓት የሚፈጸም በመሆኑ የቻልን አባላት ቀብር ላይ በመገኘት ወንድማችንን እንድናጽናና ስንል እንጠይቃልን።

የሰንበት ት/ቤታችን አባል የሆነው የወንድማችን ዲ/ን ፈቃዱ (ትንሹ) እናት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩ በመሆኑ ወንድማችንን በመኖሪያ ቤቱ በመገኘት እንድናጽናና ይሁን።
አድራሻው ጎላ በኤክስትሪም ሆቴል መውጫ

ማስታወቂያ፦
የገድላት እና የድርሳናት ንባብ ከመነበቡ በፊት እና ከተነበበ በኋላ የሚዜም ሲሆን ጸሎት ላይ በቋሚነት አጥንተን የምንሞክረው ይሆናል ዜማዉን ለመያዝ ይረዳ ዘንድ ሰምታችሁ እድትመጡ እናሳስባለን ። የዚህ ዜማ ጥናት ተጀምሯል።
መዝሙር ክፍል

የሰንበት ት/ቤታችን አባል የሆነው የወንድማችን አብረሃም አስራት እናት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። የቀብር ሥነ ሥርዓቱም በአራብሳ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን በ 6:00 ሰዓት የሚፈጸም በመሆኑ የቻልን አባላት ቀብር ላይ በመገኘት ወንድማችንን እንድናጽናና ስንል እንጠይቃልን። ካልቻልን ደግሞ የካ አባዶ በሚገኘው የወንድማችን መኖሪያ ቤት በመገኘት ማጽናናት እንችላለን።
ነፍስ ይማር!

⚫️ ሀዘን..
10/09/2013 ዓ.ም
የወንድማችን የወንድምዬ አዋሽ አባት ያረፉ ስለሆነ ቀብር 9:00 ሰዓት ለቡ በሚገኘው ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ገብርኤል መሆኑ ከወዳጅ ዘመዶቹ ስለደረሰን በተጠቀሰው ሰዓት እና ቦታ እንገናኝ
ለወንድማችን መጽናናቱን ይስጥልን
አሜን

🔵🔴 እንኳን ለታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።
††† ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ †††
ሊቀ ሊቃውንት እዝራ ሐዲስ እንደሚሉት:- "ቅዱስ ያሬድ ለኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከራስ ጸጉሯ እስከ እግር ጥፍሯ : ሙሉ አካሏ ነው::"
††† የሊቁ ዜና ሕይወት በጥቂቱ †††
††† ቅዱስ ያሬድ የተወለደው በ505 ዓ/ም አክሱም አካባቢ ሲሆን እናቱ ክርስቲና (ታኡክልያ) አባቱ ደግሞ ይስሐቅ (አብድዩ) ይባላሉ:: ሊቁ በሕጻንነቱ ምሥጢር (ትምሕርት) አልገባው ብሎ ይቸገር ነበር:: ትምህርት እንቢ ያለው ሰነፍ ስለ ነበር አይደለም በጥበበ እግዚአብሔር እንጂ::
ምን ትምህርት ባይገባው ጾምና ጸሎትን ያዘወትር ነበር:: ልቡናው ደግሞ በእመቤታችንና በልጇ ፍቅር የታሠረ ነበር አንድ ቀን ግን መምሕሩ የነገሩት ቀለም አልያዝሕ አለው ሲፈትኑትም ባለመመለሱ ተገረፈ::
ዱላው በጣም ስለ ተሰማው ቅዱሱ ከመምህሩ ኮብልሎ ማይ ኪራሕ አካባቢ ሲደርስ ደክሞት አርፎ እግዚአብሔር ትጋትንና ተስፋ አለመቁረጥን ከትል አስተማረው ትሏ ስድስት ጊዜ ወድቃ በሰባተኛው ፍሬዋን ስትበላት ተመልክቷልና::
ከዚህ በኋላ ቅዱስ ያሬድ ወደ መምሕሩ ተመልሶ ይቅርታ ጠይቆ ትምሕርት ጀመረ ሊቁም ትጋትንና ጸሎትን ከሰጊድ ጋር አበዛ እግዚአብሔር ደግሞ በድንግል እናቱ አማካኝነት የምሥጢር ጽዋን አጠጣው::
ካህኑ ያሬድ እንዲያ አልገባህ ያለው ምስጢር ተገልጦለት በጥቂት ጊዜ ብሉይን ከሐዲስ በምሥጢር ባሕርም ይዋኝ ጀመር::
ያን ጊዜ ሰማያዊ ዜማ አልተገለጠም ነበርና በጸሎት ላይ ሳለ ተደሞ መጣበት ሦስት መላእክት በሦስት ወፎች አምሳል መጥተው አነጋገሩት ድንገትም ነጥቀው ወደ ሰማያት ወደ ልዑላኑ መላእክት ዘንድ አደረሱት ሊቁ በሰማያት ልዩ ምሥጢር ልዩ ምስጋናና ልዩ ዜማን አዳመጠ ይሕንን ምስጋና ብዙ ቅዱሳን ቢሰሙትም ቅዱስ ያሬድ ግን ይዞት እንዲወርድ ተፈቀደለት::
ሊቁ ወደ ምድር ተመልሶ በታላቅ ተመስጦ አክሱም ጽዮን ውስጥ በሃሌታ አመሰገነ ሕዝቡና ንጉሡም ከጣዕሙ የተነሳ አደነቁ:: ቅዱስ ያሬድ ለተወሰነ ጊዜ በአክሱምና ደብረ ዳሞ ሲያገለግል ቆይቶ ከመሬት ክንድ ከስንዝር ከፍ ብሎ ለእመቤታችን አንቀጸ ብርሃንን ደርሶላት ከሃገሩ ወጣ::
††† ቅዱስ ያሬድ በቀሪ የሕይወቱ ዘመናት:-
1. አምስት ያሕል መጻሕፍትን ጽፏል::
2. በጣና ቂርቆስ : በዙር አባና በሌሎችም ቦታዎች ወንበር ዘርግቶ ብዙ ደቀ መዛሙርትን አፍርቷል::
3.በሰሜን ተራሮች አካባቢ በትጋሃ መላእክትና በተባሕትዎ ኑሯል::
††† በ576 (571) ዓ/ም በተወለደ በ71 ዓመቱ በዚህች ቀን ተሰውሯል::
🔵🔴 ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት