የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
2.58K subscribers
6.08K photos
67 videos
60 files
1.7K links
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
Download Telegram
​​🔳🔳🔳🔳 ግንቦት ፩ 🔳🔳🔳🔳

አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች ክብርት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚኽች ዕለት ተወለደች፡፡

የክብርት እመቤታችን ልደት ለሰማያውያን መላእክትና ለአዳም ልጆች ሁሉ ታላቅ ደስታ ሆነልን

እንኳን አደረሳችሁ
ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት
​​#ሰኔ 4

በዚችም ዕለት በልኪም ከሚባል አገር ሳኑሲ በሰማዕትነት ሞተ፡፡
በዚችም ዕለት ሐራቅሏ ከሚባል ሀገር ቅዱስ አባት ዮሐንስ አረፈ፡፡
በዚችም ዕለትየአርቃድዮስ የእኅቱ የዲሙናስያ የግብጻውያኑ የአሞኒና የሚናስ የንጉስ ዲዮቅልጢያኖስ ጭፍሮችም የገድላቸው ፍጻሜ ሆነ፡፡
በዚችም ዕለት በከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ ዘመን ተጋዳይ የሆነች ቅድስት ሶፍያ አንገቷን በመቆረጥ በሰማዕትነት አረፈች፡፡
በዚችም ዕለት የአባ አሞንና የሚናስ መታሰቢያቸው ሆነ፡፡

#ወርኀዊ በዓል

#ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ (ወንጌላዊው ) ፣አባ #መቃርዎስ፣ አባ #አብርሐ
ከሰንበት ት/ቤታችን ጋር በመተባበር በማህበረ ቅዱሳን የሬዲዮ ጣቢያ ላይ የተዘጋጀ
​​" ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ።"
(ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5: 16)

የተከበራችሁ የሰንበት ት/ቤታችን ባለትዳር አባላት። በኮሮና በሽታ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው ወርሐዊ ጉባኤያችን የፊታችን እሑድ 03/12/12 አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ የምንጀምር መሆኑን በመግለፅ እንዲገኙ በአክብሮት ጠርተናችኋል።
በእለቱ
1. የዘወትር ጸሎት
2. ጸሎተ ወንጌል
3. ትምህርተ ወንጌል ይኖረናል።

"...ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤..."
(የማቴዎስ ወንጌል 17: 4)