Channel name was changed to «ፍኖተ ብርሃን(Official Channel)»
አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማኝ፥ ጩኸቴም ወደ አንተ ይድረስ። በመከራዬ ቀን ፊትህን ከኔ አትመልስ፤ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፤ በጠራሁህ ቀን ፈጥነህ ስማኝ። ዘመኔ እንደ ጢስ አልቃለችና፥ አጥንቶቼም እንደ መቃጠያ ተቃጥለዋልና። እህል መብላት ተረስቶኛልና ተቀሠፍሁ ልቤም እንደ ሣር ደረቀ። ከጩኸቴ ድምፅ የተነሣ አጥንቶቼ ከሥጋዬ ጋር ተጣበቁ።እንደ ምድረ በዳ እርኩም መሰልሁ፤ በፈረሰ ቤት እንዳለ እንደ ጕጕት ሆንሁ። ተጋሁ፥ በሰገነትም እንደሚኖር ብቸኛ ድንቢጥ ሆንሁ። ጠላቶቼ ሁልጊዜ ይሰድቡኛል፥ የሚያሳድዱኝም ተማማሉብኝ። አመድን እንደ እህል ቅሜአለሁና፥ መጠጤንም ከእንባዬ ጋር ቀላቅያለሁና፥ ከቍጣህና ከመዓትህም የተነሣ፤ አንሥተኸኛልና፥ ጥለኸኝማልና። ዘመኖቼ እንደ ጥላ አዘንብለዋል፤ እኔም እንደ ሣር ደርቄአለሁ።
አንተ ግን፥ አቤቱ፥ ለዘላለም ትኖራለህ፥ መታሰቢያህም ለልጅ ልጅ ነው። አንተ ተነሥ ጽዮንንም ይቅር በላት፥ የምሕረትዋ ጊዜ ነውና፥ ዘመንዋም ደርሶአልና፤ ባሪያዎችህም ድንጋዮችዋን ወድደዋልና፥ ለመሬትዋም አዝነዋልና። አቤቱ፥ አሕዛብ ስምህን፥ ነገሥታትም ሁሉ ክብርህን ይፈራሉ፤ እግዚአብሔር ጽዮንን ይሠራታልና፥ በክብሩም ይገለጣልና። ወደ ችግረኞች ጸሎት ተመለከተ፥ ልመናቸውንም አልናቀም።
ይህ ለሚመጣ ትውልድ ይጻፍ፥ የሚፈጠርም ሕዝብ ለእግዚአብሔር እልል ይላል፤ እግዚአብሔር ከመቅደሱ ከፍታ ሆኖ ተመልክቶአልና፥ ከሰማይ ሆኖ ምድርን አይቶአልና፤ የእስረኞችን ጩኸት ይሰማ ዘንድ፥ ሊገድሉ የተፈረደባቸውን ያድን ዘንድ፤ የእግዚአብሔርን ስም በጽዮን ምስጋናውንም በኢየሩሳሌም ይናገሩ ዘንድ፤ አሕዛብ በአንድነት በተሰበሰቡ ጊዜ መንግሥታትም ለእግዚአብሔር ይገዙ ዘንድ። በኃይሉ ጎዳና መለሰለት። የዘመኔን አነስተኛነት ንገረኝ።በዘመኔ እኵሌታ አትውሰደኝ፤ ዓመቶችህ ለልጅ ልጅ ናቸው።
አቤቱ፥ አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ፥ ሰማያትም የእጅህ ሥራ ናቸው። እነርሱ ይጠፋሉ፥ አንተ ግን ትኖራለህ፤ ሁላቸው እንደ ልብስ ያረጃሉ፥ እንደ መጐናጸፊያም ትለውጣቸዋለህ፥ ይለወጡማል፤ አንተ ግን ያው አንተ ነህ፥ ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም። የባሪያዎችህም ልጆች ይኖራሉ፥ ዘራቸውም ለዘላለም ትጸናለች።
መዝሙረ ዳዊት 102 : 1 - 28

" ለማርያም ድንግል መንበረ ተድላ ወሪዶ ገብርኤል ምድረ ገሌላ።ትወልዲ አምላክ በብሥራተ ቃሉ ይቤላ። "
እንኳን አደረሰን።
🙏🙏ለእመቤታችን መልካም ዜናን ያበሠረ መልአክ ለእኛም መልካም ዜናን ያብሥረን።🙏🙏

ዜና ዕረፍት
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት እና የጅቡቲ አብያተ ክርስቲያናት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዳንኤል ዐረፉ፡፡ ትላንት ማምሻውን በመንበረ ፓትርያሪኩ በሚገኘው መኖሪያቸው ያረፉት ብፁዕነታቸው፣ ከልብ ሕመም ጋራ በተያያዘ በሀገር ውስጥ እና በአሜሪካ የሕክምና ክትትል ሲደረግላቸው ቆይቷል፡፡
ከሳምንት በፊት በአሜሪካ በነበሩበት ወቅት የልብ ቀዶ ሕክምና እንዲደረግላቸው ቢጠየቁም፣ "አልፈልግም፤ አገሬ ገብቼ ልሙት፤" ብለው እንደተመለሱ ታውቋል፡፡የቀብራቸው ሥነ ሥርዐት ነገ ዓርብ፣ ታኅሣሥ 24 ቀን 2012ዓ.ም. በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንደሚከናወን ተጠቁሟል፡፡
(ሐራ ዘተዋሕዶ )

የሰ/ት/ቤታችን ልማት ክፍል እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት በሰላም አደረሳችሁ እያለ ለበዓሉ ማክበሪያ ይሆን ዘንድ ኃይማኖቱን እና ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ የጌታችንን ግርግም በተመጣጣኝ ዋጋ አቅርቦላችኋል።
ዜና ዕረፍት
የወንድማችን ሚሊዮን ሽርጋ አባት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ቀብር ቀጨኔ መድኃኔዓለም ቤ/ክ 9፡00 ላይ ነው። ቀብር መድረስ ያልቻልን ቤታቸው ፍልውሃ አካባቢ ስለሆነ ሄደን እንድናጽና ይሁን።
የአባታችንን ነፍስ ይማርልን።
ለቤተሰቦቻቸውም መጽናናቱን ያድልልን።

የሰንበት ት/ቤቱ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት።
⬇️
⬇️