የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
2.64K subscribers
6.38K photos
67 videos
82 files
1.72K links
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
Download Telegram
#ሐምሌ_3

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሐምሌ ሦስት በዚህች ቀን የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት #ቅዱስ_ቄርሎስ አረፈ፣ የሮሜ ሊቀ ጳጳሳት #ቅዱስ_ክልስቲያኖስ አረፈ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ቄርሎስ

ሐምሌ ሦስት በዚህች ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሃያ አራተኛ የሆነ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባት ቄርሎስ አረፈ። ይህም ቅዱስ የእናቱ ወንድም በሆነው በአባ ቴዎፍሎስ ዘንድ አደገ ጥቂት ከፍ ባለ ጊዜም ወደ አስቄጥስ ወደ መቃርስ ገዳም ላከው በዚያም አምላ*ካውያት የሆኑ መጻሕፍትን ተማረ እግዚአብሔርም መጽሐፍን አንድ ጊዜ አንብቦ እስከሚአጸናው ድረስ ዕውቀትንና ማስተዋልን ሰጠው።

ከዚህም በኋላ ደግሞ ያስተምረው ዘንድ ለአባ ሰራብዮን ሰጠው ከእርሱም ዘንድ ያለውን ትምህርቱን በፈጸመ ጊዜ ወደ ሊቀ ጳጳሳት ቴዎፍሎስ መለሰው። እርሱም እጅግ ደስ ተሰኘበት እግዚአብሔርንም አመሰገነው። ከዚህም በኋላ ሁልጊዜ መጻሕፍትን እንዲያነብና ሕዝቡን እንዲያስተምር በሊቀ ጵጵስና ሥራ ውስጥ ሾመው።

ከትምህርቱም ጣዕም የተነሣ ዝም ይል ዘንድ ማንም አይወድም ነበር። አባ ቴዎፍሎስም ከአረፈ በኋላ በእስክንድርያ ከተማ ላይ ይህን አባ ቄርሎስን ሊቀ ጵጵስና ሾሙት በዘመኑም በትምህርቱ ቤተ ክርስቲያን በራች። ይኸው አባት ቄርሎስ የቁስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳት የነበረው ንስ*ጥሮስ በካደ ጊዜ በንጉሥ ቴዎዶስዮስ ዘመን የሁለት መቶ ኤጲስቆጶሳት ጉባኤ ማኅበርን በኤፌሶን ከተማ ሰበሰበ።

ይህን አባት ቄርሎስንም መርጠው ሊቀ ጉባኤ አደረጉት። ንስጥ*ሮስንም ተከራከረው ስሕተ*ቱንም ገለጠለት። ከስሕ*ተቱም ባልተመለሰ ጊዜ አውግ*ዘው ከመንበረ ሢመቱ አሳደ*ዱት። ይህም አባት ቄርሎስ ዐሥራ ሁለት አንቀጾችን ደረሰ በውስጣቸውም የቀናች ሃይማኖትን ገለጠ ከእነርሱ በኋላ ግን ብዙዎች ድርሳናትን ተግሣጻትንና መልእክቶችን ደረሰ።

እሊህም በሁሉ ቦታ በምእመናን እጆች ይገኛሉ። ይህም አባት ቄርሎስ እግዚአብሔር ቃል ከትስብእቱ ጋራ ከተዋሐደ በኋላ በሥራው ሁሉ በምንም በምን የማይለያይ አንድ አካል አንድ ባሕርይ እንደሆነ አስረዳ። ይህም አባት ቄርሎስ ሃይማኖታቸው ከቀና ከሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት አባቶች ሃይማኖት ወጥተው ክርስቶስን ወደ ሁለት የሚከፍሉትን መናፍ*ቃንን ሁሉንም አው*ግዞ ለያቸው።

በወንጌላዊ ማርቆስ መንበር ላይ ሠላሳ ሁለት ዓመት ኖረ መልካም የሆነ ሥራውንም ፈጽሞ በሰላም አረፈ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ክልስቲያኖስ

በዚህችም ቀን ከእርሱ በፊት ለነበረው ሊቀ ጳጳሳት ዮናክንዲኖስ ደቀ መዝሙሩ የነበረ የሮሜ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባት ክልስቲያኖስ አረፈ። ይህ አባ ዮናክንዲኖስ በሚያርፍበት ጊዜ በእርሱ ፈንታ አባ ክልስቲያኖስን ሊቀ ጵጵስና እንዱሾሙት አዘዘ እርሱንም አባ ክልስቲያኖስን በሮሜ አገር ነጣቂ ተኩላዎች አሉና ልጄ ሆይ ተጠበቅ ብሎ አዘዘው። ከዚህም በኋላ አባ ዮናክንዲኖስ ባረፈ ጊዜ ይህን አባት ክልስቲያኖስን በእርሱ ፋንታ ሊቀ ጵጵስና ሾሙት።

በዚያን ወራት ደግ ንጉሥ አኖሬዎስ ነበረ። ከርሱም በኋላ ዐመ*ፀኛ ሉልያኖስ ነገሠ ። እርሱም ክልስቲያኖስን ከመንበሩ አሳድዶ መና*ፍቁ ንስ*ጥርስን ሊቀ ጵጵስና ሾመው የከተማ ሰዎች ግን አባረሩት እንጂ አልተቀበሉትም በከሀዲው ንጉሥም ልብ በክልስቲያኖስ ላይ ቂም ነበረ ሊገድ*ለውም ይሻ ነበር።

እርሱ አባ ክልስቲያኖስ ግን በሮሜ ከተማ ከሚገኙ ገዳማት በአንዱ ገብቶ ኖረ እግዚአብሔርም ብዙ ድንቆችንና ተአምራቶችን በእጆቹ ያደርግ ነበር። ከዚህም በኋላ ከሀዲው ንጉሥ ወደ ጦርነት ሔደ የእግዚአብሔር መልአክ የመላእክት አለቃ ሩፋኤልም ለክልስቲያኖስ ተገለጠለት ወደ አንጾኪያ ከተማ ወደ ሊቀ ጳጳሳት ድምትርያኖስ ይሔድ ዘንድ አዘዘው በዚያም ኑር አለው።

ንጉሡ ከጦርነት እንደተመለሰ ይገድ*ልህ ዘንድ በልቡ አስቧልና። ከእንቅልፉም በነቃ ጊዜ ከዚያ ገዳም ወጣ ከእርሱ ጋራም ሁለት መነኰሳት ነበሩ። ወደ እንጾኪያም ከተማ ደርሶ ቅዱስ ድምትርያኖስን አገኘው ከዐመፀኛው ንጉሥም የደረሰበትን ሁሉ ነገረው እርሱም በአንጾኪያ ከተማ ከሚገኙ ገዳማት በአንዱ ገዳም አኖረው።

ከዚህም በኋላ ቅዱሳን ሊቃነ ጳጳሳት አግናጥዮስና ዮናክንዲኖስ በሌሊት ራእይ ለንጉሡ ተገለጡለት ከእርሳቸውም ጋር የነበረው አንዱ እጅግ የሚያስፈራና ግሩም ነበረ። እርሱም ንጉሡን እንዲህ አለው ሊቀ ጳጳሳቱን ክልስቲያኖስን አገሩን ለምን አስተውከው እነሆ እግዚአብሔር ነፍስህን ከአንተ ይወስዳል በጠላቶችህም እጅ ትሞታለህ።

ንጉሥም ጌታዬ ምን ላድርግ አለው እነዚያም ሁለቱ አባቶች በእግዚአብሔር ልጅ ሕማም በመቀበሉ ታምናለህን ብለው መለሱለት እኔ አምናለሁ አላቸው ዳግመኛም መልእክትን ልከህ ልጃችን ክልስቲያኖስን ወደ መንበሩ መልሰው አሉት። ከእንቅልፉም በነቃ ጊዜ መልእክትን ጽፎ ወደ ድምትርያኖስ እንዲህ ብሎ ላከ ስለ ሊቀ ጳጳሳት ክልስቲያኖስ በእኔ ላይ አትዘን ወደ መንበረ ሢመቱ ይመልሱት ዘንድ ሊቀ ጳጳሳት ክልስቲያኖስ ያለበትን ለመልእክተኞቼ ታመላክታቸውና ታደርሳቸው ዘንድ እለምንሃለሁ።

መልክተኞችም በሔዱ ጊዜ አገኙትና መለሱት ሕዝቡም በታላቅ ክብርና በብዙ ደስታ ተቀበሉት። በዚያም ወራት ንጉሡ ከጦርነት በደኅና ተመለሰ ቤተ ክርስቲያንም በዕረፍትና በሰላም ኖረች። የንስጥሮስም ክህ*ደቱ በተገለጠ ጊዜ በእርሱ ምክንያት አንድነት ያላቸው ማኅበር ተሰበሰቡ። ይህ አባት ክልስቲያኖስም በደዌውና በእርጅናው ምክንያት ወደጉባኤው መምጣት አልተቻለውም ነገር ግን ንስ*ጥሮስን ከሚያወግዝ ደብዳቤ ጋራ ሁለት ቀሳውስትን ላከ።

ክብር ይግባውና ጌታችንም ከዚህ ኃላፊ ዓለም ድካም ሊአሳርፈው በፈቀደ ጊዜ ዮናክንዲኖስና አትናስዮስ ተገለጡለት እንዲህም አሉት ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሕይወት ጠርቶሃልና አንተ ወደ እኛ ስለምትመጣ አስጠንቅቃቸው አሉት። ከእንቅልፉ ነቅቶ ወገኖቹን ጠራቸው እንዲህም አላቸው ተኵላዎች ወደዚች ከተማ ይገቡ ዘንድ አላቸውና ተጠንቀቁ።

ይህንም ከተናገረ በኋላ ዳግመኛ እንዲህ አለ እንነሣና እንሒድ እነሆ ቅዱሳን ይሹኛልና ሁለቱ ሌሎች ናቸው። በዚችም ሰዓት ከዚች ዓለም በአንድነት እንወጣለን እነርሱም የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ቄርሎስና የፃን ሀገር ኤጲስቆጶስ ሉቅያስ ናቸው። ይህንንም ብሎ በሰላም አረፈ።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን አባቶቻችን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12
ሁለተኛ ዙር ምዝገባ

ተጀመረ...

አንጋፋው የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያትና ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ት/ቤት ሁለተኛ ዙር የተልዕኮ ትምህርት ለማስተማር ምዝገባ ጀመረ

ትምህርቱ በቤተክርስቲያናችን ሊቃውንት የሚሰጥ ነው ለመመዝገብ

https://t.me/+OZ5RaCkSyMhmMTlk በዚህ ሊንክ ገብተው

ስም
ስልክ
አድራሻ በመስጠት መመዝገብ ይችላሉ

ሼር በማድረግ ይተባበሩ

የፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት
ሐምሌ_4

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሐምሌ አራት በዚህች ቀን #የቅዱሳን_አቡቂርና_ዮሐንስ የሥጋቸው ፍልሰት ሆነ፣  #የነቢዩ_ሶፎንያስ እረፍት ነው፣ የዐሥራ ሁለቱ #ደቂቀ_ነቢያት መታሰቢያቸው ነው።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱሳን_አቡቂርና_ዮሐንስ

ሐምሌ አራት በዚች ቀን የቅዱሳን አቡቂርና ዮሐንስ የሥጋቸው ፍልሰት ሆነ። ይህም እንዲህ ነው እሊህ ቅዱሳን የካቲት ስድስት ቀን ሰማዕታት ሆነው በሞቱ ጊዜ ምእመናን ሥጋቸውን ተሸክመው ወስደው በእስክንድርያ ከተማ በስተሰሜን ባለች በቅዱስ ወንጌላዊ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሥውር አኖሩዋቸው እስከ ሊቀ ጳጳሳት ቄርሎስ ዘመንም በዚያ ኖሩ።

የእግዚአብሔር መልአክም ለቅዱስ ቄርሎስ ተገለጸለት ወደ ወንጌላዊ ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያንም ሔዶ የቅዱሳን የአቡቂርንና የዮሐንስን ሥጋቸውን አውጥቶ እንዲሸከም አዘዘው። እርሱም ተነሥቶ ሔደ ከእርሱም ጋራ ብዙ ሕዝቦች ነበሩ በደረሱም ጊዜ ጸለዩ ምድሩንም ሲቆፍሩ ሥጋቸው በውስጡ ያለበት ቦታ ተገለጠላቸው በባሕር ዳርቻ ወደ አለች ወደ ሌላዪቱም የቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን በታላቅ ክብር የቅዱሳኑን ሥጋቸውን ተሸክመው አድርሰው በዚያ አኖሩ።

በዚያም ቤተ ክርስቲያን ሠሩላቸው በዚችም ቀን ታላቅ በዓል አደረጉ ከሥጋዎቻቸውም ድንቆች ተአምራት ተገለጡ አረማውያንም ተሰበሰቡ ይህንንም ድንቅ ተአምር በአዩ ጊዜ ጣዖቶቻቸውን ትተው ክርስቲያኖች ሆኑ። በዚያቺም የጣዖቶች ቤት አሸዋ በላይዋ ተከመረባት ታላቅ ኮረብታም ሆነ። የቅዱሳንም ሥጋቸው ታምራትንና ለበሽተኞች ታላቅ ፈውስን ያደርጋል።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ነቢዩ_ሶፎንያስ

በዚህችም ቀን ደግሞ የአማርያ ልጅ፣ የሴዴቅያስ ልጅ፣ የጎዶልያ ልጅ፣ የኩሲ ልጅ የሶፎንያስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው። እርሱም በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ዘመን ትንቢት ተናገረ። እንዲህም አለ እግዚአብሔር ከዚህ ዓለም ፈጽመው ይጠፋሉ አለ ከብቶችና ሰዎች ያልቃሉ። የባሕር ዓሣዎችና በሰማይ የሚበሩ አዕዋፍም ያልቃሉ።

ዳግመኛም ስለሞአብ እንዲህ አለ ስለዚህ ሞአብ እንደ ሰዶም ትሆናለች የአሞንም ልጆች እንደ ገሞራ ልጆች ይሆናሉ ደማስቆም እንደ እህል ታልቃለች። እርሱ እንደ ተነበየው እነዚያ አገሮች በናቡከደነጾር ምርኮ ይጠፋሉና።

ዳግመኛም ስለ ፋርስና ስለ ነነዌ ትንቢት ተናገረ እንዲህም አለ የፋርስን ሰዎች አጠፋቸዋለሁ ነነዌንም ፍርስራሽና ውኃ እንደሌለባት ምድረ በዳ አድርጋታለሁ መንጋዎችም በመካከሏ ይሠማሩባታል። ይህቺም ከተማ በመቄዶናዊው እስክንድር እጅ ጠፍታለች።

ዳግመኛም ስለ ክርስቶስ መምጣት እንዲህ ተናገረ። ያን ጊዜም ሁሉ የእግዚአብሔርን ስም ይጠራ ዘንድ በአንድ ሕግም ይገዙልኝ ዘንድ የአሕዛብን ሁሉ አንደበት ወደ ሕግ እመልሳለሁ። ደግሞም እንዲህ አለ ከኢትዮጵያ ወንዞች ማዶ መሥዋዕቴን ያመጡልኛል።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ደቂቀ_ነቢያት

ዳግመኛም በዚች ቀን ስለ ክርስቶስ ትንቢታቸውን እንደ ፈሳሽ ውኃ ያጐረፉ የዐሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያት መታሰቢያቸው ነው።

ከ12ቱ ደቂቀ ነቢያት አንዱ ነው፡፡ 12ቱ ቅዱሳን ደቂቀ ነቢያት የሚባሉት፡- ሆሴዕ፣ አሞጽ፣ ሚክያስ፣ ኢዩኤል፣ አብድዩ፣ ዮናስ፣ ናሆም፣  እንባቆም፣ ሶፎንያስ፣ ሐጌ፣ ዘካርያስ እና ሚልክያስ ናቸው፡፡

ሌሎቹ ዋና (ዓበይት) ነቢያት የሚባሉት አራት ሲሆኑ እነርሱም ኢሳይያስ፣ ኤርምያስ፣ ሕዝቅኤልና ዳንኤል ናቸው፡፡ ከሆሴዕ እስከ ሚልክያስ ድረስ ያሉት ነቢያት ‹‹ደቂቀ ነቢያት›› የተባሉት ምክንያት አንድም የነቢያት ልጆች በመሆናቸው ነው፡፡ ሌላው ደግሞ የጻፏቸው ትንቢቶቻቸው ዓበይት ነቢያቱ ከጻፏቸው ጋር በንፅፅር ሲታይ አነሥተኛ ስለሆነ ነው፡፡

'ነቢይ' ማለት እግዚአብሔር የመረጠውና የእግዚአብሔርን መልእክት ለሕዝቡ የሚያስተላልፍ ብሎም የተሠወረውንና የሚመጣውን ሁሉ በግልጽ የሚመለከት ማለት ነው፡፡ ነቢያት ሲባሉ በአጠቃላይ ምግባር ሃይማኖታቸው ያማረ፣ ትሩፋት ተጋድሎአቸው የሰመረ ነውና አካሄዳቸው ሁሉ ከእግዚአብሔር ጋር ነው፡፡

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን አባቶቻችን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12
#ሐምሌ_5

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሐምሌ አምስት በዚች ቀን የክቡራንና የዐበይት አባቶቻችን ሐዋርያት #የቅዱስ_ጴጥሮስ እና #የቅዱስ_ጳውሎስ የሰማዕትነታቸው መታሰቢያ ነው።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ጴጥሮስ

ሐምሌ አምስት በዚህች ቀን የሐዋርያት የቅዱስ ጴጥሮስ የሰማዕትነት መታሰቢያ ነው። ይህም ጴጥሮስ ከቤተ ሳይዳ ነበር ዓሣ አጥማጅም ነበር ጌታችንም ከተጠመቀባት ዕለት ማግሥት አግኝት መረጠው ከእርሱ አስቀድሞም ወንድሙ እንድርያስን አግኝቶ መረጠው።

መድኃኒታችንንም እስከ መከራው ጊዜ ሲአገለግለው ኖረ ፍጹም ሃይማኖት ለጌታውም ቅንዓትና ፍቅር ነበረው። ስለዚህም በሐዋርያት ሁሉ ላይ አለቃ አድርጎ ሾመው። ጌታችንም ሰዎች ማን እንደሆነ ማንም እንደሚሉት ስለ ራሱ በጠየቃቸው ጊዜ ሌሎቹ ኤርሚያስ ይሉሃል ወይም ኤልያስ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው ይሉሃል አሉት።ጴጥሮስ ግን የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ አንተ ነህ አለ።

ጌታችንም የሃይማኖት አለት የቤተ ክርስቲያንም መሠረት ነህ ብሎ ብፅዕና ሰጠው የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻ ቁልፍ ሰጥቼሃለሁ አለው። አጽናኝ የሆነ የመንፈስ ቅዱስንም ጸጋ ከተቀበለ በኃላ ተናጋሪዎች በሆኑ በዚህ ዓለም ተኩላዎች መካከል ገባ በውስጣቸውም ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰበከ ቁጥር የሌላቸው ብዙዎች አሕዛብንም መልሶ የዋሆች ምእመናን አደረጋቸው።

ጌታችንም የማይቁጠሩ ታላላቅ ድንቆችና ተአምራቶችን በእጆቹ አደረገ ጥቅም ያላቸዉ ሦስት መልእክቶችም ጽፎ ለምእመናን ላካቸው ለማርቆስ ወንጌሉን ተርጎሞ አጽፎታል። ከዚያም በሗላ ወደ ሮሜ ከተማ ገባ የከተማው መኳንንት ወደ ሚሰበሰቡበት ወደታላቁ የጨዋታ ቦታም ሔዶ በታላቅ ድምፅ እንዲህ ብሎ ተናገረ የሚራሩ ብፁዓን ናቸው ለርሳቸውም ይራሩላቸዋልና የዚህንም ተከታታይ ቃሎች ተናገሩ በዚያም ከዚያ የነበሩ አራት የድንጊያ ምሰሶዎችም በሚያስፈራ ድምፅ አሜን አሉ የተሰበሰቡትም ይህን ቃል በሰሙ ጊዜ ደነገጡ ከንድ ሰው ነበረ ከእነዚያ ድንጋዮች ቃልን ስለ ሰማ ያን ጊዜ ጋኔኑ ጣለው ከእርሱም ወጥቶ ሔደ መኳንንቱም ፈርተዋልና ስለዚህ ነገር እያደነቁ ወደ ቤታቸው ገቡ።

ከከተማ መኳንንቶችም ቀዉስጦስ የሚባል አንዱ ወደ ቤቱ በገባ ጊዜ ስሟ አክሮስያ ለምትባል ሚስቱ ዓለምን ስለ መተው ለድኖችም ሰለመራራትና የመሳለለውን ቃል ጴጥርስ እንዴት እንዳስ ተማረ ነገራት እርሷም በሰማች ጊዜ በልቧ ነቅታ ይህ ነገር መልካምና ድንቅ ነው አለች ጴጥሮስ ያስተማረውንም ሁሉ ያደርጉ ዘንድ በአንድነት ተስማሙ ከዚህም በሗላ ገንዘባቸውን ሁሉ ለድሖች ሰጡ ከዕለት ራት በቀር ምንም አላስቀሩም። ከጥቂት ቀኖችም በሗላ ንጉሡ ስለ መንግሥት ስራ ከርሱ ጋራ ለመማከር በቶሎ እንዲደርስ ወደርሱ መልእክትን ላከ። ቀውስጦስም ይህን በሰማ ጊዜ ገንዘብ ስላልነበረው ፈርቶ ደነገጠ ተጨነቀም ምክንያቱም አመካኝቶ ይሠወር ዘንድ ከሚስቱ ጋራ ተማከረ እሷም ግን ምክንያት አታድርግ ነገር ግን ወደ ንጉሡ ሒድ የጴጥሮስ አምላክ ጎዳናህን ያቅናልህ አለችው።

እርሱም ነገርዋን ተቀብሎ ወደ ንጉሡ ሔደ በመንገድም በእግዚአብሔር የታዘዘ ብዙ በረከትን አገኘ ወደ ንጉሱም ደረሰ ንጉሡም በደስታ እና በክብር ተቀበለው። ከሦስት አመት በሗላም ወደ ቤቱ በተመለሰ ጊዜ ሁለት ልጆቹ የተመረዘ ውኃ ጠጥተው እነሆ ሙተው ነበር ሚስቱም ለእርሱ መንገርን ፈራች ብዙ ምሳሌዎችን ከመሰለቸለት በሗላ ነገረችው በሰማ ጊዜም እጅግ አዝኖ አለቀሰ። ሚስቱም እንዲህ አለችው ጌታዬ ሆይ ልባችን የሚጽናናበትን እርሱ ያደርግልናልን የጴጥሮስ ፈጣሪ እግዚአብሔርን እንለምነው ሊጸልዩም በጀመሩ ጊዜ ቀውስጦስና አክሮስያ ሆይ የደቀ መዝሙሬ የጴጥሮስ ቃል ስለ ሰማችሁና ስለተቀበላችሁት ስለዚህ ልጆቻችሁን በሕይወታቸው እሰጣችሗለሁ የሚል ቃልን ከሰማይ ሰሙ ያን ጊዜም ልጆቻቸው ድነው ተነሡ ቀውጦስና ሚስቱም ደስ አላቸው የተመሰገነ እግዚአብሔርንም አመሰገኑት።

እኝህም ከሞት የተነሡ ልጆች ለቅዱስ ጴጥረስ ደቀ መዝሙሮች ሆኑ የአንዱ ስም ቀሌምንጦሶ ነው እርሱም ቅዱስ ጴጥኖስ ያየውንና ጌታችን በሥጋ ወደ ሰማይ በሚዐርግ ጊዜ የገለጠለትን ምሥጢር ሁሉ የነገረው ነው ሰዎች ሊያዪአቸው የማይገባቸውን መጻሕፍትን አስረከበው። ይህንም ቀሌምንጦስን ሊቀ ጵጵስና ወንድሙንም ዲቁና ሾማቸውከዚህም በሗላ ዳግመኛ ቅዱስ ጴጥሮስ አምላክን የወለደች የንጽሕት ድንግል እመቤታችን ማርያም ክብርዋን በምሳሌ አየ።

በቀስት አምሳል ደመናን አይቷልና በላይዋም የብርሃን ድንኳን ነበር በድንኳኑም ውስጥ አምላክን የወለደች ቅድስት ድንግል ማርያም ተቀምጣለች። በእጆቻቸውስጥ የነበልባል ጦሮችንና ሰይፎችን የያዙ መላእክትና የመላእክት አለቆች በዙሪያዋ ነበሩ እንዲህም እያሉ ያመሰግኗት ነበር ከእርሷ የድኅነታችን ፍሬ የተገኘ የሰመረች የወይን ተክል አንቺ ነሽ።

መሕፀንሽ የእግዚአብሔርን በግ የተሸከመ ንጽሕት አዳራሽ አንቺ ነሽ ሁለተኛውም እንዲህ ይላት ነበር የብርሃን እናቱ ሆይ የምህረት መገኛ ሆይ ደስ ይበልሽ የአማልክት አምላክ የፍጥረት ሁሉ ጌታ የሆነ የመድኅን ዙፋን ሆይ ደስ ይበልሽ ክብርና ምስጋናን የተመላሽ የፍጥረቱ ሁሉ እመቤት ደስ ይበልሽ። መላእክትም ምስጋናዋንና ሰላምታዋን ባደረሱ ጊዜ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእርስዋ ተገልጦ ከእርሷ በቀር ማንም ሊያውቀው የማይቻል ነገርን ነገራት ወዲያውኑም ምድር ተናወጸች ሊነገር የማይቻል ሚስጥራትንም ገለጠላት ።

ከዚህም በኋላ መድኃኒታችን በሀገሩ ሁሉ ቅዱስ ወንጌልን ዘንድ ጴጥሮስን አዘዘው ጴጥሮስም ወጥቶ ሔደ ኢዮጲ ወደምትባል የባሕር ዳርቻና ልድያ ወደምትባል አገር ደረሰ። በአንዲት ዕለትም በኢዮጲ ሳለ ብርህት ደመና ዞረችው እንሆም ሰፊ መጋረጃ ወደርሱ ወረደች በውስጧም የእንስሳት የምድተ በዳ አውሬዋችና የሰማይ አዕዋፍ አምሳል ነበር ጴጥሮስ ሆይ ተነሥና አርደህ ብላ የሚል ቃል ም ከሰማይ ጠራው ጴጥሮስም አቤቱ አይገባኝም እርኩስ ነገር አልበላም ወደ አፌም ከቶ አልገባም አለ።

ያም ቃል ዳግመኛ ጠራውና እግዚአብሔር ንጹ ያደረገውን እርኵስ ነው አትበል አለው ያም ቃል ሥስት ጊዜ እንዲህ መላልሶ ነገረው በየንግግሩም ወደ እሪያዎች ወደ አራዊትና አዕዋፍ ስእሎች ጣት ያመለክተው ነበር ከዚህ በኋላ ያቺ መጋረጃ ወደ ሰማይ ተመለሰች። ጴጥሮስም ስላየው እራእይ አደነቀ ይህም እራእይ ወደ ፈጣሪያቸወረ እግዚአብሔር የሚመለሱ አሕዛብን ስለመቀበል እንደሆነ አስተዋለ ለወንድሞቹ ሐዋርያትም አሕዛብ የእግዚአብሔር ቃልን እንደተቀበሉ የመቶ አለቃ ቆርኔሌዎስንም ከወገኖቹ ጋር እንዳጠመቀው ነገራቸው ።

ከዚህ በኋላ ጴጥሮስ ከዮሐንስ ጋራ ጌታችን እንዳዘዛቸው ወደ አንጾኪያ ከተማ ገቡ የአገራቸውን ሁኔታ ይጠይቅ ዘንድ ጴጥሮስ ዮሐንስን ላከው ሰዎችንም ክፉ ነገርን ተናገሩት ሊገድሉትም ፈለጉ እያለቀሰም ተመለሰ ሰውነቱም ተበሳጨች ጴጥሮስም አለው አባቴ ሆይ የእሊህ ጐስቋሎች ክፋታቸው እንዲህ ከሆነ ወደ ነገስታቱና ወደ መኳንንቱ ገብተን በገፀታችን ሰም በሰበክን ጊዜ ምን እንሆን ይሆን እንዴትስ ሃይማኖት እናስተምራለን።
ቅዱስ ጴጥሮስ ወዳጄ ሆይ የሃያውን ቀን መንገድ በአንዲት ሌሊት ያመጣን እርሱ ሥራችንን መልካም ያደርግልናል አትፍራ አትዘንም አለው። ከዚህ በኃላ ወደ ከተማ መካከል ገብተው ክብር ይግባውና በጌታችን ስም ሰበኩ የከተማ ሰዎችና የጣዖታቱ አገልጋዮች በእነርሱ ላይ ተሰበሰቡ ታላቅ ድብደባንም ደበደቧቸ አጐሳቆሏቸውም ግማሽ የራስ ጠጉራቸውን ላጭተው ተዘባበቱባቸው አስረውም በግንብ ወስጥ ጣሏቸው።

ከዚህ በኋላ ይረዳቸው ዘንድወደ እግዚአብሔር ጸለዮ ወዲያውኑም ክብር ይግባውና ጌታችን መዳኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኪሩቤልና ሱራፌል እያጀቡት ተገለጠላቸውና እንደህ አላቸው የመረጥኳቹ ጴጥሮስና ዮሐንስ ሆይ በዘመኑ ሁሉ እኔ ከእናንተጋር እኖራለሁና አትፍሩ አትዘኑም ለመዘባበቻም በራሳቹ መካከል ስለላጩአቹ አታድንቁ ይህም መመኪያና ክብር የክህነት ስርዓትና ምልክትንም ይሆናችኋል ካህን የሚሆን ሁሉ ያለዚህ ምልክት ሥጋዬንና ደሜን ማቀበል አይችልም ።

ይህ ምልክት እያለው የሚሞት ካህንም ኃጢአቱ ይሠረይለታል። ይህን ካላቸው በኃላ ከእርሳቸው ዘንድ በክብር ዐረገ። ከዚህም በኃላ ጳውሎስ መጥቶ ዮሐንስን ተገናኘው የዚህ አገር ሰዎች ያደረጉብህ ምንድነው አለው እርሱም ስለ እኔ አታድንቅ የሐዋርያትንም አለቃ በእኔ ላይ በአደረጉት አማሳል አድርገውበታልና አለው። ጳውሎስም አጽናናቸው እንዲህም አላቸው እኔ በጌታችን ፈቃድ ወደ ከተማው ውስጥ ገብቼ እናንተንም አስገባችኃለሁ።

ከዚህም በኃላ ጳውሎስ ሒዶ ምክንያትን ፈጠረ ጣዖተቸውንም እንደሚአመልክ መስሎ ሐዋርያትን እንዲአቀርቡለትና ስለ ሥራቸውም እንዲጠይቃቸው የከተማውን መኳንንት አነጋገራቸው። መኳንንቱም ወደ ጳውሎስ እንዲአቀርቧቸው አዘዙ በቀረቡም ጊዜ ጳውሎስ ስለ ሥራቸው ጠየቃቸው። እነርሱም ድንቆችንና ተአምራቶችን ለሚአደርግ ለክርስቶስ ደቀ መዝሙሮቹ እንደሆኑ ነገሩት።

ዳግመኛም እናንተ እንደርሱ ማድረግ ትችላላችሁን አላቸው እነርሱም አዎ በእርሱ ስም ሁሉን ሥራ መሥራት እንችላለን አሉት። ከዚህም በኃላ ከእናቱ ማሕፀን ዕውር ሆኖ የተወለደውን ዐይኑን አበሩ። የንጉሡንም ልጅ ከሞተ በሦስት ወሩ ሥጋውም ከተበላሸ በኃላ ከመቃብር አስነሡት። ንጉሡና የከተማ ሰዎች ሁሉ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ።

ጴጥሮስም ምድሩን ረግጦ ውኃን አፈለቀ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱሰወ ስም አጠመቋቸው በቀናች ሃይማኖትም እንዲጸኑ አደረጓቸው። ከዚህም በኃላ በሎዶቅያ ያሉ ምእመናን የቂሳሮስ ባሕር ከወሰኑ አልፎ ብዙ ሰዎችን ከአትክልት ቦታዊቻቸውና ከከብቶቻቸው ጋራ እንዳሠጠማቸው ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ላኩ ጴጥሮስም ተወዳጅ ዮሐንስን ወደ እነርሱ ላከ።

ዮሐንስም ወደ እነርሱ ሲጓዝ በጎዳና በግ አገኘ በጉንም እንዲህ ብሎ ላከው ወደ ቂሳሮስም ወንዝ ሒድ የክርስቶስ ደቀ መዝሙሩ ወደ አንተ ልኮኛል ወደ ቀድሞው ወሰንህ ተመለሰህ ትገባ ዘንድ አንተ በእግዚአብሔር ቃል የታሠርክ ነህ ብሎሃል በለው። ያን ጊዜ በጉ ሒዶ እንዳዘዘው አደረገ ወንዙም ሸሽቶ ወደ ቦታው ተመለሰ ቁጥር የሌላቸው ብዙዎች የከተማ ሰዎችም ይህን አይተው በጌታ አመኑ።

ከዚህም በኃላ ቅዱስ ጴጥሮስ አልፎ ወደ ሮሜ ከተማ ገባ በዚያም ሥራ መሠሪው ሲሞን ተቃወመው እርሱንም ከአየር ላይ አውርዶ ጥሎ አጠፋው ይህንንም ድንቅ ሥራ አይተው ብዙዎች ሕዝቦች አመኑ። የከተማው ገዥ የአክርጶስ ቁባቶችም የቅዱስ ጴጥሮስን ትምህርት ተቀበሉ ሌሎችም የከበሩ ብዙዎች ሴቶች ትምህርቱን በመቀበል ከባሎቻቸው ርቀው ንጽሕናቸውን ጠበቁ።

ስለዚህም ነገር ቅዱስ ጴጥሮስን ሊገድሉት የሮሜ መኳንንት ተማከሩ። የአልታብዮስ ሚስትም እንዳይገድሉት ከሮሜ ከተማ ወጥቶ እንዲሔድ ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ላከች ምእመናን ወንድሞችም ውጣ አሉት እርሱም ቃላቸውን ተቀበለ ትጥቁንም ለውጦ ከከተማው ወጣ። በሚወጣበትም ጊዜ መስቀል ተሸክሞ ወደ ከተማ ሲገባ ጌታችንን አገኘውና አቤቱ ጌታዬ ወዴት ትሔዳለህ አለው።

ጌታም ልሰቀል ወደ ሮሜ ከተማ እሔዳለሁ ብሎ መለሰለት ቅዱስ ጴጥሮስም አቤቱ ዳግመኛ ትሰቀላለህን አለው። ያን ጊዜም ጎልማሳ ሳለህ ወገብህን በገዛ እጅህ ታጥቀህ ወደ ወደድከው ትሔዳለህ በሸመገልክ ጊዜ ግን እጅህን ታነሣና ሌላ ያስታጥቅሃል ወደማትወደውም ይወስድሃል ያለውን የጌታችንን ቃል አሰበ አስተዋለውም። ያን ጊዜም ወደ ከተማው ተመልሶ ክብር ይግባውና ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ የሆነውን ለወንድሞች ነገራቸው እነርሱም እጅግ አዘኑ።

ንጉሥ ኔሮንም ቅዱስ ጴጥሮስን እንዲሰቅሉት አዘዘ ሊሰቅሉትም በያዙት ጊዜ ወታደሮችን እንዲህ ብሎ ለመናቸው የክብር ንጉሥ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደላይ ሆኖ ስለተሰቀለ እኔ ቁልቁል ልሰቀል ይገባኛል። ወዲያውኑም እንደነገራቸው ሰቀሉት። ተሰቅሎ ሳለም ለምእመናን የሕይወትን ቃል አስተማራቸው በቀናች ሃይማኖትም እንዲጸኑ አዘዛቸው ከዚህም በኃላ ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ጳውሎስ

በዚህችም ቀን ዳግመኛ ልሳነ ዕረፍት የክርስቶስ አንደበት የዕውቀት አዘቅት የቤተ ክርስቲያን መብራት የቅዱስ ሐዋርያ ጳውሎስ የሰማዕትነቱ መታሰቢያ ነው። እንደ ስሙም ትርጓሜ መሪ አመስጋኝ ወደብ ጸጥታ ነው። ይህም ጳውሎስ አስቀድሞ በክርስቶስ ያመኑትን የሚያሳድድ ነበረ እርሱም ከብንያም ወገን የፈሪሳዊ ልጅ ነው።ወላጆቹም ሳውል ብለው ስም አወጡለት ትርጓሜውም ስጦታ ነው።

ቁመቱ ቀጥ ያለ መልኩ ያማረ ፊቱ ብሩህ ቅላቱ እንደ ሮማን ቅርፍት ደበብ ያለ ዐይኑም የተኳለ የሚመስል አፍንጫው ቀጥ ያለ ሸንጎበታም ጉንጩ እንደ ጽጌ ረዳ ነበረ። እርሱም ሕገ ኦሪትን አዋቂ ነበረ ለሕጉም ቀናተኛ ሆኖ ምእመናን አስዳጅ ነበረ። ወደ ሊቀ ካህናቱም ሔዶ በመንገድ የሚያገኘው ሰው ቢኖር ወንዶችንና ሴቶችን እንደ ታሠሩ ወደ ኢየሩሳሌም ይመልሳቸው ዘንድ ለደማስቆ ከተማና ለምኮራቦች የፈቃድ ደብዳቤ ለመነ።

ሲሔድም ወደ ደማስቆ ከተማ አቅራቢያ በደረሰ ጊዜ ድንገት ከሰማይ መብረቅ ብልጭ አለበት በምድር ላይም ወደቀ ወዲያውም ሳውል ሳውል ለምን ታሳድደኛለህ የሚለውን ቃል ሰማ። ሳውልም አቤቱ አንተ ማነህ አለው አንተ የምታሳድደኝ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነኝ በሾለው ብረት ላይ ብትረግጥ አንተን ይጎዳሃል አለው። ከርሱ ጋራ ቁመው: የነበሩ ሰዎችም ንግግሩን ይሰሙ ነበር ነገር ግን የሚያዩት አልነበረም። ሳውልም ከምድር ተነሣ ዐይኖቹም ተገልጠው ሳሉ አያይም ነበር እየመሩም ወደ ደማስቆ አስገቡት በዚያም ሳያይ ሳይበላና ሳይጠጣ ሦስት ቀን ሰነበተ።

በዚያም በደማስቆ ከደቀ መዛሙርት ወገን ሐናንያ የሚባል አንድ ሰው ነበረ ጌታም በራእይ ተገለጠለትና ሐናንያ ብሎ ጠራው እርሱም አቤቱ ጌታዬ እነሆኝ አለ። ጌታም ተነሥና ቀጥተኛ ወደምትባለው መንገድ ሒድ በይሁዳ ቤትም ጠርሴስ ከሚባል አገር የመጣ ሳውል የሚባል ሰው ፈልግ እርሱ አሁን ይጸልያልና አለው። ሐናንያ ግን መልሶ እንዲህ አለ አቤቱ ስለዚያ ሰው በኢየሩሳሌም በቅዱሳኖችህ ላይ የሚያደርገውን ክፉ ነገር ሁሉ ከብዙ ሰዎች ሰምቻለሁ ወደዚህም ከካህናቱ አለቃ አስፈቅዶ የመጣ ስምህን የሚጠሩትን ሁሉ ሊአሥር ነው። ጌታችንም ተነሥና ሔድ በአህዛብና በነገሥታት በእስራኤልም ልጆች ፊት ሰሜን ይሸከም ዘንድ ለእኔ የተመረጠ ዕቃ አድርጌዋለሁና ።
እኔምሰ ስለ ስሜ መከራ ይበቀል ዘንድ እንዳለው አሳየዋለሁ። ያን ጊዜም ሐናንያ ሔደ ወደ ቤትም ገባ ወንድሜ ሳውል በመንገድ ስትመጣ የታየህ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታይ ዘንድ የመንፈስ ቅዱስም ጸጋ ይሞላብህ ዘንድ ወደ አንተ ልኮኛል አለው። ያን ጊዜም የሸረሪት ድር የመሰለ ከዐይኖቹ ላይ ተገፎ ወደቀ ዐይኖቹም ተገለጡ።

ወዲያውም አየ ተነሥቶም ተጠመቀ እህልም በልቶ በረታ። ከደቀ መዛሙርትም ጋር በደማስቆ ጥቂት ቀን ሰነበተ። በዚያው ጊዜ የእግዚአብሔር ልጅ ነው ብሎ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰበከ አስተማረም። የሰሙትም ሁሉ አደነቁ እንዲህም አሉ በኢየሩሳሌም ይህን ስም የሚጠሩትን ሁሉ ያሳድድ የነበረው ይህ አልነበረምን ወደዚህስ የመጣው እያሠረ ወደ ሊቀ ካህናቱ ሊወስዳቸው አይደለምን።

አጽናኝ መንፈስ ቅዱስም አደረበት ዕውነተኛውንም ሃይማኖት ግልጽ አድርጎ አስተማረ። ለኦሪት ሕግ የሚቀና እንደ ነበረ እንዲሁ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሠራት ሕገ ወንጌል ዕጽፍ ድርብ ቅንዓትን የሚቀና ሆነ ከዚህም በኃላ በአገሮች ሁሉ ዞሮ ሰበከ በጌታችንም ስም ሰበከ። ድንቆችንና ተአምራትንም አደረገ። ቁጥር የሌላቸው ብዙዎች አሕዛብንም አሳመናቸው ነገር ግን ብዙ ጊዜ በመገረፍ በመደብደብና በመታሠር ብዙ መከራ ደረሰበት መከራውንም ሁሉ ታግሦ በሁሉ ቦታ ዙሮ አስተማረ።

በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ እንደ ተጻፈ የእግዚአብሔርን ሥራ ሲሠሩ ሲጾሙና ሲጸልዩ መንፈስ ቅዱስ እኔ እነርሱን ለመረጥሁለት ሥራ ሳውልንና በርናባስን ለዩልኝ አላቸው። ከዚህም በኃላ ጾመውና ጸልየው እጃቸውንም በራሳቸው ላይ ጭነው ሾሙአቸው ከመንፈስ ቅዱስም ተሹመው ወደ ሴሌውቅያ ወረዱ። በደሴቱም ሁሉ ሲዘዋወሩ ጳፉ ወደ ምትባል አገር ደረሱ።

በዚያም ሐሰተኛ ነቢይ የሆነ ስሙ በርያሱስ የሚባል አንድ ሥራየኛ አይሁዳዊ ሰው አገኙ እርሱም ሰርግዮስ ጳውሎስ ከሚባል ብልህ ሰው ከሆነ አገር ገዥ ዘንድ የነበረ ነው። የእግዚአብሔርን ቃል ሊሰማ ወደ በርናባስንና ሳውልን ጠራቸው። የስሙ ትርጓሜ እንዲህ ነበርና ኤልማስ የሚሉት ያ ሥራየኛ ሰው ይከራከራቸው ነበረ ገዥውንም ማመንን ሊከለክለው ወዶ ነበር። ጳውሎስ በተባለው ሳውል ላይም መንፈስ ቅዱስ መላበት።

አተኲሮም ተመለከተው ኃጢአትንና ክፋትን ሁሉ የተመላህ የሰይጣን ልጅ የፅድቅ ሁሉ ጠላት ሆይ የቀናውን የእግዚአብሔርን መንገድ እያጣመምኽ ተው ብትባል እምቢ አልኽ እነሆ አሁን የእግዚአብሔር ልጅ በአንተ ላይ ተቃጥታለች ትታወራለህም እስከ እድሜ ልክህም ፀሐይን አታይም አለው። ወዲያውኑም ታወረ ጨለማም ዋጠው የሚመራውንም ፈለገ አገረ ገዢውም የሆነውን አይቶ ደነገጠ በጌታችንም አመነ።

ከዚህ በኃላ ሒደው ወደ ሊቃኦንያ ከዚያም ወደ ልስጥራንና ደርቤን ከተማ ወደ አውራጃውም ሁሉ ገብተው አስተማሩ። በልስጥራን ከተማም ከእናቱ ማሕፀን ጀምሮ እግሩ ልምሾ የሆነ አንድ ሰው ነበረ ተቀምጦ ይኖር ነበረ እንጂ ለምሾ ከሆነ ጀምሮ ቆሞ አልሄደም። ጳውሎስንም ሲያስተምር አደመጠው ጳውሎስም ተመልክቶ ሃይማኖት እንዳለው እንደሚድንም ተረዳ።

ድምፁንም ከፍ አድርጎ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሥና ቀጥ በልኽ ቁም እልሀልሁ አለው ወዲያውኑ ተነሥቶ ሔደ። አሕዛብም ጳውሎስ ያደረገውን አይተው በጌታችን አመኑ። እርሱም በዚያ ሳለ አይሁድ ከአንጾኪያና ከኢቆንያ መጥተው ልባቸውን እንዲአስጨክኑባቸው አሕዛብን አባበሏቸው።

ጳውሎስንም በድንጊያ ደበደቡት ጎትተው ወደ ውጭ አወጡት። በማግስቱም ከበርናባስ ጋራ ወደ ደርቤን ከተማ ሄዱ። በዚያችም ከተማ አስተማሩ ብዙ አህዛብንም ወደ ሃይማኖት አስገቡ ለቤተ ክርስቲያንም ቀሳውስትን ሾሙላቸው ከዚያም ወደ መቄዶንያ አልፈው ሔዱ ጋኔን ሟርት የሚያሠራትን አንዲት ልጅ አገኙ ከምታገኘው ዋጋ ለጌቶቿ ብዙ ትርፍን ታስገባ ነበር።

እንዚህ ሰዎች የልዑል እግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸው የሕይወትንም መንገድ ያስተምሯችኋል ብላ እየጮኸች ከጳውሎስ ኋላ ተከተለች ብዙ ቀንም እንዲሁ ታደርግ ነበር። ጳውሎስንም አሳዘነችው መለስ ብሎም መንፈስ ርኩስን በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንድትወጣ አዝዤሃለሁ አለው ወዲያውኑም ተዋት።

ከዚህ በኃላም ሐለብ ከሚባል አገር ደረሰ የጢሞቴዎስንም እናት ስሟ በድሮናን ከሞት አስነሣት። በዚያም ያዙት ለዚያች አገር ጣዖትም ሊሠዉት ወድደው በሚነድ እሳት ውስጥ ጨመሩት። ስለእነርሱም እየማለደ እጆቹን በመስቀል ምልክት አምሳል ዘረጋ። አሕዛብም በአዩት ጊዜ ስለዚህ ድንቅ ሥራ አደነቁ።

ከእሳት መካከልም እንደወጣ ማለዱት ምንም ምን ሳይነካው ወጣ ሰገዱለትም ክብር ይግባውና በጌታችንም አመኑ የአገሩ ሹም አርስጦስም አመነ። ሰባቱ የጣዖት ካህናቶች ግን ሸሽተው ተሠወሩ። ቅዱስ ጳውሎስም በጭላት አምሳል የተቀረጸውን ምስል ጠራው ምስሉም በአንበሳ ምሳሌ መጥቶ በምኩራቡ መካከል በጳውሎስ ፊት ቆመ።

ቅዱስ ጳውሎስም የሚያመልኩህ ካህናቶችህ ወዴት አሉ አለው አንበሳውም ያሉበትን እስክነግርህ ድረስ ጌታዬ ጥቂት ታገሠኝ አለው። ካህናቱም ወሰተሸሸጉበት ሔዶ አንዱን አንገቱን በአፉ ይዞ እየጎተተ አምጥቶ እንደ በድን በአደባባዩ መካከል ጣለው። ሰባቱንም እንዲሁ እየአንዳንዱን እየጎተተ አመጣቸው።

ሕዝቡም ሊገድሏቸው ወደዱ። ጳውሎስም ዛሬ በዚች ከተማ ማዳን እንጂ መግደል አይገባም አለ ከዚህም በኃላ ሁሉንም አጠመቃቸው ሃይማኖትንም አስተማራቸው። ያንንም አንበሳ የሆነ የጭላት ምስል አንበሳ ሆይ አትፍራ ስለ አገለገከኝ እስከ ምሻህ ድረስ ኑሮህ በበረሀ ይሁን አለው። ያን ጊዜም ወደ በረሀ ሔደ።

ጳውሎስም ከዚያ ተነሥቶ አካ ወደ ሚባል ከተማ ሔደ ስክንጥስ ከሚባል ደቀ መዝሙርም ጋራ ተገናኘ አይሁድም ዜናውን ሰምተው ከአሕዛብ ጋራ ተሰበሰቡ ይዘውም ጭንቅ የሆነ ሥቃይን አሠቃዩት ዳግመኛም ሁለት በሮችን አመጡ ከስክንጥስ ጋራም አሥረው በከተማው ጥጋጥግ በስለታም ድንጋይ ላይ አስጐተቷቸው ደማቸውም እንደ ውኃ ፈሰሰ ዐጥንታቸውም እስከሚታይ ድረስ ሥጋቸው ተቆራረጠ።

ወደ ጌታም ጸለዩ ያን ጊዜም በሮቹ ከሚነዳቸው ጋራ ደንጊያ ሆኑ። ሕዝቡም በአዩ ጊዜ ለመኮንኑ ነገሩት እርሱም ተቆጣ ወደርሱም እንዲአቀርቧቸውና በደንጊያ እንዲወግሩአቸው አዘዘ በቅዱስ ጳውሎስም ላይ እጅግ ተቆጥቶ አንተ የሥራይ ሰው እነሆ አሠቃይሃለሁ አለው በበሬ ቅርጽ የተሠሩ ሁለት የናስ ቀፎዎችንም ያመጡ ዘንድ አዘዘ።

ዝፍት ሙጫና ድኝ አምጥተው በውጭ ቀላቅለው ሁለቱን የናስ ቀፎዎች በውስጥም በውጭም ቀቧቸው። ሐዋርያትንም በውስጥ ጨምረው በእሳት ምድጃ ውስጥ አስገቧቸው ሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊትም እሳት አነደዱባቸው።

መዳኒታችንም ክርስቶስም ከመላእክቶቹ ጋር መጣ እሳቱንም ከዚያ ፈልሶ ወደ ከተማው ውስጥ ገብቶ የከተማውም ሰዋችሁሉ እንዲከባቸው አደረገው በተጨነቁም ጊዜ ጮኹ አለቀሱም መዳን ከፈለጋቹ ፈጥናቹ በአደባባዩ በአንድነት ተሰብሰቡ የሚል ቃል ከሰማይ ጠራቸው ጳውሎስም ወደ በረሀ አሰናብቶት የነበረውን አንበሳ መጣ ጳውሎስ በስሙ በሚያስተምርበት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እመኑ እያለ ጮኸ።
ከዚህም በኋላ ወደ እሳቱ ምድጃ ተመልሶ ጳውሎስንና ስክንጥስን ከእሳቱስ ውስጥ ወጡ አላቸው ያንጊዜም የራሳቸው ጠጉር እንኳ ሳይቀነብር ወጡ በላያቸውም ላይ የቃጠሎ ሽታ የለም። ይህንንም ድንቅ ሥራ አይተው በጌታችን በናዝሬቱ ኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን እያሉ ጮኹ ከዚህም በኋላ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቃቸው ስክንስንም ቅስና ሾመላቸው። ከዚሁ በኋላም ከሐዋርያ ፊልጶስ ጋራ ወደ ሁለት አገሮች በአንድነት ሔዱ በዚህም በጌታችን ስም ሰበኩ የአገሩ አለቆችም ያዙአቸው እጆቻቸውንና እግሮቻቸውንም አሠሩአቸው በአንገቶቻቸውም የብረት ሰንሰለቶችን አስገቡ ራሳቸውንም የሚሸፍን የሚሸፍን የብረት ቆብን ሠሩላቸው በእጅና በመሐል አጆቻቸውና በክንዶቻቸው እያንዳንዱን የብረት አጅ ጨመሩ ከብረቶችም ጋር ቸነከሩአቸው።

ሁለተኛም እስከ አንገት የሚደርስ በትከሻ አምሳል ሠሩ በፉትና በኋላም ቸነከሩአቸው ደግሞም መላ አካላቸውን የሚከብና ከአካላቸው ምንም እንዳይታይ የሚሸፍን የብረት ሠሌዳ ሠሩ ከወገቦቻቸውም ጋራ ቸነከሩት ችንካሮችም ተረከዛቸውን ነድለው ወደ ጭኖቻቸው እስከሚደርሱና እስከ አቈሳሏቸው ድረስ የብረት ጫማ ሠርተው እግሮቻቸውን ቸነከሩ። ደግሞ በመሸፈኛ አምሳል የብረት ሰናፉል ሠሩ ቀማሚዋችም መጡ አንድ መክሊት የሚመዝን እርሳስንም አመጡ ታላቅ የብረት ጋንንም ሰባት ልጥር የሰሊጥ ቅባትን አመጡ ሰቡንና አድሮ ማሩን የእሳቱንም ኋይል አብዝቶ የሚያነደውን ቅመሙን ከሙጫውና ከድኙ ጋር ቀላቀሉ ከዋርካና ከቁልቋል ከቅንጭብም ደም ሰባት ልጥር አንድ የወይን አረግንና ቅባት ያላቸውን ዕንጨቶች ሁሉ አመጡ።

በጋን ውስጥ ያበሰሉትንና ያሟሙትንም ልዩ ልዩ ቅመማ ቅመም አምጥተው ከስጋቸው ጋር እስከሚጣበቅ በቅዱሳን ሐዋሪያት ሥጋ ላይ ባሉት ሠሌዳዎች ውስጥ ጨመሩት በእግራቸው እስከ ራሳቸውም ከፍ ከፍ እስከሚል ድረስ በእሳት ያቀለጡትን ያንን እርሳስ ጨመሩ ርዝመቱ ዐሥራ አምስት ክንድ በሆነ ወፍራም የጥድ ምሰሶ ላይም አቆሟቸውና ከበታቻቸው ፍሬ በሌለው በወይን ሐረግና በተልባ እሳቱን አቀጣጠሉ አንዳንዱ የእሳቱ ነበልባል ከሥጋቸው በላይ ከፍ ከፍ አለ ሐዋርያት ግን ወደ እግዚአብሔር ይፀልዩ ነበር።

ከመኳንንቱም በአንድ ልብ ርኅራኄን አሳደረና እንዲፈቷቸው አዘዘ ፈቷቸው በፈቷቸውና ሠሌዳውን ከስጋቸው ላይ በአስወገዱ ጊዜ ቆዳቸው ተገፈፈና ከብረቱ ሰሌዳዋች ጋር ወጣ ብዙ ደምም ከስጋቸው ፈሰሰ። ሰይጣንም በከተማው ሰዎች ለብ አደረና ሐዋርያትን ወደ እሳት ውስጥ መለሱአቸው ያን ጊዜ ጌታችን ወርዶ የእሳቱን ነበልባል አጠፋው ዝናምን የተመላች ብርህት ደመናም መጥታ ቅዱሳን ሐዋርያትን ከበበቻቸው ከዚያችም አገር አንድ ጊዜ በደንጊያ በመወገር አንድ ጊዜም በፍላጸ በመንደፍ ብዙ ተሠቃዩ ከዚህም በሗላ ሙታንን በአነሡ ጊዜ የከተማው ሰዎች ሁሉ አመኑ አጠመቋቸውም ቤተ ክርስቲያንንም ሰሩላቸው ካህናትንም ሾሙላቸው በቀናት ሐይማኖትም እስቲጸኑ አስተማሩአቸው ከዚያም ወጥተው ጌታችን ወደ አበዘዛቸው ወደ ሌላ አገር ሔዱ።

ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለጳውሎስ ተገለጸለትና የመረጥኩህ ጳውሎስ ሆይ ሰላም ለአንተ ይሁን። መታሰቢያህ የሚያደርገውን በውስጧ የሚጸልየውን ስለትንና መባንም የሚሰጠውን በመታሰቢያህም ቀን ለድኇች የሚመጸውተውን ሁሉ ከአንተ ጋራ በመንግሥተ ሰማያት አኖራቸዋለሁ አለው።

በስምህ የታነፁትንም አብያተ ክርስቲያናት መላእክቶቼን እንዲጠብቋቸው አደርጋቸዋለሁ ብዙ ቃል ኪዳንም ሰጠው በመለኮታዊ አፉ አፉን ሳመውና ከእርሱ ዘንድ ወደ ሰማያት በክብር ዐረገ። ከዚህም በሗላ እልዋሪቆስ ወደምትባል ታላቅ ሀገር እስከ ሚደርስ በብዙ አገሮች ውስጥ ተመላለሰ በዚያም የብርሃን እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተገልጻለት አረጋጋችው ረዳችውም በመጋቢት ሃያ ዘጠኝ እንደጻፍነው የአገሩን ሰዎች እንዲአጠምቃቸውና እንዲአስተምራቸው አዘዘችው።

ከዚህም በሗላ ወደ ሮሜ ከተማ ገብቶ በውስጧ ሰበከ ከበስብከቱም ብዙዎች ሰዎች አምነው የክርስትና ጥምቀትን አጠመቃቸው በመጻሕፍትነት የታወቁ ዐሥራ አራት መልእክቱም ለሮሜ የተጻፈችው ናት። መልካም ሩጫውንም ከፈጸመ በሗላ ንጉሥ ኔሮን ይዞ ድኑ ሥቃይን አሠቃየው እራሱንም በሰይፍ እድቆርጢት ለሰያፊ ሰጠው ከሰያፊውም ጋራ አልፎ ሲሔድ ከንጉሥ ኔሮን ዘመዶች የሆነች አንዲት ብላቴና አገኘችው እርሷም ክብር ይግባውና በጌታችን ያመነች ነበረች ስለርሱም አለቀሰች።

እርሱ ግን መጎናጸፊያሽን ስጨኝ እኔም ዛሬ እመልስልሻለሁ አላት እርሷም መጎናጸፊያዋን ሰጠችውና ራስ ወደ ሚቆርጡበት ቦታ ሔደ ለሰያፊውም ራሱን በአዘነበለ ጊዜ በመጎናጸፊያዋ ፊቱን ሸፈነ ሰያፊውም የቅዱስ ጳውሎስን ራስ ቆርጦ በዚያች ብላቴና መጎናጸፊያ እንደገደለው ለንጉሥ ሊነግረው በተመለሰ ጊዜ ያቺ ብላቴና አገኘችው ያ ጳውሎስ ወዴት አለ አለችው ራስ የሚቆረጥበት ቦታ ወድቋል ራሱም በመጎናጸፊያሽ ተሸፍኗል አላት።

እርሷም እንዲህ ብላ መለሰችለት ዋሽተሃል እነሆ ጴጥኖስና ጳውሎስ በእኔ ዘንድ አልፈው ሔዱ እነርሱም የመንግሥት ልብሶችን ለብሰዋል በራሳቸውም ላይ በዕንቁ የተጌጡ ዐይንን የሚበዘብዙ አክሊላትን አድርገዋል መጎናጸፊያዬንም ሰጡኝ እርሷም እነሗት ተመልከታት ብላ ለዚያ ሰያፊ አሳየችው ከርሱ ጋራ ለነበሩትም አሳየቻቸው አይተውም አደነቁ ስለዚህም ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ።

የዚህም ሐዋርያ ጳውሎስ ተአምራቶቹ ቁጥር የሌላቸው እጅግ የበዙ ናቸው።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳት ሐዋርያት ጸሎት ይማረን በረከታቸው የቅዱሳት ሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን ልጆች ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን።

ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12
ቅዱስ ፓትርያርኩ ወደ አዲስ አበባ ተመለሱ።


ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትና  ከሀገር ሽማግሌዎች  ጋር  በክልል ትግራይ መቐለ የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው ወደ አዲስ አበባ ተመልሷል ።

ምንጭ: ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት

ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12
🔴#ስንክሳር ሐምሌ_6

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሐምሌ ስድስት በዚች ቀን እንደ ርሱ ያሉ ኤልያስና ኄኖክ ወደ አሉባት ብሔረ ሕያዋን #የነቢዩ_ዕዝራ ዕርገት ሆነ፣ #ቅድስት_ንስተሮኒን አረፈች፣ ጳውሎስ የተባለ #ቅዱስ_መርቄሎስ በሰማዕትነት ሞተ፣ የቅዱስ አብሮኮሮንዮስ እናት #ገድለኛዋ_ቴዎዳስያ በሰማዕትነት ሞተች፣ የገርአልታው #አቡነ_አብርሃም መታቢያቸው ነው፣ ሐዋርያው #ቅዱስ_በርተሎሜዎስ መታሰቢያ ነው፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ዕዝራ_ነቢይ

ሐምሌ ስድስት በዚች ቀን እንደ እርሱ ያሉ ኤልያስና ኄኖክ ወደ አሉባት ብሔረ ሕያዋን የዕዝራ ዕርገት ሆነ። ይህም ነቢይ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ የሚጽፍ ነበረ እርሱም ከሌዊ ወገን ነበረ። ከእግዚአብሔርም ጋራ ግሩም የሆነ ነገርን መናገር ጀመረ እንዲህም አለ ምድርን በፈጠርካት ጊዜ አዳምን ታስገኝ ዘንድ አዘዝካት አስገኘችውም።

ሁለተኛው የጥፋት ውኃ በጊዜው እንደ መጣና ሁሉን እንዳጠፋ ተናገረ ኖኅ አብርሃምና ዳዊት እንዴት እንደ ተመረጡ ደግሞ ተናገረ። ዳግመኛም ነፍስ ከሥጋዋ እንደምትወጣና ሰባት ቀኖች እንደምትዞር ከዚያም በኋላ እንደ ሥራዋ ወደተዘጋጀላት ቦታዋ እንደምትገባ ተናገረ።

ከዚያም ስለ ፍርድ ቀን ተናገረ። ከእግዚአብሔር ከጌትነቱ ብርሃን በቀር ፀሐይና ጨረቃ መብራትና ብርሃንም እንደሌሉ ተናገረ። ዳግመኛም በልቧ እጅግ በምትጨነቅ በምታዝንና በምትተክዝ ሴት አምሳል ጽዮንን አያት ልብሶቿም የተቀደዱ ነበሩ ልጇም ወደ ጫጕላው ቤት በገባበት ቀን እንደሞተ ነገረችው። ከዚህም በኋላ እርሷን ከማየቱ የተነሣ ፈርቶ በድንጋፄ እስከ ወደቀ ድረስ ፊቷ በድንገት እንደ መብረቅ በራ።

ደግሞም ዐሥራ ሁለት ክንፎችና ሦስት ራሶች ያሉት ንስር ከባሕር ሲወጣ ከክንፎቹም ውስጥ ራሶች ሲወጡ አየ እኒህም በየዘመናቸው ገዝተው የጠፉ ነገሥታት ናቸው። ደግሞም ስለ መድኃኒታችን ክርስቶስ መወለድ ተናገረ እንዲህም አለ። አንበሳ እያገሣ ከበረሀ ወጣ በሰው አንደበትም ሲናገር ንስሩንም ሲገሥጸው ሰማሁት አለ።

ዳግመኛም ስለ ክርስቶስ እንዲህ ብሎ ትንቢት ተናገረ። በሌሊት ታላቅ ነፋስ ከባሕር ሲወጣ አየሁ ከማዕበሉ የተነሣ ባሕሩ ይታወክ ነበር ነፋሱም እንደ ሰው አምሳል ሁኖ ከባሕር ሲወጣ አየሁ። ደግሞም ከብዙ ኃይልና ክብር ጋር በሰማይ ደመና ማረጉን በአብ ቀኝ መቀመጡንም አይቶ ተናገረ።

ዳግመኛም በፈሳሹ ማዶ ያኖራቸው ዘጠኙ ነገድ እንደሚሰበሰቡ ተናገረ። ከዚህም በኋላ የነቢያት መጻሕፍትና የአባቶችን ትውልድ የያዙ መጻሕፍት ተደምስሰው መጥፋታቸውን በአሰበ ጊዜ ወደ በረሀ ገብቶ በጾምና በጸሎት ምሕላ ያዘ። ከእርሱም ጋር አምስት ጠቢባን ጸሐፊዎችን ወሰደ።

ከዕንጨቱም አንጻር ቃል ጠርቶት ዕዝራ አፍህን ክፈት ብሎ ኅብሩ እሳት የሚመስል ውኃን የተመላ ጽዋን ሰጠው። ያንንም ጽዋ ጠጣ ያን ጊዜም ልቡናው ጥበብን አገሣ። ተገልጾለትም መጻሕፍትን ሁሉ ሰበሰበ ለእነዚያም ሰዎች ልዑል አምላክ ዕውቀትን ሰጣቸው። መጻሕፍትንም ሁሉ በየተራቸው ጻፉ። በዚያም አርባ ቀን ኖሩ እነዚያ ግን ቀን ቀን ይጽፋሉ ማታ ማታም ይመገባሉ እርሱ ግን ቀን ይጽፋል ማታም ዝም አይልም በእነዚያ አርባ ቀኖችም ሁሉ መጻሕፍት ተጻፉ።

ከዚህም በኋላ ልዑል እንዲህ ሲል ተናገረው የዕውቀት ምሥጢር የጥበብም ምሥጢር እንደ ፈሳሽ ውኃም ያለ ዕውቀት ላላቸው ታስተምራቸው ዘንድ ይህን ተመልከት እንዳለውም አደረገ። በአራተኛውም ዘመን ከሚቈጠሩ ከብዙ ሱባዔ በአምስተኛው ሱባዔ ይህ ዓለም ከተፈጠረ ከአምስት ሺ ዘመን በኋላ ጨረቃ ሠርቅ አድርጋ ጨለማዋን ባጣች በአሥረኛው ቀን በሦስተኛው ወር በዘጠና አንድ እንደእርሱ ያሉ ደጋግ ሰዎች ወዳሉበት ዕዝራን ወሰዱት።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅድስት_ንስተሮኒን_ዘኢየሩሳሌም

በዚህችም ዕለት ቅድስት ንስተሮኒን አረፈች። እርሷም ከኢየሩሳሌም ሰዎች ውስጥ ነበረች። እርሷም አስቀድማ ኃጢአተኛ ነበረች ከዚያም በኋላ ንስሓ ገብታ ወደ እግዚአብሔር በተቃጠለ ልብ ተመለሰች የሥጋን ፍላጐቶች ሁሉ ናቀች እመምኔት እስከ ሆነች ድረስ በበጎ ሥራ ሁሉ ትሩፋትንና ተጋድሎን አበዛች።

እኅቶችም ከገድል ብዛትና ምግብን ከመተው የተነሣ ሥጋዋ እንዳለቀ አይተው ሥጋሽን እንድትረጂ ጥቂት እህል በወጥ ብዪ አሏት። አብዝተውም ግድ ባሏት ጊዜ ልጆቼ ሆይ ወደ ቀድሞ ልማዴ እንዳልመለስ ጥቂት ወጥ ስለመብላት አትድከሙ ስለዚህ ወጥ አልበላም አለቻቸው። ከዚህ በኋላ በሰላም አረፈች።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_መርቄሎስ_ሐዋርያ

በዚህችም ዕለት ጳውሎስ የተባለ ቅዱስ መርቄሎስ በሰማዕትነት ሞተ። ይህም ከሰባ ሁለቱ አርድእት ውስጥ ነው። እርሱም ሐዋርያትን አገልግሎአቸዋል። ወንጌልንም ለመስበክ ከእነርሱ ጋር ሔደ። የሐዋርያው የቅዱስ ጴጥሮስን መልእክቶች አደረሰ በመከራውም ጊዜ አገለገለው። ከእርሱም ጋር መከራ ተቀበለ ከእርሱም አልተለየም።

ወደ ሮሜ አገርም ከርሱ ጋር ገብቶ ቅዱስ ወንጌልን አስተማረ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ማመን ከአረማውያን ብዙዎቹን መለሳቸው። ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስም በሰማዕትነት በሞተ ጊዜ ይህ ረድእ መርቄሎስ መጥቶ ከመስቀል ላይ አወረደው በከበሩ ልብሶችም ከሽቱ ጋር ገነዘው። በሣጥንም አድርጎ ከምእመናን በአንዱ ቤት አኖረው።

የሐዋርያው ጴጥሮስ ደቀ መዝሙርም እንደሆነ በኔሮን ዘንድ ወነጀሉት ንጉሡም ወደ እርሱ አቅርቦ ጠየቀው እርሱም ለሐዋርያው ጴጥሮስ ደቀ መዝሙሩ እንደሆነ አመነ ደግሞም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዕውነተኛ አምላክ እንደሆነ ታመነ።

ስለዚህም ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃየው ገረፈውም ዘቅዝቀው ሰቅለውም ከበታቹ ጢስን አጤሱበት። ከዚህም በኋላ ንጉሡ እንዴት ሁነህ መሞት ትሻለህ በምን አይነት ሞት ልግደልህ ንገረኝ አለው። ቅዱሱም እንዲህ ብሎ መለሰ እኔ ሕይወት በሆነ በክርስቶስ ስም መሞት እሻለሁ አንተ ግን በፈለግኸው ዓይነት ግደለኝ ፈጥነህም ወደ ፈለግኸው አድርሰኝ።

ያን ጊዜም ንጉሡ ኔሮን እንዲገርፉትና እንደ መምህሩ ጴጥሮስ ዘቅዝቀው እንዲሰቅሉት አዘዘ እንዲሁም አደረጉበት። የሰማዕታትንና የሐዋርያትን አክሊል ተቀበለ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅድስት_ቴዎዳስያ_ሰማዕት

በዚህችም ቀን የቅዱስ አብሮኮሮንዮስ እናት ገድለኛዋ ቴዎዳስያ በሰማዕትነት ሞተች፡፡ ከእርሷ ጋርም ሁለት መኳንንቶችና አሥራ ሁለት ሴቶች በሰማዕትነት ሞቱ።

ይህም እንዲህ ነው ይቺ ቅድስት ልጇ አብሮኮሮንዮስን ክርስቲያን ነው ብለው እንደወነጀሉትና ለሞት እስቲደርስ ጽኑዕ ሥቃይን እንዳሠቃዩት ሰማች። ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በዚያች ሌሊት ተገለጠለት ከሥቃዩም አዳነው ያለ ምንም ጉዳት ጤናማ ሆነ።

እኒህ ሁለቱ መኳንንትና ዐሥራ ሁለት ሴቶች ከእናቱ ጋር በአዩት ጊዜ እጅግ አደነቁ እንዲህ ብለውም ጮኹ እኛ በአብሮኮሮንዮስ አምላክ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን መኰንኑም ራሶቻቸውን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ በመንግሥተ ሰማያትም የክብር አክሊልን ተቀበሉ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አቡነ_አብርሃም_ዘገርአልታ
ዳግመኛም በዚህች ዕለት የገርአልታው አቡነ አብርሃም መታቢያቸው ነው፡፡ ኢትዮጵያዊ ጻድቅ ሲሆኑ የትውል ሀገራቸው ትግራይ ነው፡፡ በሥርዓተ ገዳማትና በሥርዓተ ቀኖና ዐዋቂነታቸው ወደር የማይገኝላቸው አባት ናቸው፡፡ ከመጀመሪያዎቹ የኢትዮጵያውያን ቅዱሳን ውስጥ አንዱ ናቸው፡፡ በስማቸው የተሠራው ገዳም በትግራይ ገርዓልታ የሚገኝ ሲሆን አጽቢ መንበርታ ደብረ ጽዮን አቡነ አብርሃም ገዳም ይባላል፡፡  ስለ አቡነ አብርሃም ከዚኽ ያለፈ ዝርዝር መረጃ ማግኘት አልተቻለም፡፡ በገዳማቸው ያሉ አባቶችም የጻድቁን የዕረፍታቸውን ቀን ከመጠቆም ያለፈ ነገር ለመናገር ገድሉ የላቸዉም፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ሐዋርያው_በርተሎሜዎስ

በዚህች ዕለት ሐዋርያው ቅዱስ በርተሎሜዎስ መታሰቢያ ነው፡፡ ወንጌልን ይሰብክ ዘንድ ዕጣ የደረሰው አልዋሕ በሚባል አገር ነው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ሊያደርሰው አብረው ወደ አልዋሕ ሄዱ፡፡ ወደ ከተማው ለመግባት ምክንያት ፈለጉና ቅዱስ ጴጥሮስ ቅዱስ በርተሎሜዎስን ‹‹አትክልተኛ ባለሙያ ነው›› ብሎ የወይኑን ቦታ እንዲጠብቅለት ለአንድ ባለጸጋ መኰንን ባሪያ አድርጎ ሸጠው፡፡ ባለጸጋውም በርተሎሜዎስን በ30 እስቴታር ገዝቶት ሄደ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ገንዘቡን ደብቆ ለቅዱስ በርተሎሜዎስ በድብቅ ሰጥቶት እንዲመጸውተው ነግሮት ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ፡፡ አልዋሕ ከገባ በኋላ ቅዱስ በርተሎሜዎስ የወይን ቦታው አለቃ ሆኖ 40 ቀን ተቀመጠ፡፡ ወንጌሉን ባለመስበኩ በሀዘን እያለቀሰ ጌታችንን በጸሎት ጠየቀው፡፡ በገንዘቡ ገዝቶት ባሪያው ያደረገው ባለጸጋውም የወይኑን ቦታ ያይ ዘንድ እንደመጣ መርዘኛ እባብ ነድፎት ሞተ፡ ሕዝቡም ተሰብስቦ ሲያለቅስ በርተሎሜዎስ ግን ወደ ጌታችን ከጸለየ በኋላ ሄዶ ባለጸጋውን ሰው ከሞት አስነሣው፡፡ በዚህም ሕዝቡ ሁሉ አምነው ተጠምቀዋል፡፡

በርተሎሜዎስም ወደ ሌሎች አገሮች ሄዶ አስተማረ፡፡ ጌታችን ወደ በርበሮች ዘንድ ሄዶ ወንጌልን እንዲሰብክ አዘዘው፡፡ ረዳት እንዲሆነውም እንድርያስን ከደቀ መዝሙሩ ጋር ላከለት፡፡ የሀገሪቱ ሰዎች ግን እጅግ ክፉዎች ነበሩ፡፡ በሐዋርያቱም ፊት በአስማት አስደናቂ ተአምራት እያሳዩ ትምህርታቸውን የማይቀበሏቸው ሁኑ፡፡ ይህን ጊዜ ጌታችን ሰውን ከሚበሉ አገር አንዱን ገጸ ከልብ ይታዘዝላቸው ዘንድ በሚያዙትም ነገር ሁሉ ከትእዛዛቸው እንዳይወጣ አዘዘው፡፡ ሐዋርያትም ወደ በርበሮች አገር ዳግመኛ በገቡ ሰዓት ይበሏቸው ዘንድ ኃይለኛ አራዊትን አውጥተው ለቀቁባቸው፡፡ ያ ገጸ ከልብም በአራዊቱ ላይ ተነሥቶ እየነጠቀ በላቸው፡፡ ይህንንም የተመለከቱት በርበሮች እጅግ ፈርተው በድንጋጤ ብቻ የሞቱ አሉ፡፡ በሐዋርያቱም እግር ሥር ወደቁ፡፡ ሐዋርያቱም አስተምረው ካሳመኗቸው በኋላ አጥምቀዋቸዋል፡፡ ከዚህ በኋላ ቅዱስ በርተሎሜዎስ እግዚአብሔርን ወደማያውቁ አገሮች ሄዶ ብዙ ተአምራትን እያደረገ አስተምሮ አጠመቃቸው፡፡ የከሃዲው ንጉሡ የአግሪጳን ሚስትም ትምህርቱን ሰምታ በጌታችን አመነች፡፡ ንጉሡ አግሪጳም በዚህ እጅግ ተቆጥቶ ቅዱስ በርተሎሜዎስን ብዙ ካሠቃየው በኋላ አሸዋ በተሞላ ትልቅ ከረጢት ውስጥ ከቶ ከነሕይወቱ ባሕር ውስጥ እንዲጥሉት አደረገ፡፡ ምእመናንም ሥጋውን አውጥተው በክብር ቀብረውታል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ በርተሎሜዎስ ይኽች ዕለት መታሰቢያ በዓሉ እንድትኾን አባቶቻችን አዘዋል፡፡

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን አባቶቻችንና እናቶቻችን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።https://t.me/finotebirhan12
ውድ የተከበራችሁ የሰንበት ት/ቤታችን አባላት ይህ ሥርዓተ አምልኮ ዘፍልሰታ የሚለው መጽሐፍ በሰ/ት/ቤታችን የልማት ሱቅ እየተሸጠ ይገኛል። እርስዎም መጽሐፉን በመግዛት እንዲያነቡ ጋብዘንዎታል።
የፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት ልማት ሱቅ

ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
አሜን፡፡
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

በክልል ትግራይ በተካሄደው ጦርነት በቤተ ክርስቲያናችን የበላይ መዋቅርና በክልል ትግራይ አህጉረ ስብከት መካከል የነበረው አስተዳደራዊ መዋቅር ተቋርጦ መቆየቱን ተከትሎ የተፈጠረው አለመግባባት በውይይት ተፈቶ መዋቅራዊ አንድነታችን በድጋሚ ተጠናክሮ እንዲቀጠል ሀገራዊ የሰላም እርቁ ከተፈጸመበት ማግስት ጀምሮ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ፊርማ በተደጋጋሚ በደብዳቤ ሲጠየቅ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

ምንም እንኳን ቅዱስ ሲኖዶሱ ችግሩ በውይይት እንዲፈታ ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪ ሲያደርግ የቆየ ቢሆንም በክልሉ ያሉት ብፁዓን አባቶችና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በተከፈተው የሰላምና የውይይት በር ከመጠቀም ይልቅ መዋቅራዊ አደረጃጀቱን በመጣስ መንበረ ሰላም የትግራይ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት መሥርተናል በሚል ተገቢነት የሌለው መግለጫ ከመስጠትም አልፎ ሲመተ ኤጲስ ቆጶሳት መፈጸም አለበት የሚል ውሳኔ በማሳለፍ 10 ኤጲስ ቆጶሳትን ሐምሌ 9 ቀን 2015 ዐ.ም. ለመሾም ፕሮግራም መያዙን በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን መግለጫ መስጠታቸውን ተከትሎ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሰኔ 29 ቀን 2015 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ በጉዳዩ ላይ ከተወያየ በኋላ በጦርነቱ ወቅት ለነበረው የመዋቅራዊ ግንኙነት ጉድለትና የሰብአዊ ድጋፍ እጥረት በይፋዊ መግለጫ ይቅርታ የተጠየቀ ቢሆንም ለይቅርታው አዎንታዊ ምላሽ አለመሰጠቱ በእጅጉ አሳዛኝ መሆኑ፤
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለችግሩ መፈታት ባላት ቁርጠኝነት በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የሚመራ የሰላም ልዑክ ወደ ክልሉ በመላክ በክልሉ ለደረሰው ጉዳት ሰብአዊ ድጋፍ የሚውል ብር20,000,000.00(ሃያ ሚሊየን ብር) ለክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ያስረከበች ሲሆን በዚህም ወቅት ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ለተደረገው የከበረ አቀባበል ቅዱስ ሲኖዶስ አመስግኗል፡፡

ይሁን እንጁ የሰላም ልዑኩ ዋና ተልእኮ የሆነውን በክልሉ ከሚገኙ ብፁዓን አባቶች ጋር ለመወያየት የተያዘውን አጀንዳ በተመለከተ በብፁዕ ወቅዱስ አባታችን የተመራው የሰላም ልዑክ በመቀሌ ሀገረ ስብከት በደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል የተገኘ ቢሆንም ቤተ ክርስቲያን በመዘጋቱ ምክንያት ቅዱስ ሲኖዶሱ ምልዓተ ጉባኤ በእጅጉ አዝኗል፡፡

በመሆኑም የተፈጠረውን ችግር ተከትሎ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ አንቀጽ 19 ንዑስ ቁጥር 13 የሕግ ድንጋጌ መሠረት ሐምሌ 6 ቀን 2015 ዓ.ም. ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አሳልፏል፡፡

በትግራይ ክልል ሐምሌ 9 ይደረጋል የተባለው የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ የሕገ ቤተ ክርስቲያንና አንቀጽ 37 እና 38 ያላከበረና ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን አንጻር ተገቢ ያልሆነ የቤተ ክርስቲያንን ማዕከላዊነት የሚጥስ፣ የቤተ ክርስቲያንን አንድነት የሚጎዳና በጦርነት የተጎዳውን ሀብት ንብረቱ የወደመበትን ገዳማቱና አብያተ ክርስቲያናቱ የተጎዱበትን ሕዝብ የማይጠቅም ተገቢነት የሌለው በመሆኑ እንዲቆም ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

በትግራይ ክልል ተከስቶ የነበረውን ችግር የፌዴራል መንግሥትና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ችግሩን በውይይት የፈቱት መሆኑ እየታወቀ የሰላም ባለቤት የሆነችው ቤተ ክርስቲያን እስካሁን ሰላም መፈለጓ ያልተቋረጠ ቢሆንም አለመሳካቱ የሚያሳዝን በመሆኑ ለሰላም የሚደረገው ጥረት ዘላቂ መፍትሔ እስከሚገኝ ድረስ የማይቋረጥ መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ ይገልጻል፡፡

በመሆኑም ክቡር የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና ክቡር አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት እንዲሁም የፌዴራልና የክልሉ መንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እየተደረገ ያለውን ሕገ ቤተ ክርስቲያንን ያልተከተለ የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ እንዲያስቆሙልን ብሎም ሰላም ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት በመደገፍ ችግሮቹ በውይይት እንዲፈቱ መንግሥታዊ እገዛ በማድረግ የውይይት መድረክ እንዲያመቻቹልን ሲል የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

በመላው ዓለም የምትገኙ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና ሕዝበ ክርስቲያን እናት ቤተ ክርስቲያናችሁ ያስተላለፈችውን የሰላም ጥሪ ተግባራዊ ሆኖ አንድነቷ ጸንቶ ይኖር ዘንድ በጸሎት ተግጋችሁ ከቤተ ክርስቲያናችሁ ጎን እንድትቆሙ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ 

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

ሐምሌ 6 ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም አዲስ አበባ
   ኢትዮጵያ

ምንጭ :-ኢኦተቤ

ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12

የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12
#ሐምሌ_7

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሐምሌ ሰባት በዚች ቀን #ሥሉስ_ቅዱስ በአብርሃም ቤት የተገለጡበት ነው፣ ኢትዮጵያዊው ሊቅ #ቅዱስ_የአባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ ልደቱና ዕረፍቱ ነው፣ ቅዱስ አባት የባሕታውያን አለቃ የሆነ መስተጋድል #አባ_ሲኖዳ አረፈ፣ የሮሜ ከተማ ሊቀ ጳጳሳት #ቅዱስ_አግናጥዮስ በሰማዕትነት ሞተ፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅድስት_ሥላሴ

ሐምሌ ሰባት በዚች ቀን ሥሉስ ቅዱስ በአብርሃም ቤት የተገለጡበት ነው፡፡ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በስም በአካል በግብር ሦስትነት በባሕርይ በሕልውናና በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ተገኙ፣ በዚህ ጊዜ ያልፋሉ አይባሉም መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸውና፡፡ ርሕሩሐን ናቸውና በእናት ሥርዓት ‹‹ቅድስት ሥላሴ›› እንላቸዋለን፡፡ የሚጠላቸው (የማያምንባቸውን) አይጠሉም፡፡ የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል፣ በቤቱም መጥተው ያድራሉ፡፡ ከፍጥረታት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የአብርሃምን ያህል በሥላሴ ዘንድ የተወደደ ፍጡር የለም፡፡ አባታችን ቅዱስ አብርሃም የደግነት ሁሉ አባት ነውና በኬብሮን በመምሬ ዛፍ ሥር ሥላሴን ተቀብሎ አስተናግዷል፡፡

አባታችን አብርሃም በ99 ዓመቱ እናታችን ሣራ በ89 ዓመቷ ሥላሴን በድንኳናቸው አስተናገዱ፡፡ አብርሃም እግራቸውን አጠበ፡፡ በጀርባውም አዘላቸው፡፡ ምሳቸውንም አቀረበላቸው፡፡ እነርሱም እንደሚበሉ ሆኑለት፡፡ በዚያው ዕለትም የይስሃቅን መወለድ አበሠሩት፡፡ አብርሃም ከደግነቱና እንግዳ ከመውደዱ የተነሣ በተመሳቀለ ጎዳና ላይ ድንኳን ሠርቶ የወጣ የመረደውን፣ የመጣ የሄደውን ሁሉ እየተቀበለ እግዚአብሔርን እያገለገለ የሚኖር ጻድቅ ነበር፡፡ ለዚህም ነው አብርሃም በወይራ ግራር (በመምሬ) ዛፍ ሥር ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር አንድነቱን ሦስትነቱን የገለጠለት፡፡ ዘፍ 18፡1-25፣ ሮሜ 4፡-3፡፡ ቀትር ሰዓት ላይ በድንኳኑ ደጅ ተቀምጦ እንግዳ ሲጠብቅ እግዚአብሔር ታየው ተነጋገረው፡፡ አንገቱን ቀና አድርጎ ዐይኑን አራምዶ በተመለከተ ጊዜ እነሆ ሦስት ሰዎች ከበላዩ ባለ ተራራ ላይ ቆመው አያቸው፣ ወደ እርሱም ሲወርዱ አይቶ ፈጥኖ ሄዶ ከሰግደላቸው በኋላ ‹‹አቤቱ በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ እንደሆነ ባሪያህን አትለፈኝ ብዬ እለምናለሁ፤ ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ እግራችሁን ታጠቡ…›› እያለ በትሕትና በመጋበዝ ወደ ድንኳኑ አስገብቶ በሚገባ ጋበዛቸው፡፡ ‹‹በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ›› ብሎ አንድነታቸውን፣ ‹‹ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ እግራችሁን ታጠቡ›› ብሎ የሦስትነታቸውን ምስጢር ገልጾአል፡፡

ያች ሥላሴ የገቡባት የአብርሃም ድንኳን የእመቤታችን ምሳሌ ናት፡፡ ሥላሴ ወደ አብርሃም ድንኳን እንደገቡ ሁሉ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያምም አብ ለአጽንዖ፣ መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ፣ ወልድ በተለየ አካሉ ሥጋዋን ለመዋሐድ የማደራቸው ምሳሌ በመሆኑ አማናዊቷ የሥላሴ ማደሪያ የአብርሃም ድንኳን እመቤታችን ናት፡፡ ሉቃ 1፡35፡፡

እግዚአብሔርም አብርሃምን የዛሬ ዓመት ልጅ እንደሚወልድ ነግሮት በዓመቱ ይስሐቅን ወልዷል፡፡ ሁለቱ ሰዎች ከአብርሃም ድንኳን ወጥተው ወደ ሰዶም ወደ ገሞራ ሄዱ፣ አብርሃምም ይሸኛቸው ዘንድ አብሯቸው ሄደ፡፡ የሄዱትም ሁለቱ ሰዎች አብና መንፈስ ቅዱስ ናቸው፡፡ ነገር ግን አንዱ ወልድ በአብርሃም ቤት ቀርቷል ይኸውም ከቤተ አብርሃም ሰው እንደሚሆን ለማጠየቅ ነው፡፡ አብርሃምም ተመልሶ በእግዚአብሔር ፊት ቆመ፡፡ እግዚአብሔርም የሚሠራውን ሁሉ ከአብርሃም አይሠውርም ነበርና የሰዶምን የገሞራን ጥፋት ነገረው፡፡ አብርሃምም ይቅር እንዲላቸው አብዝቶ ለመነላቸው፡፡ ሥሉስ ቅዱስን የአብርሃሙ ሥላሴን በምግባር በሃይማኖት ሆነን እናገለግል ዘንድ የቅዱሳኑ ጸሎት ይርዳን!

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አቡነ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ

በዚህች ዕለት ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ልደቱና ዕረፍቱ ነው፡፡ አባቱ ሕዝበ ጽዮን ዘትግራይ እናቱ አምኃ ጽዮን ዘወለቃ ይባላሉ፡፡ ስለሆነም ሀገሩ ትግራይና ወሎ ቦረና ነው፡፡ ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ በመባል የሚታወቀው ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በድርሰቱ ከቅዱስ ያሬድ ቀጥሎ ስሙ የሚነሣ ታላቅ መመኪያችን የሆነ ጻድቅ አባታችን ነው፡፡ አባ ጊዮርጊስ ከመናኝ ጻድቅነቱ በተጨማሪ በመላእክትም ዘንድ የተመሰከረለት ታላቅ ፈላስፋና ደራሲም ነው፡፡ በድርሰቱ ላይ ስለ ሰማይ፣ ስለ መብረቅ፣ ስለ ደመና፣ ስለ ዝናብ አፈጣጠር፣ ስለ አራቱ ዓለማትና ስለ ሰባቱ ሰማያት… በእነዚህና በመሳሰሉት በመንፈሳዊው በሚገባና እጅግ በሚያስደንቅ መንገድ ተፈላስፎባቸዋል፡፡

ጻድቁ ድርሰቶቹን እርሱ ካለበት ወደ ሌላ ቦታ ለመላክ ንፋስ ይታዘዝለት ነበር፡፡ ስለ ጾምና ስለ በዓላት የደረሰውን ድርሰቱን ለሸዋው ንጉሥ ደብዳቤ ጽፎ በነፋስ ጭኖ ልኮለታል፡፡ አስደናቂ ገደሙ ወሎ ቦረና ውስጥ ይገኛል፡፡ ጋስጫ በድሮ ስሟ ደብረ ባሕርይ ትባላለች፡፡ በአጠገቡም ራሱ አባ ጊዮርጊስ የፈለፈላቸው ብዙ ዋሻዎች አሉ፡፡ ከአባ ጽጌ ድንግል ጋር ለመገናኘት እንዲያመቻቸው ብለው የሠሩት ድልድይ ‹‹የእግዜር ድልድይ›› ይባላል፡፡ በእግር 5 ሰዓት የሚያስኬድ መንገድ ነው፡፡ የአባ ጊዮርጊስ ጋሥጫ ገዳም የአውሬ ሰጋጅና ባሕታዊ ያለበት አስደናቂ ገዳም ነው፡፡ በየዓመቱ የስቅለት ዕለት ቁመቱ 60 ክንድ የሆነ ዘንዶ ከመቅደሱ ወጥቶ ግብረ ሕመማት ከሚነበብበት ከአትሮንሱ ሥር ሆኖ ተጠምጥሞ እራሱን ቀና አድርጎ ሲሰግድ ውሎ ካህኑ ሲያሰናብት ማታ ተመልሶ ወደ መቅደሱ ይገባል፡፡ ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ የተሰኘውን የዚህን ድንቅ አባታችንን ዜና ሕየወቱን በደንብ መመልከቱ ተገቢና አስፈላጊ ነው፡፡

የተወለደው በ1357 ዓ.ም በወሎ ክፍለ ሀገር በቦረና ወረዳ ሰግላ በተሰኘች ቦታ ነው፡፡ የተወለደው በቅዱስ ዑራኤል አብሳሪነት ነው፡፡ ወላጆቹ አስቀድሞ ልጅ አልነበራቸውምና በስለት ነው ያገኙት፡፡ አባ ጊዮርጊስ በመጀመርያ እናቱ ፈሪሐ እግዚአብሔርን እያስተማረች በጥበብና በዕውቀት አሳደገችው፡፡ ቀጥሎም የመጀመርያውን የቤተ ክርስቲያን ትምህርት የተማረው ከአባቱ ነበር፡፡ ሊቅ የነበረው አባቱ ካስተማረው በኋላ በ1341 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ ከመጡትና እስከ ዐፄ ዳዊት ዘመነ መንግሥት ጳጳስ የነበሩት ከአቡነ ሰላማ መተርጕም ዘንድ ወስዶ ዲቁና አሹሞታል፡፡

ዲቁና ከተቀበለ በኋላ ለትምህርት ወደ ሐይቅ እስጢፋኖስ ወሰደው፡፡ አባ ጊዮርጊስ በሐይቅ እስጢፋኖስ ትምህርት አልገባው ብሎ ለሰባት ዓመታት ተቀምጦ ነበር፡፡ አብረውት የሚማሩት ተማሪዎች ‹‹ይህ ትምህርት የማይገባው ስለ ምንድን ነው? በእርሱ ኃጢአት ነው ወይስ በወላጆቹ?›› ይሉት ነበር፡፡ በዚያ ጊዜ የሐይቁ መምህር የነበረው ዐቃቤ ሰዓት ሠረቀ ብርሃን ለአባቱ ‹‹ልጅህ ትምህርት አይገባውምና የቤተ መንግሥት ነገር አስተምረው›› ብሎ መለሰው፡፡ አባቱ ሕዝበ ጽዮን ግን ‹‹አንድ ጊዜ ለእግዚአብሔር ሰጥቼዋለሁ፤ እዚያው ገዳሙን ያገልግል›› ብሎ እንደ ገና ወደ ሐይቅ ላከው፡፡ አባ ጊየርጊስ ከቀለም ትምህርቱ ይልቅ በሥራ እየደከመ የገዳሙን አባቶች ይረዳ ጀመር፡፡ በገዳሙ እንጨት ይሰብር ውኃ ይቀዳ ይልቁንም ደግሞ አብዝቶ እህል በመፍጨት ያገለግል ነበር፡፡ አባ ጊዮርጊስ እህል ይፈጭበት የነበረውን የድንጋይ ወፍጮና ንፍሮ ይቀቅልበት የነበረው የድንጋይ ትልቅ ማሰሮ አሁንም ድረስ በሐይቅ ገዳም በክብር ተጠብቀው ይገኛሉ፡፡ ጊዮርጊስ ግን ትምህርቱን ለመረዳት የዘገየ ሆነ፣የእግዚአብሔር ቃልም አልገባውም ነበር፡፡ ይህም ስለ ኃጢአቱ አይደለም፡፡
የእግዚአብሔር ሥራና

ጌትነቱ በእርሱ ላይ ይገለጥ ዘንድ ነው እንጂ፡፡ ጸጋ ያለመከራ አይሰጥምና ያለመፈተንም ማብዛት አይቻልም፡፡ ጌታችንን ዕውር ሆኖ ስለተወለደው ሕፃን ደቀ መዛሙርቱ በጠየቁት ጊዜ ‹‹ይህ ሕፃን ዕዉር ሆኖ የተወለደው በማን ኃጢአት ነው? በራሱ ነውን ወይስ በወላጆቹ?›› አሉት፡፡ ጌታችንም ‹‹እርሱም አልበደለም፣ ወላጆቹም አልበደሉም፣ የእግዚአብሔር ሥራ በእርሱ ላይ ይገለጥ ዘንድ ነው እንጂ›› አላቸው፡፡ ዮሐ 9፡1፡፡ ሐዋርያትም መንፈስ ቅዱስ እስኪወርድላቸው ድረስ በትንሽ ዕውቀት ነበሩ፡፡ ‹‹በመጻሕፍት ያለውን ገና ዐላወቁምና›› ተብሎ እንደተጻፈ እንዲሁ አባ ጊዮርጊስም ዕውቀት ስለ ተሰወረውና ጓደኞቹ በትምህርት ሲቀድሙት ባየ ጊዜ እጅግ አዘነ፡፡ ስለዚህም በጾምና በጸሎት ወደ እግዚአብሔር መጮኽ ጀመረ፡፡ ሁልጊዜም በሥዕለ ማርያም ሥር እየተንበረከከ ጥበብን እንዲሰጠው ወደ እግዚአብሔር አብዝቶ በመለመን እንባንም በማፍሰስ ይጸልይ ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ እመቤታችን ተገለጠችለትና አረጋጋችው፡፡ ዳግመኛም እንደምትመጣ ቀን ቀጥራው ከእርሱ ተሰወረች፡፡

በሰጠችውም ቀጠሮ መሠረት በነሐሴ 21ኛው ቀን እመቤታችን ሚካኤልና ገብርኤል በቀኝና በግራ ሆነው ኪሩቤልንና ሱራፌልን አስከትላ ተገለጠችለትና «አይዞህ ዕውቀት የተሰወረብህ ትምህርት ስለማይገባህ ሳይሆን የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ እንዲገለጥ ነው» አለችው፡፡ ‹‹የመረጥሁህ የልጄ ወዳጅ ጊዮርጊስ ብላ በስሙ ጠራችው፡፡ ከዕውቀት ወንዝ የመጣና ከጥበብ ምንጭ የተገኘ ከመለኮት ባሕር የተቀዳ ይህን ንጹሕ ጽዋ ንሣ ጠጣ›› በማለት ጽዋዓ ልቡናን አጠጣችው፡፡

ይኸውም ጽዋዕ ልቦና በዮሴፍ ቤት በጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት የጠጡት መንፈሳዊና ሰማያዊ መጠጥ ነው፤ በበዓለ ሃምሳ ከጠጡት ያልተለየ ነው፡፡ ይኸውም የሚናገር እሳት፣ የሚያድን እሳት፣ መለኮታዊ እሳት ነው፡፡ ከዚህም በኋላ አባ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያንን ያስጌጠበት የመጻሕፍትን ምስጢራት፣ የማኅሌትንና የድርሳናትን ቃል፣ ምስጋናዎችንም ሁሉ እመቤታችን ገለጠችለት፡፡

እመቤታችን ማርያም ለብፁዕ ጊዮርጊስ ጽዋውን ካጠጣችው በኋላ ያን ጊዜ አምስት የምሥጢር ቃላትን አስተማረችው፡፡ የኅሊናን ዓይኖች ያበራሉና የልቡናንም ጆሮዎች ይከፍታሉና፡፡ ከዚህ በኋላ ከእርሱ ተሰወረች፤ ከማይተኙ ከትጉሃን መላእክትም ጋር ወደ ሰማይ ዐረገች፡፡ የአምስቱ የምሥጢር ቃላት ትርጉምም ዕውቀትን የተመሉ መንፈሳውያን አባቶቻችን እንደ ነገሩን ከእመቤታችን ማርያም እጅ በተሰጠው በመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ትምህርት ሳይማር በአንድ ቀን የዳዊትን መዝሙር ማጥናት ነው፡፡ መዝሙረ ዳዊትን ግን ዕብራውያን በአምስቱ የስሜት ሕዋሳት ቁጥር ለአምስት ከፍለውታል፡፡ እነዚህም መስማት፣ ማየት፣ ማሽተት መቅመስና፣ መዳሰስ ናቸው፡፡ የመጀመሪያው ክፍል መጨረሻው 40ኛው መዝሙር ነው፤ የሁለተኛው ክፍል መጨረሻው 71ኛው መዝሙር ነው፡፡ ሦስተኛው ክፍል መጨረሻው 88ኛው መዝሙር ነው፤ አራተኛው ክፍል መጨረሻው 105ኛው መዝሙር ነው፡፡ አምስተኛው ክፍል መጨረሻው 150ኛው ነው፡፡ የእነዚህም ክፍላት መጨረሻ ለይኩን ለይኩን ባለ ጊዜ ይታወቃል፡፡ አባ ጊዮርጊስም የእነዚህን ምስጢር በልቡ ጠበቃቸው፡፡ አምስቱንም ቃላት በልቡ መዝገብነት ሰወራቸው፤ ሊገልጣቸው እግዚአብሔር አልፈቀደላትምና በተረዳ ነገር ግን መዝሙረ ዳዊት ነው፡፡ የገነትን ፍሬዎች ሁሉ የሰበሰበ መዝሙረ ዳዊት የገነት አምሳል ነውና አጋንንትን ያሳድዳል መላእክትንም ያቀርባል፡፡ እመቤታችንም ከእርሱ ተለይታ ካረገች በኋላ ከዚያችም ሰዓት ጀምሮ የልቡ ዓይን ተከፈተለት፡፡ ኅሊናውም በመንፈስ ቅዱስ ክንፎች ተመሰጠ፡፡ ወደ አብም ደረሰ፤ በዚያም ኢየሱስን በአባቱ ቀኝ ተቀምጦ ጰራቅሊጦስንም በአንድ አኗኗር አገኘው፡፡

ከዚህ በኋላ በሐይቅ እስጢፋኖስ የዜማ የቅኔና የመጻሕፍትን ትርጓሜ ትምህርቱን በሚገባ ተምሮ አጠናቀቀ፡፡ በዕውቀቱም ቀድሞ የሚያውቁት ሁሉ ይደነቁበት ነበር፡፡ አባ ጊዮርጊስ የያሬድን ዜማ ከአቡነ ሳሙኤል ተማረ፡፡ በዚያ ዘመን በዐፄ ዳዊት አማካይነት በሰሜን ኢትዮጵያ የያሬድ ድጓ ዋና ማዕከል በሆነው በደብረ ነጎድጓድ ተሾሞ ያስተምር ነበር፡፡ የማስተማር ሥራውን የጀመረው በዚያው በሐይቅ እስጢፋኖስ ነበር፡፡

ከሐይቅ በኋላ በዚያ ዘመን ሸግላ በመባል ትጠራ ወደ ነበረችው ወደ ትውልድ ሀገሩ ወደ ጋሥጫ ተጓዘ፡፡ አባ ጊዮርጊስ ወደ ሸግላ ሲመጣ አባቱ በጣም አርጅቶና መንኩሶ ነበር፡፡ ስለዚህም በአባቱ እግር ተተክቶ በቤተ መንግሥቱ ያለችውን ሥዕል ቤት እንዲያገለግል ወደዚያው አስገቡት፡፡ በቤተ መንግሥቱም የንጉሡን ልጆች ከማስተማሩም በላይ በቤተ መንግሥቱ ዙርያ ከነበሩት ሊቃውንት መካከል አባ ጊዮርጊስ አንዱ ነበር፡፡ በአንድ ወቅት ግብፃዊው ጳጳስ አቡነ በርተሎሜዎስ “ሥላሴን አንድ ገጽ” ብለው ያምናሉ ተብለው በተከሰሱ ጊዜ ነገሩን እንዲያጣሩ ከተመረጡት ከቄስ ሐፄ ተከሥተ ብርሃንና ከሐይቁ መምህር ከዐቃቤ ሰዓት ዮሴፍ ጋር አብሮ ተልኮ ነበር፡፡ እነዚህ ሦስት አበው ጳጳሱን ካነጋገሩ በኋላ ክሱ ውሸት መሆኑን በማረጋገጥ ስለ ምሥጢረ ሥላሴ የሚገልጠውን የጳጳሱን እምነት በጽሑፍ ይዘው መጡ፡፡ በቤተ መንግሥቱ በነበረ ጊዜ የንጉሡን ልጆች ይስሐቅን፣ ቴዎድሮስን፣ እንድርያስን፣ ሀብተ ኢየሱስን፣ ሕዝቅያስን፣ ኢዮስያስን፣ ዘርዐ ያዕቆብንና ሴት ልጁን እሌኒን በምግባርና በሃይማኖት ቀርጿቸዋል፡፡ ከእነዚህም መካከል ዘርዐ ያዕቆብ በድርሰቱ ሲመስለው ቴዎድሮስ ደግሞ በሕይወት መስሎታል፡፡ ዐፄ ዳዊት የአባ ጊዮርጊስን ሊቅነትና መልካም ሥነ ምግባር በሚገባ ስላወቀ በጋብቻ ሊዛመደው ወዶ ስለነበር ልጁን እንዲያገባ ዘወትር ይጠይቀው ነበር፡፡ አባ ጊዮርጊስ ግን በድንግልና ጸንቶ ለመኖር እንደሚፈልግ ከመግለጽ አልተቆጠበም፡፡ የዐፄ ዳዊት ጥያቄ ስለበዛበት ወደ አቡነ በርተሎሜዎስ ሄዶ ቅስናን ከተቀበለ በኋላ ወዲያው መነኮሰ፡፡

ከመነኮሰ በኋላ ወደ ሸግላ በመምጣት ለነገሥታትና በቤተ መንግሥቱ ለነበሩ ካህናት እንዲሁም በቤተ መንግሥቱ ለነበሩ ታላላቆች፣ ለንቡራነ እድና ለመኳንንት፣ ለመሳፍንትና በቤተ መንግሥቱ ለነበሩ ባለሟሎች ሁሉ መምህር ሆነ፡፡

አባ ጊዮርጊስ በሸግላ በነበረ ጊዜ በወባ በሽታ ታምሞ ሊሞት ደርሶ ነበር፡፡ ታምሞ በነበረ ጊዜ አንድ ሌሊት የከበሩ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱስ ጳውሎስ ተገልጠውለት ‹‹ከእኛ ጋር ትኖር ዘንድ ልንወስድህ መጣን›› አሉት፡፡ እርሱም ‹‹የድርሰት ሥራዬን ሳልሠራና እግዚአብሔርንም አብዝቼ ሳላመሰግነው አሁን አትውሰዱኝ›› ሲል ለመናቸው፡፡ እነርሱም ልመናውን ተቀብለውት ከሕመሙ ፈውሰውት ሄዱ፡፡ ለዚህም ነው ከበሽታው እንደ ተፈወሰ ወድያው የድርሰት ሥራውን የጀመረው፡፡ የመጀመርያ መጽሐፉን ጽፎ እንደ ጨረሰ ጠፍቶበት ነበር፡፡ በማግሥቱ በዚያው ላይ ሊጨምር በወደደ ጊዜ የተጻፈበት ጥራዝ ቀለሙ ጠፍቶ ነጭ ሆኖ አገኘው፡፡ ስለዚህም የተሰረቀ መስሎት ልቡ አዘነ፡፡ የተስተካከሉ ጥራዞችንም በቈጠረ ጊዜ ደኅና ሁነው አገኛቸው ሁለተኛም በድጋሚ ጻፈ፡፡ በማግሥቱም እንደ መጀመሪያው ነጭ ሁኖ አገኘው እስከ ሦስትና ዐራት ቀንም እየተደጋገመ እንዲሁ ሆነ፡፡ ከዚህ በኋላ አባታችን ወደ እመቤታችን ይጸልይ ጀመረ፡፡ ‹‹ይህ የሆነ በኃጢአቴ ነውን? ወይስ አይደለም? ግለጭልኝ›› አላት፡፡ አንድ ቀንም በሌሊት እኩሌታ ወደ ቤተ ክርስቲያን ለጸሎት ሲሄድ እመቤታችን በድንገት በማይነገር ክብር ለጊዮርጊስ ተገለጠችለት፡፡ ከእርሷም ጋር የቅዱሳን ማኅበር ሁሉ ነበሩ፡፡ በእጇም ከፀሐይና ጨረቃ የበለጠ የሚያበራ መጽሐፍን ይዛ
ነበር፡፡ ጊዮርጊስም

ባየ ጊዜ ወደ መሬት ወደቀ፡፡ እንደ በድንም ሆነ፡፡ እመቤታችንም አነሣችውና ‹‹ሳትጠይቀኝ መጽሐፌን ትጽፍ ዘንድ ለምን ደፈርህ?›› አለችው፡፡ ‹‹እኔ ወድጄህ ከእናትህስ ማኅፀን መርጬህ ለጴጥሮስ፣ ለጳውሎስና ለዮሐንስ አደራ ሰጥቼህ የለምን?›› አለችው፡፡ አባ ጊዮርጊስም ‹‹እመቤቴ ሆይ ይቅር በይኝ፣ ደስ የሚያሰኝሽ መስሎኝ ይህን ባለማወቅ ሠርቼዋለሁና›› አላት፡፡ እመቤታችንም ‹‹ወዳጄ ሆይ ይቅር ብየሃለሁ›› አለችው፡፡ ‹‹ልትጽፈው የወደድኸው መጽሐፍም እነሆ በእጄ አለ፣ ከአሁን በኋላ የተወደደ ልጄ በአንደበትህ ሊገልጸው ወዷል፡፡ ነገር ግን ከአርያም ከሰማይ ኀይልን እስክትለብስ ድረስ አትቸኩል፡፡›› ይህንም ብላው ከእርሱ ተሰወረች፡፡ ያን ጊዜም ልቡ እንደ ፀሐይ በራ፣ የመለኮትም ባሕር በኅሊናው አበራ፡፡ በመንፈስ ቅዱስም መስተዋትነት የተሰወረውን ሁሉ አየ፡፡

የመጀመርያው ድርሰቱ አርጋኖን የተሰኘውና በቅኔ ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የሚያመሰግነው መጽሐፉ ነው፡፡ እግዚአብሔርን በሚወድ በንጉሥ ዳዊት ዘመንም አርጋኖን መጽሐፍን ይደርስና ይጽፍ ጀመረ፡፡ በሦስትም ስሞች ጠራው እነዚህም አርጋኖና ውዳሴ፣ መሰንቆ መዝሙር፣ ዕንዚራ ስብሐት ናቸው፡፡ ስለ መጽሐፉም ጣፋጭነት ንጉሡ ዐፄ ዳዊት ድርሰቱን በጣም ከመውደዱ የተነሣ በወርቅ ቀለም አጻፈው፡፡ ወርቁን የሚያንጸባርቅበት ድንጋይ (ዕንቊ) ባጣ ጊዜ እመቤታችን ማርያም በሌሊት ራእይ ዘማት በሚባል አገር እንዳለ ለጊዮርጊስ ነገረችው ኅብሩንም አሳየችው፡፡ አባታችን ጊዮርጊስም ከደረስኳቸውና ከተናገርኋቸው ድርሳናት ሁሉ አርጋኖን ውዳሴ ይጣፍጣል ይበልጣል አለ፡፡

‹‹እንደዚሁም በፈጣሪው ቸርነት በእመቤታችን ረድኤት ብዙ ድርሳናትንና የጸሎት መጻሕፍትን ደረሰ፡፡ የእሊህም ድርሳናት ስማቸውና ቁጥራቸው በሊቃውንት ዘንድ የታወቀ ነው፡፡ እሊህም ውዳሴ መስቀል፣ መጽሐፈ ብርሃን፣ መጽሐፈ ሰዓታት የመዓልትና የሌሊት፣ መጻሕፍተ ቅዳሴያት ናቸው፡፡ ጸሎተ ፈትቶ (የፍታቴ ጸሎት) የሐዋርያት ማኅሌት፣ መልክአ ቊርባን፣ እንዚራ ስብሐት፣ አርጋኖን ውዳሴ፣ ፍካሬ ሃይማኖት፣ ውዳሴ ሐዋርያት፣ ኖኅተ ብርሃን ይኸውም ከመጽሐፈ አርጋኖን ጋር አብሮ የታተመው ነው፡፡ ፍካሬ ሃይማኖት፣ መጽሐፈ ምስጢር፣ ሕይወታ ለማርያም፣ ተአምኆ ቅዱሳን፣ ጸሎት ዘቤት ውስተቤት፣ ውዳሴ ስብሐት፣ ሰላምታ፣ ጸሎተ ማዕድ፣ ቅዳሴ እግዚእ ካልእ፣ መዝሙረ ድንግልና የመሳሰለው ነው፡፡›› ቅዱስ ገድሉ እንደሚናገረው የአባ ጊዮርጊስ ‹‹ድርሳናት ስማቸውና ቁጥራቸው በሊቃውንት ዘንድ የታወቀ ነው›› ብሎ ከጀመረ በኋላ በቁጥር የተወሰኑትን ድርሰቶቹን ብቻ ጠቅሶ መጨረሻ ላይ ‹‹… እና የመሳሰለው ነው›› ብሎ ይደመድመዋል፡፡ ሊቀ ብርሃናት መርቆሬዎስ አረጋ ደግሞ የአባ ጊዮርጊስ ድርሰቶች ከ12 ሺህ በላይ ቢሆኑም ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት እየሰጡ ያሉት በጣም ጥቂቶቹ ብቻ መሆናቸውን በቅዱሳን ታሪክ መጽሐፋቸው ላይ ጠቅሰውታል፡፡ ሌሎች ሊቃውንት አባቶቻችንም የአባ ጊዮርጊስን ድርሰቶች ከግምት ባለፈ ሁኔታ በቁጥር ወስኖ ለማስቀመጥ አስቸጋሪ መሆኑን ይገልጣሉ፡፡ ይኸውም ወደፊት ራሱን የቻለ በቂና ብዙ ጥናት ማድረግ ሳያስፈልገን እንደማይቀር አመላካች ነው፡፡

የመጀመርያውን ድርሰቱን አርጋኖንን እመቤታችን አብዝታ ስለወደደችለት ዚማት በሚባለው ሀገር በነበረ ጊዜ ‹‹ከድርሰቶችህ ሁሉ እንደ አርጋኖን የምወደው የለም›› ብላዋለች፡፡ ከዚህ በኋላ የደረሰው ድርሰት ውዳሴ መስቀል ይባላል፡፡ ቀጥሎም መጽሐፈ ስብሐት ዘመዓልት ወዘሌሊት የተባለውን ወይም እርሱ ራሱ መጽሐፈ ብርሃን ብሎ የሰየመውን መጽሐፍ አዘጋጅቷል፡፡ መጽሐፉም የእግዚአብሔርን የምስጋናውን መንገድ ያበራል፣ አብርቶ ያመለክታልና፣ ልዑላነ ብርሃን የሆኑትን የማኅበረ ቅዱሳንንና የትጉኃንን የምስጋናቸውን መንገድ ያመለክታልና፣ የእመቤታችንንም የምስጋናዋን ጣዕም ይገልጣልና መጽሐፉ «መጽሐፈ ብርሃን» ተባለ፡፡ በዘመኑ በነበረው ልማድ ካህናቱ ቍርባን በሚያቀብሉ ጊዜ ሕዝቡ ወደ ካህናቱ መጥተው ሲቀበሉ ንግሥቲቱ ግን ካለችበት ድረስ ካህናቱ ሄደው ነበር የሚያቆርቧት፡፡ አባ ጊዮርጊስ ግን ‹‹ይህ ቁርባን ንጉሠ ነገሥት ነውና ንግሥቲቱ ወደዚህ መጥታ ልትቀበል ይገባታል እንጂ እኛ መሄድ የለብንም›› ሲል ተቃወመ፡፡ ይህ ነገር ንግሥቲቱንና አባ ጊዮርጊስን ስላጋጫቸው ዐፄ ዳዊት ችግሩን ለመፍታት አባ ጊዮርጊስን ወደ ሀገረ ዳሞት ንቡረ እድነት ሾሞ ላከው፡፡

ከዚህ በኋላ አባ ጊዮርጊስ ዋናው ትኩረቱ በድርሰቱ ላይ በማድረግ ወደ ጳጳሱ ወደ አቡነ በርተሎሜዎስ ዘንድ በመሄድ የቅዳሴ ድርሰት ለመድረስ እንዲፈቀድለት ጠይቆ ሲፈቀድለት የቅዳሴ ድርሰት ማዘጋጀት ጀመረ፡፡ አባ ጊዮርጊስ ነገረ ሃይማኖትን ጠንቅቆ የተረዳና የሚያስረዳ ስለነበር በዘመኑ የተነሡ የሃይማኖት ክርክሮች ሁሉ እርሱ ከሌለ አይሳኩም ነበር፡፡ በዚያ ጊዜ በሸዋ በይፋት ራሳቸውን ቤተ እስራኤል እያሉ የሚጠሩ አይሁድ ነበሩ፡፡ ከአቡነ ዜና ማርቆስ ጀምሮ ብዙ መምህራን ወደነዚህ ሕዝቦች እየተሠማሩ ወንጌልን አስተምረዋል፡፡ አቡነ ዜና ማርቆስ ወደ ክርስትና ለተመለሱት ቤተ እስራኤላውያን በእመቤታችን፣ በቅዱስ ሚካኤል፣ በአባ ኖብና በሰማዕቱ በጊጋር ስም አራት አብያተ ክርስቲያናትን አሠርተው ነበር፡፡ ይህ ሁሉ ቢሆንም ቤተ እስራኤላውያኑ ሙሉ በሙሉ ወደ ክርስትና አልተመለሱም ነበር፡፡ ከእነዚህ አይሁድ መካከል አንዱ ከክርስቲያኖች ጋር በነገረ ሃይማኖት ለመከራከር ጥሪ አቀረበ፡፡ ‹‹ክርስቲያኖች ከረቱኝ ወደነርሱ ሃይማኖት እገባለሁ እኔ ከረታኋቸውም ወደኔ ሃይማኖት ይገባሉ›› ሲል ነገሩን ጥብቅ አደረገው፡፡ ዐፄ ዳዊት ይህን ጉዳይ ሲሰማ በጣም ስለ ተናደደ ሊቃነ ካህናቱን፣ ንቡራነ እዱንና የመጻሕፍት ዐዋቂዎችን ሁሉ ከየሀገሩ እንዲሰባሰቡ አዘዘ፡፡ ነገር ግን በዚህ ጊዜ አባ ጊዮርጊስ ታሞ አልጋ ላይ ነበር፡፡ አይሁዳዊው በአንድ ወገን መምህራኑ በአንድ ወገን ሆነው ክርክሩን ጀመሩ፡፡ የመጀመርያው እድል የተሰጠው ለአይሁዳዊው በመሆኑ ቀጥሎ ያለውን ጥያቄ አቀረበ፡- ‹‹እናንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነው የምትሉት ይሄ ክርስቶስ እውነት የእግዚአብሔር ልጅ ከሆነ፣ ወደ ቢታንያ በመጣ ጊዜ አልዓዛር የተቀበረበትን ቦታ ሳያውቅ ቀርቶ ‹አልዓዛርን የት ቀበራችሁት?› ብሎ እንደ ጠየቀ በወንጌላችሁ ተጽፏል፡፡ ለዚህ መልስ ስጡኝ፣ እኔንም ከመጽሐፈ ኦሪቴ ጠቅሳችሁ ጠይቁኝ?›› ሲል የመከራከርያ ነጥቡን አቀረበ፡፡ ሊቃውንቱም በዚህ ጊዜ ታሞ አልጋ ላይ የነበረውን አባ ጊዮርጊስን እንዲመጣላቸው ፈልገው ‹‹እንዲህ ያለው ነገር ያለ እርሱ አይሆንምና አባ ጊዮርጊስ ይምጣ›› ሲሉ ለዐፄ ዳዊት ጥያቄ አቀረቡ፡፡ አባ ጊዮርጊስም በአልጋ ላይ እያለ እንዲመጣ ተደርጎ በአልጋ ላይ ሆኖ በጉባኤው ላይ ተገኘ፡፡ ጉባኤተኞቹ የቀረበውን ጥያቄ በነገሩት ጊዜ አባ ጊዮርጊስ የሰጠውን መልስ እንዲህ የሚል ነው፡- ‹‹እኔ ግን በወንጌል ሳይሆን በኦሪት እከራከርሃለሁ፡፡ የምኩራብ መጻሕፍት ሁሉ ለቤተ ክርስቲያን የታወቁ ናቸውና፡፡ ምኩራብ ዘራች ቤተ ክርስቲያንም አጨደችው፤ ምኩራብ ፈተለችው ቤተ ክርስቲያን ለበሰችው፤ አዳምን በገነት ሳለ አዳም ሆይ ወዴት ነህ? ብሎ የጠየቀው ማነው? አብርሃምንስ ሚስትህ ሣራ ወዴት ናት? ብሎ የጠየቀው ማነው? እስቲ መልስልኝ? ሰይጣንንስ ከወዴት መጣህ? ብሎ የጠየቀው ማነው? እግዚአብሔር አብ አይደለምን?›› እያሉ የጥያቄ ዓይነት ባሽጎደጎዱለት ጊዜ አይሁዳዊው መልስ አጥቶ ዝም አለ፡፡ መልስ በማጣቱም አፈረ፡፡ ንጉሡ፣ ሊቃውንቱና