የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
2.58K subscribers
6.08K photos
67 videos
60 files
1.7K links
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
Download Telegram
​​የጎላ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት የሕጻናት ክፍል 120 ሕጻናትን በዛሬው ዕለት በሰንበት ት/ቤታችን አስመረቀ
===============
እኛ : አምላከ ቅዱስ ሚካኤል አስከ ፍጻሜው አፅንቶ በቤቱ ያቆይል አልን..

እናንተስ እስቲ መርቋቸው.............
​​በሰንበት ትምህርት ቤታችን የመጀመሪያ ስራ የሆነውን የያሬዳዊ ወረብ መጽሐፍ እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ነገ 08/06/12 ለሽያጭ ይቀርባል። ስለመጽሐፉም አጭር ገለጻ ከመዝሙር ጥናት በኋላ ይደረጋል።
​​አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም የካቲት አሥራ ሁለት ቀን በዚህች ዕለት የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል በዓል መታሰቢያ ነው፡፡
በዚህች ቀን ክብር ምስጋና ይግባውና እግዚአብሔር የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልን የረዓይት ወገን ወደሚሆን ወደ ሶምሶን ልኮታልና፤ ሊገድሉት የፈለጉትን የፍልስጥኤምን ሰዎች ድል እስኪያደርጋቸው ድረስ ረድቶታልና በእነሱ ላይ እግዚአብሔር ኃይል ሰጥቶት አጠፋቸው ከእነሱ በአንዲት ቀን በአህያ መንጋጋ ሺህ ሰው ገደለ፡፡
ውሃ ጠምቶት ሊሞት በደረሰ ጊዜም የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ታይቶ አፀናው ከአህያ መንጋጋ አጥንትም ውሃ አወጣለት ጠጥቶም ከውሃ ጥም ዳነ
የፍልስጥኤም ሰዎች ድል በሆኑ ጊዜ ከሚስቱ ጋር ተማክረው ዓይኑን አጥፍተው ወደ ጣዖታቸው ቤት ወሰዱት፡፡ የእግዚአብሔር መልእክተኛ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ታየው ተነጋገረው ኃይልንም ሰጠውና ሁሉንም አጠፋቸው፡፡
ስለዚህ ነገር የቤተክርስቲያን መምህራን በየወሩ በአሥራ ሁለት ቀን የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤልን በዓል መታሰቢያ እናደርግ ዘንድ አዝዘውናል፡፡
++++++++++++++++++

ሰላም ለዝክረ ስምከ፡፡ ሚካኤል ሆይ የያሬድ ልጅ ሄኖክ እንደጻፈው ከልዑል ስም አጠራር ጋር ለተባበረ ስም አጠራርህ ሰላም እላለሁ፡፡ የእግዚአብሔር የምክሩ አበጋዝ ሆይ የተቸገሩትን የተጨነቁትን ዘወትር እንደምትረዳቸው ሁሉ እኔንም ለመርዳት ክንፍህን ዘርግተህ ፈጥነህ ድረስልኝ፡፡