Watch ልዑለ መንበር on our telegram channel https://youtu.be/lUKx4F-sO9g
[የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል]
✍ ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ [በድጋሚ ፓስት የተደረገ]
♥♥♥ ቅዱስ ገብርኤል ከሊቃነ መላእክት አንዱ ሲኾን፤ የሚኖርበት ሰማይም ራማ ሲባል አርባብ በተባለ ነገድ ላይ የተሾመ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት ቊጥሩ በኹለተኛነት የሚገኝ ነው፤ ይኽ መልአክ በባቢሎን በእሳት ውስጥ የተወረወሩትን ሦስቱን ሕፃናት የታደገ መልአክ ሲኾን በተለይም ለቅድስት ድንግል ማርያም የአምላክን ሰው መኾን ያበሠረ መልአክ ስለኾነ መጋቤ ሐዲስ በመባል ይታወቃል፡፡
♥♥♥ ነቢዩ ዳንኤል ለንጉሡ ለናቡከደነጾር ሕልሙን ከተረጐመለት በኋላ ዳንኤልንና ሠለስቱ ደቂቅን በባቢሎን አውራጃ ላይ ከፍተኛ ሹመትን በየደረጃቸው ሹሟቸዋል (ዳን ፪፥፵፰‐፵፱)፡፡
♥♥♥ ኾኖም ግን ናቡከደነጾር ቁመቱ ስሳ ክንድ ወርዱ ስድስት ክንድ የኾነውን የወርቁን ምስል አሠርቶ በባቢሎን አውራጃ በዱራ ሜዳ ላይ በማቆም ኹሉም ላቆመው ምስል ምረቃ ተሰብስበው ሳሉ፤ ዐዋጅ ነጋሪው የዘፈን ድምፅ ሕዝቡ ሲሰሙ ንጉሡ ላቆመው ምስል ተደፍተው እንዲሰግዱ ትእዛዝን የማይቀበሉ ግን በሚነድደው እሳት እቶን እንደሚጣሉ ሲናገር ሕዝቡም አሕዛቡም ለምስሉ ይሰግዱ ይረበረቡ ዠመር (ዳን ፫፥፩‐፯)፡፡
♥♥♥ ሦስቱ ሕፃናት አናንያ አዛርያ ሚሳኤል ግን አንሰግድም በማለታቸው “እሉ እደው ዘሤምኮሙ ለግብረ በሐውርተ ባቢሎን አበዩ ሰጊደ ለምስል ዘወርቅ ዘገበርከ” በባቢሎን አውራጃ ሥራ ላይ የሾምካቸው እነዚኽ ሰዎች ወንዶች ላቆምኸው ምስል አይሰግዱም በማለት ነገሩት።
♥♥♥ ናቡከደነጾርም በብስጭትና በቊጣ እንዲመጡ በማዘዙ፤ መጥተው ከፊቱ ሲቆሙ “ላቆምኹት ለወርቁ ምስል አለመስገዳችኊ እውነት ነውን? ባትሰግዱ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ትጣላላችኊ፤ ከእጄስ የሚያድናችኊ አምላክ ማን ነው?” በማለት ሲናገራቸው የሚያመልኩት አምላክ ከሚነድደው እሳት ሊያድናቸው እንደሚችል ገለጹለት።
♥♥♥ ርሱም በቊጣ የእቶኑ እሳት ከሚነደው ይልቅ ሰባት እጥፍ ማለት 49 ክንድ አድርገው እንዲያነዱ በማዘዝ አናንያ፣ አዛርያ፣ ሚሳኤል፣ ታሥረው እንዲጣሉ በሰራዊቱ ውስጥ ላሉት ኀያላን መመሪያ ስላስተላለፈ፤ ወርዋሪዎቹም ከሰናፊላቸውና ከቀሚሳቸው ከመጐናጸፊያቸው ጋር በእሳቱ ላይ ሲጥሏቸው ከወላፈኑ ከፍተኛነት የተነሣ ወታደሮቹ ተቃጥለዋል (ዳን ፫፥፲፫‐፳፫)፡፡
♥♥♥ ያን ጊዜ “ወወረደ መልአከ እግዚአብሔር ወዘበጦ ለነበልባለ እሳት ወረሰዮ ከመ ነፋስ ቆሪር ዘጊዜ ጽባሕ” ይላል መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ወርዶ በበትረ ብርሃን ቢመታው እንዳረረ ውርጭ ኾኗል፤ ያን ጊዜ ወአንሰሶሰዉ ማእከለ እሳት ወአእኰቱ እግዚአብሔርሀ ወባረክዎ ይላል በእሳቱ ጒድጓድ መኻከልም በመመላለስ እግዚአብሔርንም ፈጽመው አመስግነውታል (መዝሙረ ሠለስቱ ደቂቅ ቊ ፩)፡፡
♥♥♥ ይኽም ከእሳቱ መኻከል ሳሉ የተገለጸላቸው አስደናቂ ምስጋና ልዩ የኾነ የነገረ ሥጋዌ ምስጢርን የያዘ እንደኾነ የነገረ ነቢያት ሊቃውንት አስተምረዋል፤ ይኸውም 49 ክንድ ኸደ ላይ በወጣው በእሳቱ መኻከል ኹነው ለስድስት ጊዜ ብቻ፦
✍ “ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ ስቡሕኒ ውእቱ ወልዑልኒ ውእቱ ለዓለም”
★ (የአባቶቻችን ፈጣሪ እግዚአብሔር ይመስገን፤ የተመሰገነ ነው፤ ለዘለዓለሙም የከበረ ነው) በማለት አመሰገኑ (መዝሙረ ሠለስቱ ደቂቅ ቊ ፳፯‐፴፪)።
♥♥♥ 49 ክንድ የወጣው እሳት እና እሳት ውስጥ ኾነው 6 ጊዜ "ይትባረክ" (ይመስገን) ያሉት ቢደመር 55 ይኾናል፤ ይኽም የ5500 ዘመን ምሳሌ ነው፤ ይኽም 5500 ዘመን ተፈጽሞ በ6ኛው ሺሕ አምላክ ሰው ኾኖ ከሲኦል እሳት ነፍሳትን ነጻ እንደሚያወጣ ያመለክታል።
♥♥♥ በመቀጠልም፦
✍ “ይባርክዎ ኲሉ ግብረ እግዚእ ለእግዚአብሔር ስቡሕኒ ውእቱ ወልዑልኒ ውእቱ ለዓለም”
★ (እግዚአብሔር የፈጠራችው ፍጥረቶች ኹሉ እግዚአብሔርን ያመሰግኑታል፤ ርሱ የተመሰገነ ነው ለዘላለሙም ከፍ ከፍ ያለ ነው) እያሉ “ያመሰግኑታል” የሚለውን ቃል ለ 33 ጊዜ ብቻ ያኽል ተናግረዋል (መዝሙረ ሠለስቱ ደቂቅ ቊ ፴፫‐፷፭)፡፡
♥♥♥ በሊቃውንቱ ትንታኔ ሠለስቱ ደቂቅ ስድስት ጊዜ መላልሰው መናገራቸው ከ፮፻ ዘመናት በኋላ ምስጉን የኾነው የባሕርይ አምላክ ከሰማየ ሰማያት መውረዱን ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱን ማጠየቃቸው ሲኾን፤ ከዚያው ቀጥለው ደግሞ ሠላሳ ሦስት ጊዜ “ያመሰግኑታል” እያሉ ቃሉን ደጋግመው ማለታቸው፤ ምስጉን የኾነው አምላክ ከቅድስት ድንግል ማርያም ከተወለደ በኋላ ሠላሳ ሦስት ዓመት በዚኽ ዓለም የሚኖር እንደኾነ ተገልጾላቸው የተናገሩ መኾኑን አስተምረዋል፡፡
♥♥♥ ይኽነንም ምስጢር ቀደምት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ሲተነትኑ፦
“...ወተነበዩ ስድስተ ጊዜያተ ለአጠይቆ ከመ እምድኅረ ስድስቱ ምእት ዓመት ይትወለድ ክርስቶስ፡፡ ወእምድኅሬሁ ሰብሕዎ ለእግዚአብሔር እንዘ ይብሉ ይባርክዎ ኲሉ ግብረ እግዚእ ለእግዚአብሔር ስቡሕኒ ውእቱ ወልዑልኒ ውእቱ ለዓለም ዘንተኒ ተነበዩ ሠላሳ ወሠለስተ ጊዜያተ ለአጠይቆ ከመ እምድኅረ ተወልደ ክርስቶስ ይነብር ውስተ ዓለም ሠላሳ ወሠለስተ ጊዜያተ ለአጠይቆ”
❖✔ (የሚነድደው እሳት ፈጽሞ አልነካቸውም የሚነድደውን እሳት እንደ ውሃ የቀዘቀዘ አድርጎታልና፤ በዚያን ሰዓት እግዚአብሔርን እንዲኽ እያሉ አመሰገኑት፤ የአባቶቻችን ፈጣሪ እግዚአብሔር ይክበር ይመስን፤ ለዘለዓለሙ ክቡር ምስጉን ነው፤ እንዲኽ እያሉ ስድስት ጊዜ ተናገሩ፤ ከስድስት መቶ ዘመን በኋላ ክርስቶስ እንዲወለድ ለማጠየቅ፤ ከዚኽም በኋላ እንዲኽ እያሉ እግዚአብሔርን አመሰገኑ፤ እግዚአብሔርን ፍጥረቱ ኹሉ ያመሰግኑታል ክቡር ምስጉንምስጢር ለዘላለሙ ይክበር ይመስገን እያሉ፤ ይኽነንም ሠላሳ ሦሰት ጊዜ ተናገሩ፤ ክርስቶስ ከተወለደ በኋላ በዚኽ ዓለም ሠላሳ ሦስት ዓመት እንዲኖር ለማጠየቅ) በማለት ልዩዉን ምስጢር አስተምረውናል፡፡
♥♥♥ ንጉሡ ናቡከደነጾርም ባለመቃጠላቸው፤ በእሳት ውስጥ ኹነውመልክ በማመስገናቸው ተደንቆ አማካሪዎቹን “ሦስት ሰዎች አስረን በእሳት ውስጥ ጥለን አልነበረም? እነሆ እኔ የተፈቱ በእሳቱም መኻከል የሚመላለሱ አራት ሰዎች አያለኊ፤ የአራተኛውም የአማልክትን ልጅ ይመስላል” በማለት፤ ስማቸውን ጠርቶ እናንተ የልዑል አምላክ ባሪያዎች ውጡ ሲላቸው ሦስቱ ሕፃናት ከእሳቱ ወጡ፤ ያን ጊዜ መሳፍንቱ ኹሉ የራሳቸው ጠጒር እንዳልተቃጠለ፤ ሰናፊላቸው እንዳልተለወጠ፤ የእሳቱ ሽታ እንኳ እንዳልደረሰባቸው አዩ፡፡
♥♥♥ያን ጊዜ ንጉሡ “በርሱ የታመኑ ባሪያዎቹን ያዳነ የሲድራቅ የሚሳቅ የአብደናጎም አምላክ ይባረክ” በማለት ምስጋናውን አቅርቧል (ዳን ፫፥፳፱‐፴)፡፡ እነዚኽ ሦስቱ ሕፃናት አናንያ፣ አዛርያ፣ ሚሳኤል በእቶነ እሳት ቢጣሉም እንኳ፣ ስለ እምነታቸው ብርታት ምስጢር ተገልጾላቸው በ፮፻ ዘመን አምላክ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ፴፫ ዓመት በዚኽ ዓለም ኖሮ ነፍሳትን ከሲኦል እሳት ነጻ እንደሚያወጣ የተገለጸላቸውን ልዩ ምስጋና፣ ዛሬ ኹላችን በቃል ኪዳኗና በምልጃዋ ከገሃነመ እሳት ከምንድንባት ከምትራራልን እናት ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ፈጽሞታልና፤ ታላቁ ሊቅ አባ ጊዮርጊስ በኆኅተ ብርሃን የነገረ ማርያም መጽሐፉ ላይ:-

✍ “መሃኪቶሙ እምውስተ እቶነ እሳት ለአናንያ ወአዛርያ ወሚሳኤል በእደ ቅዱስ ገብርኤል” (በቅዱስ ገብርኤል እጅ አናንያን፣ አዛርያን፣ ሚሳኤልን በእቶን እሳት ውስጥ የራራሺላቸው አንቺ ነሽ) በማለት ምስጢሩን እንደወርቅ አንከብሎ እንደ ሸማ ጠቅልሎ ገልጾታል፡፡
♥♥♥ በተጨማሪም ሠለስቱ ደቂቅ በብሉይ ዘመን ያሉ የጻድቃን ምሳሌ፤ በውጪ ያሉት በብሉይ ኪዳን ዘመን የነበሩ የኃጥአን ምሳሌ፤ የእሳቱ ጉድጓድ የሲኦል ምሳሌ፤ በውስጡ ያሉትን ትቶ በውጪ ያሉትን እንዳቃጠለ ኹሉ በተመሳሳይ መልኩ የእግዚአብሔር ረድኤት ጻድቃንን ይጠብቅ ነበርና ምንም ሲኦል ቢወርዱ በብሉይ ኪዳን ዘመን መከራው እንዳላገኛቸው፤ ኃጥአንን ግን መከራው የማግኘቱ ምሳሌ እንደኾነ መተርጉማን ያመሰጥሩታል፨
❖ነገረ ማርያም በብሉይ ኪዳን ክፍል 2 ከሚለው መጽሐፌ የተወሰደ
[የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል ፈጣን ተራዳኢነቱ አይለየን]
✍ ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ

#ማስታወቂያ:-
1. የሽያጭ ሰራተኛ በመሆን መስራት የምትፈልጉ #በጎአድራጎት ክፍሉን ማናገር ትችላላችሁ።
2. አባላት ወደ ቤተክርስቲያን ስንመጣ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን የጠበቀ አለባበስ እንድንለብስ እንዲሁም ፀጉር ማሳደግ፣(ለሴቶች ጥፍር ቀለም መቀባት፣ ኩል መኳል፣ ቀለም ያለው ሊፕስቲክ መቀባት) እንደማይገባ #አባላት ጉዳይ አስታውቋል።
3. ዩኒፎርም ያልመለሳችሁ አባላት ዩኒፎርም በአስቸኳይ እንድትመልሱ #ንብረት ክፍሉ አሳስቧል።
4. የሐሙስ መደበኛ ጥናት ስለተጀመረ አባላት መጥታችሁ ማጥናት እንደምትችሉ #መዝሙር ክፍል አስታውቋል።

Channel name was changed to «ፍኖተ ብርሃን(Official Channel)»
አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማኝ፥ ጩኸቴም ወደ አንተ ይድረስ። በመከራዬ ቀን ፊትህን ከኔ አትመልስ፤ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፤ በጠራሁህ ቀን ፈጥነህ ስማኝ። ዘመኔ እንደ ጢስ አልቃለችና፥ አጥንቶቼም እንደ መቃጠያ ተቃጥለዋልና። እህል መብላት ተረስቶኛልና ተቀሠፍሁ ልቤም እንደ ሣር ደረቀ። ከጩኸቴ ድምፅ የተነሣ አጥንቶቼ ከሥጋዬ ጋር ተጣበቁ።እንደ ምድረ በዳ እርኩም መሰልሁ፤ በፈረሰ ቤት እንዳለ እንደ ጕጕት ሆንሁ። ተጋሁ፥ በሰገነትም እንደሚኖር ብቸኛ ድንቢጥ ሆንሁ። ጠላቶቼ ሁልጊዜ ይሰድቡኛል፥ የሚያሳድዱኝም ተማማሉብኝ። አመድን እንደ እህል ቅሜአለሁና፥ መጠጤንም ከእንባዬ ጋር ቀላቅያለሁና፥ ከቍጣህና ከመዓትህም የተነሣ፤ አንሥተኸኛልና፥ ጥለኸኝማልና። ዘመኖቼ እንደ ጥላ አዘንብለዋል፤ እኔም እንደ ሣር ደርቄአለሁ።
አንተ ግን፥ አቤቱ፥ ለዘላለም ትኖራለህ፥ መታሰቢያህም ለልጅ ልጅ ነው። አንተ ተነሥ ጽዮንንም ይቅር በላት፥ የምሕረትዋ ጊዜ ነውና፥ ዘመንዋም ደርሶአልና፤ ባሪያዎችህም ድንጋዮችዋን ወድደዋልና፥ ለመሬትዋም አዝነዋልና። አቤቱ፥ አሕዛብ ስምህን፥ ነገሥታትም ሁሉ ክብርህን ይፈራሉ፤ እግዚአብሔር ጽዮንን ይሠራታልና፥ በክብሩም ይገለጣልና። ወደ ችግረኞች ጸሎት ተመለከተ፥ ልመናቸውንም አልናቀም።
ይህ ለሚመጣ ትውልድ ይጻፍ፥ የሚፈጠርም ሕዝብ ለእግዚአብሔር እልል ይላል፤ እግዚአብሔር ከመቅደሱ ከፍታ ሆኖ ተመልክቶአልና፥ ከሰማይ ሆኖ ምድርን አይቶአልና፤ የእስረኞችን ጩኸት ይሰማ ዘንድ፥ ሊገድሉ የተፈረደባቸውን ያድን ዘንድ፤ የእግዚአብሔርን ስም በጽዮን ምስጋናውንም በኢየሩሳሌም ይናገሩ ዘንድ፤ አሕዛብ በአንድነት በተሰበሰቡ ጊዜ መንግሥታትም ለእግዚአብሔር ይገዙ ዘንድ። በኃይሉ ጎዳና መለሰለት። የዘመኔን አነስተኛነት ንገረኝ።በዘመኔ እኵሌታ አትውሰደኝ፤ ዓመቶችህ ለልጅ ልጅ ናቸው።
አቤቱ፥ አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ፥ ሰማያትም የእጅህ ሥራ ናቸው። እነርሱ ይጠፋሉ፥ አንተ ግን ትኖራለህ፤ ሁላቸው እንደ ልብስ ያረጃሉ፥ እንደ መጐናጸፊያም ትለውጣቸዋለህ፥ ይለወጡማል፤ አንተ ግን ያው አንተ ነህ፥ ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም። የባሪያዎችህም ልጆች ይኖራሉ፥ ዘራቸውም ለዘላለም ትጸናለች።
መዝሙረ ዳዊት 102 : 1 - 28

" ለማርያም ድንግል መንበረ ተድላ ወሪዶ ገብርኤል ምድረ ገሌላ።ትወልዲ አምላክ በብሥራተ ቃሉ ይቤላ። "
እንኳን አደረሰን።
🙏🙏ለእመቤታችን መልካም ዜናን ያበሠረ መልአክ ለእኛም መልካም ዜናን ያብሥረን።🙏🙏

ዜና ዕረፍት
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት እና የጅቡቲ አብያተ ክርስቲያናት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዳንኤል ዐረፉ፡፡ ትላንት ማምሻውን በመንበረ ፓትርያሪኩ በሚገኘው መኖሪያቸው ያረፉት ብፁዕነታቸው፣ ከልብ ሕመም ጋራ በተያያዘ በሀገር ውስጥ እና በአሜሪካ የሕክምና ክትትል ሲደረግላቸው ቆይቷል፡፡
ከሳምንት በፊት በአሜሪካ በነበሩበት ወቅት የልብ ቀዶ ሕክምና እንዲደረግላቸው ቢጠየቁም፣ "አልፈልግም፤ አገሬ ገብቼ ልሙት፤" ብለው እንደተመለሱ ታውቋል፡፡የቀብራቸው ሥነ ሥርዐት ነገ ዓርብ፣ ታኅሣሥ 24 ቀን 2012ዓ.ም. በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንደሚከናወን ተጠቁሟል፡፡
(ሐራ ዘተዋሕዶ )

የሰ/ት/ቤታችን ልማት ክፍል እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት በሰላም አደረሳችሁ እያለ ለበዓሉ ማክበሪያ ይሆን ዘንድ ኃይማኖቱን እና ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ የጌታችንን ግርግም በተመጣጣኝ ዋጋ አቅርቦላችኋል።