ፍኖተ ወንጌል ሰንበት ት/ቤት
674 subscribers
1.76K photos
16 videos
460 links
በአሰላ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ካቴድራል ፍኖተ ወንጌል ሰንበት ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።

የቴሌግራም ቻናል:-  @Finote_Wongel
የቴሌግራም ግሩፕ:- @FinoteWongel27
የቲክቶክ ገፅ:- https://www.tiktok.com/@finotewongel27
Youtube:- https://www.youtube.com/@Finote_Wongel

©ፍኖተ ወንጌል ሰንበት ት/ቤት
Download Telegram
🌿🌷🌿🌷🌿🌷🌿🌷🌿🌷🌿🌷🌿
"ወንድሞቻችን ኾይ እምነት አለኝ ምግባር ግን የለኝም የሚል ሰው ቢኖር ምን ይጠቅመዋል?

በውኑ እምነቱ ልታድነው ትችላለችን?

ከወንድሞቻችን÷ ወይም ከእኅቶቻችን÷ የታረዙ ወይም የዕለት ምግብ ያጡ ቢኖሩ÷ ከእናንተም አንዱ÷ “በሰላም ኺዱ÷ እሳት ሙቁ÷ ትጠግባላችኹም” ቢላቸው÷ ለችግራቸውም የሚሹትን ባይሰጣቸው ምን ይጠቅማቸዋል?

እንዲኹም ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው፡፡

                      ያዕ. ፪÷፲፬-ፍጻ
1
"ወርኃ ሢመትከ ወርኃ ታሥሪን
እንተ ይኤድሞ ለዐይን
ጸገየ ወይን ወፈረየ ሮማን።
..........................................
ለዓይን ደስ በሚያሰኘው በተሾምህበት ወራት
(በዕብራይስጥ) ታሥሪን በሚባል በጥቅምት ወር፣
ወይን አበበ ፤ ሮማንም አፈራ።"
                         ~ መልክዓ እስጢፋኖስ

እንኳን ለቅዱስ እስጢፋኖስ በዓለ ሢመት በሰላም አደረሳችሁ!

በረከተ እስጢፋኖስ ለሁላችን ይብዛልን!

ሥዕሉ በመናገሻ አምባ ማርያም የሚገኝ እጅግ ጥንታዊ የንዑድ ክቡር ሊቀ ዲያቆናት ወቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ ሥዕል ነው።

8🥰1
ክፋትን_ከአንተ_አርቃት

"ሰይጣን ክርስቶስ በልብህ ውስጥ ያለ መሆን አለመሆኑን ያውቃል፡፡ ይኸውም ስትቆጣ ወይም ስትጮህ ወይም የማይረቡ ከንቱ ነገሮችን ስትናገር ሲያይህ ጠላት በአንተ ዘንድ እግዚአብሔር እንደሌለ ያውቃል ያን ጊዜ በውስጥህም በውጭህም ያለውን ሳይቀር ይገዛል ፤ መዝጊያ እንደሌለው ቤት እንደ ክፉ ሌባ ይገባና ውስጥህን ይበረብረዋል፡፡"

ቅዱስ_ባስልዮስ
"ኀጢአታችን በራሳችን ላይ በዝቶአልና በደላችንም ወደ ሰማይ ከፍ ብሎአልና አምላኬ ሆይ ፊቴን ወደ አንተ አነሣ ዘንድ አፍራለሁ እፈራለሁም "
        ዕዝ 9÷6
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
EOTC TV | በምሥራቅ አርሲ ዞን ለተገደሉ ኦርቶዶክሳውያን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ eotctv

"ስምሽን ስጠራ ልቡናውን እንዳያጸናብኝ ዐውቄ ፣ አምኜ ወደ ልጅሽ እጄን እዘረጋለኹ፡፡ 🤲

ስምሽን በመጥራት ስለምነው ምሕረቱን አውቀዋለኹ፤ አይዘገይብኝም፡፡ ይቅርታውንም አውቀዋለኹ ከመዓት የራቀ እውነተኛ የባሕርይ አምላክ ነውና፡፡" 🤲🤲🤲
         መጽሐፈ አርጋኖን ዘሐሙስ
5
ይህን ያውቁ ኖሯል?


ሰው ወደ ሰንበት ትምሕርት ቤት የሚመጣው ክርስቲያን ለመሆን ነው።

"ብጹዕ አቡነ ኤርሚያስ "
🥰7
"አቤቱ ጌታዬ ንጉሤ ሆይ ራሴን ጥፋት አስመልክተኝ እንጂ በወንድሜ ላይ እንድፈርድ አታድርገኝ ፡፡"

  ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ ከአርሲ የኦርቶዶክሳውያን ጭፍጨፋ ለተረፈው ህጻን ህክምና የሚውል የ70ሺ ብር ድጋፍ በማድረግ አጽናንተው ተመልሰዋል።
***

የወላይታ ሀገረስብከት ከአርሲ የኦርቶዶክሳውያን ጭፍጨፋ በታምር ተርፎ በወላይታ ሶዶ ክርስቲያን ሆስፒታል በህክምና ላይ ለሚገኘው የአራት ዓመት ህጻን የመጀመርያ ዙር የህክምና ወጪ ማስፈጸሚያ የሚውል የ70ሺ ብር የገንዘብ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን

በብፁዕ አቡነ ይስሐቅ የተመራው የወላይታ ሀገረስብከቱ ልዑክ ህጻኑ ወደ ተኛበት ክርስቲያን ሆስፒታል በመጓዝ ቤተሰቡን በማጽናናት እና ከእዚህ በኃላ እነርሱ ላይ የሚደርሰው ማንኛውም አይነት ችግር ሀገረስብከቱ እንደሚወጣው ጭምር በማሳሰብ ተመልሰዋል።

ይህኝን ታላቅ የበረከት አባት አመስግኑልኝ !
13🥰2👏2
🍂🌿

ወንድምህን አትናቀው

ወዳጄ ሆይ! ክርስቲያን ነህን? እንኪያስ በፍጹም ወንድምህን አትናቀው። እህትህን አትናቃት። ምንም ይሁን ምን ሰው አትናቅ። ይህ የምትንቀው ወንድም በተለይ ክርስቲያን ከሆነ ክርስቶስን እየሰደብከዉ እንደሆን አስተውል።

"እንዴት?"  ያልከኝ እንደሆንም ይህ የምትንቀው ወንድምህ የከደርስቶስ ሕዋስ (ብልት) ኾኗል። የክርስቶስ ሕዋስ ከኾነ ደግሞ እሱን ናቅኸው ማለት ክርቶስን ናቅኸው ማለት ነው።

ወንድምህን የምትንቅ ከሆነም በጲላጦስ አደባባይ ጌታን ከገረፉት፣ እራቁቱን ከሰቀሉት፣ ሐሞትንና ከርቤን ቀላቅለው ከሰጡት፣ በፊቱ ላይም ከተፉበት ሰዎች በምንም አትተናነስም። ስለዘህ ወንድምህን ከመናቅ ተጠንቀቅ።

📝ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

🍂🌿
👍31
የጌታችን የመድኃኒታችን የመድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት መታሰቢያ በአሰላ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ካቴድራል በታላቅ ድምቀት ይከበራል።


ሐሙስ ጥቅምት 27 አይቀርም።
🥰54👍2
"አንተ በክርስቶስ ከተጠመድክ እርሱ በግል ጉዳዩችህ ይጠመዳል ።"

ቅዱስ አባ ሙሴ ጸሊም
3
ማስታወቂያ 📢

መንፈሳዊ የ9ኛ ክፍል(ሳልሳይ) ትምህርት መጀመሩን ሰምተዋል?

ከዚህ በፊት በየትኛውም ደብር መንፈሳዊ ኮርስ እስከ 8ኛ ክፍል( ካዕላይ) የተማራቹ 9ኛ ክፍል(ሣልሳይ) በመግባት ትምህርታቹን መከታተል ትችላላችሁ።መንፈሳዊ ትምህርቱን መከታተላችሁን ማስረጃ ማቅረብ ግዴታ ነው።

🕰 ትምህርቱ የሚሰጥበት ሰዓት አርብ ፣ ቅዳሜ እና እሁድ ከሰዓት 11:30- 1:00 ሰዓት ድረስ።

📍 ትምህርቱ የሚሰጥበት ቦታ በአሰላ ደብረ መ/መ/ዓ/ካቴድራል በሰንበት ት/ቤቱ አዳራሽ

👍51
ፍኖተ ወንጌል ሰንበት ት/ቤት pinned «ማስታወቂያ 📢 መንፈሳዊ የ9ኛ ክፍል(ሳልሳይ) ትምህርት መጀመሩን ሰምተዋል? ከዚህ በፊት በየትኛውም ደብር መንፈሳዊ ኮርስ እስከ 8ኛ ክፍል( ካዕላይ) የተማራቹ 9ኛ ክፍል(ሣልሳይ) በመግባት ትምህርታቹን መከታተል ትችላላችሁ።መንፈሳዊ ትምህርቱን መከታተላችሁን ማስረጃ ማቅረብ ግዴታ ነው። 🕰 ትምህርቱ የሚሰጥበት ሰዓት አርብ ፣ ቅዳሜ እና እሁድ ከሰዓት 11:30…»
"በሥራና በእውነት እንጂ በቃልና በአንደበት እንዋደድ።"
  
  1ኛ ዮሐ 3÷18




መንፈሳዊ ትምህርት መማር የምትፈልጉ:-

በአሰላ ደ/መ/መ/ዓ/ካቴድራል በፍኖተ ወንጌል ንዋያተ ቅድሳት መሸጫ በመገኘት መመዝገብ ትችላላችሁ።
እንኳን ለ2018ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሰላም አደረሳችሁ!

"አንተ ግን በተማርበትና በተረዳህበት ነገር ጸንተህ ኑር!" ፪ኛ ጢሞ ፫፥፲፬


እነሆ ዘንድሮም እንደአምናው በሰ/ት/ቤቱ የሚሰጠው ተከታታይ መንፈሳዊ ትምርት ለመስጠት ዝግጅታችንን ጨርሰን ተማሪዎችን በመመዝገብ ላይ እንገኛል።
በሁለቱም ቋንቋዎች በአፋን ኦሮሞና በአማርኛ ከ1-9ኛ ክፍል ነባርና አዲስ ተማሪዎችን ለማስተማር ዝግጅታችንን ጨርሰናል ይምጡና ይመዝገቡ ይማሩ!

የመመዝገቢያ ቦታ

👉ዘወትር ቀን ከ10:00 ሰዓት ጀምሮ በአውደ ምህረት፣ በሰ/ት/ቤቱ አዳራሽና ቤተ መጽሐፍት

👉ሁሌም በስራ ሰዓት በሰ/ት/ቤቱ ነዋየ ቅዱሳት መሸጫ

👉 በፈለጉት ሰዓት ባሉበት ሆነው በሚከተለው ሊንክ በመግባት በonline መመዝገብ ይችላሉ( https://forms.gle/9RDHjM9H9Ymy924R6 )

ለበለጠ መረጃ

👉0968903347
👉0998646565
👉0938117125
1