🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿
እንኳን ለቅዱሳን አባቶቻችን አቡነ አረጋዊ እና ሙሽራው ገብረ ክርስቶስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችኹ አደረሰን።
በዚህች ቀን ታላቁና የከበረው አባታችን አቡነ_አረጋዊ (ዘሚካኤል) የተሰወሩበት ዕለት ነው።
እኚህ አባት ከዘጠኙ ቅዱሳን አባቶች አንዱ ሲሆኑ አባታቸው ይስሐቅ የሮም ንጉሥ ነበሩ፡፡ እናታቸው ንግሥት እድና ይባሉ ነበር፡፡
የመጀመሪያ ስማቸው #ዘሚካኤል ነው፡፡ ጥበብ መንፈሳ ሲማሩ አድገው ወደ #እስክንድርያ_ገዳም ገቡ፡፡ አበምኔቱ #አባ_ጳኩሚስ በፈቃደ እግዚአብሔር የመጡ መሆናቸውን አውቀው #መዓረገ_ምንኩስና ሰጥተዋቸዋል፡፡
ዳግመኛም በዚህች ዕለት ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ‹‹ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስን ልከተለው እሔዳለሁ›› በማለት ለክብር የበቃበት ዕለት ነው፡፡
የቅዱስ ገብረ ክርስቶስም ሕይወት እንደ ቅዱስ አባታችን አቡነ አረጋዊ ክርስቶስን የመከተል ሕይወት ነው፡፡ የቊስጥንጥንያ ንጉሥ የሆነው አባቱ ቴዎዶስዮስ እና እናቱ መርኬዛ ከሮም ንጉሥ ልጅ ጋር ቢያጋቡትም ክርስቶስን ለመከተል ከሙሽራ ቤት የወጣ ታላቅ የትሕትና እና የትዕግሥት መምህር ነው፡፡
የጻድቃን አባቶቻችን በረከታቸው ይደርብን:: አሜን

"ሰላም ለዘሚካኤል ዘተሰምየ አረጋዌ። እስመ ሑረቱ በጥበብ ወፍናዊሁ ልባዌ። ምስሌሁ ኅቡረ ዘበአሐዱ ህላዌ። ሰላም ለቅዱሳን ዘተሰነዓው ስንዓዌ። ከመ በጸሎት ይሥዓሩ ሥርዓቶ ለአርዌ"።
ትርጉም፦
"አረጋዊ ተብሎ የመጠሪያ ስም የወጣለት ለኾነ ለዘሚካኤል ሰላምታ ይገባል፤ አኪያኺያዱ በጥበብና ጐዳናውም በማስተዋል ነውና በጸሎት የአውሬ ዲያብሎስን ሥርዐቱን ይደመስሱ ዘንድ በአንድ አኗኗር ከርሱ ጋር አንድነት ስምምነትን ላደረጉ ለቅዱሳን ሰላምታ ይገባል። "
ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ)
በዚህች ቀን ታላቁና የከበረው አባታችን አቡነ_አረጋዊ (ዘሚካኤል) የተሰወሩበት ዕለት ነው።
እኚህ አባት ከዘጠኙ ቅዱሳን አባቶች አንዱ ሲሆኑ አባታቸው ይስሐቅ የሮም ንጉሥ ነበሩ፡፡ እናታቸው ንግሥት እድና ይባሉ ነበር፡፡
የመጀመሪያ ስማቸው #ዘሚካኤል ነው፡፡ ጥበብ መንፈሳ ሲማሩ አድገው ወደ #እስክንድርያ_ገዳም ገቡ፡፡ አበምኔቱ #አባ_ጳኩሚስ በፈቃደ እግዚአብሔር የመጡ መሆናቸውን አውቀው #መዓረገ_ምንኩስና ሰጥተዋቸዋል፡፡
ዳግመኛም በዚህች ዕለት ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ‹‹ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስን ልከተለው እሔዳለሁ›› በማለት ለክብር የበቃበት ዕለት ነው፡፡
የቅዱስ ገብረ ክርስቶስም ሕይወት እንደ ቅዱስ አባታችን አቡነ አረጋዊ ክርስቶስን የመከተል ሕይወት ነው፡፡ የቊስጥንጥንያ ንጉሥ የሆነው አባቱ ቴዎዶስዮስ እና እናቱ መርኬዛ ከሮም ንጉሥ ልጅ ጋር ቢያጋቡትም ክርስቶስን ለመከተል ከሙሽራ ቤት የወጣ ታላቅ የትሕትና እና የትዕግሥት መምህር ነው፡፡
የጻድቃን አባቶቻችን በረከታቸው ይደርብን:: አሜን
🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿
🙏3
የ፻፴፫ኛው የቅዱስ ሲኖዶስ መደበኛ ምልዐተ ጉባኤ የሦስተኛ ቀን ውሎ ውሳኔዎች
💠የአርሲ ሀገረ ስብከት ጉዳይ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት አጣሪ ልኡክ ተልኮ በሪፖርት መሠረት በቋሚ ሲኖዶስ እንዲታይና ውሳኔ እንዲሰጥበት።
💠የሸካ ዞን ራሱን የቻለ ሀገረ ስብከት ሆኖ እንዲደራጅ ለዚህ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል እንዲመሩና እንዲደራጁ
💠"ገድለ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ" በሚል በአንድ ግለሰብ ተዘጋጀና የተሠራጨ መጽሐፍ ከኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ትምህርት የወጣ በመሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ ያወገዘ፤ ስለሆነም ቤተ ክርስቲያን ለምንም እንዳትጠቀምበት፣ እንዳይሰራጭና ለማጣቀሻም እንዳያገለግል ተብሎ ተወስኗል።
💠የዩናይትድ ኪንግደም ሀገረ ስብከትን በተመለከተ የክፍሉ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ያዕቆብ በሀገረ ስብከቱ በአካል ተገኝተው መዋቅሩን እንዲያጠናክሩና የአፈጻጸም ሪፖርቱንም ለግንቦት ርእክበ ካህናት እንዲቀርብ ወስኗል።
💠በሰሜን አሜሪካ ካሊፎሪኒያ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት መንፈሳዊ ኮሌጅ እንዲቋቋምና የአብነት ትምህርት ማስመስከሪያ እንዲከፈት ቅዱስ ሲኖዶስ ፈቅዷል። የመዋቅራዊ አደረጃጀቱን በተመለከተ አፈጻጸሙ ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ትምህርትና ማሰልጠኛ መምሪያ ጋር በመሆን እንዲከወንና ለግንቦቱ ርክበ ካህናት እንዲቀርብ
💠የምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት በግንቦት 15/2017 ዓ/ም በሰጠው ውሳኔ መሠረት ያለጣልቃ ገብነት በብፁዕ አቡነ መቃርዮስ እንዲመራ!
💠ብፁዕ አቡነ አብርሃም የሚመሩት የኤድመንተንና አካባቢው ተብሎ ይጠራ የነበረው ሀገረ ስብከት #መካከለኛው ካናዳ ኤድመንተን እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ተብሎ እንዲጠራ ተወስኗል። የዘገባው ምንጭ Eotc tv ነው

❤2🙏1
" ተአምር ነው ! "
ተሽከርካሪው 150 ሜትር ርዝማኔ ያለው ገደል ገብቶ አርሶ አደር ግቢ ውስጥ ቢያርፍም ከቀላል ጉዳት ውጪ ያጋጠመ ከባድ ጉዳትና ሞት የለም።
በትግራይ ክልል የሚገኘው የጥንታዊው አቡነ አረጋዊ ገዳም ዝክር በየዓመቱ የአገር ውስጥና ከውጭ የሚመጡ ምእመናን በተገኙነት ጥቅምት 14 ነው የሚከበረው።
ታዲያ " ቶዮታ ሪቮልዩሽን " በሚባለው ተሽከርካሪ ባለቤቱ እራሱን ጨምሮ 5 ሰዎች ጭኖ ዓመታዊው የአቡነ አረጋዊ ገዳም ለመሳለም በመጓዝ ላይ እያለ ተሽከርካሪው መንገድ ስቶ ተንሸራቶ ገደል ይገባል።
ተሽከርካሪው የገባበት ገደል ርዝማኔው 150 ሜትር ነው ብለዋል የአይን እማኞች።
ተሽከርካሪው መንገድ ስቶ ወደ ገደል ከተወረወረ በኃላ በፎቶው እንደሚታየው ወደ አንድ አርሶ አደር ቤት ግቢ ገብቶ ተዘቅዝቆ አርፏል።
ከአስፈሪ ገደል ተወርውሮ በሚታየው መልኩ ያረፈው ተሽከርካሪ በአርሶ አደር ቅጥር ግቢ ከነበሩት ሰዎችና እንስሳት ላይ አንድ ቀላል ጉዳት ከማድረሱ ውጪ የተከሰተ ከባድ ጉዳትና ሞት የለም።
ክስቱቱን ለሰሙት " ተአምር " ያስባለ እንደሆነ የቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ ቤተሰብ አባል ገልጾልናል።
አሽከርካሪዎች ለማሽከርከር በሚያዳግቱና ተዳፋት በሆኑ መንገዶች ላይ ሲያሽከረክሩ እርጋታና ማስተዋል ሊለያቸው አይገባም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia

❤5🙏1
ሠላም ለዝክረ ስምከ
እስከ አለም ዳርቻዎች ስመ ጥር የሆንክ ቅዱስ እስጢፋኖስ ሆይ ለዘለላሙ የማይሞት ህያው የሆነ የመላእክት ፈጣሪ እግዚአብሔር በክንፈ ረድኤቱ ለፃፈው ስም አጠራርህ ሠላምታ ይገባል🕯🤲🤲🤲
ሠላም ለአፉከ
ቅዱስ እስጢፋኖስ ሆይ የወልደ ማርያም ልጅ ክርስቶስ በአብ ቀኝ መቀመጡን በግልፅ ላስተማረ አፍህ ሠላምታ ይገባል🕯🤲🤲🤲
ሠላም ለበድነ ስጋከ
ቅዱስ እስጢፋኖስ ሆይ በሽተኞች ይድኑዘንድ ሙታንን ያስአሳ ዘንድ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስልጣን ለተሰጠህ ስጋ ሠላምታ ይገባል🕯🤲🤲🤲
አሜን 🙏🙏🙏 ከሰማእቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ ረድኤቱ በረከቱን ያሳትፈን ፀሎት ልመናው አይለየን ይጠብቀን አሜን///፫///🤲🤲🤲
ኑ አብረን እናንግስ።

🙏2🔥1
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ
በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የሚመራው፣ የሐዋርያት መንበር ወራሽ የሆነው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ
“ወይኩን ጉባኤ ሊቃነ ኤጴስ ቆጶሳት ወኤጲስ ቆጶሳት ክልዔተ ጊዜ በበዓመት ወይትናገሩ በእንተ ግብረ አብያተ ክርስቲያናቲሆሙ ወያሰስሉ ዕቅፍታተ …
የሊቃነ ጳጳሳትና የጳጳሳት ምልዓተ ጉባኤ በዓመት ሁለት ጊዜ ይሁን ስለአብያተ ክርስቲያናት የሚገባውን ሁሉ ይነጋገሩ የሐዋርያዊ ተልእኮ መሰናክሎችንም ሁሉ ያስወግዱ” ተብሎ በመጀመሪያው የሐዋርያት ቀኖና፣ በሁለተኛው ቀሌምንጦስ በተደነገገው መሠረት ምልዓተ ጉባኤው ከጥቅምት 11 - ጥቅምት 17 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ስለ ቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ፣ ማኅበራዊና የምጣኔ ሀብት ዕድገት፣ ስለ ሀገር ሰላምና አንድነት፣ ስለ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደርና ሐዋርያዊ ተልእኮ መስፋፋት ስለ ሰው ልጅ ሁሉ ደኅንነት ሰፊ ውይይት አድርጓል፡፡
ወቅቱን ያማከሉና ዘላቂ የቤተ ክርስቲያንን ተቋማዊ ሕልውና የሚያረጋግጡ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ልዕልናንን የሚያስጠብቁ፣ ለምእመናን ደኅንነትና ለአገልጋዮች ሕይወት በሚጠቅሙ፣ መንሳፈዊ አስተዳደርንና ማኅበራዊ ጉዳዮችን መሠረት ባደረጉ አጀንዳዎች ላይ በመንፈስ ቅዱስ አንድነት በመወያየት ለቤተ ክርስቲያናችንና ለሀገራችን ጠቃሚ የሆኑ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡
በዚሁ መሠረት፡-
ሁለንተናዊ ሰላምና መረጋጋት የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሃይማኖታዊ መሠረቷ፥ የሥርዓተ ቅዳሴዋና የምሥጢራት አገልግሎቷ አካል፣ የመንፈሳዊና ማኅበራዊ ሥምሪቷ ማእከላዊ ዐምድ በመሆኑ በግንቦት 2017 ዓ.ም. ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የተሠየመው የሀገራዊ ሰላምና የቤተ ክርስቲያን አንድነት ኮሚቴ ሥራውን አጠናክሮ እንዲቀጥል፤ የደረሰበትንም ውጤት ለግንቦት 2018 ዓ.ም ምልዓተ ጉባኤ እንዲያቀርብ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥብቅ መመሪያን አስተላልፏል
በትግራይ አህጉረ ስብከት የሚገኘው ሕዝበ ክርስቲያን ሕዝባችንና ወገናችን ስለሆነ አብያተ ክርስቲያናቱና ገዳማቱም የቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ ሀብቶች በመሆናቸው፣ አህጉረ ስብከቱም የተደራጁት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በመሆኑ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሕግና ቀኖና ተጠብቆ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ልዕልና ተከብሮ፣ የመዋቅር ግንኙነቱን ወደ ቀደመ ቦታው እንዲመለስ የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የሰላም፣ የአንድነትና የይቅርታ በር ክፍት መሆኑን ከመግለጽ ጋር ቅዱስ ሲኖዶስ በክልሉ ለሚገኙት አባቶች፣ ካህናትና ምእመናን ያልተቋረጠ የሰላም ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
የቀድሞዎቹ ቅዱሳን አባቶቻችን ዋጋ ከፍለው፣ ቀኖናዊ ሥርዓቷንና ክብሯን ጠብቀውና አስጠብቀው ፣ አንድነቷን አጽንተው ያወረሱንን አሐቲ ቤተ ክርስቲያን የቀደመ ሉዓላዊ ክብሯ እንደተጠበቀ ለመጭው ትውልድ ማስተላለፍ የበለጠ ዋጋ ያሰጣልና ቀደም ሲል ለዚሁ ጉዳይ የተሠየመው ኮሚቴ ሥራውን አጠናክሮ እንዲቀጥል፣ ሊቃውንቱ፣ ካህናቱና መላው ሕዝባችንም የቤተ ክርስቲያንን አንድነት ለማጠናከር በሚደረገው ጥረት ሁሉ የበኩላችሁን እንድትወጡ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በአጽንኦት ያሳስባል፡፡
ቅዱስ ሲኖዶስ አባት እንዲመደብላቸው ጥያቄ ባቀረቡ አህጉረ ስብከት ዙሪያ የውሳኔ ሐሳብ የሚያቀርቡ ብፁዓን አባቶችን በመሰየምና ተገቢውን ውይይት በማድረግ፡
ሀ) ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ የኢሉ አባቦራ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ የምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከትን ደርበው እንዲመሩ፣
ለ) ብፁዕ አቡነ ቶማስ የአዊና መተከል አህጉረ ስብከት ሊቀጳጳስ የምሥራቅ ጎጃምን ሀገረ ስብከት ደርበው እንዲመሩ፣
ሐ) ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ የደቡብ ወሎና ከሚሴ አህጉረ ስብከትን ደርበው እንዲመሩ፣
መ) ብፁዕ አቡነ ኒቆዲሞስ የምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ጳጳስ የምሥራቅ ወለጋና ሆሮ-ጉድሩ ወለጋ አህጉረ ስብከትን ደርበው እንዲመሩ
ሠ) በተጨማሪም የሸካ ዞን ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ተብሎ ራሱን ችሎ በሀገረ ስብከት ደረጃ እንዲቋቋም፣ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ሀገረ ስብከቱን እንዲያደራጁና እንዲመሩ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
ነባሩና ጥንታዊው የቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ገድል እንደተጠበቀ ሆኖ ገድለ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ በሚል ያለአግባብ በአንድ ግለሰብ ተዘጋጅቶ እየተሠራጨ ያለው መጽሐፍ በሊቃውንት ጉባኤ ተመርምሮ ያለበት ግድፈትና የስሕተት ትምህርት በሙሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሰ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ የማይወክል ሆኖ በመገኘቱ ተወግዟል፤
በውስጡ የያዛቸውም የተሳሳቱ ትምህርቶች በሙሉ ተቀባይነት ስለሌላቸው መጽሐፉ ለጥናትና ምርምርም ሆነ ለማጣቀሻ አገልግሎት እንዳይውል፣ በሥርጭት ላይ የዋለው መጽሐፍ እንዲታገድና በድጋሚም እንዳይታተም፣ ለየአህጉረ ስብከቱ ሠርኩላር እንዲተላለፍ፣ የአፈጻጸም ክትትል እንዲደረግና አጠቃላይ ሁኔታው በሊቃውንት ጉባኤ በኩል በሚዲያ እንዲገለጽ፣ የአስተምህሮ ስሕተትን በማካተት አሳትመው ያሰራጩት ግለሰብ በቋሚ ሲኖዶስ ተጠርተው እንዲጠየቁና የፈጸሙትን ስሕተት ዐውቀው ወደፊት ተመሳሳይ ስሕተት እንዳይፈጽሙ ጥብቅ መመሪያ እንዲሰጣቸው፣
መጽሐፉ እንዲመረመር ያደረገው የደብረ ሊባኖስ አንድነት ገዳምና የገዳሙ የቅኔ መምህር መጋቤ ምሥጢር አባ ክንፈሚካኤል ወልደ ገብርኤል የምስጋና ደብዳቤ እንዲጻፍላቸው ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
በሰሜን ካሊፎርኒያ ኔቫዳና አሪዞና ሀገረ ስብከት የኆኅተ ሰማይ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ወቅድስት አርሴማ አንድነት ገዳም መንፈሳዊ ኮሌጅና የአብነት ምስክር ጉባኤ ቤት ለማቋቋም በጠየቀው መሠረት እንዲፈቀድ ሆኖ የትምህርት አሰጣጥ ፖሊሲውና ሥርዓተ ትምህርቱ፣ የሰው ኃይል አደረጃጀቱና መዋቅራዊ ተጠሪነቱ ተዘጋጅቶ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ተጠንቶ ከውሳኔ ሐሳብ ጋር ለግንቦት 2018 ርክበ ካህናት ምልዓተ ጉባኤ እንዲቀርብ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤
በምዕራብና በመካከለኛው ካናዳ የሚገኙት ሁለቱ አህጉረ ስብከት ከአሁን በፊት በ2017 ዓ.ም. በተሰጠው ውሳኔ መሠረት ያለ ጣልቃ ገብነት በየራሳቸው እንዲተዳደሩና የኤድመንተንና አካባቢው ሀገረ ስብከት የመካከለኛው ካናዳ ኤድመንተንና አካባቢው ሀገረ ስብከት በሚል ሥያሜ እንዲስተካከል ምልዓተ ጉባኤው ወስኗል፡፡
በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ በአረርቲ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በዓል ለማክበር ሄደው አዲሱን ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን በመጐብኘት ላይ እያሉ አደጋ በደረሰባቸው ምዕመናን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የተሰማውን ሐዘን እየገለጸ እግዚአብሔር አምላካች ላረፉት ወገኖቻችን ዕረፍተ ነፍስ እንዲሰጥልን ከመጸለይ ጋር አካላዊ ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች ለማሳከምና የተጎጂ ቤተሰቦችን ለመርዳት የገንዘብ ድጋፍ እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡ ለወደፊቱም በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ዙሪያ በሚገነቡ ሕንጻ ግንባታዎች አደጋ ከመድረሱ በፊት ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ በአጽንዖት ያሳስባል፤

❤3
በመላው ኢትዮጵያ በሚገኙ ገዳማት ያሉት መነኰሳትና መነኰሳይያት ለአገልግሎትና ጉዳይ ለማስፈጸም ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ ክብራቸውና ገዳማዊ ሕይወታቸው ተጠብቆ ጉዳያቸውን እስከሚፈጽሙ ድረስ የገዳማት ኅብረቱ ባቀረበው ጥያቄ መሠረት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በኩል ማረፊያ የሚሆን ቦታ እንዲዘጋጅላቸው፣
የአንድነት ገዳማት ኅብረቱ መተዳደሪያ ደንብ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሕግ አገልግሎት መምሪያ በኩል ታይቶና ተመርምሮ እንዲቀርብ፣
በአጠቃላይ በአንድነት ገዳማት ኅብረት የቀረበው የገዳማውያንና ገዳማውያት ማረፊያ እና የገቢ ማስገኛ ሁለገብ ሕንጻ ግንባታ የትግበራ ዕቅድ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት በኩል በዘርፉ ባለሙያዎች ታይቶና ተገምግሞ ከባለሙያ አስተያየቶችና የውሳኔ ሐሳብ ጋር ተጠንቶ ለግንቦት 2018 ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ እንዲቀርብ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ወስኗል፡፡
በበዓላት አከባበር፣ በመንፈሳዊ አገልግሎት አፈጻጸም ዙሪያ የሚታዩ ግድፈቶች፣ ያልተገቡ እንቅስቃሴዎችና ከሥርዓት የወጡ የአገልግሎት አፈጻጸሞች መታረም ስላለባቸው በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት በሚሰየሙ ሊቃውንትና ባለሙያዎች ለመመሪያና ለማስተማሪያ የሚሆን ሰነድ ተዘጋጅቶ እንዲቀርብ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ተገቢውን ውሳኔ ያስተላለፈ መሆኑን እየገለጽን ያለጠባሳ የሚያድኑ ሐኪሞች፣ ያለቅሬታ የሚያስታርቁ ሽማግሌዎች በነበሩባትና ባሉባት ሀገር ተመካክሮ ችግርን አለመፍታት ተገቢ አይደለምና ሀገራችንን እንወዳለን፣ ሕዝባችንን እናከብራለን የምትሉ፣ የዜጎችን ደኅንነት የማስጠበቅ ኃላፊነት ያለባችሁ ሁሉ ክቡር የሆነው የሰው ልጅ ሕይወት በከንቱ እንዳይጠፋ፣ አካሉ እንዳይጐድል የሀገር ልማትና መልካም ገጽታ እንዳይበላሽ ጠላት መባባሉ ቀርቶ፣ የጦር መሣሪያ ትግል ተወግዶ፣ በእኩልነትና በመስማማት ሰላማዊ የችግር አፈታት መንገድን ተከትላችሁ በውይይትና በጥበብ ልዩነቶችን በመፍታት የተሟላ ሀገራዊ ሰላም እንዲሰፍን ታደርጉ ዘንድ ቅዱስ ሲኖዶስ ከአደራ ጭምር ሐዋርያዊ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
በመጨረሻም የሀገራችን ኢትዮጵያና የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን ሕልውና ስለማይነጣጠሉ፣ ሀገራችን በሉአላዊነቷ እንድትቀጥል የቤተ ክርስቲያናችን የአንድነት መዋቅሯ የበለጠ ተጠናክሮ፣ የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮዋ ሰፍቶ፣ ለትውልድ እንድትሻገር፣ ሕዝባችን ደኅንነቱና ሰላሙ ተጠብቆ እንዲኖር ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ጀምሮ ሁሉም የቤተ ክርስቲያናችን መምህራን፣ ካህናትና ሕዝባውያን፣ መነኰሳትና መነኰሳይያት በሙሉ በፍቅርና በአንድነት ዘወትር በመጸለይ ዘመኑ ከደረሰበት አሠራርና ጥበብ በላቀ ሁኔታ ከፍ ብለን ትውልዱን ለመዋጀት እንድንችል የበኩላችሁን እንድትወጡ በማሳሰብ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ዓመታዊ ስብሰባውን አጠናቋል፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
አሜን!
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም
ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ጥቅምት 17 ቀን 2018 ዓ.ም.
አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ

🌿🌷🌿🌷🌿🌷🌿🌷🌿🌷🌿🌷🌿
"ወንድሞቻችን ኾይ እምነት አለኝ ምግባር ግን የለኝም የሚል ሰው ቢኖር ምን ይጠቅመዋል?
በውኑ እምነቱ ልታድነው ትችላለችን?
ከወንድሞቻችን÷ ወይም ከእኅቶቻችን÷ የታረዙ ወይም የዕለት ምግብ ያጡ ቢኖሩ÷ ከእናንተም አንዱ÷ “በሰላም ኺዱ÷ እሳት ሙቁ÷ ትጠግባላችኹም” ቢላቸው÷ ለችግራቸውም የሚሹትን ባይሰጣቸው ምን ይጠቅማቸዋል?
እንዲኹም ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው፡፡
ያዕ. ፪÷፲፬-ፍጻ

❤1
"ወርኃ ሢመትከ ወርኃ ታሥሪን
እንተ ይኤድሞ ለዐይን
ጸገየ ወይን ወፈረየ ሮማን።
..........................................
ለዓይን ደስ በሚያሰኘው በተሾምህበት ወራት
(በዕብራይስጥ) ታሥሪን በሚባል በጥቅምት ወር፣
ወይን አበበ ፤ ሮማንም አፈራ።"
~ መልክዓ እስጢፋኖስ
እንኳን ለቅዱስ እስጢፋኖስ በዓለ ሢመት በሰላም አደረሳችሁ!
በረከተ እስጢፋኖስ ለሁላችን ይብዛልን!
ሥዕሉ በመናገሻ አምባ ማርያም የሚገኝ እጅግ ጥንታዊ የንዑድ ክቡር ሊቀ ዲያቆናት ወቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ ሥዕል ነው።
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨

❤8🥰1
ክፋትን_ከአንተ_አርቃት
"ሰይጣን ክርስቶስ በልብህ ውስጥ ያለ መሆን አለመሆኑን ያውቃል፡፡ ይኸውም ስትቆጣ ወይም ስትጮህ ወይም የማይረቡ ከንቱ ነገሮችን ስትናገር ሲያይህ ጠላት በአንተ ዘንድ እግዚአብሔር እንደሌለ ያውቃል ያን ጊዜ በውስጥህም በውጭህም ያለውን ሳይቀር ይገዛል ፤ መዝጊያ እንደሌለው ቤት እንደ ክፉ ሌባ ይገባና ውስጥህን ይበረብረዋል፡፡"
ቅዱስ_ባስልዮስ

"ኀጢአታችን በራሳችን ላይ በዝቶአልና በደላችንም ወደ ሰማይ ከፍ ብሎአልና አምላኬ ሆይ ፊቴን ወደ አንተ አነሣ ዘንድ አፍራለሁ እፈራለሁም "
ዕዝ 9÷6
ዕዝ 9÷6
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
EOTC TV | በምሥራቅ አርሲ ዞን ለተገደሉ ኦርቶዶክሳውያን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ eotctv
ይህን ያውቁ ኖሯል?
"ብጹዕ አቡነ ኤርሚያስ "
ሰው ወደ ሰንበት ትምሕርት ቤት የሚመጣው ክርስቲያን ለመሆን ነው።
"ብጹዕ አቡነ ኤርሚያስ "
🥰7
"አቤቱ ጌታዬ ንጉሤ ሆይ ራሴን ጥፋት አስመልክተኝ እንጂ በወንድሜ ላይ እንድፈርድ አታድርገኝ ፡፡"
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ ከአርሲ የኦርቶዶክሳውያን ጭፍጨፋ ለተረፈው ህጻን ህክምና የሚውል የ70ሺ ብር ድጋፍ በማድረግ አጽናንተው ተመልሰዋል።
***
የወላይታ ሀገረስብከት ከአርሲ የኦርቶዶክሳውያን ጭፍጨፋ በታምር ተርፎ በወላይታ ሶዶ ክርስቲያን ሆስፒታል በህክምና ላይ ለሚገኘው የአራት ዓመት ህጻን የመጀመርያ ዙር የህክምና ወጪ ማስፈጸሚያ የሚውል የ70ሺ ብር የገንዘብ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን
በብፁዕ አቡነ ይስሐቅ የተመራው የወላይታ ሀገረስብከቱ ልዑክ ህጻኑ ወደ ተኛበት ክርስቲያን ሆስፒታል በመጓዝ ቤተሰቡን በማጽናናት እና ከእዚህ በኃላ እነርሱ ላይ የሚደርሰው ማንኛውም አይነት ችግር ሀገረስብከቱ እንደሚወጣው ጭምር በማሳሰብ ተመልሰዋል።
ይህኝን ታላቅ የበረከት አባት አመስግኑልኝ !

❤13🥰2👏2