ፍኖተ ወንጌል ሰንበት ት/ቤት
676 subscribers
1.76K photos
16 videos
460 links
በአሰላ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ካቴድራል ፍኖተ ወንጌል ሰንበት ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።

የቴሌግራም ቻናል:-  @Finote_Wongel
የቴሌግራም ግሩፕ:- @FinoteWongel27
የቲክቶክ ገፅ:- https://www.tiktok.com/@finotewongel27
Youtube:- https://www.youtube.com/@Finote_Wongel

©ፍኖተ ወንጌል ሰንበት ት/ቤት
Download Telegram
"አቅቶት ወደ ቀደመ አኗኗሩ ይመለሳል"
                       ~ ቅዳሴ ማርያም ቁ ፹፮
..........................................................
  የብሕንሳው አባ ሕርያቆስ በቅዳሴ ማርያም ድርሰቱ እንዲህ ብሎ ነበር :- " ይህንንም (አምላክን ስለመጽነስሽ) ባሰብኩ ጊዜ ኅሊናዬ የልጅሽን የባሕሩን ጥልቅነት ሊዋኝ ይወዳል፤ የወዳጅሽ የመሠወሪያው ማዕበልም ያማታዋል። ዳግመኛም ባሰብኩ ጊዜ ኅሊናዬ ተሠውሮ ወደላይ ወጥቶ የሕያው መሠወሪያ የሆነውን ሊገልጥ ይወዳል ። ከነደ እሳትነቱ የተነሣ ይፈራል፣ ከዐየራት ከእርቧቸው እርቦ አይደርስም ። ይህንንም ባሰብኩ ጊዜ ኅሊናዬ በነፋስ ትከሻ ተጭኖ በምሥራቅና በምዕራብ በሰሜንና በደቡብ በዳርቻዎችም ሁሉ ሊበር ይወዳል ። የፍጡራንን አኗኗር ያይ ዘንድ የአብሕርትንም ጥልቅነታቸውን ይለካ ዘንድ የሰማይን ርዝመቱን ያውቅ ዘንድ በሁሉ ዘንድ በሁሉም ይዞራል ። አቅቶት ወደ ቀደመ አኗኗሩ ይመለሳል።"

  እመቤቴ ሆይ እኔም እኮ የልጅሽን ቸርነት፣ ደግነት፣ ርኅራኄውን ባሰብኩ ጊዜ ኅሊናዬ ኃጢአቴን በንስሐ አራግፎ በልጅሽ የፍቅር ባሕር ውስጥ ሊዋኝ ይወዳል። ግን ምን ዋጋ አለው? የኃጢአት ፍቅር ገና ከልቡናዬ አልተነቀለምና የፍትወቴ ማዕበል ወደ ቀደመ አኗኗሩ ያማታዋል። ዳግመኛም የልጅሽ ይቅር ባይነቱ፣ እንደ በደሌ ብዛት እኔን ያልቀሰፈበት ትዕግሥቱ እያስደነቀኝ እግረ ኅሊናዬ ኃጢአቴን ይናዘዝ ዘንድ ወደ ልጅሽ ሹማምንቶች ካህናት ሊበር ይወዳል። ከአንድ ካህን ፊት ኃጢአቱን ተናግሮ ራሱን ለማዋረድ ግን ከትዕቢቱ የተነሳ ይፈራል። አቅቶትም ወደ ቀደመ የኃጢአት አኗኗሩ ይመለሳል።

  ማርያም ሆይ፤ ዳግመኛም ኅሊናዬን በኃጢአቴ ከልጅሽ ተለይቼ የኖርኩበት ዘመን በቁጭት ዕረፍት ነስቶት በንስሐ ወደ ልጅሽ ዕቅፍ ለመግባት ይናፍቃል። የቀረ ሕይወቴን በጽድቅ ልጅሽን እያስደሰትኩ እኖር ዘንድ፣ የልጅሽን የትህትናውን ጥልቅነት እየለካሁ፣ የምሕረቱን ስፋት አውቅ ዘንድ ኅሊናዬ በሁሉ ዘንድ በሁሉም ይዞራል። ግን አቅቶት ወደ ቀደመ አኗኗሩ ይመለሳል።

  እመብርሃን ሆይ ይህ ብቻ መሰለሽ? ኃጢአት ልሰራ በተዘጋጀሁ ጊዜ በኅሊናዬ የልጅሽ መስቀል ይታሰበኛል። ልጅሽን ከመበደል ያድኑኝ ዘንድ በምሥራቅ እና በምዕራብ፣ በሰሜንና በደቡብ፣ በዳርቻዎች ሁሉ ያሉ ቅዱሳንን አፌ ይጠራቸዋል። የልጅሽ የወዳጅሽ ፍቅር ግን በልቤ አልጸናምና አካሌ አቅቶት ወደ ቀደመ ኃጢአቱ ክፉኛ ወድቆ ይመለሳል።

  "እስመ ተነድፈ ልብየ በፍቅርኪ ፤ ልቤ በፍቅርሽ ተነድፏልና" ብዬ ስንቴ እያዜምኩ ሰዓታት ቆሜልሽ ነበር። እንደ አባ ጊዮርጊስ እኮ እኔም ልቤ በአንቺ ፍቅር ይሰወር ዘንድ፣ በልጅሽ ቃልኪዳን በተሰጠኝ እናትነትሽ ይከለል ዘንድ እልፍ ጊዜ ደጅ ይጠናል። ግን ምን ዋጋ አለው? የክፋቴ፣ የበደሌ ብዛት ከንጽሕናሽ እርቦ አያደርሰኝም።

  እመአምላክ ሆይ አሁንም ኅሊናዬ የልጅሽን ሕግ በቀን እና በሌሊት ያነብ ዘንድ፣ ኃያላንን በሚያጸናቸው በልጅሽ ቃል ልቤ ይታነጽ ዘንድ ቅዱሳት መጻሕፍትን ሊገልጥ ይወዳል፣ በልጅሽ ቃል መሰረት መኖር አቅቶት ግን ወደ ቀደመ አኗኗሩ ይመለሳል። ዳግመኛም ኅሊናዬ የቅዱሳንን አኗኗር አይቶ የእግዚአብሔርን ቃል በተግባር የነገሩትን ዋኖቹን ያስብ ዘንድ፣ የኑሮአቸውን ፍሬ እያየሁ በእምነት እመስላቸው ዘንድ በገድላቸው እና በድርሳናቸው ትከሻ ተጭኖ ይዞራል። ቅዱሳንን መምሰል አቅቶት ግን "እንደሚጠፉ እንስሶች" ወደመምሰሉ ይመለሳል። ዕብ 13፥7 ፣ መዝ 48 ፥ 12

  ድንግል ሆይ፣ አሁንም ሰውነቴ ልጅሽ ይቅር ብሎኝ ወደረሳው ኃጢአቴ እንዳይመለስ የጾም ጸሎት፣ ስግደት ትሩፋትን አብዝቶ ሊፈጽም ይወዳል። አላደርገውም ብሎ የተገዘተበትን ኃጢአት ግን አቅቶት ወደ ትፋቱ እንደሚመለስ ውሻ ተመልሶ ይጨማለቅበታል። እመቤቴ ሆይ፣ ዳግመኛም ኅሊናዬ ያንቺን ቅንጣት ንጽሕና ገንዘብ ያደርግ ዘንድ፣ ልቤም ካንቺ የማይወሰን ርኅራሄሽ ተካፍሎ የልጅሽ ማደሪያ ይሆን ዘንድ ይወዳል። ግን አቅቶት ባንቺ ንጽሕና ልክ በኃጢአት ወደ መቆሸሹ ይመለሳል።

  ድንግል ሆይ መልሺኝ እኔም እመለሳለሁ። ወደ ቀደመ የኃጢአት አኗኗሬ አይደለም፤ ወደ ቀደመ ጥቂት ጽድቄ እንጂ! ወደ ቀደመ በደሌ አይደለም፣ ወደ ቀደመ ቅንጣት ንጽሕናዬ እንጂ። ወደ ቀደመ ድካሜ አይደለም፣ ወደ ቀደመ በልጅሽ ኃይል ወደበረታሁበት ማንነቴ እንጂ! አቅቶኝ ወደ ምመለስበት ኃጢአት ሳይሆን ተመልሼ ወደምነሳበት ጽድቅ መልሺኝ!

  ድንግል ሆይ ልጅሽ መሐሪ ይባል ዘንድ "ለጻድቃን ያይደለ ለኃጥአን አሳስቢ፣ ለንጹሐን ያይደለ ለተዳደፉት አሳስቢ።" ቅዱስ ዲዮስቆሮስ በቅዳሴው ልጅሽን እንዲህ ይለዋልና :- "ጻድቃንን ግን ከሥራቸው የተነሳ ትምራቸዋለህ፣ እንደ ጽድቃቸውም ትሰጣቸዋለህ፤ እኛን ኃጥአንን ብትምረን ያን ጊዜ መሐሪ ትባላለህና።"

..........................................
ዲያቆን ዮሐንስ
4
🍂🍂🍂🍂

ምጽዋት ብዛት ወይስ ጥራት?

የማትፈልገውን ሳይሆን ለአንተ ምርጥ የምትለውን መስጠት ልመድ። የአገልግሎት ዘመኑን የጨረሰ ልብስ፣ ለመመገብ አስቸጋሪ የሆነ፣ የሻገተ ወይንም የደረቀ ምግብ መስጠት የተለመደ በሆነበት ዘመን ላይ ስላለህ የምታደርገውን ሁሉ ተጠንቅቀህ አድርግ።

🍂
አንተ የማትለብሰው ስለማይለበስልህ ነው። የማትበላው በጤናህ ላይ ችግር ስለሚያስከትልብህ ነው፤ ታድያ ለወንድምህስ የምትሰጠው ለሕመም የሚዳርገውን ነውን? መሆን የለበትም። ይልቁንም ለወንድምህ ከምትበላው አካፍለው። ከምትለብሳቸው ሁለቱ ልብሶች አንዱን ስጠው። የሚጎዳውን ብዙ ነገር ከምትሰጠው የሚጠቅም ትንሽ ነገር ስጠው። ለአንተ የምትመኝውን ጥራት ለወንድምህም አድርግ። "እውነት እላችኋለሁ ከሁሉም ከሚያንሱት ከነዚህ ወንድሞቼ ያደረጋችሁት ለኔ አደረጋችሁት" ማቴ 25፥40 ያለውን ቃል መለስ ብለህ አስብና የምትሰጠውን ጎጂ ነገር ለክርስቶስ እንደምትሰጠው ተረዳ።

🍂
አቤልና ቃየል ለእግዚአብሔር ያቀረቡት መሥዋእት እንዴት እንደነበረ አሰብ። "አቤልም ደግሞ ከበጎቹ በኩራትን ከስቡ አቀረበ። እግዚአብሔርም ወደ አቤልና ወደ መሥዋእቱ ተመለከተ።"ዘፍ 4፥4 ለምን መረጠለት? ብትል አቤል ካለው ሁሉ መርጦ የተሻለውን ለእግዚአብሔር መስዋዕት አድርጎ ስላቀረበ ነው። በሐዋርያት ሥራ 4፥34-35 ላይ ሰፍሮ የሚገኝውን የሐዋርያቱ ሕይወት ምን ይመስል እንደነበረ የሚናገረውን ቃል አስተውለህ አንብበውና የአንተ ምጽዋት የአንተ ሥጦታ የትኛው ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ራስህን ጠይቅ።

"
እውነት እላችኋለሁ ከሁሉም ከሚያንሱት ከነዚህ ወንድሞቼ ያደረጋችሁት ለኔ አደረጋችሁት" ማቴ 25፥40

  
ብጹዕ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

🍂🍂🍂🍂
👏3😁1
"ከንቱ ውዳሴ በመንገድ ሁሉ የሚከተልህ የተሸሸገና ጭንብል ያጠለቀ ሌባ ነው። አሳዳጅ በመሆኑ በጣም ደኅንነት በሚሰማህ አሳቻ ሰዓት ሳታውቀው ይዘርፈሀል፤ ይገድልህማል። "

ቅዱስ ጎርጎርዮስ
ካህናት ዲያቆናትን መስቀል ሲያሳልሙ "በረከተ እስጢፋኖስ ይኅደር በላዕሌከ ፣ የቅዱስ እስጢፋኖስ በረከት በላይህ ይደር" ይላሉ። ይህች በረከት መብል ለማሰናዳት ብትሾምም ቃለ እግዚአብሔርን በጸጋ እና በሞገስ ወደ ማስተማር የተሻገገረች፣ ክርስትናን በአንድ ቦታ ብቻ ይጸና ዘንድ ብትሰየምም፣ በውግረተ አእባን ክርስቲያኖችን በትና ወንጌልን በዓለም ሁሉ ያዳረሰች በረከት ናት።

  የቅዱስ እስጢፋኖስ በረከት አይሁድ ሊቃወሟት ስለማይችሉ ላለመሰማት ጆሮአቸውን የሚደፍኑባት፣ የሐሰት ክስ ማዕበል ቢወርድባትም በቅዱሱ ፊት ከፀሐይ ሰባት እጅ የምታበራ፣ በድንጋይ ወግረው ሊያስቀሯት ቢሞክሩም ከድንጋዩ ዝናብ አሻግራ ቅድስት ሥላሴን አይታ የመንፈስ ቅዱስን መውረድ ፈጽማ የምታደንቅ በረከት ናት።

  እኛም በረከተ እስጢፋኖስን ተስፋ እና ኃይል በማድረግ ሰማዕቱ በዕሪና ባያቸው በአብ፣ በወልድ፣ በመንፈስ ቅዱስ ስም አምነን ክቡር የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል መማር ማስተማር እንጀምራለን። ንዑድ ክቡር የሚሆን የሰማዕታት መጀመሪያ ቅዱስ እስጢፋኖስንም እንዘክራለን።

  ጥቅምት 17/2018 ዓ.ም ቅዱስ እስጢፋኖስ በተሰየመበት ዓመታዊ ክብረ በዓሉ ነው። ስለሆነም በአሰላ ደ/መ/መ/ዓ/ካቴድራል በዓለ ንግሱ በድምቀት ይከበራል።

ኑ አብረን እናንግስ🙏
6🥰5👍1🕊1
የጥቅምት ቅዱስ ሲኖዶስ  የመክፈቻ  ጸሎት።
5
"ዳዊት በቀንም በማዕልትም ሕጉን የሚያነብ ብጹዕ ነው ብሏልና ፡፡ በጎዳናም ቢሆን ፤ በቤትም ቢሆን ፤ ስትተኛም ቢሆን ፤ ከእርሱ ይቅርታንና ቸርነትን ታገኝ ዘንድ ፤ ፈጣርህ እግዚአብሔርን በፍፅም ህሊናህ ፤ በፍፅም አእምሮህ ፤ በፍጹም ልቦናህ ፤ ውደደው" !! ።

       መፅሐፈ ዲዲስቅልያ
7
የእስጢፋኖስ መንገድ

ለእውነት እስከ ሞት መታመን።
እኒህ ድንጋይ ያነሡትኮ አላዋቂነታቸው ሸፍኗቸው እንጂ ዘለዓለማዊ ሕይወት የሚገኝበትን ትምህርት የሚነግራቸውን ሰው አይገድሉትም ነበር።

ብንችል እንደ ቅዱስ እስጢፋኖስ እንሁን። አርአያ እናድርገው። ባንችል ግን ቢያንስ ዘለዓለማዊ የሕይወት ትምህርት በሚያስተምሩን ላይ ድንጋይ አናንሳ።

ድንጋይ ለእስጢፋኖስ የሰማዕትነትን ክብር ያገኘበት ሲሆን፣ ድንጋይ ላነሡት ደግሞ የሕይወት ትምህርትን የሚነግራቸውን ሰው ያጡበት ነው።

የንግግራችን፣ የሐሳባችን፣ የድርጊታችን ማዕከል ዘለዓለማዊው ሕይወት ይሁን። እውነት ሐሳባችን ወይም ንግግራችን ወይም እያንዳንዱ ተግባራችን ወደ ዘለዓለማዊው ሕይወት ለምናደርገው ጉዞ ግብአት ይሆናል??! ራስን ቆም ብሎ መመርመር ይገባል።

የሰማዕቱ በረከት ይደርብን

ጥቅምት 17/2018 ዓ.ም የሰማዕቱ በዓለ ንግስ በአሰላ ደ/መ/መ/ዓ/ካቴድራል በድምቀት ይከበራል።

ኑ አብረን እናንግስ!
🙏31
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ የመጀመሪያ ቀን ውሎው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውሳኔ ሰጠ።
(ጥቅምት ፲፪ ቀን ፩፻፲፰ ዓ.ም)

የቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤትን በመወከል መግለጫውን የሰጡት መምህር ዳንኤል ሰይፈሚካኤል  ጉባዔው በመጀመሪያውን ቀን ጉባዔው ፲፮ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ማጽደቁን ገልጸዋል።
በጠዋቱ ውሎ  ፯ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን አጀንዳ እንዲቀርጹ ውሳኔ ያሳለፈ ሲሆን እነዚህም ሊቃነ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ፣ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ፣ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ፣ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል፣ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ፣ ብፁዕ አቡነ ሩፋኤልና ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ናቸው ፡፡ ኮሚቴው በብፁዕ አቡነ ጎርጎሬዎስ በሰብሳቢነት በብፁዕ አቡነ ዲዎስቆሮስ በአስረጂነት ተሰብስቧል።
ምልዓተ ጉባኤው በከሰዓቱ ውሎም ከ፲፮ቱ አጀንዳዎች በ፬ቱ ላይ ውሳኔ የሰጠ መስጠቱን ለመገናኛ ብዙኃን ድርጅት ያስታወቀ ሲሆን እነዚህም ውሳኔዎች

፩- ቅዱስነታቸው በጠዋቱ የመክፈቻ ጸሎት ያስተላለፉት መልዕክት
በቀጣይ የሥራ መመሪያ አድርጎ ምልዓተ ጉባዔው አጽድቋል፡፡
፪-ከጥቅምት ፬-፲ በነበረው የሰበካ መንፈሳዊ ዓለም ዓቀፍ ጉባኤ የነበሩ የቡድን ውይይቶች በቃለ ጉባኤ ቀርቦ ቃለ ጉባዔውን ምልዓተ ጉባዔው የ፳፻፲፰ ዓ.ም የሥራ መመሪያ አድርጎ አፅድቋል፡፡

፫-ሀገራዊ ሰላምን አስመልክቶ ምልዓተ ጉባዔው በግንቦት ተወያይቶ ሊቃነ ጳጳሳትን የያዘ ኮሚቴ ያዋቀረ ሲሆን ኮሚቴው የተሰጠውን ኃላፊነት አጠንክሮ እንዲቀጥል ተወያይቶ አጽድቋል፡፡

፬-በትግራይ የተፈጠረው ወቅታዊ ክፍፍልን አስመልክቶ የተወያየ ሲሆን በውይይቱም ህዝቡ ህዝባችን አብያተ ክርስቲያናቱም የቤተክርስቲያን ሀብት እንደመሆናቸው ቀደም ብሎ የተዋቀረው የሰላም ኮሚቴ ሥራውን አጠንክሮ እንዲቀጥል በምልዓተ ጉባኤው ወስኗል።

©ኢኦተቤ
5
" የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር ፈቃዴ ነው፤ ስለ ከንፈሮችህ ቃል ጭንቅ የሆኑ መንገዶችን ጠበቅሁ።"
    
        መዝሙረ ዳዊት 17: 4
🙏2
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የሁለተኛ ቀን በተለያዩ አጀንዳዎች ውሳኔ አሳለፈ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ በዛሬው ሁለተኛ ቀን ውሎው በአጃንዳ ቁጥር 5 እና 6 ላይ በሁለት አጀንዳዎች ውይይት በማድረግ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡

ረዳት ፕሮፌሰር መምህር ዳንኤል ሰይፈሚካኤል የጥናትና ምርምር መምሪያ እና የቅዱስ ሲኖዶስ የኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ ለመገናኛ ብዙኃን አገልግሎት ድርጅት #EOTCTV የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በዛሬው ጥቅምት 13 ቀን 2018 ዓ.ም በወሰናቸው ውሳኔዎች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ቅዱስ ሲኖዶስ አጀንዳ ቁጥር 5 የነበረው ውይይት ከተለያዩ የቤተክርስቲያኒቷ አህጉረ ስብከቶች ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት እንዲመደብላቸው ጥያቄ የቀረቡትን የተመለከተ ነበር፡፡

ይህንንም ጥያቄ መልስ ለመስጠትና ውሳኔ ለማሳለፍ አስቀድሞ ምልዓተ ጉባኤው አምስት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን ለኮሚቴነት በመሰየም የቀረቡትን ጥያቄዎች በማየት የውሳኔ ሐሳብ ለምልዓተ ጉባኤው እንዲያቀርቡ  በማድረግ አምስት  አባቶችን ሰይሟል፡፡የተሰየሙት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትም ከምልዓተ ጉባኤው ጎን ለጎን  የቀረቡትን ሦስት ጥያቄዎች  በኮሚቴው በማየት የምክረ ሐሳብና የውሳኔ ሐሳብ  ለምልዓተ ጉባኤው አቅርበዋል፡፡

ብፁዓን አባቶችም ባቀረቡት የውሳኔ ሐሳብም ምክንያት  ምልዓተ ጉባኤውም ሰፊ ውይይት በማድረግ  አሳልፏ በዚህም መሠረት፡
 
1ኛ. የምሥራቅ ጎጃም  ሀገረ ስብከት ያቀረበውን አባት  ይመደብልን የሚል ጥያቄ  በተመለከተ ብፁዕ አቡነ ቶማስ የአዊና የመተከል አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከትን  ደርበው የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከትን እንዲመሩና እንዲይዙ ምልዓተ ጉባኤው ወስኗል፡፡

በ2ኛ ደረጃ ደግሞ ከደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ ያቀረቡት  እንዲሁ አባት እንዲመደብ ጥያቄ ነው፡፡ ብፁዕነታቸው በሚመሩአቸው የደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት  የከሚሴ የደቡብ ወሎ ልዩ ዞን  ሁለቱን ሀገረ ስብከቶች አባት እንድመደብላቸው  ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት የብፁነታቸውን ጥያቄ ተቀብሎ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በአቀረቡት የውሳኔ ሐሳብ መሠረት  ለአግልግሎትም እንዲመች በአቅራቢያ የሚገኙትን የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ደርበው እንዲመሩ ምልዓተ ጉባኤው  ወስኗል፡፡
    
በ3ኛ ደረጃ ከምሥራቅ ወለጋ፣ ከምዕራብ ወለጋ ከሆሮ ጉድሩ ወለጋ የቀረቡ አባት እንዲመደብ የቀረቡ ጥያቄዎችን በአጀንዳ ቀርጾ በብፁዓን አባቶች በቀረበው የውሳኔ ሐሳብ መሠረት የምሥራቅ ወለጋንና የሆሮ ጉድሩን ብፁዕ አቡነ ኒቆዲሞስ የምሥራቅ ሐረርጌ ጳጳስ ሀገረ ስብከታቸውን እንደያዙ  ደርበው እንዲመሩ የቅዱስ ሲኖዶስ  ምልዓተ ጉባኤ ወስኗል፡፡
የምዕራብ ወለጋን በተመለከተ ደግሞ ብፁዕ አቡነ ኤውስጣቴዎስ  የአሉባቦር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ  የምዕራብ ወለጋና ደርበው እንዲመሩ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ወስኗል፡፡  እነዚህን ውሳኔዎች ሲወስንም ቅዱስ ሲኖዶስ አሁን በተደራቢ እንዲመሩ የተያዙት አህጉረ ስብከት   በዘላቂነት ሊቃነ ጳጳሳት  ተመድበው እስከፈታ ድረስ የተወሰነ ውሳኔ መሆኑን ነው  ረዳት ፕሮፌሰር መምህር ዳንኤል ሰይፈሚካኤል ለመገናኛ ብዙኃን አገልግሎት ድርጅት #EOTCTV  የገለጹት።

በ6ኛ ተራ ቁጥር የነበረው አጀንዳ የኢትዮጵያ ገዳማት ኅብረት ያቀረበውን ጥያቄ በተመለከተ ውይይት የተደረገበት አጀንዳ ነው፡፡  በዚህ አጀንዳ ላይ  የገዳማቱ የሥራ አስፈጻሚ አባላት የሆኑት  አባቶች ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ቀርበው ጥያቄአቸውን በንባብ አሰምተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ገዳምት ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ  ያደረጋቸውን ሥራዎች የሚገልጽ በዚያም በየደረጃው በገዳማት መምሪያና በቋሚ ሲኖዶስ  በተሰጡአቸአቸው የመተዳደሪያ ደንቦች ሥራቸውን እያካሄዱ እንደሆነ ከዚያም ደግሞ የገዳማቱ አባቶች ለተልዕኮና ለተለያዩ ጉዳዮች ወደ አዲስ አበባ በሚመጡበት ጊዜ ማረፊያ ስለሚያስፈልጋቸው ለቅዱስ ሲኖዶስ ባቀረቡት መሠረት ይህን የመሰለውን አጀንዳዎቻቸውን ለቅዱስ ሲኖዶስ በንባብ አሰምተዋል፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስም የአባቶችን  በመስማት  ውይይት በማድረግ ውሳኔ አሳልፏል፡፡  በዚሁ መሠረት በአንደኛ ደረጃ የገዳምቱ ኅበረት ያቀረቡት  ከገዳም ለአገልግሎትና ለተለያየ ተልእኮ  ወደ  አዲስ አበባ ሲመጡ የሚያርፉበት ቦታ ያለውን አስፈላጊነት  ምልዓተ ጉባኤው በመገንዘብ  በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ተመቻችቶ  በዚያ መልስ እንዲሰጣቸውና  በሁለተኛ ደረጃ የገዳማት ኅብረቱ  ለገዳማት ዘላቂ ልማትና ራስን ለመቻል  በልማት ለሚያካሂዷቸው እንቅስቃሴዎች  ጥያቁዎችን የተመለከተ ነው፡፡  ይህንንም ጥያቄ ምልዓተ ጉባኤው በሰፊው በመወያየት  ጉዳዩ ጥናት የሚያስፈልገው፣ የሕግ አስተያየት የሚያስፈልገው በመሆኑ ጥያቄው ለመንበረ ፓትርየርክ ጠቅላይ ቤተክህነት  በቋሚ ሲኖዶስ ክትትል ወደፊት ውሳኔ  ይሰጠዋል በማለት ምልዓተ ጉባኤው ወስኗል፡፡ 

በዛሬው ዕለት በአጀንዳ ቁጥር 5 እና 6  ቅዱስ ሲኖዶስ  ያደረገው ውይይት ይህን ይመስላል፡፡
በቀጣይ በቀሪዎቹ አጀንዳዎች ላይ  ምልዓተ ጉባኤው ውይይቱን የሚቀጥል ይሆናል፡፡
©EOTC TV
1
🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿
እንኳን ለቅዱሳን አባቶቻችን አቡነ አረጋዊ እና ሙሽራው ገብረ ክርስቶስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችኹ አደረሰን።

"ሰላም ለዘሚካኤል ዘተሰምየ አረጋዌ። እስመ ሑረቱ በጥበብ ወፍናዊሁ ልባዌ። ምስሌሁ ኅቡረ ዘበአሐዱ ህላዌ። ሰላም ለቅዱሳን ዘተሰነዓው ስንዓዌ። ከመ በጸሎት ይሥዓሩ ሥርዓቶ ለአርዌ"።

ትርጉም፦
"አረጋዊ ተብሎ የመጠሪያ ስም የወጣለት ለኾነ ለዘሚካኤል ሰላምታ ይገባል፤ አኪያኺያዱ በጥበብና ጐዳናውም በማስተዋል ነውና በጸሎት የአውሬ ዲያብሎስን ሥርዐቱን ይደመስሱ ዘንድ በአንድ አኗኗር ከርሱ ጋር አንድነት ስምምነትን ላደረጉ ለቅዱሳን ሰላምታ ይገባል። "

ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ)


በዚህች ቀን ታላቁና የከበረው አባታችን አቡነ_አረጋዊ (ዘሚካኤል) የተሰወሩበት ዕለት ነው።

እኚህ አባት ከዘጠኙ ቅዱሳን አባቶች አንዱ ሲሆኑ አባታቸው ይስሐቅ የሮም ንጉሥ ነበሩ፡፡ እናታቸው ንግሥት እድና ይባሉ ነበር፡፡

የመጀመሪያ ስማቸው #ዘሚካኤል ነው፡፡ ጥበብ መንፈሳ ሲማሩ አድገው ወደ #እስክንድርያ_ገዳም ገቡ፡፡ አበምኔቱ #አባ_ጳኩሚስ በፈቃደ እግዚአብሔር የመጡ መሆናቸውን አውቀው #መዓረገ_ምንኩስና ሰጥተዋቸዋል፡፡

ዳግመኛም በዚህች ዕለት ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ‹‹ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስን ልከተለው እሔዳለሁ›› በማለት ለክብር የበቃበት ዕለት ነው፡፡


የቅዱስ ገብረ ክርስቶስም ሕይወት እንደ ቅዱስ አባታችን አቡነ አረጋዊ ክርስቶስን የመከተል ሕይወት ነው፡፡ የቊስጥንጥንያ ንጉሥ የሆነው አባቱ ቴዎዶስዮስ እና እናቱ መርኬዛ ከሮም ንጉሥ ልጅ ጋር ቢያጋቡትም ክርስቶስን ለመከተል ከሙሽራ ቤት የወጣ ታላቅ የትሕትና እና የትዕግሥት መምህር ነው፡፡ 

የጻድቃን አባቶቻችን በረከታቸው ይደርብን:: አሜን

🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿
🙏3
የ፻፴፫ኛው የቅዱስ ሲኖዶስ መደበኛ ምልዐተ ጉባኤ የሦስተኛ ቀን ውሎ ውሳኔዎች

💠የአርሲ ሀገረ ስብከት ጉዳይ በመንበረ ፓትርያርክ  ጠቅላይ ቤተ ክህነት አጣሪ ልኡክ ተልኮ  በሪፖርት መሠረት በቋሚ ሲኖዶስ እንዲታይና ውሳኔ እንዲሰጥበት።

💠የሸካ ዞን  ራሱን የቻለ ሀገረ ስብከት ሆኖ እንዲደራጅ ለዚህ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል እንዲመሩና እንዲደራጁ

💠"ገድለ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ" በሚል በአንድ ግለሰብ ተዘጋጀና የተሠራጨ መጽሐፍ  ከኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ትምህርት የወጣ በመሆኑ  ቅዱስ ሲኖዶስ ያወገዘ፤ ስለሆነም  ቤተ ክርስቲያን ለምንም እንዳትጠቀምበት፣  እንዳይሰራጭና  ለማጣቀሻም እንዳያገለግል ተብሎ ተወስኗል።

💠የዩናይትድ ኪንግደም ሀገረ ስብከትን በተመለከተ የክፍሉ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ያዕቆብ በሀገረ ስብከቱ በአካል ተገኝተው መዋቅሩን እንዲያጠናክሩና የአፈጻጸም ሪፖርቱንም ለግንቦት ርእክበ ካህናት እንዲቀርብ ወስኗል።

💠በሰሜን አሜሪካ ካሊፎሪኒያ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት  መንፈሳዊ ኮሌጅ እንዲቋቋምና የአብነት ትምህርት  ማስመስከሪያ እንዲከፈት ቅዱስ ሲኖዶስ ፈቅዷል። የመዋቅራዊ አደረጃጀቱን በተመለከተ አፈጻጸሙ ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት  ትምህርትና ማሰልጠኛ መምሪያ ጋር በመሆን እንዲከወንና ለግንቦቱ ርክበ ካህናት እንዲቀርብ

💠የምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት በግንቦት 15/2017 ዓ/ም በሰጠው ውሳኔ መሠረት  ያለጣልቃ ገብነት  በብፁዕ አቡነ መቃርዮስ  እንዲመራ!

💠ብፁዕ አቡነ አብርሃም የሚመሩት  የኤድመንተንና አካባቢው ተብሎ ይጠራ የነበረው ሀገረ ስብከት  #መካከለኛው ካናዳ ኤድመንተን እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ተብሎ እንዲጠራ ተወስኗል። የዘገባው ምንጭ  Eotc tv ነው
2🙏1
" ተአምር ነው ! "

ተሽከርካሪው 150 ሜትር ርዝማኔ ያለው ገደል ገብቶ አርሶ አደር ግቢ ውስጥ ቢያርፍም ከቀላል ጉዳት ውጪ ያጋጠመ ከባድ ጉዳትና ሞት የለም።

በትግራይ ክልል የሚገኘው የጥንታዊው አቡነ አረጋዊ ገዳም ዝክር በየዓመቱ የአገር ውስጥና ከውጭ የሚመጡ ምእመናን በተገኙነት ጥቅምት 14 ነው የሚከበረው።

ታዲያ " ቶዮታ ሪቮልዩሽን " በሚባለው ተሽከርካሪ ባለቤቱ እራሱን ጨምሮ 5 ሰዎች ጭኖ ዓመታዊው የአቡነ አረጋዊ ገዳም ለመሳለም በመጓዝ ላይ እያለ ተሽከርካሪው መንገድ ስቶ ተንሸራቶ ገደል ይገባል።

ተሽከርካሪው የገባበት ገደል ርዝማኔው 150 ሜትር ነው ብለዋል የአይን እማኞች።

ተሽከርካሪው መንገድ ስቶ ወደ ገደል ከተወረወረ በኃላ በፎቶው እንደሚታየው ወደ አንድ አርሶ አደር ቤት ግቢ ገብቶ ተዘቅዝቆ አርፏል።

ከአስፈሪ ገደል ተወርውሮ በሚታየው መልኩ ያረፈው ተሽከርካሪ በአርሶ አደር ቅጥር ግቢ ከነበሩት ሰዎችና እንስሳት ላይ አንድ ቀላል ጉዳት ከማድረሱ ውጪ የተከሰተ ከባድ ጉዳትና ሞት የለም።

ክስቱቱን ለሰሙት " ተአምር " ያስባለ እንደሆነ የቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ ቤተሰብ አባል ገልጾልናል።

አሽከርካሪዎች ለማሽከርከር በሚያዳግቱና ተዳፋት በሆኑ መንገዶች ላይ ሲያሽከረክሩ እርጋታና ማስተዋል ሊለያቸው አይገባም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
5🙏1