ፍኖተ ወንጌል ሰንበት ት/ቤት
676 subscribers
1.76K photos
16 videos
460 links
በአሰላ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ካቴድራል ፍኖተ ወንጌል ሰንበት ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።

የቴሌግራም ቻናል:-  @Finote_Wongel
የቴሌግራም ግሩፕ:- @FinoteWongel27
የቲክቶክ ገፅ:- https://www.tiktok.com/@finotewongel27
Youtube:- https://www.youtube.com/@Finote_Wongel

©ፍኖተ ወንጌል ሰንበት ት/ቤት
Download Telegram
፦ በእግዚአብሔር ቤት በመቅደሱ ውስጥ እንገናኝ  — ነሀምያ 6፥10
🥰4
የእግዚአብሔር ልጅነት ባገኘንባት ቅጽበት ክርስቲያን የሆንን እኛ  እንደተተከለ ተክል ነንና  በሕይወት መንገዳችን ሁሉ የእግዚአብሔር ቃልና የቤተ ክርስቲያን ድምጽ እየተመገብን የምንፈካ አበባ ነን።

 
9
ማኅሌተ ጽጌ

ክፍል ፩

እንዘ ተሐቅፊዮና ክበበ ጌራ ወርቅ ሲባል

መዞሩ ምሥጢሩ ምንድ ነው?

ማኅሌተ ጽጌ በሚቆምበት ጊዜ “እንዘ ተሐቅፊዮና ክዘበ ጌራ ወርቅ ሲባል የሚዞርበት ምሥጢሩ በጽጌ ማሕሌት ጊዜ የሚባሉ ብዙ ወረቦች ነበሩ ለሥርዓተ ዑደቱ እነዚህ ወረቦች ለምን ተመረጡ ስንል በመጀመሪያ እነዚህ ሁለት ወረቦች ሁሉንም ምሥጢር ያስተባበረ መልእክት ስላላቸው ነው፤

ይኸውም "እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፥ አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፥ ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላሕ፥ ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፥ ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ፡፡"

🌹🌸🌹🌸🌹🌸🌹🌸🌹🌸🌹🌸🌹🌸🌹🌸

ነጭና ቀይ መልክ ያለው አበባ ልጅሽን ይዘሽ ወደ ቤተ መቅደስ #ዕለተ_ንጽሕ ተብሎ በሙሴ እንደተጻፈው በወለድሽ በ፵ ቀን ወደ ቤተ መቅደስ እንደ ገባሽ ርግቤ ሆይ ከኀዘን ታረጋጊኝ ዘንድ ነዪ፤ አዛኝቱ ድንግል ሆይ! ደስተኛ ከሆነው ከገብርኤልና እንደ አንቺ ሩኅሩኅ ከሆነው ከቅዱስ ሚካኤል ጋር ነዪ።»

በማለት ፀዓዳ በመለኮቱ ወቀይሕ በትስብእቱ የሚባል ልጇን ታቅፋ ወደ ቤተ መቅደስ እንደገባች ወደ ልቡናዬ ግቢ ከኀዘኔም አረጋጊኝ ብሎ ይማፀናል።

ሊቁ እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፤

ነጭና ቀይ የኾነ አበባ ልጅሽን ታቅፈሽ ሲል

መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ይዞ ነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በነጭና በቀይ ይመሰላል፡፡ መፍቀሬ ጥበብ ሰሎሞን ከመዝሙራት በሚበልጥ መዝሙሩ ላይ "ወልድ እኁየ ጸዐዳ ወቀይሕ፤ ውዴ ነጭና ቀይ ነው... ከእልፍ የተመረጠ ነው" መሐ 5÷10 ብሎ ከዘመረው መዝሙር ወስዶ ነው፡፡

ይኸውም ነጭ የድል አድራጊነት ምልክት ሲሆን ቀይ የመሥዋዕትነት ምሳሌ ነው፤ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ በከፈለው መሥዋዕትነት አዳምንና ልጆቹን ከሞት ባርነት አድኗል፤ ዲያብሎስንና ሠራዊቱን ድል አድርጓልና፡፡ ነጭ የመለኮቱ ቀይ የትስብእቱ ምሳሌ ነው፡፡ ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተለየ አካሉ ሰው ሆኗልና፡፡

ደስተኛ ከሆነው ከገብርኤል ጋር ነዪ››

ማለቱ ገብርኤል ደስተኛ የሆነው በምን ምክንያት ነው? ያሉ እንደሆነ እርሷን ያበሥር ዘንድ በተላከ ጊዜ ራሱን ከመላአክት መካከል እንደ ዕድለኛ በመቁጠር እጅግ ተደስቶ ነበርና፡፡

ይህንን #ሊቁ_ቅዱስ_ኤፍሬም

"ዐቢይ ውእቱ ክብር ዘተውኅበ ለከ ኦ ገብርኤል መልአክ ዜናዊ ፍሡሐ ገጽ ሰበከ ለነ ልደተ እግዚእ ዘመጽእ ኀቤነ፤ ወአብሠርካ ለማርያም ድንግል ዘእንበለ ርስሐት ወትቤላ ተፈስሒ ኦ ምልዕተ ጸጋ እግዚአብሔር ምስሌኪ::"

ደስተኛ ሆነህ የምሥራችን የተናገርክ መልአኩ ገብርኤል ሆይ ለአንተ የተሰጠህ ክብር ታላቅ ነው፤ ወደ እኛ የመጣ የጌታን ልደቱን ነገርከን ለድንግል ማርያም ጸጋን የተመላሽ ሆይ እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ናውና ደስ ይበልሽ ብለህ አበሠርካት።››   ብሎ ገልጾታል።

ቅዱስ ገብርኤል መጋቤ ብሥራቷ መሆኑ ለእርሱ ትልቅ ክብር ነውና፡፡

እንደ_አንቺ_ርኅሩኅ ከሆነው ከሚካኤል ጋር ነዪ ማለቱ ደግሞ ቅዱስ ሚካኤል #ለሰው_ልጅ_በመራራት ይመስላታልና ነው፡፡

ይቆየን...

ክፍል ፪ን ማታ ከ ፪ሰዓት በኋላ የምንለቅ መሆኑን ከወዲሁ ለመግለጽ እንወዳለን።

💐💐💐💐
8
ማኅሌተ ጽጌ

ክፍል ፪

👉"ክበበ ጌራ ወርቅ" ሲባል መዞሩ ደግሞ ቅዱስ ጊዮርጊስን ስለሚያነሣ ነው፤

ቅዱስ ጊዮርጊስ በኢትዮጵያ ጉዳይ እመቤታችንን ይጋራታልና፤ ይኸውም ኢትዮጵያን ከእመቤታችን ቀጥሎ በዐሥራትነት ተቀብሏታል፡፡ ይኸውም የኢትዮጵያ ገበዝ እስከ መባል አድርሶታል።

ይሀን በሚያስተባብር መልኩ #ሊቁ_እንዲህ_ብሏል

"ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ ዘየሐቱ፥
ዘተጽሐፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፥
አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፥
አንቲ ኵሎ ታሰግዲ ሎቱ፥
ወለኪሰ ይሰግድ ውእቱ::"

"የስሙ ምልክትና የሞቱ መታሰቢያ የተጻፈብሽ ከሚያበራ ወርቅ ይልቅ እንደ ዕንቍ የጠራ ንጽሕና ያለሽ የጊዮርጊስ የመንግሥቱ ሽልማት የአበባ አክሊል ማርያም ሆይ አንቺ ለእርሱ ሁሉን ታሰግጂለታለሽ፣ እርሱም ለአንቺ ይሰግዳል:: " በማለት ዘምሯል።

ሊቃውንቱ ይህን እየወረቡ ቀሳውስቱ የእመቤታችንን ሥዕልና የቅዱስ ጊዮርጊስን ሥዕል ይዘው ይዞራሉ፤

ይኸውም ስደቷን ለማዘከር እንዲሁም የኢትዮጵያን መልክአ ምድር ዞራ መጎብኘቷንና ሀገሪቱን በቃል ኪዳን መረከቧን ለማሰብ ነው፤

የጊዮርጊስ ሥዕል አብሮ መዞሩ ስለሦስት ምክንያት ነው

#የመጀመሪያው-ምክንያት

ከላይ ለመግለጥ እንደተሞከረው እመቤታችን በስደቷ ወራት የኢትዮጵያ ባለአደራ ሆና እንደተሰጠች ቅዱስ ጊዮርጊስም የኢትዮጵያ ጠባቂ ሆኖ ተሰጥቷል፡፡ ስለዚህ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይህንን ጥምር ምሥጢር ለማዘከር የጊዮርጊስን ሥዕል ከእመቤታችን ሥዕል ጋር ይዛ ሥርዓተ ዑደት ታከናውናለች።

#ሁለተኛው_ምክንያት

ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት ሲኾን ሰማዕትነት ደግሞ እሳትና ስለት ብቻ አይደለም፤ ስደትም ሰማዕትነት ነው እሞሙ ለሰማዕት›› የተባለች እመቤታችን ሰማዕትነትን ባርካ ለሰማዕታት አለቃ ለቅዱስ ጊዮርጊስ እንደሰጠችው ለማስረዳት ነው፡፡

#ሦስተኛው_ምክንያት

ቅዱስ ጊዮርጊስ ለእመቤታችን ካለው ልዩ ፍቅርና አክብሮት የተነሣ
‹ደምርኒ ፍልሰትየ ምስለ ፍልሰትኪ ፍልስቴን ከፍስስትሽ ጋር ደምሪልኝ::› ብሎ ተማፅኗት ነበርና፤

ይኸውም አልቀረም የቅዱስ ጊዮርጊስ ፍልሰተ ዐፅሙ እመቤታችን ከሞት ተነሥታ ከመቃብር በፈለሰችበት በነሐሴ ፲፮ ቀን አብሮ ይከበራል፡፡

ይህ ከሥዕሉ ጋር ምን ያገናኘዋል ያልን እንደኾነ

ፍልሰት የሚለው ቃል ብዙ ትርጉም ያለው ቃል ነው፤ ፈለሰ ተሰደደ ተንከራተተ ሀገር ጥሎ ቁርበት ጠቅልሎ ሄደ ማለት ነው ፍልሰቴን ከፍልስትሽ ጋር ደምሪልኝ ማለቱ ስደቴን ከስደትሽ መከራዬን ከመከራሽ ጋር ደምሪልኝ ማለቱ ነው፤

ይህን ምሥጢር የተረዳች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዘመነ ጽጌ የሰማዕቱን መከራና ስደት ከእመቤታችን መከራና ስደት ጋር ታስባለች።

#ባሕረ_ጥበባት_ቅዱስ_ያሬድ -

"አእሚረ ጊዮርጊስ ንጽሐ ሥጋሃ ሊቀ ሰማዕታት ሰገደ ላቲ ወአምኃ ለንግሥተ ሰማይ፤ ወይቤላ ጊዮርጊስ ለማርያም ደምርኒ እም ከመ ኅቡረ ንባዕ ሠናየ ገድለ ተጋደሉ፡፡ "

"የሰማዕታት አለቃ ቅዱስ ጊዮርጊስ ለሰማይ ንግሥት ለእመቤታችን ንጽሕናዋን አውቆ እጅ በመንሣት ሰገደላት ጊዮርጊስ ማርያምን እንዲህ አላት እናት ሆይ በአንድነት እንገባ ዘንድ ከገድል ከትሩፋትሽ አንድ አድርጊኝ አላት፥ መልካም ገድልንም ተጋደለ።»

በማለት ከላይ የተገለጠውን ኀይለ ቃል ይበልጥ አጉልቶ አምልቶ ይነግረናል።

ይቆየን.....

💐💐💐💐
4
"አቅቶት ወደ ቀደመ አኗኗሩ ይመለሳል"
                       ~ ቅዳሴ ማርያም ቁ ፹፮
..........................................................
  የብሕንሳው አባ ሕርያቆስ በቅዳሴ ማርያም ድርሰቱ እንዲህ ብሎ ነበር :- " ይህንንም (አምላክን ስለመጽነስሽ) ባሰብኩ ጊዜ ኅሊናዬ የልጅሽን የባሕሩን ጥልቅነት ሊዋኝ ይወዳል፤ የወዳጅሽ የመሠወሪያው ማዕበልም ያማታዋል። ዳግመኛም ባሰብኩ ጊዜ ኅሊናዬ ተሠውሮ ወደላይ ወጥቶ የሕያው መሠወሪያ የሆነውን ሊገልጥ ይወዳል ። ከነደ እሳትነቱ የተነሣ ይፈራል፣ ከዐየራት ከእርቧቸው እርቦ አይደርስም ። ይህንንም ባሰብኩ ጊዜ ኅሊናዬ በነፋስ ትከሻ ተጭኖ በምሥራቅና በምዕራብ በሰሜንና በደቡብ በዳርቻዎችም ሁሉ ሊበር ይወዳል ። የፍጡራንን አኗኗር ያይ ዘንድ የአብሕርትንም ጥልቅነታቸውን ይለካ ዘንድ የሰማይን ርዝመቱን ያውቅ ዘንድ በሁሉ ዘንድ በሁሉም ይዞራል ። አቅቶት ወደ ቀደመ አኗኗሩ ይመለሳል።"

  እመቤቴ ሆይ እኔም እኮ የልጅሽን ቸርነት፣ ደግነት፣ ርኅራኄውን ባሰብኩ ጊዜ ኅሊናዬ ኃጢአቴን በንስሐ አራግፎ በልጅሽ የፍቅር ባሕር ውስጥ ሊዋኝ ይወዳል። ግን ምን ዋጋ አለው? የኃጢአት ፍቅር ገና ከልቡናዬ አልተነቀለምና የፍትወቴ ማዕበል ወደ ቀደመ አኗኗሩ ያማታዋል። ዳግመኛም የልጅሽ ይቅር ባይነቱ፣ እንደ በደሌ ብዛት እኔን ያልቀሰፈበት ትዕግሥቱ እያስደነቀኝ እግረ ኅሊናዬ ኃጢአቴን ይናዘዝ ዘንድ ወደ ልጅሽ ሹማምንቶች ካህናት ሊበር ይወዳል። ከአንድ ካህን ፊት ኃጢአቱን ተናግሮ ራሱን ለማዋረድ ግን ከትዕቢቱ የተነሳ ይፈራል። አቅቶትም ወደ ቀደመ የኃጢአት አኗኗሩ ይመለሳል።

  ማርያም ሆይ፤ ዳግመኛም ኅሊናዬን በኃጢአቴ ከልጅሽ ተለይቼ የኖርኩበት ዘመን በቁጭት ዕረፍት ነስቶት በንስሐ ወደ ልጅሽ ዕቅፍ ለመግባት ይናፍቃል። የቀረ ሕይወቴን በጽድቅ ልጅሽን እያስደሰትኩ እኖር ዘንድ፣ የልጅሽን የትህትናውን ጥልቅነት እየለካሁ፣ የምሕረቱን ስፋት አውቅ ዘንድ ኅሊናዬ በሁሉ ዘንድ በሁሉም ይዞራል። ግን አቅቶት ወደ ቀደመ አኗኗሩ ይመለሳል።

  እመብርሃን ሆይ ይህ ብቻ መሰለሽ? ኃጢአት ልሰራ በተዘጋጀሁ ጊዜ በኅሊናዬ የልጅሽ መስቀል ይታሰበኛል። ልጅሽን ከመበደል ያድኑኝ ዘንድ በምሥራቅ እና በምዕራብ፣ በሰሜንና በደቡብ፣ በዳርቻዎች ሁሉ ያሉ ቅዱሳንን አፌ ይጠራቸዋል። የልጅሽ የወዳጅሽ ፍቅር ግን በልቤ አልጸናምና አካሌ አቅቶት ወደ ቀደመ ኃጢአቱ ክፉኛ ወድቆ ይመለሳል።

  "እስመ ተነድፈ ልብየ በፍቅርኪ ፤ ልቤ በፍቅርሽ ተነድፏልና" ብዬ ስንቴ እያዜምኩ ሰዓታት ቆሜልሽ ነበር። እንደ አባ ጊዮርጊስ እኮ እኔም ልቤ በአንቺ ፍቅር ይሰወር ዘንድ፣ በልጅሽ ቃልኪዳን በተሰጠኝ እናትነትሽ ይከለል ዘንድ እልፍ ጊዜ ደጅ ይጠናል። ግን ምን ዋጋ አለው? የክፋቴ፣ የበደሌ ብዛት ከንጽሕናሽ እርቦ አያደርሰኝም።

  እመአምላክ ሆይ አሁንም ኅሊናዬ የልጅሽን ሕግ በቀን እና በሌሊት ያነብ ዘንድ፣ ኃያላንን በሚያጸናቸው በልጅሽ ቃል ልቤ ይታነጽ ዘንድ ቅዱሳት መጻሕፍትን ሊገልጥ ይወዳል፣ በልጅሽ ቃል መሰረት መኖር አቅቶት ግን ወደ ቀደመ አኗኗሩ ይመለሳል። ዳግመኛም ኅሊናዬ የቅዱሳንን አኗኗር አይቶ የእግዚአብሔርን ቃል በተግባር የነገሩትን ዋኖቹን ያስብ ዘንድ፣ የኑሮአቸውን ፍሬ እያየሁ በእምነት እመስላቸው ዘንድ በገድላቸው እና በድርሳናቸው ትከሻ ተጭኖ ይዞራል። ቅዱሳንን መምሰል አቅቶት ግን "እንደሚጠፉ እንስሶች" ወደመምሰሉ ይመለሳል። ዕብ 13፥7 ፣ መዝ 48 ፥ 12

  ድንግል ሆይ፣ አሁንም ሰውነቴ ልጅሽ ይቅር ብሎኝ ወደረሳው ኃጢአቴ እንዳይመለስ የጾም ጸሎት፣ ስግደት ትሩፋትን አብዝቶ ሊፈጽም ይወዳል። አላደርገውም ብሎ የተገዘተበትን ኃጢአት ግን አቅቶት ወደ ትፋቱ እንደሚመለስ ውሻ ተመልሶ ይጨማለቅበታል። እመቤቴ ሆይ፣ ዳግመኛም ኅሊናዬ ያንቺን ቅንጣት ንጽሕና ገንዘብ ያደርግ ዘንድ፣ ልቤም ካንቺ የማይወሰን ርኅራሄሽ ተካፍሎ የልጅሽ ማደሪያ ይሆን ዘንድ ይወዳል። ግን አቅቶት ባንቺ ንጽሕና ልክ በኃጢአት ወደ መቆሸሹ ይመለሳል።

  ድንግል ሆይ መልሺኝ እኔም እመለሳለሁ። ወደ ቀደመ የኃጢአት አኗኗሬ አይደለም፤ ወደ ቀደመ ጥቂት ጽድቄ እንጂ! ወደ ቀደመ በደሌ አይደለም፣ ወደ ቀደመ ቅንጣት ንጽሕናዬ እንጂ። ወደ ቀደመ ድካሜ አይደለም፣ ወደ ቀደመ በልጅሽ ኃይል ወደበረታሁበት ማንነቴ እንጂ! አቅቶኝ ወደ ምመለስበት ኃጢአት ሳይሆን ተመልሼ ወደምነሳበት ጽድቅ መልሺኝ!

  ድንግል ሆይ ልጅሽ መሐሪ ይባል ዘንድ "ለጻድቃን ያይደለ ለኃጥአን አሳስቢ፣ ለንጹሐን ያይደለ ለተዳደፉት አሳስቢ።" ቅዱስ ዲዮስቆሮስ በቅዳሴው ልጅሽን እንዲህ ይለዋልና :- "ጻድቃንን ግን ከሥራቸው የተነሳ ትምራቸዋለህ፣ እንደ ጽድቃቸውም ትሰጣቸዋለህ፤ እኛን ኃጥአንን ብትምረን ያን ጊዜ መሐሪ ትባላለህና።"

..........................................
ዲያቆን ዮሐንስ
4
🍂🍂🍂🍂

ምጽዋት ብዛት ወይስ ጥራት?

የማትፈልገውን ሳይሆን ለአንተ ምርጥ የምትለውን መስጠት ልመድ። የአገልግሎት ዘመኑን የጨረሰ ልብስ፣ ለመመገብ አስቸጋሪ የሆነ፣ የሻገተ ወይንም የደረቀ ምግብ መስጠት የተለመደ በሆነበት ዘመን ላይ ስላለህ የምታደርገውን ሁሉ ተጠንቅቀህ አድርግ።

🍂
አንተ የማትለብሰው ስለማይለበስልህ ነው። የማትበላው በጤናህ ላይ ችግር ስለሚያስከትልብህ ነው፤ ታድያ ለወንድምህስ የምትሰጠው ለሕመም የሚዳርገውን ነውን? መሆን የለበትም። ይልቁንም ለወንድምህ ከምትበላው አካፍለው። ከምትለብሳቸው ሁለቱ ልብሶች አንዱን ስጠው። የሚጎዳውን ብዙ ነገር ከምትሰጠው የሚጠቅም ትንሽ ነገር ስጠው። ለአንተ የምትመኝውን ጥራት ለወንድምህም አድርግ። "እውነት እላችኋለሁ ከሁሉም ከሚያንሱት ከነዚህ ወንድሞቼ ያደረጋችሁት ለኔ አደረጋችሁት" ማቴ 25፥40 ያለውን ቃል መለስ ብለህ አስብና የምትሰጠውን ጎጂ ነገር ለክርስቶስ እንደምትሰጠው ተረዳ።

🍂
አቤልና ቃየል ለእግዚአብሔር ያቀረቡት መሥዋእት እንዴት እንደነበረ አሰብ። "አቤልም ደግሞ ከበጎቹ በኩራትን ከስቡ አቀረበ። እግዚአብሔርም ወደ አቤልና ወደ መሥዋእቱ ተመለከተ።"ዘፍ 4፥4 ለምን መረጠለት? ብትል አቤል ካለው ሁሉ መርጦ የተሻለውን ለእግዚአብሔር መስዋዕት አድርጎ ስላቀረበ ነው። በሐዋርያት ሥራ 4፥34-35 ላይ ሰፍሮ የሚገኝውን የሐዋርያቱ ሕይወት ምን ይመስል እንደነበረ የሚናገረውን ቃል አስተውለህ አንብበውና የአንተ ምጽዋት የአንተ ሥጦታ የትኛው ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ራስህን ጠይቅ።

"
እውነት እላችኋለሁ ከሁሉም ከሚያንሱት ከነዚህ ወንድሞቼ ያደረጋችሁት ለኔ አደረጋችሁት" ማቴ 25፥40

  
ብጹዕ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

🍂🍂🍂🍂
👏3😁1
"ከንቱ ውዳሴ በመንገድ ሁሉ የሚከተልህ የተሸሸገና ጭንብል ያጠለቀ ሌባ ነው። አሳዳጅ በመሆኑ በጣም ደኅንነት በሚሰማህ አሳቻ ሰዓት ሳታውቀው ይዘርፈሀል፤ ይገድልህማል። "

ቅዱስ ጎርጎርዮስ
ካህናት ዲያቆናትን መስቀል ሲያሳልሙ "በረከተ እስጢፋኖስ ይኅደር በላዕሌከ ፣ የቅዱስ እስጢፋኖስ በረከት በላይህ ይደር" ይላሉ። ይህች በረከት መብል ለማሰናዳት ብትሾምም ቃለ እግዚአብሔርን በጸጋ እና በሞገስ ወደ ማስተማር የተሻገገረች፣ ክርስትናን በአንድ ቦታ ብቻ ይጸና ዘንድ ብትሰየምም፣ በውግረተ አእባን ክርስቲያኖችን በትና ወንጌልን በዓለም ሁሉ ያዳረሰች በረከት ናት።

  የቅዱስ እስጢፋኖስ በረከት አይሁድ ሊቃወሟት ስለማይችሉ ላለመሰማት ጆሮአቸውን የሚደፍኑባት፣ የሐሰት ክስ ማዕበል ቢወርድባትም በቅዱሱ ፊት ከፀሐይ ሰባት እጅ የምታበራ፣ በድንጋይ ወግረው ሊያስቀሯት ቢሞክሩም ከድንጋዩ ዝናብ አሻግራ ቅድስት ሥላሴን አይታ የመንፈስ ቅዱስን መውረድ ፈጽማ የምታደንቅ በረከት ናት።

  እኛም በረከተ እስጢፋኖስን ተስፋ እና ኃይል በማድረግ ሰማዕቱ በዕሪና ባያቸው በአብ፣ በወልድ፣ በመንፈስ ቅዱስ ስም አምነን ክቡር የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል መማር ማስተማር እንጀምራለን። ንዑድ ክቡር የሚሆን የሰማዕታት መጀመሪያ ቅዱስ እስጢፋኖስንም እንዘክራለን።

  ጥቅምት 17/2018 ዓ.ም ቅዱስ እስጢፋኖስ በተሰየመበት ዓመታዊ ክብረ በዓሉ ነው። ስለሆነም በአሰላ ደ/መ/መ/ዓ/ካቴድራል በዓለ ንግሱ በድምቀት ይከበራል።

ኑ አብረን እናንግስ🙏
6🥰5👍1🕊1
የጥቅምት ቅዱስ ሲኖዶስ  የመክፈቻ  ጸሎት።
5
"ዳዊት በቀንም በማዕልትም ሕጉን የሚያነብ ብጹዕ ነው ብሏልና ፡፡ በጎዳናም ቢሆን ፤ በቤትም ቢሆን ፤ ስትተኛም ቢሆን ፤ ከእርሱ ይቅርታንና ቸርነትን ታገኝ ዘንድ ፤ ፈጣርህ እግዚአብሔርን በፍፅም ህሊናህ ፤ በፍፅም አእምሮህ ፤ በፍጹም ልቦናህ ፤ ውደደው" !! ።

       መፅሐፈ ዲዲስቅልያ
7
የእስጢፋኖስ መንገድ

ለእውነት እስከ ሞት መታመን።
እኒህ ድንጋይ ያነሡትኮ አላዋቂነታቸው ሸፍኗቸው እንጂ ዘለዓለማዊ ሕይወት የሚገኝበትን ትምህርት የሚነግራቸውን ሰው አይገድሉትም ነበር።

ብንችል እንደ ቅዱስ እስጢፋኖስ እንሁን። አርአያ እናድርገው። ባንችል ግን ቢያንስ ዘለዓለማዊ የሕይወት ትምህርት በሚያስተምሩን ላይ ድንጋይ አናንሳ።

ድንጋይ ለእስጢፋኖስ የሰማዕትነትን ክብር ያገኘበት ሲሆን፣ ድንጋይ ላነሡት ደግሞ የሕይወት ትምህርትን የሚነግራቸውን ሰው ያጡበት ነው።

የንግግራችን፣ የሐሳባችን፣ የድርጊታችን ማዕከል ዘለዓለማዊው ሕይወት ይሁን። እውነት ሐሳባችን ወይም ንግግራችን ወይም እያንዳንዱ ተግባራችን ወደ ዘለዓለማዊው ሕይወት ለምናደርገው ጉዞ ግብአት ይሆናል??! ራስን ቆም ብሎ መመርመር ይገባል።

የሰማዕቱ በረከት ይደርብን

ጥቅምት 17/2018 ዓ.ም የሰማዕቱ በዓለ ንግስ በአሰላ ደ/መ/መ/ዓ/ካቴድራል በድምቀት ይከበራል።

ኑ አብረን እናንግስ!
🙏31
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ የመጀመሪያ ቀን ውሎው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውሳኔ ሰጠ።
(ጥቅምት ፲፪ ቀን ፩፻፲፰ ዓ.ም)

የቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤትን በመወከል መግለጫውን የሰጡት መምህር ዳንኤል ሰይፈሚካኤል  ጉባዔው በመጀመሪያውን ቀን ጉባዔው ፲፮ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ማጽደቁን ገልጸዋል።
በጠዋቱ ውሎ  ፯ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን አጀንዳ እንዲቀርጹ ውሳኔ ያሳለፈ ሲሆን እነዚህም ሊቃነ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ፣ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ፣ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ፣ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል፣ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ፣ ብፁዕ አቡነ ሩፋኤልና ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ናቸው ፡፡ ኮሚቴው በብፁዕ አቡነ ጎርጎሬዎስ በሰብሳቢነት በብፁዕ አቡነ ዲዎስቆሮስ በአስረጂነት ተሰብስቧል።
ምልዓተ ጉባኤው በከሰዓቱ ውሎም ከ፲፮ቱ አጀንዳዎች በ፬ቱ ላይ ውሳኔ የሰጠ መስጠቱን ለመገናኛ ብዙኃን ድርጅት ያስታወቀ ሲሆን እነዚህም ውሳኔዎች

፩- ቅዱስነታቸው በጠዋቱ የመክፈቻ ጸሎት ያስተላለፉት መልዕክት
በቀጣይ የሥራ መመሪያ አድርጎ ምልዓተ ጉባዔው አጽድቋል፡፡
፪-ከጥቅምት ፬-፲ በነበረው የሰበካ መንፈሳዊ ዓለም ዓቀፍ ጉባኤ የነበሩ የቡድን ውይይቶች በቃለ ጉባኤ ቀርቦ ቃለ ጉባዔውን ምልዓተ ጉባዔው የ፳፻፲፰ ዓ.ም የሥራ መመሪያ አድርጎ አፅድቋል፡፡

፫-ሀገራዊ ሰላምን አስመልክቶ ምልዓተ ጉባዔው በግንቦት ተወያይቶ ሊቃነ ጳጳሳትን የያዘ ኮሚቴ ያዋቀረ ሲሆን ኮሚቴው የተሰጠውን ኃላፊነት አጠንክሮ እንዲቀጥል ተወያይቶ አጽድቋል፡፡

፬-በትግራይ የተፈጠረው ወቅታዊ ክፍፍልን አስመልክቶ የተወያየ ሲሆን በውይይቱም ህዝቡ ህዝባችን አብያተ ክርስቲያናቱም የቤተክርስቲያን ሀብት እንደመሆናቸው ቀደም ብሎ የተዋቀረው የሰላም ኮሚቴ ሥራውን አጠንክሮ እንዲቀጥል በምልዓተ ጉባኤው ወስኗል።

©ኢኦተቤ
5
" የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር ፈቃዴ ነው፤ ስለ ከንፈሮችህ ቃል ጭንቅ የሆኑ መንገዶችን ጠበቅሁ።"
    
        መዝሙረ ዳዊት 17: 4
🙏2