Relationships
7.96K subscribers
31 photos
1 file
9 links
በቅርቡ የፍቅር ነክ ጽሁፎች ውድድር


@fikir_yishalegnal

👉የፍቅር ደብዳቤ ለመጻፍ
👉የልደት መልካም ምኞት
👉የፍቅር ጥቅሶች
👉ሌሎችም

እኛን ለማግኘት

❇️ @mer677_bot









.











.



















.
Download Telegram
Audio
መሰማት ያለበት ምርጥ ሙዚቃ

ከሰማችሁ በኃላ #Share አድርጉ🙏🙏
9 ወር አርገዛ ስንት ዓመት አጥበታ
ሳዝን እያዘነች ስስቅ እየሳቀች ይኸዉ
ዉለታሽን ልከፍል ብነሳ ያንቺ ፍቅር እጅጉን ከበደኝ ዘለአለም ብለፋ ፍቅርሽ በልጦ ታየኝ ዉዷ እናቴ ከስኬቴ ጀርባ
ያለሽዉ አንቺ ነሽ እምዬ ቃላት አጣሁልሽ
ስምሽን ስጠራዉ ጭንቄ ይለቀኛል መጭዉ አመት 2⃣0⃣1⃣1⃣ የሰላም የጤና ይሁንልሽ ከማንም እና ከምንም በላይ እወድሻለሁ

🤵ከ -- 9 ወር የተሸከምሽዉ ልጅሽ
👩 ለ - ዉዷ እናቴ
አስቲ 💝Like 💝like 💝share 💝share
💚💛❤️ 💚💛❤️
ሰላም የRelationships ቤተሰቦች ቻናላችን ሰኞ ሀምሌ 30/2010 አንደኛ አመቱን ያከብራል፡፡
በመሆኑም ልዩ 💘 የፍቅር ሳምንት 💘መሰናዶዎችን አዘጋጅተናል፡፡
በዚህ ሳምንት
የጠበሳ ዘዴዎች
በፍቅር ውስጥ የሚነሱ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
የፍቅር ደብዳቤዎችና
የፍቅር ታሪኮች
የይቅርታ ደብዳቤዎች ይቀርባሉ፡፡

በተጨማሪም ከሰኞ ጀምሮ
💝በፌስቡክ እና
💝በYouTube ዝግጅቶቻችን ወደ እናንተ ማስተላለፍ እንጀምራለን፡፡
#share
@fikir_yishalegnal
@fikir_yishalegnal
ያላችሁን የፍቅር ታሪክ ወደ @mer677 ላኩልን፡፡ ብዙ like ለሚያገኘው ሽልማት አለው፡፡
#share
@fikir_yishalegnal
በተጨማሪም ያላችሁን
💌የፍቅር ደብዳቤ፣
✉️የይቅርታ ደብዳቤ እና
🎉የመልካም ልደት ምኞት ወደ @mer677 ላኩልን፡፡
#share
@fikir_yishalegnal
💖💖💖💖ዉድ የቻናላችን ተከታዮች ቻናላችን ዛሬ አንደኛ አመት የምስረታ በዓሉን እያከበረ ይገኛል።
ይህን በማስመልከት ሳምንቱን በሙሉ እናንተን ይጠቅማሉ እና ያዝናናሉ ያልናቸውን የተለያዩ ፍቅር ነክ ጽሁፎችን ወደ እናንተ እናስተላልፋለን።
🌹🌹🌹
በቻናላችን ላይ እንዲተላለፍ የምትፈልጉትን
🌷የፍቅር ታሪክ፣
🌷 የፍቅር ደብዳቤ
🌷 የመልካም ልደት ምኞት ወይም
🌷ካነበባችሁት ልታጋሩን የምትፈልጉት ነገር ካላቹ ወደ
@mer677
@kal143 ብትልኩልን በደስታ እናስተላልፋለን።
🥇🥇🥇
እንዲሁም ቻናላችን እዚህ ለማድረስ መልዕክቶቻችን ለሌሎች በማጋራት እና በአስተያየት ለደገፋችሁን በሙሉ ምስጋናችን በያላችሁበት ይድረሳችሁ ብለናል።
ወደፊትም ቻናላችን ከዚ የተሻለ እንዲሰራ አስተያየታችሁ አይለየን። የቻናላችን ተደራሽነት ለመጨመርም መልዕክቶቻችን ለጓደኞቻችሁ በማጋራት እርዱን። ሁላችሁንም እናከብራችኋለን፣እንወዳችኋለን፣ እናመሰግናለን።
💓💓💓💓💓💓
በፍቅር እንኑር
💓💓💓💓💓💓
@fikir_yishalegnal
@fikir_yishalegnal
@fikir_yishalegnal
#share
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Channel photo updated

ተራርቆ ፍቅር ዉጤታማ ይሆን?

ከአንድ የቻናላችን ተከታይ የደረሰን ጥያቄ ነው።
💖💖💖💖💖
በእርግጥ ፍቅራችሁ ወደ ተሻለ ምዕራፍ የመሸጋገር እድል ይኖረዋል። ይሁንና ተራርቆ ፍቅር እንደመሆኑ መጠን ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮችን ከወዲሁ በመገንዘብ በተቻለ መጠን ለማስወገድ ጥረት ማድረግ ይኖርባችኋል። እንደሚታወቀው ለቀናትና ለወራት ተነፋፍቆ መገናኘት አጓጊና አስደሳች የመሆኑን ያህል አደጋወችም አሉት ምክንያቱም ተነፋፍቃችሁ ከርማችሁ ስትገናኙ ጉጉታችሁ ሁሉ ለመተያየት እንጅ የፍቅር ግንኙነታችሁን በአትኩሮት ለማስተዋል አይሆንም። ይህ ተራርቆ የሚመሰረት የፍቅር ግንኙነት በአጠቃላይ ሶስት ችግሮች አሉበት።

💓💓💓💓
1 የፍቅረኛችን ትክክለኛ ባህሪና ማንነት ለማወቅ ይከብደናል፡ ከፍቅረኛችን ጋር ለምሳሌ ለ3 ቀናት አብረን ብናሳልፍ በእነዚ ቀናት በተቻለን አቅም በውስጣችን የሌለንን ጨምረን ጥሩ ባህሪ ነው ለማሳየት የምንሞክረው፤ መቼም አስቸጋሪ ባህሪዎቻችን ለ72 ሰዓታት መደበቅ አያቅተነም። ይህ ደግሞ እርስ በእርስ እንዳንተዋወቅ ትልቅ እንቅፋት የሚሆንብን ነገር ነው። ጓደኛችን ለማወቅ ትንሽ ጨነቅነቅ ሲል...ለምሳሌ ችግር ሲገጥመው፣ ሲፈራ፣ ሲታመም...ወዘተ ነው ማየት ያለብን። በእነዚህ ጊዜያት ትክክለኛ ባህርያቱ ይገለጣሉና።

💓💓💓💓💓
2 ችግሮችን ከመጋፈጥ ይልቅ ችላ ማለት እና መሸሽ ይታያል።
በእንዲህ አይነቱ ግንኙነት ዉስጥ ችግር ሲከሰት፣ በጋራ የመጋፈጡ ነገር እምብዛም አይስተዋልም። ለምሳሌ ከፍቅረኛህ ጋር በተለያያቹ በሁለት ወራችሁ ተገናኝታችሁ እራት እየበላችሁ እሷ ድንገት አንድ የሚያናድድ ነገር ነገር ትናገራለች እንበል።ታዲያ አንተ ለዚህ ምላሽ ሰጥተህና ሁኔታውን ተጋፍጠህ ምሽቱንና በቀሪ ቀናት የሚኖራችሁን ጣፋጭ ጊዜ ታበላሻለህ ወይስ ዝም ትላለህ? ብዙዎች ለጊዜው ስሜታቸው እንዳይጎዳ የሚመርጡት ዝምታን ነው። ይህ ዝምታ ሁለታችሁ በጋራ ችግሮቻችሁን መፍታት እንዳትማሩ እና ግንኙነታችሁን ጥልቅ ወደሆነ የመግባባት እና የመጣጣም ደረጃ እንዳታሳድጉ እንቅፋት ይሆንባችኋል። እነዚህ ያልተፈቱ ችግሮችና ያላወጣናቸው የተለያዩ ስሜቶች ደግሞ አንድ ቀን የሚፈነዱ ፈንጅዎች/emotional time bomb/ ናቸው። የፍቅር ግንኙነታችሁ ላይ ላይውን ጤናማ ቢመስልም ማንኛውም ጤናማ የፍቅር ግንኙነት ሊያልፍ የሚገቡትን ደረጃዎች እንዲያልፍ አልፈቀዳችሁለትም።

💓💓💓💓💓
3 በውስጣችን ከእውነታው የራቀ ምስል ይቀረጻል።
ከፍቅረኛችሁ ጋር በምታሳልፉት ሁለትም ሆነ ሶስት ቀናት ዉስጥ ምናልባት ወደ ተለያዩ ምግብ ቤቶችበመሄድ የመረጣችሁትን ምግብ ትመጋባላችሁ። ወደ ሲኒማ፣ትያትር፣ጭፈራ ቤት ...የተለያዩ መዝናኛ ቦታዎች በመሄድ ደስታን በየ አይነቱ ትሸምታላቹ።ሁሉም ሲሰለቻቹ ደግሞ ወደ ያዛችሁት ክፍል ገብታችሁ አንዳችሁ በሌላኛችሁ ዉስጥ በፍቅር ትቀልጣላችሁ። ጓደኛ የለ፣ቤተሰብ የለ ዘመድ የለ...ሁለታችሁ ብቻ! ይህ ግን ስለ ግንኙነታችሁ ሆነ ወደፊት በጋራ ስለሚኖራችሁ ህይዎት የተሳሳተ መረጃ ነው የሚሰጣችሁ። እንደውም ኮ ከፍቅር ጓደኛችሁ ይልቅ መዝናናቱ ይበልጥ ሊያስደስታቹህ ይችላል። ለዚህ ነው ብዙ ጥንዶች አብረው መኖር ሲጀመሩ ማኩረፍና ማጉረምረም የሚጀምሩት።”እንዲህ ኮ አልመሰለኝም” ማለት የሚመጣው። እውነታው ግን ይሄ ነው። ትዳር ወይም አብሮ መኖር ማለት የአንድ ወይም የሁለት ቀናት ፓርቲ ሳይሆን የዘወትር አብሮነት ነው።
💝💝💝
በአጭሩ በተለያየ ስፍራዎች ሆነው በፍቅር ግንኑነት ዉስጥ ያሉ ጥንዶች ፍቅራቸውን ወደ ጤናማና ዘላቂ ግንኙነት ለማሸጋገር አብረው መኖር ይገባቸዋል። ይህ ሲሆን ብቻ ነው አንዳቸውከሌላኛቸው ጋር አብረው የሚሄዱ መሆናቸውን በትክክል ማስተዋል የሚጀምሩት።ሆኖም በአንድ ጣራ ስርመኖር እስኪጀምሩ ድረስ ባሉበት ሆነው የሚከተሉትን ጠቃሚ ምክሮች ተግባር ላይ ቢያውሉት ጥሩ ዉጤት ሊያገኙበት ይችላሉ።

💝💝💝💝
1 በምትገናኙበት ወቅት ሁሉንም ነገር የበዓል ድግስ አታስመስሉት። በመጠነኛ ወጭ የተለመዱና ከእለት ተእለት ኑሯችሁ ጋር ተቀራራቢ የሆኑ ነገሮችን ብቻ አድርጉ።

💝💝💝💝
2 አስቸጋሪ የስብዕናችሁ ክፍሎችንና እውነተያ ባህሪያችሁን ከጓደኛችሁ አትደብቁ። በተቻለ መጠን ራሳችሁን ለመሆን ሞክሩ።

💝💝💝
3 እውነተኛ ስሜታችሁን አትደብቁ። ግጭቶች ሲፈጠሩም ወዲያው በመጋፈጥ ለማስወገድ ሞክሩ።

💝💝💝💝
በፍቅር እንኑር
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
@fikir_yishalegnal
@fikir_yishalegnal
@fikir_yishalegnal
🌷🌷🌷🌷🌷
#share
የእናንተንም ጥያቄዎች እዚህ ላይ @mer677
@kal143
ላኩልን እናስተናግዳለን እየተቀበልን እናስተናግዳለን፡፡
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለካ አዝኖ ኖሯል

አንቺ ስትወለጅ ያወረደው ዶፉን፡
በደመና ጋርዶ ያጨገገው ቀኑን፡
ውሽንፍሩን ለቆ ያሸበረው ህዝቡን፡
ዛሬ ምን ሆነክ ነው ብለው ቀና ብዬ፡
ልዕልቴን ነጠቁኝ አለኝ በእዬዬ፡
ለካ እንዲ ያረገው ሰማይን ያስቆጣው፡
ወደ ምድር ስትመጪ ስትወለጂ ነው፡
እናም ልንገርሻ ዛሬ ነች ያቺ እለት፡
ሰማይም አልቅሶ እዬዬ ያለባት፡
እውነትም ድንቅ ነሽ ፈረድኩ ያየሁሽ ቀን፡
ማንባትም አነሰው ሰማይ አጥቶ አንቺን፡
ፍዝዝ ብዬ ቀረው አንቺን ያየው ለታ፡
ውብትሽ ገዳይ ነው ተማረከች ነፍሴ እጇን ላንቺ ሰታ፡
በጣም ነው ምታምሪው እንደ ጊዮርጊስ እናት እንደ ቲዮቢስታ፡
እንኳንም ተወለድሽ እንኳንም መነደግሽ፡
እግዜሩ ይመስገን ለዚ ያደረሰሽ፡
መልካም ይሁንልሽ ልደትሽ ያማረ፡
የሚታወስ እንጂ አይሁን የነበረ፡
አንቺ ስትወለጅ ዘንቧል ብለው ያሉሽ፡
ሰማይ ሲያለቅስ ነው አንቺኑ ስላጣሽ፡
እኔ ምኞቴ እንዲያምር ልደትሽ፡፡

Lechannelachen Relationship ke admin Rich de habeshan gal😘😘
Andega ametachenen mekeniyat bemadereg❤️🎂🎂
መስሪያ ቤታችን ሚ.ፈ.ወ (ሚስት ፈላጊ ወንዶች) ኢንተርፕራይዝ ከዚህ በታች የተመለከተዉን የስራ መደብ ሰራተኞችን አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል።

የስራ መደቡ መጠሪያ --- ጀማሪ ሚ.የ.ሴ (ሚስት የምትሆን ሴት)

ተፈላጊ ችሎታ

ለሚስትነት የሚያስፈልጉ ቅመሞች ያሏትና መልካም ባህሪ ያላት፡፡ከዚህ በፊት በ ሚ.የ.ሴ የስራ ዘርፍ ከሌላ ከማንኛዉም ወንድ የተግባር ልምምድ ያላወሰደች፡፡እራሷን ለማስተዳደር የባል እጅ የማትጠብቅና ቅንቅን የሆኑ ባህሪያት ያልተጠናወቷት(በየደቂቃዉ አዛ የማታደርግና ባሏን በማንኛዉም ነገር የምትደግፍ)የአመት ባል ጊዜ ዶሮ ለመስራት ፎርሙላ ከእናቷ ፈጽሞ የማትጠይቅና የዶሮን 12 ብልት በልታ ለማሳየት ፈቃደኛ የሆነች እንዲሁም በተመሳሳይ ስራ ባለሙያ የሆነች ብትሆን ይመረጣል
የትምህርት ደረጃ

ቢያንስ እስከ 8ተኛ ክፍል የተማረችና እራሷን ለማሻሻል የምትጥር ነገር ግን ‹‹ተምሪያለሁ ካሁን በኋላ ምን አባክ ልታመጣ!›› እያለች ባሏን የማታስፈራራና የስነልቦና ቀዉስ የማታስከትል፡፡የፍቅር ዲግሪ እዉቅና ከሌላቸዉ ተቋማት ማለትም ከፌስቡክ ፣ትዊተር፣ዋትስአፕ፣ቫይበር፣ኢሞ፣ታንጎና የመሳሰሉት ትምህርቷን ያልተከታተለች፡፡
የስራ ቦታ

ባሏ በሄደበት ቦታ አብራ የምትሄድና በጋራ የስራ ቦታዉን ለመወሰን ፈቃደኛ የሆነች(የስራዉ ቦታ ከቤተሰቦቻችን አቅራቢያ ይሁን፣እማዬን ለማን ጥዬ አባዬ በሳምንት ሁለት ቀን እዚህ ይምጣ ምናምን ለሚሉ ሚየሴዎች መስሪያ ቤቱ በፍፁም እዉቅናን አይሰጥም..አይቀበልምም!)
ደመወዝ

-የባሏን ደሞዝ 80 ፐርሰንት ወደ እኔ አካዉንት ካልገባ ወይ እኔ ወይ አንተ! ብላ ባሏን ቁም ስቅሉን የማታሳይና በፍቅርና በመተማመን ያላቸዉን ተካፍለዉ እንደሚኖሩ የምታምን፡፡

አመልካቾች ኦሪጅናል ማንነታችሁን ከማይመለስ ኮፒ ጋር በማያያዝ መስሪያ ቤቱ ድረስ በአካል በመቅረብ በፍቅር እንኑር ህንጻ ሶስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 1 ማመልከት ትችላላችሁ፡፡ኮፒ ማንነታችሁን ብቻ ማምጣት ከውድድሩ ስለሚያሰርዝ ሚየሴዎች ጠንቀቅ በሉ!
ቁጥራቸዉ በእጅጉ ቢመናመንም ድንግል ሚየሴዎች በስራዉ እንዲሳተፉ ይበረታታሉ!

ማሳሰቢያ-- ሴት ሁሉ ሚ.የ.ሴ ሊሆን ስለማይችል ‹ለድስት ግጣሙ አይታጣም› ብላችሁ ለማመልከት የምትመጡ አመልካቾች እባካችሁ አርፋችሁ ተቀመጡ!
@fikir_yishalegnal
❤️ፍቅር ማለት ውዴ ❤️

ፍቅር ማለት ውዴ ፨
የህልሙ ዘራችን የዕውን ፍሬ አፍርቶ ፤
ቆንጅየ ልጅ ወልደን...
እሱም ፍቅር ሊማር አንደበት አውጥቶ ፤
ፍቅር ማለት.... እማ? ብሎ ቢጠይቅሽ ፤
ይህንን ንገሪው ሳትፈሪ ሳይጨንቅሽ ፤
........"ፍቅር ማለት ልጀ........
የተራ ሆሄያት ባዶ ጥርቃሚ ፤
የሶስት ፊደል ጥምረት የቀል ልቅምቃሚ ፤
የደቂቃ ስሜት.......
ወይ ጊዜያዊ ጥቅም አይደለም ምስጢሩ ፤
መስጠት+መስጠት +መሰጠት .....በቃ ሁሌም መስጠት
እናም ልጀ ይህ ነው የፍቅር ቀመሩ ፤...."
ብለሽ ንገሪልኝ እንዲገባው አርገሽ ፤
ፍቅርን ሠጥቶ .....
ምላሽ እንዳይጠብቅ በደንብ አስጠንቅቀሽ ፤
...........ደግሞም እንዲህ በይው.........
......ፍቅር ማለት ልጀ...
በአንዲት ውብ ማሳ ውስጥ..
ከአረም ከቁጥቋጦ ፈፅሞ በራቀች ፤
ከአንድ ገበሬ እጅ..
በፅናት ተዘርታ በዕምነት የበቀለች ፤
........... .............ፍቅር ቡቃያ ነች ፤
የአለምን ሃይሎች አጣምሮ ያደላት ፤
የተንኮል ገሞራ .....
የሃሜት አውሎ ንፋስ ገፍትሮ ማይጥላት ፤
ገንዘብ ጎርፍ ሆኖ.....
ስሯን ቢያጥለቀልቅ ፈፅሞ ማይነቅላት ፤
ፍቅር ቡቃያ ናት..........."
......ብለሽ ንገሪልኝ....
ግን ይህን ሁሉ ቃል ከአንደበትሽ ሰምቶ ፤
....ፍቅር ማለት እማ ????
ብሎ ከጠየቀሽ ሳይረዳው ቀርቶ ፤
....ይህንን ንገሪው
"ገበሬው አምላክ ነው ማሳዋ ልባችን ፤
ዘሩ የፍቅር ቃል ቡቃያው ልጃችን ፤"
እንዲያውም እንዲያውም....
ከተራ ቃላት ጋር ምን አፈታተነን ፤
ፍቅር ማለት ውዴ!!!! በቃ እኔና አንች ነን ።

❤️ ፍቅር በፍቅር የሆነ ግጥም ነው አይደል እስኪ እንደኔ ፎንቃ የገባለት ለምትወዷት share እ ጀለሶች።

@fikir_yishalegnal
@fikir_yishalegnal
Share and join
From Yibe to Kidu
Forwarded from 💸 HABESHA TECH & AIRDROP 💵 (哈里什)
#ሆኜ _አይናፋር ወጣት መናገር ያቃተው፣
ስገባ ስወጣ ስለአንቺ አስባለው፣
ለካስ እንዲም አለ አወይ መሸነፍ፣
በአንድ ቀን ትውውቅ ወድጄሽ ክንፍ፣
በህልሜም በእውኔም አንቺው ነሽ በሀሳቤ፣
ትመላለሻለሽ አላረፈም ልቤ.....ልቤ፣
👇👇 #ሼር
https://youtu.be/4UwEIpi7y2I
Forwarded from Deleted Account
……..(¯•.•´¯) (¯•.•´¯)
……..*•.¸(¯•.•´¯)¸.•´
…☆ º •.¸.•´ º ☆.¸¸.•´¯
………!!!нαρρу вιятн∂αу!!!……
እንኳን ተወለድክልን
Fm Mrd to Dave

❤️ love
🙏 HBD
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from 💸 HABESHA TECH & AIRDROP 💵 (Habtish)
Promoted By #Hab Promotion ከዚህ በፊት ነይ ነይልኝ የተሰኘ ስራ አድርሶናል አሁን ደግሞ አዲስ ለየት ያለውን #ሆኜ_አይናፋር የተሰኘ አዲስ ቪድዮ ክሊፕ ይዞልን መቷል ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ተጋበዙልኝ 👇👇👇

https://youtu.be/4UwEIpi7y2I
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌼🌼🌼እንኳን ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ በሰላም አሸጋገራቹ 🌼🌼🌼@Fikir_Yishalegnal አባላት ለመላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ
አዲሱ አመት የሰላም የፍቅር የመደመር እንዲሆንላቹ እንመኛለን🌼🌼🌼


@Fikir_Yishalegnal
@Fikir_Yishalegnal
Ur #1 Choice 🎼
የFacebook ፔጃችን ነው Like በማድረግ አባል ሁኑ
👇👇👇👇👇

https://www.facebook.com/Salsa-Promotion-957894047730521/