ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል
1.78K subscribers
55 photos
2 videos
1 file
332 links
........ኑ
ስሜትን በግጥም እንግለፅ
ትውልድን በጥበብ እናንፅ ።

የፍቅር ቤት እዚህ ነው !
አሰተያየት ካላችሁ
👇
@fikee12 ላይ ማድረስ ይቻላል
Download Telegram
fikee@21
<unknown>
ፍቃዱ ግርማ

ማነው ??
t.me/fikee21
👍5
ፍቃዱ ግርማ
.
.
.
ዝም ብለሽ ስሚኝ ልንገርሽ የሆዴን
ባንቺ የሆንኩትን እንድታውቂው ጉዴን
ደብተሩን ስገልጠው እየመጣሽ በአይኔ
እኔ ላንቺ ባዶ አንቺ ለኔ ቅኔ
እየሆንሽ ( *2 ) ብዙ ብዙ ታዓምር
ትምህርቴን ትቻለሁ ፍቅርሽን ስቀምር ።


t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍3
ፍቃዱ ግርማ

''' አንቺዬ ''

ሳቅሽ ለብቻውን መንፈስን ያረካል
ጨዋታሽ ሲሰማ ሙታንን ያነቃል
መላ አካልሽ ሁሉ ደስታን የተሞላ
አይንሽ ነፀብራቅ ነው ለአንደበትሽ ጥላ
ሀገሬው ስላንቺ ሁል ግዜ ያዜማል
አላፊ አግዳሚው አንቺኑ ያወራል
ደሞ ...
ደሞ አረማማድሽ የፀጉርሽ ዘለላ
አንቺን ያስወድዳል ሌላ እያስጠላ
ምን ላርገው እንግዲህ ?
እንዴት ላርገው ከቶ
ያስለፈልፈኛል ፍቅርሽ ቃል አውጥቶ ።


t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍1
ፍቃዱ ግርማ

'' ጎበዝ ''

አንዱ አንዱን ሳይበልጠው ሰው በመሆን
ልኬት
ብንኖር በሰላም አንከብድም ለመሬት ።


t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍2
ፍቃዱ ግርማ

ጥላቻ የሞላበት የሹክሹክታ መንድር
እገሌና እገሌን ከማጣላት በቀር
አላመጣም ዋንጫ አላየንም ኖቤል
ከማስገደል ወጪ አቤልን በቃኤል ።

........
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍5
'' ይገርመኛል ''

ፍቃዱ ግርማ

አንዴ ገብተሽ ከመዳፌ
ተጠልለሽ ከእቅፌ
ላያገኙሽ እየለፉ
ድካም ብቻ ሆነ ትርፉ ።

........
t.ne/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍3
ፍቃዱ ግርማ

ወርቅ አልማዝ ቢሞላ ፣
ቢትረፈረፍ ቤቱ
ፍቅር የሌለ እለት ፣
ሁሉም ነገር ከንቱ ።

.......
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍3
ፍቃዱ ግርማ

ጨፈርን እንደ ጉድ ደነስን እስኪበቃን
ደቂቃ ከሰዓት ሳንዘል አንዲት ቀን
በለፀግን አልን ልብሳችንን ጥለን
መዝናናቱን አልነው መንገዱ መች በቃን
ደግሞ ምላሳችን የልምዳችን ሱሱ
ዘምነናል ሆኗል ለጥያቄው መልሱ ።
ግን .....
እወነት ዘምነናል ?

.......
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍3
ፍቃዱ ግርማ

ጥላቻ አውሮሽ መንገድሽ ሲጠፋ
የጥፋትሽ ወሰን እያደር ሲሰፋ
ሀይ የሚልሽ ሸንጎ ዳኛ ስለጠፋ
ተኩሶ ጥሎ ቁም ሆነ ያንቺ ተስፋ ።

ይገርማል 😌


t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍1
ገብረ ክርስቶስ ደስታ

መነሻ ስእል

አያልቅም ይህ ጉዞ ........
ማስመሰል - መተርጎም
በቀለም መዋኘት
በመስመር መዋኝት
ከብርሃን መጋጨት
ለማወቅ ለመፍጠር ባዶ ቦታ መግባት ።
መፈለግ ... ... .. መፈለግ . . .
አዲስ ነገር መፍጠር
ከማይታየው ጋር ሄዶ መነጋገር ።
ህይወትን መጠየቅ
ሃሳብን መጠየቅ
አለምን መጠየቅ
መሄድ መሄድ መሄድ . . . .
ከጨረቃ በላይ
ከኮኮቦች በላይ
ከሰማዩ በላይ ።
መጎዝ ወደ ሌላ ባዶ ቦታ መግባት
በሃሳብ መደበቅ ፡
መፈለግ ማስገኘት ።
አያልቅም ይህ ጉዞ ......

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
ፍቃዱ ግርማ

'' አንቺዬ ''

ፍቅር እያጠፋሽ ጥላቻሽ በርክቶ
መቆም የቃተሽ ለት ከአንድ ስፍራ ረግቶ
ዘመቻሽ ከበዛ ጊዜ ገደብ አጥቶ
ጦር አዝምት መሆንሽ የሚያውቅልሽ ሁሉ
አንቺን በመረዳት የገባቸው ውሉ
እብድ ናት ከማላት ሌላ ምን ይበሉ ። ?

ምንም ...

......
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
እሳት ወይ አበባ

ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን

ወንድ ብቻውን ነው እሚያለቅስ

ከወዳጅ ዘመድ ርቆ
አንጀቱን በአንጀቱ ታጥቆ
ተሸሸጎ ተገልሎ ፥ ተሸማቆ ተሸምቆ
ከቤተ - ሰው ተደብቆ
መሽቶ የማታ ማታ ነው ፥ ሌት ነው የወንድ
ልጅ እንባው
ብቻውን ነው የሚፈታው .......
ብቻውን ነው የሚረታው .......
ችሎ ፥ ወጦ ፥ ተጨብጦ ፥ ተማምጦ
ተጣጥሮ
በሲቃ ግት ተወጥሮ
እንደ ደመና ተቋጥሮ
እውስጥ አንጀቱ ተቀብሮ ....
መሽቶ ፥ ረፍዶ ፥ ጀምበር ጠልቆ
የጨለማ ድባብ ወድቆ
በእንቅልፍ ጥላ ሲከበብ ፥ በዝምታ
ሲዋጥ አገር
ፍጡር ሁሉ ተሰለምልሞ ፥ ብቸኝነት
ብቻ ሲቀር ......
የኃላ የኃላ ማታ
ምድር አገሩ በእፎይታ
አይኑን በእንቅልፍ ሲያስፈታ
ሁሉ በእረፍት ዓለም ርቆ ፥ ብቸኝነት
ብቻ ሲቀርብ
ያኔ ነው ወንድ አይኑ የሚረጥብ
የብቻ ፥ እንባ አይኑ የሚረጥብ ።
.......................

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍4
ፍቃዱ ግርማ

አያድርስ ከቶ

እማታገኝውን ሺህ ግዜ መናፈቅ
ለማይሆነው ነገር ሺህ ግዜ መጨነቅ
እራስክን ከማጣት ምንም አታተርፍም
ዝብርቅርቅ ባለበት በዚህ ከንቱ አለም
አይጣልብህ እንጂ አያድርስ ከቶ
በዚች አለም ኑሮ ማንስ ያቃል ረክቶ ። ?

ማንም
.......
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍4
ፍቃዱ ግርማ

ጥላቻ

በፍቅር እንዳልደመቅን ፈክተን እንደ አበባ
ደግነትም ጠፍታ ጥላቻ እኛን ቀርባ
ተለያዩ ብትል መሪር በሆነ ቃል
ቃልህ ቃልኪዳኔ እንዴት ብሎ ያልቃል
ጥላቻ የሚሏት እኛ ሀገር ገብታ
ታየቺኝ ስትመጣ ክፋትን ጎትታ
እናማ ወንድሜ ክንድህን አበርታ
ጥላቻ ለሚሏት መቼም አትረታ ።

አይዞህ እንበርታ !

........
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍2
አባቴ ማረኝ

ምፅዋቴ ሁሉ ሆነ በብርሃን
ከጠፉት በጎችህ እኔ አንዱ አሆን ??

አላውቅም ።

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
ፍቃዱ ግርማ

እስትንፋስን እፍ ብለህ ሰው አረከኝ
ከትቢያ ለይ
ተመስገን ነው የኔ ምላሽ ከምድር
እስኪ ሰማይ
ብወድቅ እንኳን ሆነህ ምርኩዝ
አነሳሃኝ እኔ ልጅህ እንድጎብዝ
ሰርክ ሁሌ እረኛዬ
አየሆንከኝ ሀይል ብርታት መፅናኛዬ
ለችግሬ መሻገሪያ
አንተ እኮ ነህ መነፅሬ ሁሉን ማያ
ምንም እንኳን እኔ ከንቱ እየሆንኩኝ
ባሰቸግርም
እኔን ምንም ርካሽ ምንም ለመፈወስ
አትሰለችም ።

......
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
3
እናት
ፍቅር
ሐገር


አሌክስ አብረሃም

/ ከንፈር ግን ሲገርም / !

እኔ የምልሽ ወዴ ፣
የጀነት በር ማለት ከንፈርሽ ነው እንዴ ?

ምን አባቴ ልበል.......!
ስትሰሚኝ ግዜ
ፊቴ የነበረው ፎከታም ግርግዳ ዬት አባቱ
ሄደ ?
ወስጤ የተገነባው የጭንቀት ባቢሎን
ከመኔው ተናደ !
ስትስሚኝ ግዜ
በህሊናዬ ወስጥ ያንን ሁሉ አበባ
ማን ተክሎት በቀለ !
ይሄስ ሁሉ ደስታ
ከዬት ተጠራርቶ ወስጤ ተቆለለ ?

ተፈጥሮን ገልብጦ እናቴን በጥብጦ ፣
ፀሐይን በምዕራብ አወጣት ከንፈርሽ ፣

መገን አሳሳምሽ !!

ብትስሚኝ ግዜ
ዝሆኖች በረሩ
እባቦች ጋለቡ ፣
በባዶ ልቤ ወስጥ
እልፍ ሰርጎች ገቡ ........

እናት ፡ ፍቅር ፡ ሐገር
አሌክስ አብራሃም

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍2
ፍቃዱ ግርማ

ጮህን .... ጮህን
ኡ......ኡ .....
አጣን እንጂ አንድም ሰሚ
መንገዱ እየጠፋን እያጣን ጠቋሚ
አለቀስን .......... ስቅስቅ አለን
ለፋን ዳከረን..... ተንከራተትን
ሄድን ሄድን ወጣን ወረድን
አኪያሀዱ ጉዞው ጠፍቶን
ምንም አጣን
ምንም ምንም
ነገሩ ሁሉ አለብን ጥምም ።
.
.
.
.
.
.
እኛም አለን ዝም !

.......
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍1
ፍቃዱ ግርማ

አገኝሁ የልቤን መሻት
እንደ ነብሴ የምወዳት
እንደ ብሌን ምሳሳላት
እስትንፋስ ናት የምወዳት ።
ማመስገኛ ዜማ ቃሌ
አገኘሁ ተዋህዳ ከአካሌ
ሰመረልኝ ደሟ ደሜ
ፈውስ ሆነች ለህመሜ
በህይወቴ ሆናኝ ብርታት
ወጣሁባት ስንት አቀበት ።

........
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍1