ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል
1.78K subscribers
55 photos
2 videos
1 file
332 links
........ኑ
ስሜትን በግጥም እንግለፅ
ትውልድን በጥበብ እናንፅ ።

የፍቅር ቤት እዚህ ነው !
አሰተያየት ካላችሁ
👇
@fikee12 ላይ ማድረስ ይቻላል
Download Telegram
ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን

'' ፈራን ''

ፍቅርን ፈራን
እንዳልተዛመድን
እንዳልተዋለድን
ፈርተን መዋደድን
ጉርብትናን ናድን
እኛ ማለት ትተን
እኔነትን ለመድን ።

ክብር ለሎሬቱ ለዘመን ተሻጋሪ ስራው
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

join
👇
t.me/fikee21
👍5
'' ሂጂ ''

ፍቃዱ ግርማ

ያውልሽ ጎዳናው ክፍት ነው መንገዱ
ፍቅርን ጥሎ መሄድ ስላረግሺው ጀብዱ
ይቅናሽ ብዬሻለሁ ይሳካልሽ ሁሉም
መቼም ላፈቀሩት ገላ ምርቃት አይገድም
ጎጆሽ ሙሉ ይሁን ሁል ግዜ ፋሲጋ
ኑሮሽ ይደላደል ይሁን አልጋ በአልጋ
ሰላም ፡ ተስፋ ፡ ፍቅር ይትረፍረፍ በቤትሽ
የወደድሺው ገላ አብዝቶ ይመችሽ
እንግዲህ አንቺዬ ሸኝሁሽ መርቄ
ከኔ እንደሁ ጨረስን የለሽም ጥያቄ ። ?

join
👇
t.me/fikee21
ፍቃዱ ግርማ

እንዴት ግን ........

እያሰከፉ መኖር የወደደን ገላ
ላንቺ የቆመን ሰው እየሆነ ጥላ
ነብሱን ለሸጠልሽ ዋጋ ለከፈለ
መልሱ እንደዚ ነበር ማህተብሽ ዬት አለ ?
እስኪ ልጠይቅሽ መልሺልኝ አንቺም
ብልጭልጭ ነች ከንቱ አላልኩም አለም
ለግዜው አስቂ አታላይ ናት በጣም
ለስጋ ነው እንጂ ለነብስ አትስማማም
ብዬ አልነገርኩሽም
አትሂጂ ብዬ አልተማፀንኩሽም
ምን ላርግሽ እንግዲህ ፣
ወይ አትመረምሪ
ወይ አትመከሪ
አፍቃሪሽ አዝኖብሽ ባርባር ሲለው ሆዱ
አንቺ ፈጣን ነሽ ሌላ ለመልመዱ ።

Join
👇
t.me/fikee21
👍3
fikee@21
<unknown>
ፍቃዱ ግርማ

ማነው ??
t.me/fikee21
👍5
ፍቃዱ ግርማ
.
.
.
ዝም ብለሽ ስሚኝ ልንገርሽ የሆዴን
ባንቺ የሆንኩትን እንድታውቂው ጉዴን
ደብተሩን ስገልጠው እየመጣሽ በአይኔ
እኔ ላንቺ ባዶ አንቺ ለኔ ቅኔ
እየሆንሽ ( *2 ) ብዙ ብዙ ታዓምር
ትምህርቴን ትቻለሁ ፍቅርሽን ስቀምር ።


t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍3
ፍቃዱ ግርማ

''' አንቺዬ ''

ሳቅሽ ለብቻውን መንፈስን ያረካል
ጨዋታሽ ሲሰማ ሙታንን ያነቃል
መላ አካልሽ ሁሉ ደስታን የተሞላ
አይንሽ ነፀብራቅ ነው ለአንደበትሽ ጥላ
ሀገሬው ስላንቺ ሁል ግዜ ያዜማል
አላፊ አግዳሚው አንቺኑ ያወራል
ደሞ ...
ደሞ አረማማድሽ የፀጉርሽ ዘለላ
አንቺን ያስወድዳል ሌላ እያስጠላ
ምን ላርገው እንግዲህ ?
እንዴት ላርገው ከቶ
ያስለፈልፈኛል ፍቅርሽ ቃል አውጥቶ ።


t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍1
ፍቃዱ ግርማ

'' ጎበዝ ''

አንዱ አንዱን ሳይበልጠው ሰው በመሆን
ልኬት
ብንኖር በሰላም አንከብድም ለመሬት ።


t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍2
ፍቃዱ ግርማ

ጥላቻ የሞላበት የሹክሹክታ መንድር
እገሌና እገሌን ከማጣላት በቀር
አላመጣም ዋንጫ አላየንም ኖቤል
ከማስገደል ወጪ አቤልን በቃኤል ።

........
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍5
'' ይገርመኛል ''

ፍቃዱ ግርማ

አንዴ ገብተሽ ከመዳፌ
ተጠልለሽ ከእቅፌ
ላያገኙሽ እየለፉ
ድካም ብቻ ሆነ ትርፉ ።

........
t.ne/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍3
ፍቃዱ ግርማ

ወርቅ አልማዝ ቢሞላ ፣
ቢትረፈረፍ ቤቱ
ፍቅር የሌለ እለት ፣
ሁሉም ነገር ከንቱ ።

.......
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍3
ፍቃዱ ግርማ

ጨፈርን እንደ ጉድ ደነስን እስኪበቃን
ደቂቃ ከሰዓት ሳንዘል አንዲት ቀን
በለፀግን አልን ልብሳችንን ጥለን
መዝናናቱን አልነው መንገዱ መች በቃን
ደግሞ ምላሳችን የልምዳችን ሱሱ
ዘምነናል ሆኗል ለጥያቄው መልሱ ።
ግን .....
እወነት ዘምነናል ?

.......
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍3
ፍቃዱ ግርማ

ጥላቻ አውሮሽ መንገድሽ ሲጠፋ
የጥፋትሽ ወሰን እያደር ሲሰፋ
ሀይ የሚልሽ ሸንጎ ዳኛ ስለጠፋ
ተኩሶ ጥሎ ቁም ሆነ ያንቺ ተስፋ ።

ይገርማል 😌


t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍1
ገብረ ክርስቶስ ደስታ

መነሻ ስእል

አያልቅም ይህ ጉዞ ........
ማስመሰል - መተርጎም
በቀለም መዋኘት
በመስመር መዋኝት
ከብርሃን መጋጨት
ለማወቅ ለመፍጠር ባዶ ቦታ መግባት ።
መፈለግ ... ... .. መፈለግ . . .
አዲስ ነገር መፍጠር
ከማይታየው ጋር ሄዶ መነጋገር ።
ህይወትን መጠየቅ
ሃሳብን መጠየቅ
አለምን መጠየቅ
መሄድ መሄድ መሄድ . . . .
ከጨረቃ በላይ
ከኮኮቦች በላይ
ከሰማዩ በላይ ።
መጎዝ ወደ ሌላ ባዶ ቦታ መግባት
በሃሳብ መደበቅ ፡
መፈለግ ማስገኘት ።
አያልቅም ይህ ጉዞ ......

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
ፍቃዱ ግርማ

'' አንቺዬ ''

ፍቅር እያጠፋሽ ጥላቻሽ በርክቶ
መቆም የቃተሽ ለት ከአንድ ስፍራ ረግቶ
ዘመቻሽ ከበዛ ጊዜ ገደብ አጥቶ
ጦር አዝምት መሆንሽ የሚያውቅልሽ ሁሉ
አንቺን በመረዳት የገባቸው ውሉ
እብድ ናት ከማላት ሌላ ምን ይበሉ ። ?

ምንም ...

......
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
እሳት ወይ አበባ

ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን

ወንድ ብቻውን ነው እሚያለቅስ

ከወዳጅ ዘመድ ርቆ
አንጀቱን በአንጀቱ ታጥቆ
ተሸሸጎ ተገልሎ ፥ ተሸማቆ ተሸምቆ
ከቤተ - ሰው ተደብቆ
መሽቶ የማታ ማታ ነው ፥ ሌት ነው የወንድ
ልጅ እንባው
ብቻውን ነው የሚፈታው .......
ብቻውን ነው የሚረታው .......
ችሎ ፥ ወጦ ፥ ተጨብጦ ፥ ተማምጦ
ተጣጥሮ
በሲቃ ግት ተወጥሮ
እንደ ደመና ተቋጥሮ
እውስጥ አንጀቱ ተቀብሮ ....
መሽቶ ፥ ረፍዶ ፥ ጀምበር ጠልቆ
የጨለማ ድባብ ወድቆ
በእንቅልፍ ጥላ ሲከበብ ፥ በዝምታ
ሲዋጥ አገር
ፍጡር ሁሉ ተሰለምልሞ ፥ ብቸኝነት
ብቻ ሲቀር ......
የኃላ የኃላ ማታ
ምድር አገሩ በእፎይታ
አይኑን በእንቅልፍ ሲያስፈታ
ሁሉ በእረፍት ዓለም ርቆ ፥ ብቸኝነት
ብቻ ሲቀርብ
ያኔ ነው ወንድ አይኑ የሚረጥብ
የብቻ ፥ እንባ አይኑ የሚረጥብ ።
.......................

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍4
ፍቃዱ ግርማ

አያድርስ ከቶ

እማታገኝውን ሺህ ግዜ መናፈቅ
ለማይሆነው ነገር ሺህ ግዜ መጨነቅ
እራስክን ከማጣት ምንም አታተርፍም
ዝብርቅርቅ ባለበት በዚህ ከንቱ አለም
አይጣልብህ እንጂ አያድርስ ከቶ
በዚች አለም ኑሮ ማንስ ያቃል ረክቶ ። ?

ማንም
.......
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍4
ፍቃዱ ግርማ

ጥላቻ

በፍቅር እንዳልደመቅን ፈክተን እንደ አበባ
ደግነትም ጠፍታ ጥላቻ እኛን ቀርባ
ተለያዩ ብትል መሪር በሆነ ቃል
ቃልህ ቃልኪዳኔ እንዴት ብሎ ያልቃል
ጥላቻ የሚሏት እኛ ሀገር ገብታ
ታየቺኝ ስትመጣ ክፋትን ጎትታ
እናማ ወንድሜ ክንድህን አበርታ
ጥላቻ ለሚሏት መቼም አትረታ ።

አይዞህ እንበርታ !

........
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍2
አባቴ ማረኝ

ምፅዋቴ ሁሉ ሆነ በብርሃን
ከጠፉት በጎችህ እኔ አንዱ አሆን ??

አላውቅም ።

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
ፍቃዱ ግርማ

እስትንፋስን እፍ ብለህ ሰው አረከኝ
ከትቢያ ለይ
ተመስገን ነው የኔ ምላሽ ከምድር
እስኪ ሰማይ
ብወድቅ እንኳን ሆነህ ምርኩዝ
አነሳሃኝ እኔ ልጅህ እንድጎብዝ
ሰርክ ሁሌ እረኛዬ
አየሆንከኝ ሀይል ብርታት መፅናኛዬ
ለችግሬ መሻገሪያ
አንተ እኮ ነህ መነፅሬ ሁሉን ማያ
ምንም እንኳን እኔ ከንቱ እየሆንኩኝ
ባሰቸግርም
እኔን ምንም ርካሽ ምንም ለመፈወስ
አትሰለችም ።

......
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
3