ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል
1.78K subscribers
55 photos
2 videos
1 file
334 links
........ኑ
ስሜትን በግጥም እንግለፅ
ትውልድን በጥበብ እናንፅ ።

የፍቅር ቤት እዚህ ነው !
አሰተያየት ካላችሁ
👇
@fikee12 ላይ ማድረስ ይቻላል
Download Telegram
አሁን .....አሁንስ
ዐሥርቱ ትዕዛዝ ፤ ነብሴን እንደገባት
አንቺን ዐሥር ግዜ ፤ እየፈቱ ማግባት ።

( መሰለኝ )

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን
t.me/fikee21
👍1
ሰው በመሆን ስሌት

[ ፍቃዱ ግርማ ]

ሰው በመሆን ስሌት አንዱ አንዱን ካረዳ
ህይወት አትገፋም አበሳ ናት ፊዳ
ቀመሩ ቢወጣ ቢሰራ ስሌቱ
ያንዱ ለአንዱ መኖር ነበር መሰረቱ ።
Join
👇
t.me/fikee21
ተይ ..........ግን

[ ፍቃዱ ግርማ ]

ፍቅር በሶስት ፊደል በቀለም ቢቀየጥ
አነሰ መስሎሽ ነው ?
አጠረ መስሎሽ ነው ?
ተይ.......
ተይ እንደዛ አደለም ፣
ፍቅር ቃል ኪዳን ነው ፤ ፍፁም የልብ ጌጥ
ሁሌም ለእውነት ሟች ፤ አንገቱን የሚሰጥ ።
join
👇
t.me/fikee21
ምነው ዛሬ ደግሞ ...?

[ ፍቃዱ ግርማ ]

ሆዴን ባርባር አለው ልቤም ተሸበረ
ምነው አንደበቴ ፣
ካንቺ መገናኛ ቀናትን ቆጠረ
ሰዓትን ብገፋው ቀናትን ብዘለው
ደስ ይለኝ ነበር አይንሽን እንዳየው
ግን አልቻልኩም እቴ ፣
መናፈቅ ብቻ ነው እኔን የተቸረኝ
አምላክ ሰላም ያርግሽ እስከምንገናኝ
እቅፍ ድግፍ አርጎ ያክርምሽ በሰላም
መቼም የኔ ናፍቆት ዳር ድንበር የለውም ።

ብቻ ሰላም ክረሚለኝ እቴ
እማ

join
👇
t.me/fikee21
👍4
fikee21
<unknown>
ፍቃዱ ግርማ

እወዳታለሁ

t.me/fikee21
👍61
ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን

ይኼው...
ነፍስ... ያለ ወገብ ይደንሳል ፤
አቧራምም... ያለግር ይነሳል ።
እኔ
ያላንቺ ነገሬ ፤ በሙሉ ባይሰምር
ከነፋስ ፤ ከአቧራ ፣ አነሰሁልሽ የምር ።
አንድ ነገር ከላ ፤ ያላንቺ የምችለው
አሁን የሆንኩትን ፤ መሆንን ብቻ ነው ።
.
.
.
አሁን እንደምን ነኝ ?
join
👇
t.me/fikee21
👍1
ትዝታ
<unknown>
ፍቃዱ ግርማ 🎤

t.me/fikee21
አንቺ .....
ፍቃዱ ግርማ

አንቺ ብታዝኚብኝ
..... ብትቀየሚብኝ
ብታኮርፊ ግዜ
ምስቅልቅል ሆኖብኝ ፣
ሳቄ ከኔ ጠፍቶ አለሁ በትካዜ ።
ተይ ታረቂኝ ?

t.me/fikee21
👍3
በዓሉ ግርማ

እንባ እንባ ይለኛል
ይተናነቀኛል
ግን እንባ ከዬት አባቱ
ደርቋል ከረጢቱ
ሳቅ ሳቅም ይለኛል
ስቆ ላይስቅ ጥርሴ
ስቃ እያለቀሰች መከረኛ ነብሴ ።

join
👇
t.me/fikee21
👍5
ሌሬት ፀጋዬ ገ/መድህን

ይቅር ብቻ አንናገርም
እኔና አንቺ እንወያይም
ለውይይት አልታደልንም
እንዲያው ዝም እንጂ ዝም .... ዝም ።
አበባ እንሆን ወይም እሳት
ተጠምደን በምኞት ቅጣት
ሰመመን በጫረው መአት
እድሜአችንን እንዳማጥናት......
እሳት እንሆን ወይ አበባ
በሕቅ - እንቅ ስንባባ
ባከነች ልጅነታችን ፥ እየቃተትን ስናነባ ።...........

Please join
👇
t.me/fikee21
👍1
ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን

የማይነጋ ሕልም ሳልም
የማያድግ ችግኝ ሳርም
የማይድን በሽታ ሳክም
የሰው ሕይወት ስከረክም
እኔ ለእኔ ኖሬ አላውቅም ።

please join
👇
t.me/fikee21
[ ውዴ ]

ፍቃዱ ግርማ

ከጋራው ባሻገር አይኔ እያማተረ
ናፍቆት ትዝታዬ እያደር ጨመረ
ያ ሃያሉ ፍቅር ልቤን እያመሰው
ጣፋጭ አንደበትሸ ውስጤን አላወሰው ።

አልቻልኩም !
please join
👇
t.me/fikee21
👍2
አሞኛል

ፍቃዱ ግርማ

እራሴን ወገቤን ብዬም አልናገር
ጤናዬን ነስቶኛል የዘንድሮ ነገር
እንዴት አትዪኝም ፣
ጠምቶኛል ስላቸው ውሃዬን ሲደፉ
ርቦኛል ብላቸው ስንዴውን ሸጡና ፍሪዳ ከተፉ
ደግሞ አይጣል ነው እኮ ፣
ምላስ እንደ መክሊት ስለታደላቸው
እኛ ብንጮህም መስሚያ መች አላቸው ።

ለዚህ ነው ያመመኝ

join
👇
t.me/fikee21
2
እሷ
ፍቃዱ ግርማ

በደም ግባቷ ልብ የምትሰርቅ
ከሁሉም ቆንጆ የምትደነቅ
ከሀሳቤ እንኳን አንዴም የማትርቅ
ትዝታዬ ናት የምትናፈቅ
የደስታዬ ምንጭ የሳቄ ጥጉ
እሷ ናት በቃ ፣
የህይወቴ ልክ የፍቅሬ ወጉ ።

join
👇
t.me/fikee21
ፍቃዱ ግርማ

መድሃኒአለም ( 27 )

ሳገንህ እኖራለሁ እድሜ ዘላለሜን
መባህን ስቀበል እያልኩ አሜን አሜን
አምላኬ ጌታዬ ስለሆንኩኝ ከንቱ
ማረኝ የኔ አባት ሳያልፍ ሰዓቱ ።

join
👇
t.me/fikee21
👍8
ፍቃዱ ግርማ
.
.
.

የልቤ ለይ ንቅሳት
በዘመኔ የማልረሳት
የውስጤ ታላቅ ስስት
በምን ፊደል ልከትባት
በምን ተውኔት ልተወናት
በምን ጥበብ ልመስላት
በምን ድርሰት ልደርድራት
እሷ እንደሆን ፣
ድንቅ ነች ....
የምትበልጥብኝ አለም ለይ ካለው ፈጥረት ።

join
👇
t.me/fikee21
ፍቃዱ ግርማ

ሌላ ሰው አልወቅስም ከራሴ ነው ክሴ
ስቆ እያስለቀሰኝ መከረኛው ጥርሴ
እያደባደበ ሲያጣላኝ ከራሴ
ሁሉ ወዳጅ መስሎት ፣
ይሞግት ጀመረ ከምሰኪኗ ነብሴ ።

join
👇
t.me/fikee21
ፍቃዱ ግርማ

ናፈቅሺኝ

ትዝታዬ የልጅነቴ ውበት
ኬየት ነው ያለሺው አንቺ ቆንጆ ያረፈሺበት
እኮ ዬት ?
ብፈልግሽ ባስፈልግሽ በሀገሩ
በድዬሽም ቢሆን ነይ ልበልሽ እሹሩሩ
በይ ነይ !
አልገረፍ በትዝታሽ በናፍቆትሽ አልቀጣ
ላፈቀረ ገላ አይደለም ጨዋታ ይናፍቃል ቁጣ
እኮ ነይ ?
አይንሽ ከአይኔ ይገጣጠም
እንሳሳም ትቅና ደግሞ እቺ አለም
ነይ ?
ነይ ልቀፍሽ አንቺም ሁኚኝ ደና ምርኩዝ
ተስፋዬንም አለምልሚው ፣
ባንቺ ፍቅር እንድጎብዝ ።
ነይ

join
👇
t.me/fikee21
👍4
ኤፍሬም ስዩም

`` ህሊና ``
ከጫጫታው መሃል አልነበረም ስፍራው ፣
ራሱን ሸሽጎ አልታየም ከቦታው ፣
ለስጋ ዘመዱ ህሊና ባዳ ነው ፣
እንደ መስጊድ አዛን ፣
እንደ ቤተስኪያን ደዉል ፣
ህሊናም የሚጮህ ሲነጋ ነው መሰል ።

please join
👇
t.me/fikee21