ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል
2.07K subscribers
63 photos
2 videos
1 file
379 links
........ኑ
ስሜትን በግጥም እንግለፅ
ትውልድን በጥበብ እናንፅ ።

የፍቅር ቤት እዚህ ነው !
አሰተያየት ካላችሁ
👇
@fikee12 ላይ ማድረስ ይቻላል
Download Telegram
ስሜትህን ግዛ

ህጻን ልጅ ሲርበው ያለቅሳል፣ ሲናደድ ይጮሃል።
እውነተኛ ወንድ ግን ሲናደድ ዝም ይላል፤ ሲርበው ይታገሳል። በየቦታው ስሜቱን የሚዘረግፍ፣ በትንሽ ነገር የሚነጫነጭ ወንድ… ያልበሰለ ፍሬ ነው።
ረጋ ያለ መንፈስ፣ የንጉስ ባህሪ ነው።

(ከፈላስፋው ጭሰኛ)

t.me/fikee21
በጨረቃ ውበት - ምን ቢደነቅ ልቤ
ሰማይን በገመድ - አላቀርብም ስቤ።

ላንቺ ባይመስልሽም - ልቤ አንድ እውነት ያውቃል
አጉል መቀራረብ - ውበት ይደብቃል ።


📝ናትናኤል ሞላ

t.me/fikee21
❤4
እድል ያሰረውን ምኞት አይፈታውም ።

t.me/fikee21
❤1
ሞቼ ባረፍኩት እኔ አልልም
ለምን....
ከመኖር ብዙ ከመሞት ምንም ።

ፍቃዱ ግርማ / ዘ-በኩር/

t.me/fikee21
❤3💯1
አይረሳኝም አትበይ ሁሉም ይረሳል
አይተወኝም አትበይ ሁሉም ይተዋል
እራስ ደህና ነው ምን ያሳስባል ።

ፍቃዱ ግርማ /ዘ-በኩር/

t.me/fikee21
ሄድ መጣ
ገባ ወጣ
ይላል እሄ ልብሽ
አንቺ ምን አለብሽ ።

እኔማ...
ሳቅሽን ወስጄ አተምኩት በልቤ
ፈገግ ስትዪ እንዳይሽ በሀሳቤ ።

ፍቃዱ ግርማ /ዘ-በኩር/

t.me/fikee21
ሄሎ....

አቤት...

ደና ነሽ ጠፋሽ እኮ ሁሉ ሰላም ?

ደና ነኝ እግዚአብሔር ይመስግን

አትታዪም.....

አዎ አዲስ አበባ ሄጃለሁ

ቻው አይባልም? እንሂድ አይባልም?ግድ የለም.... አበባዬ ከተማውን ካስወደደሽ ይሁን ።


ብቻ

ሀሳብሽ ይሙላልሽ
መንገዱ ይቅናልሽ
የማታውቂው ሀገር ከዚ ከበለጠ
መቼም አላስቀርሽ ልብሽ ከቆረጠ ።

ከገጠር

ፍቃዱ ግርማ /ዘ-በኩር/

t.me/fikee21
❤2👏2