ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል
2.05K subscribers
62 photos
2 videos
1 file
374 links
........ኑ
ስሜትን በግጥም እንግለፅ
ትውልድን በጥበብ እናንፅ ።

የፍቅር ቤት እዚህ ነው !
አሰተያየት ካላችሁ
👇
@fikee12 ላይ ማድረስ ይቻላል
Download Telegram
ብቻ ልኑር

ሲከፋኝም ሲደላኝም
ሲያፈርሰኝም ሲሰራኝም
ሲሞላኝም ሲጎለኝም
ሕይወት ትግሏ ቢያደክመኝም
መጨለሜን አልመኝም  ።

ፍቃዱ ግርማ / ዘ-በኩር /

t.me/fikee21
❤8
መወደድን ለገፋ ልብን ላቆሰለ
ደህና ሁን ነው እንጂ ሌላ መልክት የለ

ፍቃዱ ግርማ / ዘ-በኩር /

t.me/fikee21
❤8
ሕይወት

እንዳሰብነው ሆኖ መንገዷ ባያልቅም
መኖር እንደ ማውራት ቀላል ሆኖ አያውቅም ።

ፍቃዱ ግርማ / ዘ-በኩር /

t.me/fikee21
❤5💯1
አንዳንዴ
( በእውቀቱ ስዩም)

ባልተገራ ፈረስ
በፈጣን ድንጉላ
ኑሮን ባቦ ሰጠኝ
ህይወትን በመላ
በዚህ በኩል ሲሉህ
ንጎድ ወደ ሌላ፤

እስከመቼ ድረስ
ዳር ዳሩን መራመድ ፤ በጭምት ሰው ስሌት
በክብር ካልመጣ፤ ሞክረው በቅሌት

ሰው ቅፅር አይደለም፤ በእሾህ የታጠረ
እንድትጥሰው ነው፤ ህግ የተፈጠረ::

አይሰለቺህም ወይ
መኖር በተጠንቀቅ
አንዳንዴ
አየር ላይ ደንሰህ ፤ በግንባርህ ውደቅ
አንዳንዴ
ኮርቻህን እርሳት
ርካህብህንም ሳት
ፋይዳ አይጠፋምና፤ ወድቆ ከመነሳት !

በትቢያ ላይ ወድቀው
የተነሱ አሉና፤ በሉል ባልማዝ ደምቀው !
አንዳንዴ
ልጉዋሙን ልቀቀው!

t.me/fikee21
❤6
ስሜትህን ግዛ

ህጻን ልጅ ሲርበው ያለቅሳል፣ ሲናደድ ይጮሃል።
እውነተኛ ወንድ ግን ሲናደድ ዝም ይላል፤ ሲርበው ይታገሳል። በየቦታው ስሜቱን የሚዘረግፍ፣ በትንሽ ነገር የሚነጫነጭ ወንድ… ያልበሰለ ፍሬ ነው።
ረጋ ያለ መንፈስ፣ የንጉስ ባህሪ ነው።

(ከፈላስፋው ጭሰኛ)

t.me/fikee21
በጨረቃ ውበት - ምን ቢደነቅ ልቤ
ሰማይን በገመድ - አላቀርብም ስቤ።

ላንቺ ባይመስልሽም - ልቤ አንድ እውነት ያውቃል
አጉል መቀራረብ - ውበት ይደብቃል ።


📝ናትናኤል ሞላ

t.me/fikee21
❤4
እድል ያሰረውን ምኞት አይፈታውም ።

t.me/fikee21
❤1