እንዲህ ያለም የለ
የውበትሽ ፀሐይ
አንዳች ታምር አለ ፥ ከውበትሽ ሰማይ
ፀጉርሽ ጨለማ ነው ፥ ዐይንሽ የጧት ፀሐይ
በዚህ መች አበቁ?
እኩል ይወጣሉ ፥ ሳይፈራረቁ ።
t.me/fikee21
የውበትሽ ፀሐይ
አንዳች ታምር አለ ፥ ከውበትሽ ሰማይ
ፀጉርሽ ጨለማ ነው ፥ ዐይንሽ የጧት ፀሐይ
በዚህ መች አበቁ?
እኩል ይወጣሉ ፥ ሳይፈራረቁ ።
t.me/fikee21
❤7
እናቴ
ምስጋና ለአንቺ 🙏🙏🙏
ህመምሽን ደብቀሽ በሳቅሽ ላጀብሺኝ
አንቺ እየፈረስሽ እኔን ለሰራሺኝ
ብርድና ሀሩሩ ቀድሞ እንዳይረታኝ
ከእቅፍሽ ጥላ ስር ወስደሽ የሸሸግሺኝ
የእናትነት ፍቅርሽ አንዴም ላልተለየኝ
ምስጋና ለአንቺ.....
እኔን ለሰራሺኝ እኔ ሆኜ እንድገኝ ።
ምስጋና ለአንቺ !🙏
ፍቃዱ ግርማ / ዘ - በኩር /
ምስጋና ለአንቺ 🙏🙏🙏
ህመምሽን ደብቀሽ በሳቅሽ ላጀብሺኝ
አንቺ እየፈረስሽ እኔን ለሰራሺኝ
ብርድና ሀሩሩ ቀድሞ እንዳይረታኝ
ከእቅፍሽ ጥላ ስር ወስደሽ የሸሸግሺኝ
የእናትነት ፍቅርሽ አንዴም ላልተለየኝ
ምስጋና ለአንቺ.....
እኔን ለሰራሺኝ እኔ ሆኜ እንድገኝ ።
ምስጋና ለአንቺ !🙏
ፍቃዱ ግርማ / ዘ - በኩር /
❤4👌3
❤6
❤8
❤5💯1
አንዳንዴ
( በእውቀቱ ስዩም)
ባልተገራ ፈረስ
በፈጣን ድንጉላ
ኑሮን ባቦ ሰጠኝ
ህይወትን በመላ
በዚህ በኩል ሲሉህ
ንጎድ ወደ ሌላ፤
እስከመቼ ድረስ
ዳር ዳሩን መራመድ ፤ በጭምት ሰው ስሌት
በክብር ካልመጣ፤ ሞክረው በቅሌት
ሰው ቅፅር አይደለም፤ በእሾህ የታጠረ
እንድትጥሰው ነው፤ ህግ የተፈጠረ::
አይሰለቺህም ወይ
መኖር በተጠንቀቅ
አንዳንዴ
አየር ላይ ደንሰህ ፤ በግንባርህ ውደቅ
አንዳንዴ
ኮርቻህን እርሳት
ርካህብህንም ሳት
ፋይዳ አይጠፋምና፤ ወድቆ ከመነሳት !
በትቢያ ላይ ወድቀው
የተነሱ አሉና፤ በሉል ባልማዝ ደምቀው !
አንዳንዴ
ልጉዋሙን ልቀቀው!
t.me/fikee21
( በእውቀቱ ስዩም)
ባልተገራ ፈረስ
በፈጣን ድንጉላ
ኑሮን ባቦ ሰጠኝ
ህይወትን በመላ
በዚህ በኩል ሲሉህ
ንጎድ ወደ ሌላ፤
እስከመቼ ድረስ
ዳር ዳሩን መራመድ ፤ በጭምት ሰው ስሌት
በክብር ካልመጣ፤ ሞክረው በቅሌት
ሰው ቅፅር አይደለም፤ በእሾህ የታጠረ
እንድትጥሰው ነው፤ ህግ የተፈጠረ::
አይሰለቺህም ወይ
መኖር በተጠንቀቅ
አንዳንዴ
አየር ላይ ደንሰህ ፤ በግንባርህ ውደቅ
አንዳንዴ
ኮርቻህን እርሳት
ርካህብህንም ሳት
ፋይዳ አይጠፋምና፤ ወድቆ ከመነሳት !
በትቢያ ላይ ወድቀው
የተነሱ አሉና፤ በሉል ባልማዝ ደምቀው !
አንዳንዴ
ልጉዋሙን ልቀቀው!
t.me/fikee21
❤6
ስሜትህን ግዛ
ህጻን ልጅ ሲርበው ያለቅሳል፣ ሲናደድ ይጮሃል።
እውነተኛ ወንድ ግን ሲናደድ ዝም ይላል፤ ሲርበው ይታገሳል። በየቦታው ስሜቱን የሚዘረግፍ፣ በትንሽ ነገር የሚነጫነጭ ወንድ… ያልበሰለ ፍሬ ነው።
ረጋ ያለ መንፈስ፣ የንጉስ ባህሪ ነው።
(ከፈላስፋው ጭሰኛ)
t.me/fikee21
ህጻን ልጅ ሲርበው ያለቅሳል፣ ሲናደድ ይጮሃል።
እውነተኛ ወንድ ግን ሲናደድ ዝም ይላል፤ ሲርበው ይታገሳል። በየቦታው ስሜቱን የሚዘረግፍ፣ በትንሽ ነገር የሚነጫነጭ ወንድ… ያልበሰለ ፍሬ ነው።
ረጋ ያለ መንፈስ፣ የንጉስ ባህሪ ነው።
(ከፈላስፋው ጭሰኛ)
t.me/fikee21
Telegram
ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል
........ኑ
ስሜትን በግጥም እንግለፅ
ትውልድን በጥበብ እናንፅ ።
የፍቅር ቤት እዚህ ነው !
አሰተያየት ካላችሁ
👇
@fikee12 ላይ ማድረስ ይቻላል
ስሜትን በግጥም እንግለፅ
ትውልድን በጥበብ እናንፅ ።
የፍቅር ቤት እዚህ ነው !
አሰተያየት ካላችሁ
👇
@fikee12 ላይ ማድረስ ይቻላል
በጨረቃ ውበት - ምን ቢደነቅ ልቤ
ሰማይን በገመድ - አላቀርብም ስቤ።
ላንቺ ባይመስልሽም - ልቤ አንድ እውነት ያውቃል
አጉል መቀራረብ - ውበት ይደብቃል ።
📝ናትናኤል ሞላ
t.me/fikee21
ሰማይን በገመድ - አላቀርብም ስቤ።
ላንቺ ባይመስልሽም - ልቤ አንድ እውነት ያውቃል
አጉል መቀራረብ - ውበት ይደብቃል ።
📝ናትናኤል ሞላ
t.me/fikee21
Telegram
ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል
........ኑ
ስሜትን በግጥም እንግለፅ
ትውልድን በጥበብ እናንፅ ።
የፍቅር ቤት እዚህ ነው !
አሰተያየት ካላችሁ
👇
@fikee12 ላይ ማድረስ ይቻላል
ስሜትን በግጥም እንግለፅ
ትውልድን በጥበብ እናንፅ ።
የፍቅር ቤት እዚህ ነው !
አሰተያየት ካላችሁ
👇
@fikee12 ላይ ማድረስ ይቻላል
❤4