ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል
2.05K subscribers
62 photos
2 videos
1 file
374 links
........ኑ
ስሜትን በግጥም እንግለፅ
ትውልድን በጥበብ እናንፅ ።

የፍቅር ቤት እዚህ ነው !
አሰተያየት ካላችሁ
👇
@fikee12 ላይ ማድረስ ይቻላል
Download Telegram
ያልተረዱኝ ሁሉ...
ጥንዶች ባዩ ቁጥር..
አያምሩም ይሉኛል ተቃቅፈው ሲሄዱ
ዝም ላለማት ያምራሉ እላለሁ....
አንቺን አስታወሼ ማታ ደግሞ ላለቅስ ።

ፍቃዱ ግርማ /ዘ-በኩር/

t.me/fikee21
❤4💔2❤‍🔥1👏1
እሷ
.
.
ጥርሷቿን ስትገልጥ....
ፈገግ ስትል ድንገት
ጉንጯ ለብቻውን ይሰጣል ምልክት ።
እና እሷ ማለት...... ?
በአበባ ጥርሷቿ ለአፍታ ብትስቅ
ድምፅ አልባ ሌባ ናት ልብን የምትሰርቅ ።


ፍቃዱ ግርማ / ዘ - በኩር /

t.me/fikee21
❤4👏1
ወደድክም ጠላህም ወጣት ሆነህ እየለፋህ አልሞላ ብሎህ እናትህ እሚያስፈልጋት ቦታ ለይ መዋል ወይም መሙላት ሲያቅትህ እንደማየት ቅስም ሰባሪ ነገር የለም ።

ፍቃዱ ግርማ / ዘ-በኩር /

t.me/fikee21
❤6
በዕውቀቱ ስዩም

ምሀሌተ ገንቦ:
በአጭር ቀረን ስንል፣
እድሜ ላበደሩን፤
​ቀርጸው ላሳመሩን፣
ለኮሰው ላበሩን...
ቸርስ!
​ፊታችንን አይተው እንደተቸገርን፣
ከአይናችን አውቀው፣
ስለ ማርያም ብለን እስክንለምናቸው፣
ቆመው ለልጠበቁ...
ቸርስ!
​ወድቀው ለማይጥሉ፣
ነግሰው ለሚያነግሱ፣
ነውራችንን አይተው፣
ልክ እንደድመቱ ስለሚያለባብሱ፤
​ብድር አበድረው ፈጥነው ለሚረሱ...
ቸርስ!
​ላባ ላደረጉልን የመከራ ሸክሙን፣
ቅልደው ላሳቡን፣
ተጫውተው ላከሙን፤
​ላከሙን፣
በከፋ ዘመናት፣
ላይ ጋ ስንለብስ፣
ትንግርት ሆነው ላስደመሙን...
ቸርስ!

t.me/fikee21
❤7🤝4
አታውቀውምና ፣
ዬት እንደሚያደርስህ የሕይወትህ መስመር
ቀድመህ በማንም ለይ ጣትህን አትቀስር
እናም....
ካለሆነ ለመውደድ
አትቸኩል ለመፍረድ ።

ፍቃዱ ግርማ / ዘ-በኩር/


t.me/fikee21
❤6
'ሚታየው ሁሉ ጥርሱ ፈግጎ
ያጣ አይመስልም ምንም ፈልጎ ።


ፍቃዱ ግርማ / ዘ-በኩር /

t.me/fikee21
❤4🤝1
እንዲህ ያለም የለ

​የውበትሽ ፀሐይ

​አንዳች ታምር አለ ፥ ከውበትሽ ሰማይ
ፀጉርሽ ጨለማ ነው ፥ ዐይንሽ የጧት ፀሐይ

​በዚህ መች አበቁ?
እኩል ይወጣሉ ፥ ሳይፈራረቁ ።

t.me/fikee21
❤7
እናቴ

ምስጋና ለአንቺ 🙏🙏🙏

ህመምሽን ደብቀሽ በሳቅሽ ላጀብሺኝ
አንቺ እየፈረስሽ እኔን ለሰራሺኝ
ብርድና ሀሩሩ ቀድሞ እንዳይረታኝ
ከእቅፍሽ ጥላ ስር ወስደሽ የሸሸግሺኝ
የእናትነት ፍቅርሽ አንዴም ላልተለየኝ
ምስጋና ለአንቺ.....
እኔን ለሰራሺኝ እኔ ሆኜ እንድገኝ ።

ምስጋና ለአንቺ !🙏

ፍቃዱ ግርማ  / ዘ - በኩር /
❤4👌3
መቼም እኔ አፌ አያድብም
ግን አሁን ክፉ አልናገርም
አለማመስገኔ ምን እንዳደረገኝ
አሁን ነው የገባኝ ።

ፍቃዱ ግርማ / ዘ-በኩር /

t.me/fikee21
አምላክም እንደ ሰው ፣
ግዜ እየጠበቀ ቢለዋወጥብን
ፊቱን ቢያዞርብን
ቢነፍገን የእሱን ፍቅር
ምን ይውጠን ነበር?


ፍቃዱ ግርማ / ዘ-በኩር /

t.me/fikee21
❤6
ብቻ ልኑር

ሲከፋኝም ሲደላኝም
ሲያፈርሰኝም ሲሰራኝም
ሲሞላኝም ሲጎለኝም
ሕይወት ትግሏ ቢያደክመኝም
መጨለሜን አልመኝም  ።

ፍቃዱ ግርማ / ዘ-በኩር /

t.me/fikee21
❤8
መወደድን ለገፋ ልብን ላቆሰለ
ደህና ሁን ነው እንጂ ሌላ መልክት የለ

ፍቃዱ ግርማ / ዘ-በኩር /

t.me/fikee21
❤8
ሕይወት

እንዳሰብነው ሆኖ መንገዷ ባያልቅም
መኖር እንደ ማውራት ቀላል ሆኖ አያውቅም ።

ፍቃዱ ግርማ / ዘ-በኩር /

t.me/fikee21
❤5💯1
አንዳንዴ
( በእውቀቱ ስዩም)

ባልተገራ ፈረስ
በፈጣን ድንጉላ
ኑሮን ባቦ ሰጠኝ
ህይወትን በመላ
በዚህ በኩል ሲሉህ
ንጎድ ወደ ሌላ፤

እስከመቼ ድረስ
ዳር ዳሩን መራመድ ፤ በጭምት ሰው ስሌት
በክብር ካልመጣ፤ ሞክረው በቅሌት

ሰው ቅፅር አይደለም፤ በእሾህ የታጠረ
እንድትጥሰው ነው፤ ህግ የተፈጠረ::

አይሰለቺህም ወይ
መኖር በተጠንቀቅ
አንዳንዴ
አየር ላይ ደንሰህ ፤ በግንባርህ ውደቅ
አንዳንዴ
ኮርቻህን እርሳት
ርካህብህንም ሳት
ፋይዳ አይጠፋምና፤ ወድቆ ከመነሳት !

በትቢያ ላይ ወድቀው
የተነሱ አሉና፤ በሉል ባልማዝ ደምቀው !
አንዳንዴ
ልጉዋሙን ልቀቀው!

t.me/fikee21
❤6
ስሜትህን ግዛ

ህጻን ልጅ ሲርበው ያለቅሳል፣ ሲናደድ ይጮሃል።
እውነተኛ ወንድ ግን ሲናደድ ዝም ይላል፤ ሲርበው ይታገሳል። በየቦታው ስሜቱን የሚዘረግፍ፣ በትንሽ ነገር የሚነጫነጭ ወንድ… ያልበሰለ ፍሬ ነው።
ረጋ ያለ መንፈስ፣ የንጉስ ባህሪ ነው።

(ከፈላስፋው ጭሰኛ)

t.me/fikee21
በጨረቃ ውበት - ምን ቢደነቅ ልቤ
ሰማይን በገመድ - አላቀርብም ስቤ።

ላንቺ ባይመስልሽም - ልቤ አንድ እውነት ያውቃል
አጉል መቀራረብ - ውበት ይደብቃል ።


📝ናትናኤል ሞላ

t.me/fikee21
❤4
እድል ያሰረውን ምኞት አይፈታውም ።

t.me/fikee21
❤1