ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል
1.78K subscribers
55 photos
2 videos
1 file
334 links
........ኑ
ስሜትን በግጥም እንግለፅ
ትውልድን በጥበብ እናንፅ ።

የፍቅር ቤት እዚህ ነው !
አሰተያየት ካላችሁ
👇
@fikee12 ላይ ማድረስ ይቻላል
Download Telegram
ትናፍቀኛለች

በቀንና ሌሊት በሰዓት መካከል
እሷን የመናፈቅ አለኝ ክፉ አመል
አላወጣት ነገር ከሃሳቤ ገብታ
ደም ዝውውሬ ናት የልቤ ትርታ
ገና እንደመጣች ከፊቴ እንቆመች
መሄዷን አስቤ ትናፍቀኛለች ።

ፍቄ ግርማ ( t.me/fikee21 )
👍9
Forwarded from Sanyii Guddataa (Sanyii Guddataa)
Bu'aan qormaata barattoota 12ffaa Ifoome.
Barattoonni qabxii isaanii karaa marsareetii https://eaes.edu.et/ yookiin
6484 irratti halkan sa'aatii 5:30 booddee, lakkoofsa registration isaanii galchuun beekuu ni dandeessu. Carraa gaarii
#Warra hindhageenye dhageessisaa. @segnigudeta
[ ተዋት ባክህ ልጄ ]

አለ እስከ ዛሬ ፈዞና ደንዝዞ
አያዋጣምና የመንገዷ ጉዞ
አይወጋህ እሾኳ አይጨቅጭቅህ መርፌ
ተዋት አትመልከት ተደበቅ ተቅፌ
ደብቄ ላኑርህ ሸሽጌህ በጉያ
እንዳትመካባት፣
አለም ኮንትራት ናት ጊዚያዊ መኖሪያ ።

ፍቄ ግርማ
Join
👇
( http://t.me/fikee21 )
👍7
[ ናፍቀሺኛል አበባዬ ]

እንደምነሽ አንቺ ለውሎሽ ላዳሩ
ከተለየን ወዲህ ገደለኝ ሽብሩ
እያንሰላሰልኩኝ ትዝታ ከናፍቆት
ወሎ አዳሬ ሆኗል ፣
አንቺን ሳስብ ወዬ አንቺን ሳልም ማንጋት
እናማ የኔ አለም የህይወቴ መብራት
መኖሬንም እረሳለሁ አንቺን ሳስብ ድንገት
አበባዬ የቤቴ ጌጥ
በመሄድሽ ስደናገጥ
ልቤ ደግሞ ተስፋ ሲቆርጥ
አለሁኝ እስከ ዛሬ ፣
በፍቅርሽ መዓበል ስዋጥ
ግን ለሁሉም የኔ ቆንጆ ፣
በሄድሽበት ባለሺበት ቦታ
ተመኘሁኝ ሰላም ፍቅር ደስታ ።

ፍቄ ግርማ
join
👇
( http://t.me/fikee21 )
👍83
[ ውድዬ ]

አንቺዬ እንስማማ እንኑር በፍቅር
አንቺም እኔን ስሚኝ እኔም ላንቺ ልኑር
በልቤ ላኑርሽ እንደ ታላቅ ሚስጥር
የልቤን ልንገርሽ እወነቱን ቁም ነገር
ሀሳቤ ስላንቺ ቢሆንም እርቆ
ይወድሻል ልቤ አብዝቶ ተጨንቆ
ፃፍኩልሽ አንብቢው በእንባዬ ቀለም
ሁሉም ቢሰበሰብ ለኔ እንዳንቺ የለም ።
ፍቄ ግርማ
Join
( http://t.me.fikee21 )
👍4
አዎ.....

ታላቅ መኾንን ስትፈልጉ ታላቅ መኾንን አትፈልጉ ከዛም ታላቅ ትሆናላችሁ ።!

ፍቄ ግርማ
( http://t.me/fikee21 )
👍1
የሰው ልክ

እቺን አለም ትቶ ፣
ቢመኝ የአምላክ ስራ
ሰው ሁሉ በልቡ ፣
ቢንያምን ይጥራ ።

ፍቄ ግርማ
join
👇
( http://t.me/fikee21 )
👍7
# መጀመርን አትፈራ ቆራጥ ሁን ያኔ እመነኝ ድንቁ ስው አንተ ነህ
የስው ልጅ ከእራሱጋ የሚጣለው የድሮ ማንነቱን ማሸነፍ ሲያቅተው ነው አሁን ያለበትን መቀበል ያለቻለ ሰው አበክሮ ለነጌው ይጨነቃል ይፈራል ከዚ ሁሉ ግን እራስን እደመቀበል መልካም ነገር የለም ሁሉም ችግሮች ወጀብ ናችው ያለፋሉ በፅናት መቆም ያስፈልጋል ።

ትንሿ ትግስት ከበዙ ፀፀት ታተርፋለች ታገስ/ሺ ሌላ ሚስጥር የለውም በቃ ።

( t.me/fikee21 )
👍6
አቁም

ማቆም ያለብህ ዛሬ ከሆን አሁኑኑ አቁመው ያንተው ትንሿ ስተት ናት ነጌ ተደምራ ተደማምራ የእድሜ ልክ ፀፀት የምትሆንብህ በቃ ካንተ የሚበልጥ ሰለሌለ ትክክለኛውን ማንነትህን ተቀበለውና ሌላውን መቆም ያለበትን አቁመው ።

( t.me/fikee21 )
👍7
መሆን ያለበት ይሆን ዘንድ ግድ ነው
ለምን ሆነ ? እንዴት ሆነ ? በምን ሆነ ? የሚለውን ተዎ በቃ እግዚአብሔር ላንተ ያለው አለ ብዙ አትልፋ አትፈላሰፍ ሁሉንም ነገረ ለእግዚአብሔር ስጠው አባቴ ከዛ ሁሉም በደረጃ ይኬዳል አታስብ ።

( t.me/fikee21 )
👍9
አንቺ በናፍቆትሽ ቤቴን አስጨንቂው
እኔ በትዝታ ቤትሽን ላሙቀው
ጎጆሽን ላሙቀው
ጎዳሽን ላሙቀው
ለምን ? አትይኝም
ላንቺ ያለኝን ፍቅር እኔ ነኝ የማውቀው ።

( t.me/fikee21 )
👍9
አዎ ልሰራው !
እራሴን ልሰራው እሽም ግድሙን
ዘመኑም ይወዳል አይስመሳይውን

t.me/fikee21
👍3
Channel name was changed to «ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል»
አንቺ ሆነሽ ህልሜ
እንዴት ልርሳሽ ቆሜ
በፊደል ከትቤ
አዝዬሽ በልቤ
ላኑርሽ ዝንት አለም
ለ'ኔ እንዳንቺ የለም ።

( t.me/fikee21 )
👍4
አሁን .....አሁንስ
ዐሥርቱ ትዕዛዝ ፤ ነብሴን እንደገባት
አንቺን ዐሥር ግዜ ፤ እየፈቱ ማግባት ።

( መሰለኝ )

ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን
t.me/fikee21
👍1
ሰው በመሆን ስሌት

[ ፍቃዱ ግርማ ]

ሰው በመሆን ስሌት አንዱ አንዱን ካረዳ
ህይወት አትገፋም አበሳ ናት ፊዳ
ቀመሩ ቢወጣ ቢሰራ ስሌቱ
ያንዱ ለአንዱ መኖር ነበር መሰረቱ ።
Join
👇
t.me/fikee21