ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል
2.05K subscribers
62 photos
2 videos
1 file
374 links
........ኑ
ስሜትን በግጥም እንግለፅ
ትውልድን በጥበብ እናንፅ ።

የፍቅር ቤት እዚህ ነው !
አሰተያየት ካላችሁ
👇
@fikee12 ላይ ማድረስ ይቻላል
Download Telegram
ፍቅር ለማይገባው መተረክ ትዝታ
ናፍቆት ለማይገባው ማልቀስ መንታ መንታ
መወደድ ላልገባው እራስን መገብር
አስከዬት ነው መወደድ እሰከዬት ነው ፍቅር ?
አለኝ ሲሉት ማጣት
ኖርኩኝ ሲሉ መሞት
ቆምኩ ሲሉ መውደቅ
ዳንኩ ሲሉ መድቀቅ
መጡ ሲሉ መራቅ
ቻል እንግዲህ እራሴ.....
እንዲህ ነው አንዳንዴ እያነቡ መሳቅ ።
    
  ፍቃዱ ግርማ / ዘ-በኩር /

t.me/fikee21
❤5
"ባጭር ቀረን" ስንል - እድሜ ላበደሩን
ቀርፀው ላሳመሩን
ለኩሰው ላበሩን
ቺርስ!!
።።።።
ፊታችንን ዐይተው
እንደተቸገርን - ካይናችን ላወቁ
ስለማርያም ብለን
እስክንለምናቸው - ቆመው ላልጠበቁ
ቺርስ!!!
።።።።
ወድቀው ለማይጥሉ -ነግሰው ለሚያነግሱ
ነውራችንን ዐይተው
ልክ እንደ ድመት ኩስ ፣ ለሚያለባብሱ
ብድር አበድረው ፣ ፈጥነው ለሚረሱ😉
ቺርስ!!!!
።።።።።።
ላባ ላረጉልን ፣ የመከራ ሸክሙን
ቀልደው ላሳቁን ፣ ተጫውተው ላከሙን
በቸከ ዘመን ላይ...
ስጋ ለበስ ትንግርት -ሆነው ላስደመሙን
ቺርስ!!!!!
።።።።።።።።።።።
(✍️ Bewketu Seyoum )


t.me/fikee21
❤8
Forwarded from የግጥሜ አሻራ....✍ (Bitseat ❤)
እንኳንና  ለሰው__ለፈጣሪም ቢችል
  ብዙ  ክፉ  አለ  አቃጥሮ
           ሚያስገድል

✍ብፅእት ስዩም
🤝4❤3👏1
ዝምታ ከወርቅ በላይ ወርቅ ነው ።

t.me/fikee21
❤2
ያመሻሽ ስንኞች
(በእውቀቱ ስዩም)

በቀዝቃዛ ጎጆ፤ በደብዛዛ ኩራዝ
እንባ እያጣቀስኩኝ ፤ በምገልጠው ጥራዝ፤
ኑሮየን ባጠናው፤ ፍቺው አይገለጥ
ሊቅ ሆኘ ተፈጠርሁ፤ በቂል ለመበለጥ፤

“””””
እሳቴን አንድጄ
ጭራሮ ማግጄ
ሰታቴየን ጥጄ
ሺ ጊዜ ባማስል፣ ራት አላበሰልሁ
እኔ ከማገዶው፤ ቀድሜ እየከሰልሁ፤


t.me/fikee21
❤10
ይሻል ብዬ ዛሬ ነጌ
አባበልኩሽ
አዘልኩሽ
እንዳይበርድሽ እኔ አቀፍኩሽ
ዛሬስ በቃኝ......
በቃኝ በቃኝ ልርግምሽ ነው ቆርጫለሁ
ቱ ነው  ያልኩሽ ወስኛለሁ
የምትነኪው እያንዳንዱ
ጥፍት ይበል ያልሺው ደጉ

ፍቃዱ ግርማ /ዘ -በኩር/

t.me/fikee21
❤5
ቀናት ቢያልፉ አመት ቢነጉድ
እልፍ ነገር ቢዠጎደጎድ
መጠበቁ ቢደክመኝም
ካንቺ ሌላ አልመኝም ።

ፍቃዱ ግርማ /ዘ-በኩር/

t.me/fikee21
❤6
አባቴ

እንደ ምስራቅ ፀሃይ ፊትህ የሚያበራው
እንደ አለት ድንጋይ ክንድህ የበረታው
ከባለጌ ዙፋን ሄደህ ማትቀመጥ
አቅሙ ለደከመ ብርታት የምትሰጥ
መተኪያ የሌለህ የኔ ትልቁ ክብር
አባቴ ባትሆን ምን ይወጠኝ ነበር ።

ፍቃዱ ግርማ /ዘ-በኩር/

t.me/fikee21
❤4
ምድረበዳ ሌሊት
(በእውቀቱ ስዩም)

ስንት ዘመን ሆነ?
ጥላሁን ገሰሰ
“በምሽት ጨረቃ” ብሎ ከዘፈነ?

አንዳንዴ ሳስበው፥ በጥላሁን ዘመን፥
ልክ እንደ አባት እቅፍ፥ ሌሊቱ ሲታመን
ባውሬ በቀማኛ
በሮንድ ፥በዘበኛ
ላፍታ ሳይሸበር
ፍቅር በፈቃዱ፥ ውጭ አዳሪ ነበር::

ዘመን ተቀይሮ ፥
እንኳን በሌት፥ በቀን ፍርሀት ሲሰፈን
ማነው ዛሬ ደፍሮ
“ በምሽት ጨረቃ?” ብሎ የሚዘፍን?

ያስፈራል መንገዱ
ያስፈራል፥ አጸዱ
ያስፈራል አልፎሂያጅ
ያስፈራል ጎረቤት
የሁሉም ሰው መርህ-በጊዜ ወደ ቤት!

ወትሮ እያባረረው፥
እየገፈተረው
ሀቁና ፈጠራው፥ ባንድ ላይ አድሞ
ወደ ቤቱ ገባ፥ ሰው ከጀንበር ቀድሞ
ደጁ ተቆለፈ
በሰአት እላፊ የታጠረ ትውልድ
የሌሊቱን ውበት፤ ሳይቀምሰው አለፈ::

በሰዎች ልብ ውስጥ፤ ዜማ መቀስቀሷ
ባፍለኞች ልብ ውስጥ፥ ፍቅር መጸነሷ
እያፍለቀለቃት
እስክታስለቅቃት
ከቦታዋ ደርሳ፥ የማለዳ ጀንበር
ጨረቃ ሰማይ ላይ ትንሰራፋ ነበር::

ዛሬ ሰው ቸግሯት
ብቸኝነት ገርፏት
መሪር እያነባች
ዘግይታ፥ ብቅ ብላ፥ ያለጊዜ ገባች::

t.me/fikee21
❤15
የሰው ልጅ መብሰል ስጀምር መፍረድን ያቆማል ።
❤9
ሀብታሙ ሃደራ

( አስገረመችን ! )

ደግሞ እሄ ልቧ !

ጎልያድ ከጭፍራው ፥ ደርቦ የሚጥል
ነፍስን ከስጋ ፥ ደርሶ 'ሚነጥል
የዳዊት አቻ ፥ የእግዜር ቅምጥል ።

እንዳመጣልን....

አንዱን አንስተን ፥ አንዱን ሳንጥል
ምኞት ሳይሞኝ ፥ ስጋት ሳይሰጋ
ሌት ሳንዋጋ
ነጋ ፥ !
ከእንግዲህ ምን ቀረን ?
ከእንግዲህ ምን አጣን ?
ወንዶች ሆነን ገብተን ፥ ሰዎች ሆነን ወጣን ።
❤7
በቀልድም ፡ በቁምነገርም ሰው በውስጡ እየተገፋ ውጭ ወጭወን የሚኖር ፍጥረት ነው ።

📝አለመኖር !
❤6
ፍቅርን !

አባረን አባረን....
አባረን ፈለግነው
ፈልገን አጣነው
በቃላችን ብቻ
እየተናገርነው ።


ዮሐንስ ፍቃዴ
❤5👏2💯1
ያልተረዱኝ ሁሉ...
ጥንዶች ባዩ ቁጥር..
አያምሩም ይሉኛል ተቃቅፈው ሲሄዱ
ዝም ላለማት ያምራሉ እላለሁ....
አንቺን አስታወሼ ማታ ደግሞ ላለቅስ ።

ፍቃዱ ግርማ /ዘ-በኩር/

t.me/fikee21
❤4💔2❤‍🔥1👏1
እሷ
.
.
ጥርሷቿን ስትገልጥ....
ፈገግ ስትል ድንገት
ጉንጯ ለብቻውን ይሰጣል ምልክት ።
እና እሷ ማለት...... ?
በአበባ ጥርሷቿ ለአፍታ ብትስቅ
ድምፅ አልባ ሌባ ናት ልብን የምትሰርቅ ።


ፍቃዱ ግርማ / ዘ - በኩር /

t.me/fikee21
❤4👏1
ወደድክም ጠላህም ወጣት ሆነህ እየለፋህ አልሞላ ብሎህ እናትህ እሚያስፈልጋት ቦታ ለይ መዋል ወይም መሙላት ሲያቅትህ እንደማየት ቅስም ሰባሪ ነገር የለም ።

ፍቃዱ ግርማ / ዘ-በኩር /

t.me/fikee21
❤6
በዕውቀቱ ስዩም

ምሀሌተ ገንቦ:
በአጭር ቀረን ስንል፣
እድሜ ላበደሩን፤
​ቀርጸው ላሳመሩን፣
ለኮሰው ላበሩን...
ቸርስ!
​ፊታችንን አይተው እንደተቸገርን፣
ከአይናችን አውቀው፣
ስለ ማርያም ብለን እስክንለምናቸው፣
ቆመው ለልጠበቁ...
ቸርስ!
​ወድቀው ለማይጥሉ፣
ነግሰው ለሚያነግሱ፣
ነውራችንን አይተው፣
ልክ እንደድመቱ ስለሚያለባብሱ፤
​ብድር አበድረው ፈጥነው ለሚረሱ...
ቸርስ!
​ላባ ላደረጉልን የመከራ ሸክሙን፣
ቅልደው ላሳቡን፣
ተጫውተው ላከሙን፤
​ላከሙን፣
በከፋ ዘመናት፣
ላይ ጋ ስንለብስ፣
ትንግርት ሆነው ላስደመሙን...
ቸርስ!

t.me/fikee21
❤7🤝4
አታውቀውምና ፣
ዬት እንደሚያደርስህ የሕይወትህ መስመር
ቀድመህ በማንም ለይ ጣትህን አትቀስር
እናም....
ካለሆነ ለመውደድ
አትቸኩል ለመፍረድ ።

ፍቃዱ ግርማ / ዘ-በኩር/


t.me/fikee21
❤6