ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል
1.83K subscribers
59 photos
2 videos
1 file
353 links
........ኑ
ስሜትን በግጥም እንግለፅ
ትውልድን በጥበብ እናንፅ ።

የፍቅር ቤት እዚህ ነው !
አሰተያየት ካላችሁ
👇
@fikee12 ላይ ማድረስ ይቻላል
Download Telegram
ሁሉም ሲጠምም ቀን ሲከፋብን
ኃጢያቱ በዝቶ ፀሎት ጠፋብን ።

ፍቃዱ ግርማ / ዘ-በኩር /

t.me/fikee21
👏42
ክረምት
ዝናብ ሲያካፋ
ብርዱ ሲከፋ
ሁለቱ ወራት
ሲሆኑ አመት
ወንዙ ሲሞላ ከዳር እስከ ዳር
እእሄው ዘንድሮም....
ትራስ አቅፌ ሊወጣብኝ ነው የህዳር ጀንበር ።


ፍቃዱ ግርማ / ዘ-በኩር /

t.me/fikee21
5👏2
ምንም እኮ ሊያፅናናኝ አልቻለም እና ባብድ ሊፈረድብኝ ነው ?

t.me/fikee21
3💔2
ግን እንዴት ነው እግዚአብሔር ?
ከምንም ንክኪ እራሴን አጥፍቼ
አለም ከመረረኝ ፣
መኖር እችላለሁ አንተ ጋር መጥቼ ?
እ.....


t.me/fikee21
2
አምላኬ ሆይ አንተው አስችለኝ
ከሰማይ ሆነህ ስለምታየኝ
እኔማ ደካማ ነኝ እንደምታወቀኝ
ድንቅ ችሎታ ብቃት የሌለኝ ።

ፍቃዱ ግርማ / ዘ-በኩር /

t.me/fikee21
3💘1
ለሆነውም ስላልሆነውም ሁሉ እግዚአብሔር ይመስገን ።

ለሁሉም ግዜ አለው ።

ፍቃዱ ግርማ / ዘ-በኩር /

t.me/fikee21
3💘1
እስኪ ግጥም ...

እስኪ ግጥም ልብየሚያደርስ!
ግጠሙልኝ ሮሮየን የሚናገር በሽታየን
                                     የሚፈውስ
በከንቱ ሜዳ የቀረ የብዙ ዘመን ድካሜን
ሰሚ ያጣውን ጩኸቴን የዕምባ ማሰሮ
                                          ሸክሜን!
ይናገርልኝ እንደሆን በሉስኪ ስንኝ 
                                   ቋጥሩ!
ከጥሪ ከለቅሶ ይልቅ ግጥም ያደምጣል
                                        ሀገሩ!!!

@chr 7th

t.me/fikee21
💘2💯1
ምን ሆነሻል አታልቅሺ
አይዞሽ በቃ አታልቅሺ
ይገባኛል ታደክማለች እቺ አለም
'ማያልፍ ግን ምን የለም
ጠንከር በይ እጅ አትስጪ
ጣይ ይበዛል ወደ ስኬት ስትሮጪ  ።

ፍቃዱ ግርማ / ዘ-በኩር /

t.me/fikee21
5
አዘልኩሽ
አቀፍኩሽ
ሲበዛ ሳሳሁሽ
አይኔ ብሌኔ አልኩሽ ።

አንድ አለሜ ብዬ ወስኜ ቆርጬ
አንቺን አፈቀርኩኝ ከራሴ አብልጬ

ግና  አንቺ ዛሬ.....
ገፋሺኝ እንደ ጉድ ረሳሺው ትላንትን
ረገጥሺው መወደዴን
አደማሺው ልቤን ።

እናም የኔ ቆንጆ....
ሰላም ግቢ አንቺ መሄድሽም ቢያመኝ
አመሰግናለሁ ስላጠነከርሺኝ ። 🙏

ፍቃዱ ግርማ / ዘ-በኩር /

t.me/fikee21
2🙏2
ቢጎዙ ቢጎዙ ቢያካልሉ ሀገር
የለወጥ መነሻው ማንነት ነው ስፍር ።

ስለሄዱ አይቀናም የስኬት ጎዳና
አይሳካም የለም ታቅፎ ስንፍና ።

ተቀምጦ እጅ አጣጥፎ
መክበር የለም......
ከውድቀት በር ተስልፎ ።

ስማ እንግዲ እውነት ሀቁን ፣
ዋጥ አድርገው ቢመርህም
መልፈስፈስህ ገደል ይግባ ፣
ጠንከር በል ብቸኛ ነህ የለም ማንም ።


ፍቃዱ ግርማ [ ዘ-በኩር  ]


t.me/fikee21
2
ወጣቶች ነበርን
በእውቀቱ ስዩም

ጊዜ ሲራመድ ኮቴው ድምጥ አልባ
ከየት ተነስቶ ወደ የት ገባ
ከየት ተነስቶ ወዴት ደረሰ
ጠጉር መንጥሮ፣ ፊት እያረሰ፤

ወጣቶች ነበርን
ቅጽር የሰራን ፤ አምባ የሰበርን
ኮካ ኮላውን ባሲድ በርዘን
ብንጎነጨው፤ የማይመርዘን፤
በራዱን ያጋልን፣ ሙት ልብ ያስነሳን
ግራዋ በልተን ፤ ሎሚ ያገሳን፤

ተስፋችን ብዙ፤ እድሚያችን ለጋ
ስንሰማራ፣ ትርጉም ፍለጋ

ገላችን አይፈዝ፣ ጭቃ ቢለሰን
የማናስቀይም፤ ቡትቶ ለብሰን
ገጻችን ብሩህ፤ ልባችን ሽፍታ
ስንመነጠቅ፤ ወደ ከፍታ
የስኬት ገነት፣ ደጃፏን ከፍታ
ምትቀበለን ፣ እየመሰለን
ከቁመታችን፤ በላይ የዘለልን፤

ወጣቶች ነበርን
ዛሬ እንደዋዛ
ዘንድሮን ምሰን፤ ታችአምናን ቀበርን፤


t.me/fikee21
8❤‍🔥2
ምድር ለወንድ ልጅ ፈታኝ ቦታ ነው እርግጠኛ መሆን ያለብህ አንተ ጠንካራ ትሆናለህ እንጂ ሕይወት መቼም ቢሆን ቀላል ልትሆን አትችልም ።

ፍቃዱ ግርማ / ዘ-በኩር /

t.me/fikee21
2
በክንዶቼ እቅፍ
ለዘላለም እርፍ
ላርግሽና ውስድ
አንቺን ከኔ ግምድ
ዝምድ
ውድድ
ደምሽን ከደሜ
ህልምሽን ከህልሜ
ይቀዳ ከአንድ ምንጭ..
ፍቅርሽና ፍቅሬ
ነፃነት ሞገስ ነሽ..
ኩራትና ክብሬ ።

ገደፍ በይና ከ'ኔ...
ሽጉጥ ከአንገቴ
ድፍን ሀገር ይይሽ....
ግቢና ከቤቴ ።

ፍቃዱ ግርማ / ዘ-በኩር /

t.me/fikee21
3💯3❤‍🔥2
አምላክ አስር ሰጥቶ አንድ እየለመነ
የሰው ልጅ በክፋት ልቡ ደነደነ
ያጣን ቀርቦ መርዳት
ተካፍሎ አብሮ መብላት
ቢሆን የሁሉ አመል ፣
ሁሉም ሰው ቢዘምር ለሰላም ለፍቅር
ገነትን ምድር ለይ እንሰራት ነበር ።

ፍቃዱ ግርማ / ዘ-በኩር /

t.me/fikee21
5🎉1
ስም ሆኖ ከቀረ ሰው ሆኖ መፈጠር
ካላገናዘብን ጥላቻን ከፍቅር
ዛሬ ለይ እያለን የዘራነው ክፋት
ለነገ ጉዟችን ይሆናል እንቅፋት
ተፈጥረን በአምሳሉ
የጠፋብን ውሉ
ለመልካም ተፈጥረን
መሆንን ያቃተን
ለስም የቀረብን በአካል የራቅን
ሰው ሆነን ተፈጥረን ሰው መሆን አቃተን ።


ፍቃዱ ግርማ / ዘ-በኩር /

t.me/fikee21
6👏1🎉1
 
እንቅፋት ሆነው የጣሉህ ሁሉ
ያዘኑ መስለው ያሽቃብጣሉ
የጉዳትህን ልኩን ሳያውቁ
ቁስልህን ረስተው......
ብዙዎች አሉ ቀላል ነው ብለው የሚሳለቁ
እናም......
ለአንተ ያለህ አንተው ነህና
መከራን ቻለው ቀና በልና ።

ፍቃዱ ግርማ / ዘ-በኩር /

t.me/fikee21
👏1
ናፍቀው ተነፋፍቀው
በትዝታ አልቀው
ከሰውነት ወጥተው
ከተስፋ ስር ወድቀው

የተያዩ ለታ ሰላም ሲባባሉ
ማንም ሳይሰማቸው....
በልባቸው ደሴት ፍቅርን ያዜማሉ ።

ፍቃዱ ግርማ [ ዘ-በኩር]

t.me/fikee21
4👏1💘1
እግዚአብሔር ይመስገን 🙏🙏🙏

t.me/fikee21
3🙏2
መልካም ነበረ.....
እጃችን ረጥቦ ብናሳርፈው ያን ምስኪን አባት
ውስጤ በንዴት ሳይቆጥር አመት
አካል መንፈሴ ሳይቀጣጠል ሳይለኩስ እሳት
መልካም ነበረ.....
ምትክ ለሌለው ለአንዱ ጌታ አለሁኝ ቢሉት
ምንም ቸግሮት ባይቆም ከሰው ፊት
መልካም ነበር.......
ግን ምን ያደርጋል.... ?
ቀኑ ሲከፋ ዘመን ሲዘምም
ልጅ ለአባቱ እንዴት አይሆንም?!

ከፋኝ መረረኝ.....
ወንድ ነኝና ሌሊት አለቀስኩ
ውለታው ከብዶኝ እየተሳቀኩ።

        

ፍቃዱ ግርማ  [ዘ-በኩር ]

t.me/fikee21
❤‍🔥11
ፍቅር ለማይገባው መተረክ ትዝታ
ናፍቆት ለማይገባው ማልቀስ መንታ መንታ
መወደድ ላልገባው እራስን መገብር
አስከዬት ነው መወደድ እሰከዬት ነው ፍቅር ?
አለኝ ሲሉት ማጣት
ኖርኩኝ ሲሉ መሞት
ቆምኩ ሲሉ መውደቅ
ዳንኩ ሲሉ መድቀቅ
መጡ ሲሉ መራቅ
ቻል እንግዲህ እራሴ.....
እንዲህ ነው አንዳንዴ እያነቡ መሳቅ ።
    
  ፍቃዱ ግርማ / ዘ-በኩር /

t.me/fikee21
4
"ባጭር ቀረን" ስንል - እድሜ ላበደሩን
ቀርፀው ላሳመሩን
ለኩሰው ላበሩን
ቺርስ!!
።።።።
ፊታችንን ዐይተው
እንደተቸገርን - ካይናችን ላወቁ
ስለማርያም ብለን
እስክንለምናቸው - ቆመው ላልጠበቁ
ቺርስ!!!
።።።።
ወድቀው ለማይጥሉ -ነግሰው ለሚያነግሱ
ነውራችንን ዐይተው
ልክ እንደ ድመት ኩስ ፣ ለሚያለባብሱ
ብድር አበድረው ፣ ፈጥነው ለሚረሱ😉
ቺርስ!!!!
።።።።።።
ላባ ላረጉልን ፣ የመከራ ሸክሙን
ቀልደው ላሳቁን ፣ ተጫውተው ላከሙን
በቸከ ዘመን ላይ...
ስጋ ለበስ ትንግርት -ሆነው ላስደመሙን
ቺርስ!!!!!
።።።።።።።።።።።
(✍️ Bewketu Seyoum )


t.me/fikee21
7