ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል
1.8K subscribers
55 photos
2 videos
1 file
327 links
........ኑ
ስሜትን በግጥም እንግለፅ
ትውልድን በጥበብ እናንፅ ።

የፍቅር ቤት እዚህ ነው !
አሰተያየት ካላችሁ
👇
@fikee12 ላይ ማድረስ ይቻላል
Download Telegram
በእውቀቱ_ስዩም
አገሬ

አገርን ለፈሪ፥ አይሰጡም አደራ
ዳር አድርጎት ያድራል፥ የማሀሉን ስፍራ፤

አገርን ለፈሪ፥ አደራ ብሰጠው
የዘላለም ቤቴን፥ ባንድ አዳር ለወጠው፤

አባ ነጋ ሞቶ

አባ ጽልመት መጥቶ

አገሬ እንደ ዛጎል፥ እያብረቀረቀች
ከባሕር ተገፍታ፥ የብስ ላይ ወደቀች።
14
❝ዝም ስትል የማታውቅ የሚመስላቸው ብዙ ናቸው..ምክንያቱም እነሱ በማውራት ያምናሉና ነገር ግን ያወሩትን አይኖሩትም።...አንተ ግን በማውራት አትመን ዝም ብለህ ልታወራ የፈለከውን ኑረው ከዛም ባንተ ዝምታ ውስጥ የኖርከው ህይወት ጥሶ ይወጣና አንተ ዝም እንዳልክ ሳታወራ ሰዎች ያወሩልሃል።❞

"እመጓ" ( ዶ/ር አለማየሁ ዋሴ እሼቴ /


t.me/fikee21
9
በሀሳብ ተውጬ እጄን በአፌ ጫንኩኝ
ማታ ባልሺኝ ነገር ፈገግ ስል ዋልኩኝ
ይጎሰማል እሄው ልቤ እንደ ከበሮ
ይወዘወዘኛል ያንቺው ፍቅር አስሮ ።

ፍቃዱ ግርማ / ዘ-በኩር /

t.me/fikee21
እድሜ ለበደልሽ
እድሜ ለጭካኔሽ
እድሜ ላንቺ ክፋት
ላንቺ ይብላኝ እንጂ...
እኔማ.....
እንደ ምንም  ብዬ ያቺን ቀን አለፍኳት ።

እድሜ ላንቺ እድሜ ኑሪ ነፍ አመት
ማድመጥ ጀምሪያለሁ የእራሴን ልብ ምት
ምንድን ነው ትዝታ ምን ያደርጋል ናፍቆት
ምን ያደርጋል ትላንት
ምን ያደርጋል ፀፀት ላለፈ እንደ ዘበት ።

እና
ወደ አሻሽ ሂጂ
ያሻሽን አፍቅሪ ያሻሽን ውደጂ
ከኔ የተሻለ ሰው አግኝተሽ  እንደሁ
ይቅናሽ ብዬሻለሁ ።

ፍቃዱ ግርማ / ዘ-በኩር /


t.me/fikee21
2
ብዙ ግዜ አያቴ ጋር ቁጭ ብዬ  የምትነግረኝ እሰማት ነበር ።

አንድ ቀን ማታ ቁጭ ብለን ሰለነጌ መጨነቀን እያወራን ነብር ። ከማሃል አያቴ ስሙ ልጆች ስትል ቀጠለች ። ንጉሱ የሆነችን ሴት ነጌ ጣዋት ሁለት አንገት ያለው ፈረስ ካላመጣሽ ከነ ቤተሰብሽ እስራት ነው የማስተላለፍባችሁ ይላታል ። ሴትዮዋ ጨነቃት ጠበባት እናም ወደ ጎረቢት ሄዳ ትቀመጣለች ትነሳለች ግራ የተጋቡት ጎረቢቶቿ ምን ሆነሻል ሲሉ ጠየቋት ? ንጉሱ ያላትን ነገር ነገረቻቸው አንዱ ሰውዬ እና ለዚ ነው የምትጨነቂው አላት?  አዎ አለች ። ሰውዬው አይዞሽ ለሊቱን ወይ ሁለት አንገት ያለው ፈረስ ተወልዶ ያድራል ወይ ንጉሱ ይሞታሉ ዝም ብለሽ ተኚ አላት ። ሲነጋ ንጉሱ ሞቱ ተበለ ። አያችሁ ነጌን አቅዱ እንጂ አትጨነቁ አለቺን አያቴ ።


t.me/fikee21
ይቅር በለን
( በእውቀቱ ስዩም)

የዘራም አጨደ
ያጨደም አስገባ
ያስገባም ጋገረ
የጋገረም በላ"
ከዚያ ምን ይመጣል
ፍርፍር ሆኖ ገብቶ: ፍግ ሁኖ ይወጣል::

በሸመታም ይሁን: በወራሪ ዝርፍያ
በስርአት ይሁን : በሽምያ በግፍያ
በግብዣም ይድረሰን: ወይ በመቀላወጥ
የምንበላው ህብስት: የምንጨልፈው ወጥ
ማለፍያው ሰርገኛው: ዶሮና ምስሩ
ወደታች ስንምሰው : ብዝበዛ ነው ስሩ::

የርግማኑን ራስ : ሆድ ይዘን ተፈጥረን
መቸገር ሳያንሰን
ለጠበቃ አልባዎች ሸክም አሸጋግረን
ከጥንት እስከዛሬ
ጭንቅህን በልሳን ተርጉመህ ባትነግረን
ይቅር በለን በሬ
አህያ ሆይ ማረን!!
10
ሻማዬን ለኩሼ
እጣኑን አጭሼ
በቀጤማ ጉዝጎዝ ቤቴን አሳምሬ
ከአንድ ጠርሙስ ጋር ብርጭቆ ደርድሬ
ሽር ጉድ እያልኩኝ ስጠብቅሽ ውዬ
መቅረትሽ ሳይገባኝ ፣
ከንቱ ነው የደከምኩ ትመጫለሽ ብዬ ።

ፍቃዱ ግርማ / ዘ-በኩር /

t.me/fikee21
5
ሰው ግን ምን አይነት ክፉ ፍጥረት ነው በማርያም ።
5
መኖር ምን ሆኖ ነው እንዲህ የሚያደክመው...... ?

Elias shitahun

t.me/@fikee21
እኔኑ ገረመኝ የጥርሴ ክፋቱ
ማታ ሊያስለቅሰኝ ከሰው ፊት መፍካቱ ።

ፍቃዱ ግርማ / ዘ -በኩር /

t.me/fikee21
5
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
1
ሁሉም ያልፋል ።

አልኩኝ ለብቻዬ
8👌2
ሁሉም ሲጠምም ቀን ሲከፋብን
ኃጢያቱ በዝቶ ፀሎት ጠፋብን ።

ፍቃዱ ግርማ / ዘ-በኩር /

t.me/fikee21
2👏2