ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል
1.79K subscribers
55 photos
2 videos
1 file
327 links
........ኑ
ስሜትን በግጥም እንግለፅ
ትውልድን በጥበብ እናንፅ ።

የፍቅር ቤት እዚህ ነው !
አሰተያየት ካላችሁ
👇
@fikee12 ላይ ማድረስ ይቻላል
Download Telegram
በነብስሽ ሰይፍ ሲያልፍ
አይሁድ ተሰብስበው..
ተወዳጁ ልጅሽ በአደባባይ ሲገረፍ
የጅራፉ ብዛት ለቁጥር የጠፋው
የጀርባው ግርፋት ልብሽን ሲያደማው
ተጠማሁ ሲል ጌታ በሚያሳዝን ልሳን
እመቤቴ ማርያም ምን ቃል ወጥቶሽ ይሆን
ምን ተናግረሽ ይሆን
እንዴት ብለሽ ይሆን
ባህር ለይ የቆሙ....
ዘለላ እግሮቹ በችንካር ሲመቱ
ማንም ሰው ሳይሰማሽ ምን አልሽ አዛኝቱ ??

ፍቃዱ ግርማ / ዘ - በኩር /

t.me/fikee21
t.me/fikee21
10
እንኳን ለጌታችን ለመዳኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ ፡፡

መልካም ፋሲካ 🙏

t.me/fikee21
6
ዝናቡ ሲያካፋ ፣
ንፋሱ ስነፍስ ሰው በሩን ሲዘጋ
እባክሽ አትጨክኝ ፣
እጅሽን ከፍ አርጊ ከጥላሽ ልጠጋ ።


ፍቃዱ ግርማ / ዘ-በኩር /

t.me/fikee21
8
This media is not supported in the widget
VIEW IN TELEGRAM
3
/ ገፅ 228 /

  ዮርዳኖስ  ጉዕሽ

ዛሬ የመጨረሻ ወሳኔዬን ታጥቂያለሁ ። እያንዳንዱ ትንፋሼ የምክንያት ነች ። የነገን የስሌት ቅመራ ያልተቀበለች ። ነገ ምንድነው?  የራሱ ነው ። የሚያመጣውን ራሱ ያውቃል ፤ መፍትሔውም ከጎኑ ነው ። ነገ ይቅናው ።


ፍቃዱ ግርማ / ዘ - በኩር /
4
ክፉ ሰው እራሴ ለመሆኔ ምስክር አልሻም!

t.me/fikee21
🤝6
እንደምነሽ አንቺው ለውሎሽ ለአዳሩ
እኔንስ ሆድ ባሰኝ ሲገረፍ ክራሩ ።

ፈቃዱ ግርማ ( ዘ-በኩር )

t.me/fikee21
3
ፊት ለፊቴ ዛሬ ሳያት
ቃል አጣሁኝ ምን ልበላት
ምን ልበላት በአንደበቴ
ጥሎኝ ሸሽቷል እኔነቴ ።

ፍቃዱ ግርማ ( ዘ - ዘበኩር )

t.me/fikee21
ትጎዛለች አህየው
በውጥንቅጥ መኖር
ሀሳብ ተሸክማ ተራራ የሚያክል
እናት ግን መቼ ነው ልቧ እርፍ የሚል ?
መቼ ነው የሷ ቀን ለራሷ የምትኖረው
ልጄ ሳትል ወላ ሌቱን የምታድረው
መቼ ነው ?

እናትነት የማይፈታ ሚስጥር ።

ፍቃዱ ግርማ  ( ዘ - በኩር )
9
መድፉ ሳይተኮስ ቦምቡ ሳይፈነዳ
ያ ሁሉ መኩዋንንት እንደ በግ ተነዳ ።

t.me/fikee21
👍43
የፍየል ወጠጤ ፣
ትክሻው ያበጠ ልቡ ያበጠበት
እንዋጋ ብሎ ከነብር ላከበት ።

አሉ ።

t.me/fikee21
2👏2
በእውቀቱ_ስዩም
አገሬ

አገርን ለፈሪ፥ አይሰጡም አደራ
ዳር አድርጎት ያድራል፥ የማሀሉን ስፍራ፤

አገርን ለፈሪ፥ አደራ ብሰጠው
የዘላለም ቤቴን፥ ባንድ አዳር ለወጠው፤

አባ ነጋ ሞቶ

አባ ጽልመት መጥቶ

አገሬ እንደ ዛጎል፥ እያብረቀረቀች
ከባሕር ተገፍታ፥ የብስ ላይ ወደቀች።
14
❝ዝም ስትል የማታውቅ የሚመስላቸው ብዙ ናቸው..ምክንያቱም እነሱ በማውራት ያምናሉና ነገር ግን ያወሩትን አይኖሩትም።...አንተ ግን በማውራት አትመን ዝም ብለህ ልታወራ የፈለከውን ኑረው ከዛም ባንተ ዝምታ ውስጥ የኖርከው ህይወት ጥሶ ይወጣና አንተ ዝም እንዳልክ ሳታወራ ሰዎች ያወሩልሃል።❞

"እመጓ" ( ዶ/ር አለማየሁ ዋሴ እሼቴ /


t.me/fikee21
9
በሀሳብ ተውጬ እጄን በአፌ ጫንኩኝ
ማታ ባልሺኝ ነገር ፈገግ ስል ዋልኩኝ
ይጎሰማል እሄው ልቤ እንደ ከበሮ
ይወዘወዘኛል ያንቺው ፍቅር አስሮ ።

ፍቃዱ ግርማ / ዘ-በኩር /

t.me/fikee21
እድሜ ለበደልሽ
እድሜ ለጭካኔሽ
እድሜ ላንቺ ክፋት
ላንቺ ይብላኝ እንጂ...
እኔማ.....
እንደ ምንም  ብዬ ያቺን ቀን አለፍኳት ።

እድሜ ላንቺ እድሜ ኑሪ ነፍ አመት
ማድመጥ ጀምሪያለሁ የእራሴን ልብ ምት
ምንድን ነው ትዝታ ምን ያደርጋል ናፍቆት
ምን ያደርጋል ትላንት
ምን ያደርጋል ፀፀት ላለፈ እንደ ዘበት ።

እና
ወደ አሻሽ ሂጂ
ያሻሽን አፍቅሪ ያሻሽን ውደጂ
ከኔ የተሻለ ሰው አግኝተሽ  እንደሁ
ይቅናሽ ብዬሻለሁ ።

ፍቃዱ ግርማ / ዘ-በኩር /


t.me/fikee21
2
ብዙ ግዜ አያቴ ጋር ቁጭ ብዬ  የምትነግረኝ እሰማት ነበር ።

አንድ ቀን ማታ ቁጭ ብለን ሰለነጌ መጨነቀን እያወራን ነብር ። ከማሃል አያቴ ስሙ ልጆች ስትል ቀጠለች ። ንጉሱ የሆነችን ሴት ነጌ ጣዋት ሁለት አንገት ያለው ፈረስ ካላመጣሽ ከነ ቤተሰብሽ እስራት ነው የማስተላለፍባችሁ ይላታል ። ሴትዮዋ ጨነቃት ጠበባት እናም ወደ ጎረቢት ሄዳ ትቀመጣለች ትነሳለች ግራ የተጋቡት ጎረቢቶቿ ምን ሆነሻል ሲሉ ጠየቋት ? ንጉሱ ያላትን ነገር ነገረቻቸው አንዱ ሰውዬ እና ለዚ ነው የምትጨነቂው አላት?  አዎ አለች ። ሰውዬው አይዞሽ ለሊቱን ወይ ሁለት አንገት ያለው ፈረስ ተወልዶ ያድራል ወይ ንጉሱ ይሞታሉ ዝም ብለሽ ተኚ አላት ። ሲነጋ ንጉሱ ሞቱ ተበለ ። አያችሁ ነጌን አቅዱ እንጂ አትጨነቁ አለቺን አያቴ ።


t.me/fikee21
ይቅር በለን
( በእውቀቱ ስዩም)

የዘራም አጨደ
ያጨደም አስገባ
ያስገባም ጋገረ
የጋገረም በላ"
ከዚያ ምን ይመጣል
ፍርፍር ሆኖ ገብቶ: ፍግ ሁኖ ይወጣል::

በሸመታም ይሁን: በወራሪ ዝርፍያ
በስርአት ይሁን : በሽምያ በግፍያ
በግብዣም ይድረሰን: ወይ በመቀላወጥ
የምንበላው ህብስት: የምንጨልፈው ወጥ
ማለፍያው ሰርገኛው: ዶሮና ምስሩ
ወደታች ስንምሰው : ብዝበዛ ነው ስሩ::

የርግማኑን ራስ : ሆድ ይዘን ተፈጥረን
መቸገር ሳያንሰን
ለጠበቃ አልባዎች ሸክም አሸጋግረን
ከጥንት እስከዛሬ
ጭንቅህን በልሳን ተርጉመህ ባትነግረን
ይቅር በለን በሬ
አህያ ሆይ ማረን!!
10