ሰማይ ጠቀስ ጥፋት ቤቴን ስለሞላው
አምላኬ ንገረኝ.... ?
እኔ ግን አንተ ጋር ሚዛኔ ስንት ነው ?
እየዘነጋሁኝ...
ገነትን ታክል ቤት አንተን ያክል አባት
እኔኮ ድፍረቴ...
መጥቼ እቆማለሁ ደግሜ ካንተ ፊት
እባክህን አምላክ እባክህን ጌታ
ልቤን ገስፅልኝ እንዳላመነታ
እንዳላፈገፍግ ከትልቁ ክብር
አግዘኝ ልከተል የመስቀሉን ፍቅር ።
ደግፍኝ ልሻገር ልላቀቅ ከኃጢያት
ያቺን መሪር ግዛት ሶዖልን ልልፋት
እቀፈኝ በክንድህ ለደቂቃ አልውጣ
አንተው ያዘኝ ፣
አለም መቼም አታዋጣ ።
እረ አንተው ተቆጣኝ
እረ አንተው ግረፈኝ
እረ አንተው ገስፀኝ
እረ አንተው መልሰኝ
እኔማ አልሆነኝም......
የጀመርኩት መንገድ ጭራሽ እያጠፋኝ።
ሰማይ ጠቀስ ጥፋት ቤቴን ስለሞላው
አምላኬ ንገረኝ... ?
እኔ ግን አንተ ጋር ሚዛኔ ስንት ነው?
ስንት ነው ተመኑ ለነብሴ የደከምኩት
ስንቴ ነው በአንተ ስም አለምን የጣልኳት ???
ስንት ነው የሚል ቃል እኔ እማበዛብህ
ተመኔን ሚዛኔን የደጋገምኩብህ
ነብሴ ተጨናንቃ ፍፁም ሰላመመኝ
መላ ሲጠፋኝ ነው...
እኝኝ የምልብህ አትቀየምብኝ ።
እና
ሰማይ ጠቀስ ጥፋት ቤቴን ስለሞላው
ንገረኝ አምላኬ... ?
እኔ ግን አንተ ጋር ሚዛኔ ስንት ነው ።
ፍቃዱ ግርማ / ዘ-በኩር /
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
አምላኬ ንገረኝ.... ?
እኔ ግን አንተ ጋር ሚዛኔ ስንት ነው ?
እየዘነጋሁኝ...
ገነትን ታክል ቤት አንተን ያክል አባት
እኔኮ ድፍረቴ...
መጥቼ እቆማለሁ ደግሜ ካንተ ፊት
እባክህን አምላክ እባክህን ጌታ
ልቤን ገስፅልኝ እንዳላመነታ
እንዳላፈገፍግ ከትልቁ ክብር
አግዘኝ ልከተል የመስቀሉን ፍቅር ።
ደግፍኝ ልሻገር ልላቀቅ ከኃጢያት
ያቺን መሪር ግዛት ሶዖልን ልልፋት
እቀፈኝ በክንድህ ለደቂቃ አልውጣ
አንተው ያዘኝ ፣
አለም መቼም አታዋጣ ።
እረ አንተው ተቆጣኝ
እረ አንተው ግረፈኝ
እረ አንተው ገስፀኝ
እረ አንተው መልሰኝ
እኔማ አልሆነኝም......
የጀመርኩት መንገድ ጭራሽ እያጠፋኝ።
ሰማይ ጠቀስ ጥፋት ቤቴን ስለሞላው
አምላኬ ንገረኝ... ?
እኔ ግን አንተ ጋር ሚዛኔ ስንት ነው?
ስንት ነው ተመኑ ለነብሴ የደከምኩት
ስንቴ ነው በአንተ ስም አለምን የጣልኳት ???
ስንት ነው የሚል ቃል እኔ እማበዛብህ
ተመኔን ሚዛኔን የደጋገምኩብህ
ነብሴ ተጨናንቃ ፍፁም ሰላመመኝ
መላ ሲጠፋኝ ነው...
እኝኝ የምልብህ አትቀየምብኝ ።
እና
ሰማይ ጠቀስ ጥፋት ቤቴን ስለሞላው
ንገረኝ አምላኬ... ?
እኔ ግን አንተ ጋር ሚዛኔ ስንት ነው ።
ፍቃዱ ግርማ / ዘ-በኩር /
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👌8❤7👏2
ለመጣ ለሄደው ልቡ ከባከነ
እግሩ መቆሚያ አጥቶ ሁሌ ከኳተነ
አእምሮ ሀሳቡ ከጠፋበት ውሉ
ማንም ሰው ሳይነካው፣
ደርሶ ካስቀየመው የገዛ አመሉ
በግርድፍ ፍርዳችን እብድ ነው ሳንለው
እንዲህ አይነቱን ሰው
በፍጥነት እንርዳው ።
ፍቃዱ ግርማ / ዘ-በኩር /
t.me/fikee21
እግሩ መቆሚያ አጥቶ ሁሌ ከኳተነ
አእምሮ ሀሳቡ ከጠፋበት ውሉ
ማንም ሰው ሳይነካው፣
ደርሶ ካስቀየመው የገዛ አመሉ
በግርድፍ ፍርዳችን እብድ ነው ሳንለው
እንዲህ አይነቱን ሰው
በፍጥነት እንርዳው ።
ፍቃዱ ግርማ / ዘ-በኩር /
t.me/fikee21
❤3👏2🤝1
❤7🙏2
አታውቀውምና ፣
ዬት እንደሚያደርስህ የሕይወትህ መስመር
ቀድመህ በማንም ለይ ጣትህን አትቀስር
እናም....
ካለሆነ ለመውደድ
አትቸኩል ለመፍረድ ።
ፍቃዱ ግርማ / ዘ-በኩር/
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
ዬት እንደሚያደርስህ የሕይወትህ መስመር
ቀድመህ በማንም ለይ ጣትህን አትቀስር
እናም....
ካለሆነ ለመውደድ
አትቸኩል ለመፍረድ ።
ፍቃዱ ግርማ / ዘ-በኩር/
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
❤2👏2
በነብስሽ ሰይፍ ሲያልፍ
አይሁድ ተሰብስበው..
ተወዳጁ ልጅሽ በአደባባይ ሲገረፍ
የጅራፉ ብዛት ለቁጥር የጠፋው
የጀርባው ግርፋት ልብሽን ሲያደማው
ተጠማሁ ሲል ጌታ በሚያሳዝን ልሳን
እመቤቴ ማርያም ምን ቃል ወጥቶሽ ይሆን
ምን ተናግረሽ ይሆን
እንዴት ብለሽ ይሆን
ባህር ለይ የቆሙ....
ዘለላ እግሮቹ በችንካር ሲመቱ
ማንም ሰው ሳይሰማሽ ምን አልሽ አዛኝቱ ??
ፍቃዱ ግርማ / ዘ - በኩር /
t.me/fikee21
t.me/fikee21
አይሁድ ተሰብስበው..
ተወዳጁ ልጅሽ በአደባባይ ሲገረፍ
የጅራፉ ብዛት ለቁጥር የጠፋው
የጀርባው ግርፋት ልብሽን ሲያደማው
ተጠማሁ ሲል ጌታ በሚያሳዝን ልሳን
እመቤቴ ማርያም ምን ቃል ወጥቶሽ ይሆን
ምን ተናግረሽ ይሆን
እንዴት ብለሽ ይሆን
ባህር ለይ የቆሙ....
ዘለላ እግሮቹ በችንካር ሲመቱ
ማንም ሰው ሳይሰማሽ ምን አልሽ አዛኝቱ ??
ፍቃዱ ግርማ / ዘ - በኩር /
t.me/fikee21
t.me/fikee21
❤10
❤6
❤8
❤3
❤1
❤2👏2
❝ዝም ስትል የማታውቅ የሚመስላቸው ብዙ ናቸው..ምክንያቱም እነሱ በማውራት ያምናሉና ነገር ግን ያወሩትን አይኖሩትም።...አንተ ግን በማውራት አትመን ዝም ብለህ ልታወራ የፈለከውን ኑረው ከዛም ባንተ ዝምታ ውስጥ የኖርከው ህይወት ጥሶ ይወጣና አንተ ዝም እንዳልክ ሳታወራ ሰዎች ያወሩልሃል።❞
"እመጓ" ( ዶ/ር አለማየሁ ዋሴ እሼቴ /
t.me/fikee21
"እመጓ" ( ዶ/ር አለማየሁ ዋሴ እሼቴ /
t.me/fikee21
❤9
በሀሳብ ተውጬ እጄን በአፌ ጫንኩኝ
ማታ ባልሺኝ ነገር ፈገግ ስል ዋልኩኝ
ይጎሰማል እሄው ልቤ እንደ ከበሮ
ይወዘወዘኛል ያንቺው ፍቅር አስሮ ።
ፍቃዱ ግርማ / ዘ-በኩር /
t.me/fikee21
ማታ ባልሺኝ ነገር ፈገግ ስል ዋልኩኝ
ይጎሰማል እሄው ልቤ እንደ ከበሮ
ይወዘወዘኛል ያንቺው ፍቅር አስሮ ።
ፍቃዱ ግርማ / ዘ-በኩር /
t.me/fikee21