ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል
1.79K subscribers
55 photos
2 videos
1 file
327 links
........ኑ
ስሜትን በግጥም እንግለፅ
ትውልድን በጥበብ እናንፅ ።

የፍቅር ቤት እዚህ ነው !
አሰተያየት ካላችሁ
👇
@fikee12 ላይ ማድረስ ይቻላል
Download Telegram
ካወሩት ይልቅ በልብ የያዙት ይበልጣል ።

t.me/fikee21
4
:::::::::::::::::::::::::

አንቺ ባለቀሚስ
ስምሽ በአለም ይንገስ ።
ከቀናትም ቀናት
ከሳምንትም ሳምንት
ከውራትም ወራት
ከአመት እስከ አመት
አይለይሽ ከቶ የእግዜር ምህረት
ለምን..... ?
አላለፍሽምና ቃል ኪዳን ትዛዛት ።

  ፍቃዱ ግርማ / Zበኩር /


t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
10
ለነ አፍዝ አደንግዝ
ለነ ጥላ ወጊ
ለመጫኛ ነካሽ
ለነ ወስዶ ወቃሽ

ለኮኮብ ቆጣሪ...
ለአህያ ጋላቢ
ለጠንቋይ ኮተታም
ለመተት ሰብሳቢ
አሳልፋ ሰጥታኝ ደግሞ ትስቃለች
አቦ ጥርሷ ይርገፍ እኔን ገላኛለች ።

ፍቃዱ ግርማ / ዘ - በኩር /

t.me/fikee21
3
አበክሬ ስወድቅ....
የኔ መንፈስ ሲጃጅ
ድንግል ሆይ አግዢኝ.....
የእናት ምልጃ ነው ስኬት የሚያቀዳጅ ።

ፍቃዱ ግርማ / ዘ-በኩር /

t.me/fikee21
13🙏2
መልካም ሰንበት!

ፍቃዱ ግርማ /ዘ-በኩር/

t.me/fikee21
3
አደዋ

የነፃነታችን አርማ
የኢትዮጵያ ማማ
የማይጠፋ ደማቅ አሻራ
አደዋ የደም ማህተም ......
ለዘላለም የሚያኮራ ።

እንኳን ለ130ኛው የአደዋ ድል በዓል አደረሳችሁ ። አደረሰን!

ፍቃዱ ግርማ / ዘ-በኩር/

t.me/fikee21
3
https://youtu.be/zPv5UOwIJiU?si=QP0Y5-qpDViXJvPB

ይህ የሸበላው
የጋዜጠኛው
የገጣሚው
የደራሲው
የተውኔት አዘጋጁ
የግል ስብዕና አሰልጣኙ
የማለዳ ኮኮብ ድምቀት የነበረው
የዳዊት ለማ ኦፊሻል YouTube Channel ሰለሆነ ሊንኩን በመንካት እገባችሁ Subscriber ስለምታደርጉ እናመሰግናለን ።🙏🙏🙏🙏

ፍቃዱ ግርማ / ዘ-በኩር /

t.me/fikee21
2
የመሪጌታዎችን ግሩብ ከላዬ ለይ የሚደመስስ መፍትሄ ግን የለም ወገን ?? ስልችት አለኝ የምር!
🙏31
ታሚኛለሽ አሉ!
ሞኝ ነው እያልሺኝ
አይችልም ትያለሽ....
ጠልፈሽ እየጣልሺኝ
መውደቂያ እንዳጣ እንዳይኖረኝ ወዝ
አስተበተብሺብኝ በሰባት ጠንቋይ.....
በደብተራ ምርኩዝ ።

እናም.........
ይብላኝ ብቻ ላንቺ....
ኃጢያት ላደረግሽ
ክፋትን ለዘራሽ
እኔስ እኖራለሁ ህመሜን ጨክኜ
ድምፅ ሳላወጣ ጩህቴን አፍኜ
የመሰለችኝን አንዲቷን አግብቼ
ብቻ እኖራለሁ..........
እኔ ላንቺ ጥፋት ንስሐ ገብቼ ።

ፍቃዱ ግርማ /ዘ-በኩር/

t.me/fikee21
8
የተሰናበተን ልቡ የቆረጠ.....
እርቆ የሄደ ሌላ የወደደ
መማፀን ከንቱ ነው ቀኑ ከረፈደ ።

ምን ቢነጠፉለት
ልብን ቢከፍቱለት
ከቶ አይታየውም ሌላ የወደደ
ይቅርታ ምኑ ነው ሞቆ ለበረደ ።

እናም.......
ቁልቁል ለረገጡት ግዜን ተንተርሰው
ምንድን ነው መንሰፍሰፍ.....
ደግሞ ተመልሰው
ምንድን ነው ማልቀሱ....
በድለው ለሸኙት
ምንድን ነው ይቅርታ..
በናፍቆት ለቀጡት ???

እናም.....
የተሰናበተ ልቡ የቆረጠ..
እርቆ የሄደ ሌላ የወደደ
መማፀን ከንቱ ነው ቀኑ ከረፈደ ።

ፍቃዱ ግርማ /ዘ-በኩር/

t.me/fikee21
8👏3
Forwarded from የግጥሜ አሻራ.... (Bitseat )
እንደ ቤት...እንደልብስ...እንደ  ራስ
  እንደ ሀገር
   ቢቻልማ  ኖሮ  ትላንትን  መቀየር
ካገኘሁሽ  ቦታ  ትቼሽ አልፍ  ነበር


ብፅእት ስዩም
15❤‍🔥2👍1
መንፈሳዊ ሰው የእግዚአብሔር አምሳል ነው ።

መንፈሳዊ ስው ብርቱ ነው ።

መንፈሳዊ ሰው ጠንካራ ሞራል አለው ።

መንፈሳዊ ስው ልቡ ከእግዚአብሔር ጋር ነው ።

መንፈሳዊ ሰው ከጉዳዮቹ በፊት እግዚአብሔርን ያስቀድማል ።

መንፈሳዊ ሰው በመታዘዝ እግዚአብሔርን ያስቀድማል ።

መንፈሳዊ ስው ለእግዚአብሔርም ለሰዎቾም ይታዘዛል ።

መንፍሳዊ ሰው አንዱ ችሎታው ጥልቀት ነው ።

መንፈሳዊ ሰው ልቡ በእግዚአብሔር ፊት የቀና ነው ።

'' ቃልህ ለጉሮሮዬ ጣፋጭ ነው ፤ ከማርና ከወለላ ይልቅ ለአፌ ጣፈጠኝ '' መዝ 118፡103 ።

ፍቃዱ ግርማ /ዘ-በኩር/

t.me/fikee21
14💯1
የልብ ትልቁ ተግባር የተሰወረውን ማየት ነው ።

ፍቃዱ ግርማ /ዘ-በኩር/

t.me/fikee21
6👏3
ፍሬ የሌለው ድካም አቁሙ ።

t.me/fikee21
7🤝1
እሳት ወይ አበባ

ሎሬት ፀጋዬ  ገ/መድህን

ወንድ ብቻውን ነው እሚያለቅስ

ከወዳጅ ዘመድ ርቆ
አንጀቱን በአንጀቱ ታጥቆ
ተሸሸጎ ተገልሎ ፥ ተሸማቆ ተሸምቆ
ከቤተ - ሰው ተደብቆ
መሽቶ የማታ ማታ ነው ፥ ሌት ነው የወንድ    
                               ልጅ እንባው
ብቻውን ነው የሚፈታው .......
ብቻውን ነው የሚረታው .......
ችሎ ፥ ወጦ ፥ ተጨብጦ ፥ ተማምጦ
                                 ተጣጥሮ
በሲቃ ግት ተወጥሮ
እንደ ደመና ተቋጥሮ
እውስጥ አንጀቱ ተቀብሮ ....
መሽቶ ፥ ረፍዶ ፥ ጀምበር ጠልቆ
የጨለማ ድባብ ወድቆ
በእንቅልፍ ጥላ ሲከበብ ፥ በዝምታ   
                             ሲዋጥ አገር
ፍጡር ሁሉ ተሰለምልሞ ፥ ብቸኝነት
                   ብቻ  ሲቀር ......
የኃላ የኃላ ማታ
ምድር አገሩ በእፎይታ
አይኑን በእንቅልፍ ሲያስፈታ
ሁሉ በእረፍት ዓለም ርቆ ፥ ብቸኝነት
                             ብቻ ሲቀርብ
ያኔ ነው ወንድ አይኑ የሚረጥብ
የብቻ ፥ እንባ አይኑ የሚረጥብ ።
    .......................

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
12🙏1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2
ለከፋው መድሃኒት ደርሶ ለጨነቀው
እስኪ ወዲ በሉኝ ፣
መላ መፍትሔውን ጠንቅቄ ልወቀው ።

Sad Feeling 😞

ዘ - በኩር

t.me/fikee21
6
ሰማይ ጠቀስ ጥፋት ቤቴን ስለሞላው
አምላኬ ንገረኝ.... ?
እኔ ግን አንተ ጋር ሚዛኔ ስንት ነው ?
እየዘነጋሁኝ...
ገነትን ታክል ቤት አንተን ያክል አባት
እኔኮ ድፍረቴ...
መጥቼ እቆማለሁ ደግሜ ካንተ ፊት
እባክህን አምላክ እባክህን ጌታ
ልቤን ገስፅልኝ እንዳላመነታ
እንዳላፈገፍግ ከትልቁ ክብር
አግዘኝ ልከተል የመስቀሉን ፍቅር ።

ደግፍኝ ልሻገር ልላቀቅ ከኃጢያት
ያቺን መሪር ግዛት ሶዖልን ልልፋት
እቀፈኝ በክንድህ ለደቂቃ አልውጣ
አንተው ያዘኝ ፣
አለም መቼም አታዋጣ ።

እረ አንተው ተቆጣኝ
እረ አንተው ግረፈኝ
እረ አንተው ገስፀኝ
እረ አንተው መልሰኝ
እኔማ አልሆነኝም......
የጀመርኩት መንገድ ጭራሽ እያጠፋኝ።

ሰማይ ጠቀስ ጥፋት ቤቴን ስለሞላው
አምላኬ ንገረኝ... ?
እኔ ግን አንተ ጋር ሚዛኔ ስንት ነው?

ስንት ነው ተመኑ ለነብሴ የደከምኩት
ስንቴ ነው በአንተ ስም አለምን የጣልኳት ???

ስንት ነው የሚል ቃል እኔ እማበዛብህ
ተመኔን ሚዛኔን የደጋገምኩብህ
ነብሴ ተጨናንቃ ፍፁም ሰላመመኝ
መላ ሲጠፋኝ ነው...
እኝኝ የምልብህ አትቀየምብኝ ።

እና
ሰማይ ጠቀስ ጥፋት ቤቴን ስለሞላው
ንገረኝ አምላኬ... ?
እኔ ግን አንተ ጋር ሚዛኔ ስንት ነው ።

ፍቃዱ ግርማ / ዘ-በኩር /

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👌87👏2
ለመጣ ለሄደው ልቡ ከባከነ
እግሩ መቆሚያ አጥቶ ሁሌ ከኳተነ
አእምሮ ሀሳቡ ከጠፋበት ውሉ
ማንም ሰው ሳይነካው፣
ደርሶ ካስቀየመው የገዛ አመሉ
በግርድፍ ፍርዳችን እብድ ነው ሳንለው
እንዲህ አይነቱን ሰው
በፍጥነት እንርዳው ።

ፍቃዱ ግርማ / ዘ-በኩር /

t.me/fikee21
3👏2🤝1