ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል
1.79K subscribers
55 photos
2 videos
1 file
327 links
........ኑ
ስሜትን በግጥም እንግለፅ
ትውልድን በጥበብ እናንፅ ።

የፍቅር ቤት እዚህ ነው !
አሰተያየት ካላችሁ
👇
@fikee12 ላይ ማድረስ ይቻላል
Download Telegram
እቺ በምስሉ ልይ የምናያት እናታችን አመቱ ገበየሁ ትባላለች በኦክስጅን ለ 3 አመት በደራ ጉንደ መስቀል የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታ እርዳታ ሲደርግላት የቆየ ቢሆንም አሁን ለይ ግን የተሻለ ህክምና አድርጋ ወደ ቤቷ እንድትመለስ ስንል እርዳታችሁን እንፈልጋለን ። እናታችንን እናድናት ይህ ከጎኗ የምታዩት ልጇም ህልሙን ያሳካ የእናቱን ሳቅ እንመልስለት ።

ለበለጠ መረጃ 0935983470
Dr. Tesfaye kebede
3
እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ ።

መልካም በዓል

t.me/fikee21
6
እግዚአብሔር ይመሰገን የምንለው ህይወት ያድለን አሜን ።
🙏14
ከማንነት በላይ ጥቅም በለጠና
መጠላለፍ በዛ ጠበበን ጎዳና

ፍቃዱ ግርማ [ ዘ-በኩር ]

t.me/fikee21
6👏3
ካወሩት ይልቅ በልብ የያዙት ይበልጣል ።

t.me/fikee21
4
:::::::::::::::::::::::::

አንቺ ባለቀሚስ
ስምሽ በአለም ይንገስ ።
ከቀናትም ቀናት
ከሳምንትም ሳምንት
ከውራትም ወራት
ከአመት እስከ አመት
አይለይሽ ከቶ የእግዜር ምህረት
ለምን..... ?
አላለፍሽምና ቃል ኪዳን ትዛዛት ።

  ፍቃዱ ግርማ / Zበኩር /


t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
10
ለነ አፍዝ አደንግዝ
ለነ ጥላ ወጊ
ለመጫኛ ነካሽ
ለነ ወስዶ ወቃሽ

ለኮኮብ ቆጣሪ...
ለአህያ ጋላቢ
ለጠንቋይ ኮተታም
ለመተት ሰብሳቢ
አሳልፋ ሰጥታኝ ደግሞ ትስቃለች
አቦ ጥርሷ ይርገፍ እኔን ገላኛለች ።

ፍቃዱ ግርማ / ዘ - በኩር /

t.me/fikee21
3
አበክሬ ስወድቅ....
የኔ መንፈስ ሲጃጅ
ድንግል ሆይ አግዢኝ.....
የእናት ምልጃ ነው ስኬት የሚያቀዳጅ ።

ፍቃዱ ግርማ / ዘ-በኩር /

t.me/fikee21
13🙏2
መልካም ሰንበት!

ፍቃዱ ግርማ /ዘ-በኩር/

t.me/fikee21
3
አደዋ

የነፃነታችን አርማ
የኢትዮጵያ ማማ
የማይጠፋ ደማቅ አሻራ
አደዋ የደም ማህተም ......
ለዘላለም የሚያኮራ ።

እንኳን ለ130ኛው የአደዋ ድል በዓል አደረሳችሁ ። አደረሰን!

ፍቃዱ ግርማ / ዘ-በኩር/

t.me/fikee21
3
https://youtu.be/zPv5UOwIJiU?si=QP0Y5-qpDViXJvPB

ይህ የሸበላው
የጋዜጠኛው
የገጣሚው
የደራሲው
የተውኔት አዘጋጁ
የግል ስብዕና አሰልጣኙ
የማለዳ ኮኮብ ድምቀት የነበረው
የዳዊት ለማ ኦፊሻል YouTube Channel ሰለሆነ ሊንኩን በመንካት እገባችሁ Subscriber ስለምታደርጉ እናመሰግናለን ።🙏🙏🙏🙏

ፍቃዱ ግርማ / ዘ-በኩር /

t.me/fikee21
2
የመሪጌታዎችን ግሩብ ከላዬ ለይ የሚደመስስ መፍትሄ ግን የለም ወገን ?? ስልችት አለኝ የምር!
🙏31
ታሚኛለሽ አሉ!
ሞኝ ነው እያልሺኝ
አይችልም ትያለሽ....
ጠልፈሽ እየጣልሺኝ
መውደቂያ እንዳጣ እንዳይኖረኝ ወዝ
አስተበተብሺብኝ በሰባት ጠንቋይ.....
በደብተራ ምርኩዝ ።

እናም.........
ይብላኝ ብቻ ላንቺ....
ኃጢያት ላደረግሽ
ክፋትን ለዘራሽ
እኔስ እኖራለሁ ህመሜን ጨክኜ
ድምፅ ሳላወጣ ጩህቴን አፍኜ
የመሰለችኝን አንዲቷን አግብቼ
ብቻ እኖራለሁ..........
እኔ ላንቺ ጥፋት ንስሐ ገብቼ ።

ፍቃዱ ግርማ /ዘ-በኩር/

t.me/fikee21
8
የተሰናበተን ልቡ የቆረጠ.....
እርቆ የሄደ ሌላ የወደደ
መማፀን ከንቱ ነው ቀኑ ከረፈደ ።

ምን ቢነጠፉለት
ልብን ቢከፍቱለት
ከቶ አይታየውም ሌላ የወደደ
ይቅርታ ምኑ ነው ሞቆ ለበረደ ።

እናም.......
ቁልቁል ለረገጡት ግዜን ተንተርሰው
ምንድን ነው መንሰፍሰፍ.....
ደግሞ ተመልሰው
ምንድን ነው ማልቀሱ....
በድለው ለሸኙት
ምንድን ነው ይቅርታ..
በናፍቆት ለቀጡት ???

እናም.....
የተሰናበተ ልቡ የቆረጠ..
እርቆ የሄደ ሌላ የወደደ
መማፀን ከንቱ ነው ቀኑ ከረፈደ ።

ፍቃዱ ግርማ /ዘ-በኩር/

t.me/fikee21
8👏3
Forwarded from የግጥሜ አሻራ.... (Bitseat )
እንደ ቤት...እንደልብስ...እንደ  ራስ
  እንደ ሀገር
   ቢቻልማ  ኖሮ  ትላንትን  መቀየር
ካገኘሁሽ  ቦታ  ትቼሽ አልፍ  ነበር


ብፅእት ስዩም
15❤‍🔥2👍1
መንፈሳዊ ሰው የእግዚአብሔር አምሳል ነው ።

መንፈሳዊ ስው ብርቱ ነው ።

መንፈሳዊ ሰው ጠንካራ ሞራል አለው ።

መንፈሳዊ ስው ልቡ ከእግዚአብሔር ጋር ነው ።

መንፈሳዊ ሰው ከጉዳዮቹ በፊት እግዚአብሔርን ያስቀድማል ።

መንፈሳዊ ሰው በመታዘዝ እግዚአብሔርን ያስቀድማል ።

መንፈሳዊ ስው ለእግዚአብሔርም ለሰዎቾም ይታዘዛል ።

መንፍሳዊ ሰው አንዱ ችሎታው ጥልቀት ነው ።

መንፈሳዊ ሰው ልቡ በእግዚአብሔር ፊት የቀና ነው ።

'' ቃልህ ለጉሮሮዬ ጣፋጭ ነው ፤ ከማርና ከወለላ ይልቅ ለአፌ ጣፈጠኝ '' መዝ 118፡103 ።

ፍቃዱ ግርማ /ዘ-በኩር/

t.me/fikee21
14💯1
የልብ ትልቁ ተግባር የተሰወረውን ማየት ነው ።

ፍቃዱ ግርማ /ዘ-በኩር/

t.me/fikee21
6👏3