ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል
1.79K subscribers
55 photos
2 videos
1 file
328 links
........ኑ
ስሜትን በግጥም እንግለፅ
ትውልድን በጥበብ እናንፅ ።

የፍቅር ቤት እዚህ ነው !
አሰተያየት ካላችሁ
👇
@fikee12 ላይ ማድረስ ይቻላል
Download Telegram
ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል pinned «እውነት ከልባችሁ ለምትናፍቁን ስዎች ግን ክብሩልን ። ምንም ነገር ሳንነግራችሁ ለምትረዱን ስዎች ታላቅ ክብር አለኝ 🙏 ማደጋችን የሚያሳስባችሁ ስዎች እግዚአብሔር አምላክ እናንተንም በከፍታ ለይ ያኑራችሁ ። ሲደክመን ተስፋን ላሳያችሁን በሙሉ ከልብ እናመስግናለን ። ደግሞ ልብ እንበል ሰውን መጥቀም ካልቻልን አንጉዳው 🙏 ዘ - በኩር t.me/fikee21 t.me/fikee21 t.me/fikee21»
አይዞህ
የምን ተስፋ መቁረጥ
ሞክር ደግመህ ደግመህ
ሰነፍ አይደክመውም....
ሊሳካልህ ሲል ነው ፣
አለመቻልህን አብዝቶ 'ሚነግርህ ።

አይዞህ !

ዘ - በኩር

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍5
ሞኝ አትሁን !

ማንም ሊያድንህ አይመጣም

ወላጆችህም
ወዳጆችህም
አጋርህም ሆነ
ወይም ሌላ ተዐምር አያድንህም ።

አንተን የምታድነው አንተ ብቻ ነህ አባቴ ።

ዘ - በኩር

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍6
ስማኝማ.....

ሁሉንም ነገር ለማወቅ አትባክን የራስ የሆነ ነገር ለይ ብቻ አተኩር እንጂ ።

ዘ - በኩር

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
2💊1
መጣሁ ሰልችቶኛል
መጠበቅ ደክሞኛል
ቀጠሮ መሰረዝ
ቀን መቁጥር እንደርጉዝ
እመጣለሁ ብቻ የቃላት ጋጋታ
መማል መገዘቱ ለሌለው እውነታ
አልይዝም ቀጠሮ.....
ቋሚነት ለሌለው መጥቶ ለሚጠፋ
ሰልችቶታል ልቤ ወዶ እየተገፋ ።

ዘ - በኩር

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍51
ጨካኔ መጣብን
ሸሸነው አምላክን
ረሳን ተመስገንን
ለብቻ ታገልን
ላንሰራ አንድ ቀን
ጨነቀን ጠበበን ።
አናም.......
ስፎክር ሳቅራራ
እያልኩኝ ሀገሬ ፣
እንዴት ስው አያለ
ሰው ይራበኝ ዛሬ ።

ዘ - በኩር

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍131
አዘልኩሽ
አቀፍኩሽ
ሲበዛ ሳሳሁሽ
አይኔ ብሌኔ አልኩሽ ።

አንድ አለሜ ብዬ ወስኜ ቆርጬ
አንቺን አፈቀርኩኝ ከራሴ አብልጬ

ግና አንቺ ዛሬ.....
ገፋሺኝ እንደ ጉድ ረሳሺው ትላንትን
ረገጥሺው መወደዴን
አደማሺው ልቤን ።

እናም የኔ ቆንጆ....
ሰላም ግቢ አንቺ መሄድሽም ቢያመኝ
አመሰግናለሁ ስላጠነከርሺኝ ። 🙏

ዘ - በኩር

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍9
አምላኬ ሆይ አንተ ያልከው ይሁን 🙏🙏🙏
👍13
መዝ 6 : 9
እግዚአብሔር ልመናዬን ሰማኝ እግዚአብሔር ፀሎቴን ተቀበለ ።

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍121
ቴዲ አፍሮ

የኃላው ከሌለ የለም የፊቱ ።

ዘ - በኩር

t.me/fikee21
👍6
ከልብ ማፍቅር ሞኝነት ሆኖ አያውቅም ሞኝነት ከልብ እንደተፈቀረ እያወቀ ለሚሽሽ እንጂ ።

ልብ ከፍተው ያስገቡት ልብ ከፍቶ ቢወጣ አይደንቅም ድሮም '' የአህያ ስጋ አልጋ ቢሉት መሬት '' አደል የሚሉት አበው ።

ግልፅነትህን ርካሽ አድርገው ከገመቱት እንኳን ደስ አለህ ለምን ፅልመታቸው ለይ ያንተ ብርሃን ስለከበዳቸው ነው አባቴ ።

ሀሳብህን ስታወራቸው ተረት ከመሰላቸው ስማኝ ፈጥነህ ፈቀቅ በል ለአንተ የታየህ ለነሱ አልታይ ስላላቸው ነው ። ክብድ በልባቸው ።

ማፈቀር ትልቅ ፀጋ ነው አብዝተህ ውደድ አብዝተህ አፍቅር ሁሌም ቢሆን በፍቅር ውስጥ ኑር በቃ የፍቅር ጥግ የለውም ዝም ብለህ አፍቅር ።

ዘ - በኩር

t.me/fikee21
👍132
አንዳንድ ነገሮችን የግድ ሙጥኝ ባንልባቸው መልካም ነው ። ለምን እንደዚህ አይነት ነገሮች የመሄድ እድላቸው ሰፊ ነው ። ታዳ እንዲህ ሙጥኝ ያልንበት ነገር ደግሞ ሲሄድ በጣም ውድ የሆኑ ነገሮች እንደጠፉ ትዝ ይልሃል ። ሌላውን ተወው ከሁሉም በላይ ግዜህን ታጣለህ ። ስለ እውነት ነው የምልህ ከቀመስኩት ነገር ነው እየነገርኩህ ያለው ። እየተፀፀትኩ ግን አደለም ። Be learn your mistake ሰምተሃል ።

ዘ - በኩር

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍92
ሰው አንተን ሲርቅህ እግዚአብሔር ደግሞ እንዴት እንደሚቀርብህ ታያለህ አብዝተው ባዶ ሊያደርጉህ ሲሞክሩ እግዚአብሔር አብዝቶ ሲሞላህ ታያለህ መውደቅህን በጉጉት ሲጠብቁ እግዚአብሔርን እዘህ ስትነሳ ያፍራሉ ሊስቁና ሊሳለቁብህ ሲሰለፉ እግዚአብሔር ታሪክህን ቀይሮ ተዓምር ያደርግባቸዋል እና ምን ልልህ ፈልጌ ነው አብሮነትህ መብዛት ያለበት ከእግዚአብሔር ጋር ነው የኔ ጀግና ።

ዘ - በኩር

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍14
በህይወት መንገድ ለይ ትልቅ ዋጋ ትከፍላለህ ከፍታው ለይ መወጣት የሚፈልግ ሰው መውደቁን መቁጠር የለበትም ። ሁሉም እንደሚያልፍ በእግዚአብሔር ለይ ፅኑ ተስፋ በመያዝ ሰራውን ብቻ መስራት ነው ተስፋ ደግሞ አያሳፍርም ። ዋጋ መክፈላችን ካልቀረ ደግሞ ነጌ ለሚጠቅመን ነገር ቢሆን መልካም ነው ። በዚሁ ለይ አንድ ነገር ልጨምርልህ ማንንም አትጠብቅ ማንንም ለምን መሰለህ ሁሉም የእራሱ የሆነ ሕይወት አለው ።

ዘ - በኩር

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍10
እራስን ከሰጡ ቢገፉም እንደ ጉድ
አብዝቶ ነው ማፍቀር አብዝቶ መውደድ።

ዘ - በኩር


t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍3
አንተ ጎበዝ ልቤ
ምንድን ነው መልፈስፈስ ?
ጠንክር እንደ ብረት ፣
ሲቀጠቅጡት ነው.....
መጥረቢያ በእራሱ የሚሆነው ስለት ።

ዘ - በኩር

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍71
አንቺ እንከን የለሽ የጥቅምት አበባ
እንደ ንብ ልቀስምሽ...... ?
ከልብሽ ቤት ልግባ
ክፈቺልኝ በሩን የፍቅርን አዳራሽ
አብሪ እንደ ፀሃይ ሌሊቱ እንዳይመሽ ።

ዘ - በኩር

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍7
አትሸወዱ

ስዎች በእናንተ ደረጃ መምጣት
ካልፈለጉ እዛው በደረጃቸው
ይቀመጡ ተዎቸው ።
ምን ግዜም እራሳችሁን ተከላከሉ
ሁሉም የሚሳካው እናንተ ጤነኛ
ስትሆኑ ነው ።
የአእምሮ ሰላማችሁን በደንብ
ተቆጣጠሩት አእምሮ የስው ልጅ
ትልቁ ስጦታ ነው ።

ዘ - በኩር

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fkee21
👍211
#ዋጋህን_ስታውቅ_ጩኸት_አያስፈልግህም!

ታዋቂዎቹ ብራንዶች ሮልስ ሮይስ እና ቤንትሌይ የንግድ ማስታወቂያ አይሰሩም።

ምክንያቱም፦

ምርታቸው ገዥዎችን እንደሚያመጣላቸው እርግጠኞች ናቸው።

ዋጋህን ስታውቅ ሰዎች፦
👉 እንዲወዱህ
👉 ወዳጅህ እንዲሆኑ
👉 አብረውህ እንዲሆኑ

ምናምን አትለምንም!!

በማንነትህ ተማመን።
ሁሉም ሰውም ወዳጅነትህ አይገባውም!

t.me/fikee21
👍51