ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል
1.79K subscribers
55 photos
2 videos
1 file
328 links
........ኑ
ስሜትን በግጥም እንግለፅ
ትውልድን በጥበብ እናንፅ ።

የፍቅር ቤት እዚህ ነው !
አሰተያየት ካላችሁ
👇
@fikee12 ላይ ማድረስ ይቻላል
Download Telegram
እናት ለምን ትዘን.....
እናት ለምን ይክፋት
ስስቴ ናትና....
ድካሟን ደክሜ በቅፌ ላኑራት ።

ዛሬንና ትላንት አምናና ሃቻምና
መልኳ እኔ ለይ ነው ታሪኳ ቢጠና
ሳቄ ፈገግታዬ የጥርሶቼ ድርድር
የፊቴ ገፅታ እሷን ነው የሚዘክር ።
እማ...እማዬ የኔ እናት
የህይወቴ ገድል የኔ ስንክሳር ናት
እናም.......
እናት ለምን ትዘን.....
እናት ለምን ይክፋት
ስስቴ ናትና.....
ድካሟን ደክሜ በቅፌ ላኑራት ።

እናቴ ❤️


ፍቃዱ ግርማ / Zበኩር /


t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍112
እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ማቴዎስ 2017 ዓ.ም በሰላም ተሸጋገራችሁ ።

እንኳን አደረሳችሁ!
መልካም አዲስ አመት ።


t.me/fikee21
👍6
።።።።።።።።።።።።።።

ሰው ዝም ስላለ ፤
አትበል ምን ያቃል
የአንተም ማንነትህ ፤
በአፍህ ይለካል ።


ፍቃዱ ግርማ / Zበኩር /

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍161
ልብን ከእግዚአብሔር ጋር ካደረጉ

በጨለማ ውስጥም ብርሃን አለ

በሀዘን ውስጥም ደሰታ አለ

በውድቀት ውስጥም ስኬት አለ

በመከራ ውስጥም መፅናናት አለ

በማጣት ውስጥም ማግኘት አለ

ፍፁም ከእግዚአብሔር ጋር ከሆኑ በሞት ውስጥም ሕይወት አለ

ተመስገን 🙏

ፍቃዱ ግርማ / Zበኩር /

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee1
👍10
።።።።።።።።።።።።።።

ታውቂያለሽ ሰሞኑን ልክ አደለሁም መንፈሴ ጥሩ ሁኔታ ለይ አደለም ለዛም ነው የጠፋሁብሽ የሆነ ቀን ዝም ብለሽ አታውቂም መናገር እየፈለግሽ ደግሞ ዝም ከምታወጪው ቃል ዝምታሽ በልጦ አሽንፎ አያውቅም ? እ..... ?

መናገር ፈልገሽ ቃላት የጠፉሽ ቀን የለም? ብቻ ምንም ይሁን ምን አሁን እኔ ዝምታ ውስጥ ነኝ ዝምታዬን ወድጄዋለሁ ነገር ግን ናፍቀሺኛል አንቺም ከናፈቅሺኝ ነይ አልናገርም አይን ለአይን ግን እናወራለን ።

ደግሞ ጥያቄ የሆነብኝ ነገር ቢኖር የሰው ልጅ ስሜቱን የሚረዳለት ስው ይፈልጋል የሚለው ነገርስ?

እንዳው አሁን ለይ በምልክት ተነግሮት ማወቅ የተሳነው ህዝቤ ነው የሰውን ስሜት የሚረዳ እንዳትጎጊ የምን ስሜት መረዳት ነው እውነቴን ነው የምለሽ አንቺ እራስሽ ጠንቅቀሽ አንቺነትሸን ካወቅሺው በቂ ነው ሌላ አስፈላጊ ነገር የለም ።

ሌላው ደግሞ በሕይወት መንገድ ለይ እንዳይሆኑ የለም አወቃለሁ ወሳኔሽ ግን ማሸነፍ ወይ ማሸነፍ መሆኑን አትዘንጊ ክንዶችሽ እንደ እሳት ፍም ችግርሽን መሰናክሎችሸን ሳያቃጥል ስለታዊ ማፈግፈግ የሚባል ነገር አይሰራም ።

ተሰፋሽን ከሚያቀጭጩ ሰዎች ፈፅመሽ ራቂ አሉ ባልታ ብዙ ነገር አጥፍቶብሻል ተስፋሽን በልብሽ ሰንቀሽ አስቀምጪ ። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በመልዕክቱ '' ተሰፋ አያሰፍርም '' ብሎል ።

የአንቺም ተስፋ እንደማያሳፍር እመኚ ።

''ለሚያምን ሁሉ ይቻላል "/ ማር 9:23/

እዝጎ ዝምታ ውስጥ ነኝ አላወራም ብዬሽ አልነበር አሁን እንዲህ ምታስለፈልፊኝ ጉድ !

አበው ለካ ወደው አደለም ''የወንድ ልጅ ሞቱ ሴት ናት ያሉ '' ።

በይ ደና ሁኚ ዝምታዬ ይሻለኛል ።

ፍቃዱ ግርማ / Zበኩር /

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍32
<<<<<<>>>>>>>

ምነው ሞቼ ባረፍኩት

ብዙ ግዜ ስዎች በነገሮች ተማረውም ሆነ ተስፋ በቆረጡ ግዜ ምነው ሞቼ ባረፍኩት ይላሉ ። ምናልባት እናንተም እሄንን ቃል ሲናገሩ ከብዙ ስዎች ሰምታችሁ ይሆናል ። እና ምንም ነገር ቢሆን እንዲህ ማለቱ አላስፈላጊ ንግግር ነው ። እንዳውም እንዲህ ያለው አነጋገር ከደረሰብኝ ችግር : ሰቃይ : ፈተና : እግዚአብሔር አያዋጣንም ብሎ እንደማሰብ ነው ።

በነገሮች ለይ ተሰፋ ቆርጦና ተማሮ ሞትን መመኘት ትልቅ ውድቀት ነው ። አንዱ ሲዘጋ ሌላወን ማንኳኳት ግዴታ ነው ። ማጣት ማግኝት የዚች አለም የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው ። ማጣት እንዳለ ሁሉ ማግኝት አለ፤ ማግኘትም እንዳለ ሁሉ ማጣት አለ ስለዚህ ሞትን የሚያስመኝ አንዳችም ነገር የለም ።

የሞት ወሳኔን መወሰን የችግሩ የመፍትሔ አካል ሊሆን አይችልም ። ይልቁንም ሌላ ችግር መፍጠር እንጂ ። ሞትም እርፍት የሚኖረው በጎ ስራ ስርቶ መልካም ነገሮችን ፈፅሞ ቱርፋትን አበርክቶ ሲያለፉ ነው ።

ስለዚህ ይህን ያለውን አነጋገር ከእራሳችን ልናርቀው ይገባናል ።

እንበርታ

ፍቃዱ ግርማ / Zበኩር /

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍31
=============

ተስፋ አለኝ የማይጠፋ
ከውቅያኖስ የሚስፋ
አለኝ እኔ ትልቅ ህልም
'ማይረታ ለዚች አለም ።

እሄዳለሁ በአምላክ ብርታት
ሰንቂያለሁ ፅኑ እምነት
እጎዛለሁ እሰከ ጥልቁ
ሳልበገር ለመውደቁ
እጅ አልሰጥም ለማጣቴ
ከአካሌ አትዝልም አንዲት ጣቴ ።

ፍቃዱ ግርማ / Zበኩር /


t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍7👎3
የእኛ የሁላችንም ችግር እኮ እኮ የተመከርነውንና የተነገረንን ነገር ሳንጠቀምበት ለሌላ ሰው ለመናገር የምንቸኩለው ነገር ነው የእኛ ትልቁ ድክመት እና ችግር ።

ፍቃዱ ግርማ / Zበኩር /


t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍6
ተነግሮን የማንሰማ፡ እየተመከርን ማንለማ ፡ ማፍረስ እንጂ የማንሰራ ፡
ችኩሎች የምንጣደፍ ፡ ማንና ምንን ማስቀደም የማናውቅ ፡ የሌለን የምንናፍቅ ፡ ያልቀጠረንን የምንጠብቅ ፡ ባህር በሌለበት የሙሴን በትር የምንሻ ምስጥርን ለመረዳት የማንፈልግ ፡ ጥበብ ወዴት እንዳለች ያልፈለግን በእወነቱ አኛ አደለንምን ?

ፍቃዱ ግርማ /Zበኩር /


t.me/fikee21
👍3
ውድ ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል ቤተሰቦች

እንኳን ለብርሃነ መሰቀሉ በሰላም በጤና አደረሳችሁ ።

መልካም በዓል!!!
👍12
እንኳን አደረሰን !
👍6
ቢጎዙ ቢጎዙ ቢያካልሉ ሀገር
የለወጥ መነሻው ማንነት ነው ስፍር ።

ስለሄዱ አይቀናም የስኬት ጎዳና
አይሳካም የለም ታቅፎ ስንፍና ።

ተቀምጦ እጅ አጣጥፎ
መክበር የለም......
ከውድቀት በር ተስልፎ ።

ስማ እንግዲ እውነት ሀቁን ፣
ዋጥ አድርገው ቢመርህም
መልፈስፈስህ ገደል ይግባ ፣
ጠንከር በል ብቸኛ ነህ የለም ማንም ።


ፍቃዱ ግርማ /Zበኩር /

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
2👍2
ነይ እናምልጥ ከዚህ ፅልመት
ምኞታችን ሳትገድለን እንግደላት
ወስኝና ፍጠኝ እንሩጥ
ሳትከተን ከጉድጎድ ማጥ
ህብረት ሰርታ ከኛ ጋራ ሳትቀመጥ
ሳታስቀረን ነይ እናምልጥ ።


ፍቃዱ ግርማ /Zበኩር /

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👎21
አየሽ....
አየሄዱ መውደቅ
እያነቡ መሳቅ
ተራራውን መናድ
ክፉን ሰው መውደድ
መጥፎን አልፎ መደላደል
በሕይወት ለይ ሳቅ ይሞላል ።

ፍቃዱ ግርማ /Zበኩር /

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍32
የኔ እናት

እናትና ልጅ በመንገዱ
ተቃቅፈው ሰሄዱ
በትዝታ አይቼሽ
ቀናሁኝ በጣሙን ከጎኔ አጥቼሽ ።

የኔ አለም ሳብሰለስል ሳወርድ ሳወጣ
በናፍቆት ስቀጣ
በአይን ህሊናዬ አንቺን እየሳልኩኝ
ሲሳሳቁ ፈገግ አልኩኝ ።

ናፍቀሺኛል እማ ።

ፍቃዱ ግርማ /Zበኩር /

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍52
ሰዉ ምንድን ነካው?
ይሰደድ ጀመረ እናት ሀገሩን ትቶ
ሊፀፅተው ኃላ ፣
ነፃነቱን ሸጠው ባሪያ መሆን ሽቶ ።

ፍቃዱ ግርማ /Zበኩር /

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍1
ሞኝ ፍቅር

( በእውቀቱ ስዩም )

ለ'ሱ
ሰው ብቻ አይደለችም
ጠፈር ናት ባ'ካሏ
መሬት ናት በነብሷ
ዕድሜ ልኩን ቢሮጥ
አያመልጥም ከ'ሷ ።

t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍7
ፍቃዱ ግርማ /ዘ-በኩር /


እሄው ዛሬ ዛሬ ጥፋቴ ታውቆኛል
አይጣል አትይም በጣም ናፍቀሺኛል ።
ሳቅና ጨዋታሽ
ያ ምቹ እቅፍሽ
በትዝታ መሰኮት ሲልብኝ ብቅ
እንዴት አይናፈቅ ?

እውነት አልደብቅም
መዋሸት አላውቅም
እመሰክራለሁ ነሽ የልብ አፍቃሪ
እምነት የምትሰጭ ተሰፋን የምትዘሪ ።

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍103
የቴሌብር ሱፐር አፕን በማውረድ በመመዝገብ እና በመገበያየት ተሸላሚ እዲሆኑ ጋብዤዎታለሁ. https://superapp.ethiomobilemoney.et:38443/customer/mgm/index0902.html#/?notoolbar=true&CampaignId=MGM1635518748044544&inviterId=1155736125542407&language=am&time=Sept-03-2024-Dec-02-2024
ማንም መጥቶ እንዲገፋችሁ አትፈልጉ ሁሉም የተለያየ ኃይል አለው ስለዚህ እናንተ የማትችሉት ኃይል ቢጣልባችሁ ለሕይወታችሁ አደጋ ነው ።

በእራሳችሁ ተንቀሳቀሱ ።

የምወደው ታላቅ ወንድሜ ምን ይላል
አንተ ለእራስህ በቂ ነህ ( You are enough ) ይለኝ ነበር ።
አውነቱን ነው ተንቀሳቀስ !!!
You are enough !!!

ፍቃዱ ግርማ / ዘ-በኩር /

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍41