ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል
1.79K subscribers
55 photos
2 videos
1 file
328 links
........ኑ
ስሜትን በግጥም እንግለፅ
ትውልድን በጥበብ እናንፅ ።

የፍቅር ቤት እዚህ ነው !
አሰተያየት ካላችሁ
👇
@fikee12 ላይ ማድረስ ይቻላል
Download Telegram
ማጣት አይኑ ይጥፋ ፣
እሰከ አለም ፍፃሜ
መትረፍረፍ አይራቀኝ ፣
በተሰጠኝ እድሜ

ፍቃዱ ግርማ / Zበኩር /

t.me/fikee21
👍8
አንቺዬ........

እንደምወድሽ እስካላወቅሽ ድርስ ባንቺ ዘንድ ምንም እንዳልሆንኩ አውቃለሁ ነገር ግን አንድ ቀን እንደሚገባሽ አምናለሁ ።

ደግሞ ሰው ያመነውን ሊሆን ግድ ሰለሆነ የኔው ነሽ ማለት ነው ። ደስ አይልም

እወድሻለሁ

ፍቃዱ ግርማ / Zበኩር /


t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍61
ስብከነከን በናፍቆትሽ
መቼ ይሆን እኔ ማቅፍሽ?
ነጌ ይሆን.....
ማታ ሲሆን በጨረቃ
ተደብቀን ሰው ሳይነቃ
ኮኮቦቹ ሲሉልን ብቅ
ተሾልከን ሳይታወቅ
ከጎረቤት ወይ ሲልኩሽ
ያን ግዜ ነው እኔ ማቅፍሽ ?
የኔ አበባ...
ነገሪኛ ዝም አትበይ
ናፍቀሺኛል የኔ ፀሃይ ።

ፍቃዱ ግርማ / Zበኩር /

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍14
መጀመሪያ ሰለእራስህ በደንብ አስብ በቅድሚያ ስለራስህ ተጨነቅ ምን መሆን እንደምትፈልግና ዬት መድረስ እንዳለብህ እወቅ ። ከዛ ቡኃላ ሁሉም ነገረ መሰመሩን ይይዛል አንተም ብትሆን ሌሎችን ደስተኛ የምታደርገው ለእራስህ ስትበቃ ነው ። በእያንዳንዱ እርምጃዎችህ ውስጥ መቼም ፣ የማይለይህ ፣ መቼም የማይጥልህ ፣ መቼም የሚሳሳልህ ፣ ሁሌም የሚወድህ ፣ ሁሉን የሚያስችልህ ፣ ተስፋህን የሚያለመልም እግዚአብሔር ካንተ ጋር መሆኑን ስታውቅ ደግሞ ያለውን ሰላም አጠይቀኝ ብቻ ስትቀምሰው ይገባሃል ።

ፍቃዱ ግርማ / Zበኩር /

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍10
ዛሬን ካልደከምህ ካልከፈልክ ዋጋ
ብርሃን አታይም ጨለማው ሳይነጋ
እናም....
ፈለግ ለልጆችህ
ታሪክ ለሀገርህ
ጥላቻን አጥፍተህ አስተምረህ ፍቅር
ስምህን አፅፈው በማይጠፋ ብዕር ።
በእርግጥ ያለም ቢሆን.....
አስታወስሃለሁ ፣
ዘላለም እድሜህን በአለም አትኖርም
ወደድክም ጠላህም መሞትህ አይቀርም ።

ፍቃዱ ግርማ / Zበኩር /

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍5💯1
............

ሸክም እንዲቀልህ.... ፣
እንዳይወርስህ ፀፀት
ልመደው ይቅርታን....፣
የሞት ሞት እንዳትሞት ።

ዝም ብለህ እደግ ቃላት ሳታሰማ
እመን ደግሞ በደንብ
ደብቀው የሰሩት ይወጣል ከማማ ።
ስለዚህ....
ዝም ብለህ ገስግስ
የወጣለት ጀግና ትሆናለህ ንጉስ ።

ፍቃዱ ግርማ / Zበኩር /


t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍6
::::::::::::::::::::::::::::

አዳሜ..........
መስጠት ጠላቷ ነው.. ፣
መርዳት ለቸገረው
ለማይጠቅም ነገር
ገንዘብ እየረጩ ማሰከር ግን ቀላል ነው ።

ለነርሱ!

ፍቃዲ ግርማ /Zበኩር /


t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍6
:::::::::::::::::::::::::

አንቺ ባለቀሚስ
ስምሽ በአለም ይንገስ ።
ከቀናትም ቀናት
ከሳምንትም ሳምንት
ከውራትም ወራት
ከአመት እስከ አመት
አይለይሽ ከቶ የእግዜር ምህረት
ለምን..... ?
አላለፍሽምና ቃል ኪዳን ትዛዛት ።

ፍቃዱ ግርማ / Zበኩር /


t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍91
>>>>><<<<<

ሸክም ጓዟ ቢከብደኝም
መጨለሜን አልመኝም
ቢከብድ እንኳን ከመኖር ጋር ትንቅንቁ
እጓዛለሁ እስከ ጥልቁ ።

ውብ ብርሃን እጅግ ደማቅ
በጣም ግሩም የሚደነቅ
ቁርጥ ተስፋ ያለ ክርር
የማይጠፋ አለኝ ከእግዜር ።

እጓዛለሁ !

ፍቃዱ ግርማ / Zበኩር /

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
1👍1
እብድ የፃፈው ግጥም

አድራለሁ መንገድ ለይ......
አልመርጥም መኝታ
ዝናቡን አልፈራም በረዶው ቢንታታ
አይነካኝም ብርዱ እኔ አልጠላም ንፋስ
ተፈጥሮ ገነት ናት ሌሊት የምትፈስ ።
እናም.......
አልቀልስም ጎጆ ለዚች አጭር እድሜ
ድንኳኑን የሰራሁ አብርሃም ነው ስሜ
ሰው ዝም ሲልልኝ.......
ፀጥ... ረጭ... ጭጭ ሲል ሰፈሩ
ያነጋግረኛል ሰማይና ምድሩ
ጨረቃ ክዋክብት እያሸረገዱ
ቀለቤን ይሰርቁታል ተቃቅፍ ሲሄዱ
አንዳንድ አመለኛ ተወርዋሪ ኮኮብ
ቀን ቀን የማየውን...
ይመስለኛል ወጣት ደርሶ ሚያኮበኩብ
እሄውልሽ ደግሞ........
በዚች ከንቱ ምድር የከተማው ማበራት
ክዋክበትን በልጦ.....
የወጣ ይመስላል ጨረቃን ሊያጅባት
እናም አንቺዬዋ......
አይነካኝም ብርዱ እኔ አልጠላም ንፋስ
ተፈጥሮ ገነት ናት ሌሊት የምትፈስ ።

ደግሞ.........
አመረ አለመረ ፣
ጣፈጠ አለጣፈጠም
አይባልም እቱ.....
ማነብነብ ብቻ ነው እብድ የፃፍው ግጥም ።

ሰምተሻል!


ፍቃዱ ግርማ /Zበኩር /

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍51
ነይ!
እቤት ቡና ፈልቷል
እጣኑ ተጪሶ....
ጨዋታውም ደምቋል ።
ነይ!
አዲስ ህግ እንደፍ
መስመሮች እንስራ እንዳንጠላለፍ
ነይና እንጓዝ እንሂድ በደንቡ
የጥላቻ መንፈስ የፈራርስ ግድቡ
ነይ!
አንቺ ፀደይ ኮኮብ ሰማይ
ተናፋቂ የኔ ፀሀይ ።
ነይ!
ነይ!
ነይ እሺ!

ላንቺ ስጦታ ነወ !

ፍቃዱ ግርማ /Zበኩር /

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍4
ታውቂያለሽ ሰሞኑን እንቅለፍ የለኝም ። የማስበው ፡ የማወራው ፡ የምፅፈው ሁሉ ስላንቺ ነው ። ምን ሆኜ ነው ግን?

I'm ጤነኛ ነኝ ብዬ እራሴን ብጠይቅም ያገኘሁት መልስ አልነበረም ዝም ብሎ በሀሳብ ከመንጎድ ወጪ.... ምንም ብቻ ዝም ነው ዝም ። አሃ ሰሞኑን ማታ ለይ ወክ ሳደርግ የሆነች የቆመች ታክሲ ለይ '' ዝም አይነቅዝም '' የሚል ፅሁፍ አይቼ ነበር ምናልባት ለሱ ይሆን? ግን እንጃ አላቅም ተይ ።

ምነው ገረመኝ !!! ሆሆሆሆ አለች እምዬ ነገር ሲገርማት ጉድ ። 😳😳😳

ሰሞኑን ባጭሩ !

ፍቃዱ ግርማ / Zበኩር /

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍71
ከወሰኑ ከቆረጡ
መች ያሰምጣል ጉድጎድ ማጡ
መች ያስቆማል የእሳት ብዛት
ፍፁም አምነው ከሄዱበት
አንዴ ብቻ ከደፈሩ
አይበግርም ሀሩር ቁሩ ።

አይዞህ! አይዞህ!
ድፍረ ልቤ አታመንታ
ከፍታ ነው ያ'ንተ ቦታ
ጠንከር በል እንዳትፈራ
ትወጣለህ ከተራራ ።
አይዞን አይዞን
ጀግን ጀግን
ጨክን ጨክን
ካልተገፉ እንደ ጉድ
አይገኝም መውደድ ።

አይዞን! እኔ ።


ፍቃዱ ግርማ / Zበኩር /


t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍61
እናት ለምን ትዘን.....
እናት ለምን ይክፋት
ስስቴ ናትና....
ድካሟን ደክሜ በቅፌ ላኑራት ።

ዛሬንና ትላንት አምናና ሃቻምና
መልኳ እኔ ለይ ነው ታሪኳ ቢጠና
ሳቄ ፈገግታዬ የጥርሶቼ ድርድር
የፊቴ ገፅታ እሷን ነው የሚዘክር ።
እማ...እማዬ የኔ እናት
የህይወቴ ገድል የኔ ስንክሳር ናት
እናም.......
እናት ለምን ትዘን.....
እናት ለምን ይክፋት
ስስቴ ናትና.....
ድካሟን ደክሜ በቅፌ ላኑራት ።

እናቴ ❤️


ፍቃዱ ግርማ / Zበኩር /


t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍112
እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ማቴዎስ 2017 ዓ.ም በሰላም ተሸጋገራችሁ ።

እንኳን አደረሳችሁ!
መልካም አዲስ አመት ።


t.me/fikee21
👍6
።።።።።።።።።።።።።።

ሰው ዝም ስላለ ፤
አትበል ምን ያቃል
የአንተም ማንነትህ ፤
በአፍህ ይለካል ።


ፍቃዱ ግርማ / Zበኩር /

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍161
ልብን ከእግዚአብሔር ጋር ካደረጉ

በጨለማ ውስጥም ብርሃን አለ

በሀዘን ውስጥም ደሰታ አለ

በውድቀት ውስጥም ስኬት አለ

በመከራ ውስጥም መፅናናት አለ

በማጣት ውስጥም ማግኘት አለ

ፍፁም ከእግዚአብሔር ጋር ከሆኑ በሞት ውስጥም ሕይወት አለ

ተመስገን 🙏

ፍቃዱ ግርማ / Zበኩር /

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee1
👍10
።።።።።።።።።።።።።።

ታውቂያለሽ ሰሞኑን ልክ አደለሁም መንፈሴ ጥሩ ሁኔታ ለይ አደለም ለዛም ነው የጠፋሁብሽ የሆነ ቀን ዝም ብለሽ አታውቂም መናገር እየፈለግሽ ደግሞ ዝም ከምታወጪው ቃል ዝምታሽ በልጦ አሽንፎ አያውቅም ? እ..... ?

መናገር ፈልገሽ ቃላት የጠፉሽ ቀን የለም? ብቻ ምንም ይሁን ምን አሁን እኔ ዝምታ ውስጥ ነኝ ዝምታዬን ወድጄዋለሁ ነገር ግን ናፍቀሺኛል አንቺም ከናፈቅሺኝ ነይ አልናገርም አይን ለአይን ግን እናወራለን ።

ደግሞ ጥያቄ የሆነብኝ ነገር ቢኖር የሰው ልጅ ስሜቱን የሚረዳለት ስው ይፈልጋል የሚለው ነገርስ?

እንዳው አሁን ለይ በምልክት ተነግሮት ማወቅ የተሳነው ህዝቤ ነው የሰውን ስሜት የሚረዳ እንዳትጎጊ የምን ስሜት መረዳት ነው እውነቴን ነው የምለሽ አንቺ እራስሽ ጠንቅቀሽ አንቺነትሸን ካወቅሺው በቂ ነው ሌላ አስፈላጊ ነገር የለም ።

ሌላው ደግሞ በሕይወት መንገድ ለይ እንዳይሆኑ የለም አወቃለሁ ወሳኔሽ ግን ማሸነፍ ወይ ማሸነፍ መሆኑን አትዘንጊ ክንዶችሽ እንደ እሳት ፍም ችግርሽን መሰናክሎችሸን ሳያቃጥል ስለታዊ ማፈግፈግ የሚባል ነገር አይሰራም ።

ተሰፋሽን ከሚያቀጭጩ ሰዎች ፈፅመሽ ራቂ አሉ ባልታ ብዙ ነገር አጥፍቶብሻል ተስፋሽን በልብሽ ሰንቀሽ አስቀምጪ ። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በመልዕክቱ '' ተሰፋ አያሰፍርም '' ብሎል ።

የአንቺም ተስፋ እንደማያሳፍር እመኚ ።

''ለሚያምን ሁሉ ይቻላል "/ ማር 9:23/

እዝጎ ዝምታ ውስጥ ነኝ አላወራም ብዬሽ አልነበር አሁን እንዲህ ምታስለፈልፊኝ ጉድ !

አበው ለካ ወደው አደለም ''የወንድ ልጅ ሞቱ ሴት ናት ያሉ '' ።

በይ ደና ሁኚ ዝምታዬ ይሻለኛል ።

ፍቃዱ ግርማ / Zበኩር /

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍32
<<<<<<>>>>>>>

ምነው ሞቼ ባረፍኩት

ብዙ ግዜ ስዎች በነገሮች ተማረውም ሆነ ተስፋ በቆረጡ ግዜ ምነው ሞቼ ባረፍኩት ይላሉ ። ምናልባት እናንተም እሄንን ቃል ሲናገሩ ከብዙ ስዎች ሰምታችሁ ይሆናል ። እና ምንም ነገር ቢሆን እንዲህ ማለቱ አላስፈላጊ ንግግር ነው ። እንዳውም እንዲህ ያለው አነጋገር ከደረሰብኝ ችግር : ሰቃይ : ፈተና : እግዚአብሔር አያዋጣንም ብሎ እንደማሰብ ነው ።

በነገሮች ለይ ተሰፋ ቆርጦና ተማሮ ሞትን መመኘት ትልቅ ውድቀት ነው ። አንዱ ሲዘጋ ሌላወን ማንኳኳት ግዴታ ነው ። ማጣት ማግኝት የዚች አለም የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው ። ማጣት እንዳለ ሁሉ ማግኝት አለ፤ ማግኘትም እንዳለ ሁሉ ማጣት አለ ስለዚህ ሞትን የሚያስመኝ አንዳችም ነገር የለም ።

የሞት ወሳኔን መወሰን የችግሩ የመፍትሔ አካል ሊሆን አይችልም ። ይልቁንም ሌላ ችግር መፍጠር እንጂ ። ሞትም እርፍት የሚኖረው በጎ ስራ ስርቶ መልካም ነገሮችን ፈፅሞ ቱርፋትን አበርክቶ ሲያለፉ ነው ።

ስለዚህ ይህን ያለውን አነጋገር ከእራሳችን ልናርቀው ይገባናል ።

እንበርታ

ፍቃዱ ግርማ / Zበኩር /

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍31
=============

ተስፋ አለኝ የማይጠፋ
ከውቅያኖስ የሚስፋ
አለኝ እኔ ትልቅ ህልም
'ማይረታ ለዚች አለም ።

እሄዳለሁ በአምላክ ብርታት
ሰንቂያለሁ ፅኑ እምነት
እጎዛለሁ እሰከ ጥልቁ
ሳልበገር ለመውደቁ
እጅ አልሰጥም ለማጣቴ
ከአካሌ አትዝልም አንዲት ጣቴ ።

ፍቃዱ ግርማ / Zበኩር /


t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍7👎3
የእኛ የሁላችንም ችግር እኮ እኮ የተመከርነውንና የተነገረንን ነገር ሳንጠቀምበት ለሌላ ሰው ለመናገር የምንቸኩለው ነገር ነው የእኛ ትልቁ ድክመት እና ችግር ።

ፍቃዱ ግርማ / Zበኩር /


t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍6