ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል
1.78K subscribers
55 photos
2 videos
1 file
330 links
........ኑ
ስሜትን በግጥም እንግለፅ
ትውልድን በጥበብ እናንፅ ።

የፍቅር ቤት እዚህ ነው !
አሰተያየት ካላችሁ
👇
@fikee12 ላይ ማድረስ ይቻላል
Download Telegram
ፍቃዱ ግርማ
( Zበኩር )

ይታይሽ ሀገሬ

ማንነት ጠፍቷቸው.....
ሲገዛቸው አለም
እንዲህ ነው አንዳንዴ....
ጠባቦች ሲባሉ መሙላት አይመኙም ።


...........
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
ፍቃዱ ግርማ
( Zበኩር )

እኔ ልቅደም እኔ ልብለጥ
አንተ ተያዝ እኔ ላምልጥ
ከንቱ መሆን .....
በሰው ልፋት ሰርክ መቅበጥ
እሄ አጉል አለሁ አለሁ ....
ሰው ይጥላል ከጥልቅ ማጥ ።

ሰለዚህ እንጠንቀቅ🙏

........
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍51
ፍቃዱ ግርማ
( Zበኩር )

ስሚማ ልንገርሽ ፣
ልብ ብለሽ ስሚ ታዘዢ ለባልሽ
እውነት እልሻለሁ ቀና ልብሽ ይኑርሽ
ዝሪበት በልቡ ትዝታና ናፍቆት
ቃልሽ እሺ ያብዛ ሀሳቡን ሙዪለት
ይረገም መዝለልሽ ......
ካየሺው ጋር መቅበጥ
ለምን ........?
እንደዛ ሲሆን ነው.......
ፍቅር የሚጣፍጥ ።

...........
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
ፍቃዱ ግርማ
( Zበኩር )

አንቺዬዋ ወዴ ........
ልጅ መውለድ አሁን ነው
ለምን ........?
ሲባል ሰምቻለሁ .........
ፍቅርና ገንፎ ትኩስ ትኩሱን ነው
እድሜም ቆሞ አይጠብቅ
በደቂቃ ሰዓት ወደ ሞት መንፈፏቀቅ
ስለሆነ ቅሉ .......
በዋዛ ፈዛዛ እድሜን ከምንፈጀው
እውነት እልሻለሁ .......
መውለድማ አሁነው
እናም .......
በቅጡ አዳምጪኝ
የምልሺን ስሚኝ
እድል አንዲቷ ነች ካለፈች አትገኝ
ስለዚህ እንውለድ ...
ልጄም ቅር አይበለው
በስርጌ ቀን ይገኝ ።

............
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍31👎1
ፍቃዱ ግርማ
( Zበኩር )

ይገርማል !

አንዳንዴ እያሉም መረሳት አለ ለካ
ከነ ምንም ትዝ አለመባል ጉድ ነው

ብቻ ይሁን መሰረቴን ፈጣሪዬን ሰለያዝኩ እግዚአብሔር ይመስገን።

t.me/fikee21
👍8
ፍቃዱ ግርማ
( Zበኩር )

ተስፋ

የታማሚ ተስፋው ፣
መዳህኒት አይንቅም
እድናለሁ አንጂ ፣
ሞታለሁ አያውቅም
አንደዛ ሆኖ ነው ፣
እኔም የምደክም
ነጌን ማለቴ እንጂ ፣
ዛሬስ አያስመኝም ።

t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍6
ፍቃዱ ግርማ
( Zበኩር )

መልዕክት

ለሄደባት ከዬትም
ላወረዳት ማንም
ይድረሰው መልዕክቱ
ማሰቢያ ጭንቅላት ለሆነው ጉልበቱ
ሰውነት ለራቀው እናት ለበደለ
ከመዳፏ ጎርሶ ሰሟን ላቀለለ
ቀሚሷን አወልቆ እርቃኗን ለጣላት
ሰላም ለዛች ሀገር ፍትህ ለናፍቃት ።

t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍1
ፍቃዱ ግርማ
( Zበኩር )


በቀን አንድ ገፅ ማንበብ
ሕይወት ነው ።
የመፍትሄ ስው ሆኖ መገኝት
ተመራጭ ነው ።
በእራስ ብር ከመስከር ለአንድ
ሰው መመፅወት መታደል ነው
ከሰዎች ጋር ሰለማይመለከተን
ስናወራ መዋል ሞት ነው ።
ስተትን አለማመን ጠባብነት
ነው ።
ከልክ በላይ መሮጥ መወደቅ
ነው ።
ሁሉን በልክ ማድረግ መልካም
ነው


እዚህ ላደረሰን ልዑል እግዚአብሔር ይመስገን ።
🙏🙏🙏

t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍61👎1
ፍቃዱ ግርማ
( Zበኩር )

ለእራስ የተሰጠ ምክር


እያለህ ቢያስመስል ፣
ቢያሸረግድ ሁሉም
ተጠንቀቅ ወንድሜ ፣
ካጡም ዘመድ የለም ።

ስለዚህ .....
ሰይፍ ሁን ሁለት ስለት
ባንዱ ቆርጠህ ባንዱ እንዳትስት
ለምን .......?
'ሚጠቅምህን ካለየህው ከሚጎዳህ
ያከበርከው መልሶ ነው የሚጥልህ
እንዴት .......?
ስንት...ስንቱ ተስፋ ቆርጦ ዛሬ ያለ
ባጎረሰ ተነክሶ ነው ፣
ጎዳና ለይ ወጥቶ እንዲህ የቀለለ ።


t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍3
አምላኬ ሆይ

በቅፍህ ውስጥ ለምታኖረኝ ለአነተ ምስጋና ይገባሃል ተመስገን ።

በደሌን የሸሸገህለኝ አንተ እንጂ ሌላ ማን አለ ጌታ ሆይ ? ለዘላለም ተመስገን ።

አምላኬ ሆይ ሙሉ ጤና ስለሰጠህኝ ተመስገን ።

በዚህ መሰናክል በበዛበት አለም ውስጥ እያበረታሃኝ ዛሬን ስላሳየህኝ ጌታ ሆይ ተመስገን ።

ነገርን ሁሉ በልክ እያደረክ ትዕግስትን ሰለምታለማምደኝ ተመስገን ።

መጥፎ ስራዬን አይተህ ሳይሆን በምህረትህ እኔን ደካማህን ያዳንከኝ ተመስገን ።

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍52
ፍቃዱ ግርማ
( Zበኩር )

ለእራስ የተሰጠ ምክር

ተረጋጋ ሰከን በል
ብዙ አትሩጥ አትቸኩል
ቀስ ብለህ ካልመረመርክ
ካላወጣህ ካላወረድክ
በማስተዋል ካልተራመድክ
በሌለህ ለይ ዘራፍ ብትል
ስሜት ክፉ ይጥልሃል
ዘውትር ሁሌ.......
ለምን ሆነ ከቶ አትበል
መፈተንህ ግድ ይልሃል
ፀጋ ካባ እንድትለብስ
ነጋ ጠባ ተመስገን በል
እንጂማ እራሴ ........
ከመሬት ተነስቶ .......
እንዲሁ በምኞት ሁሉም ከሰመረ
ዝንጀሮ በእራሱ ከብት ይሆን ነበረ ።


t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍3
አምላኬ ሆይ ....

አምላኬ ሆይ ተስፋ ልቆርጥ ስል መንፈሴ ሲዝልብኝ ሁሌ ከጎኔ ሆነህ አይዞህ እያልክ ስለምታፅናናኝ ተመስገን ።

ጌታ ሆይ ማጉረምረሜን ገስፀው ።

በገዛ ስህተቴ ሕይወቴን ጨለማ ስሞላው የብርሃንን መንገድ ለምታሳየኝ ለአንተ ተመሰገን ።

በንግግሬ ሁሉ እየገባህ ለምትጠብቀኝ ለአንተ ተመስገን ።

ከይሁዳ ለከፋሁት ለእኔ ምህረትህ የበዛልኝ ቸሩ አምላኬ ሆይ ተመስገነ ።

አቤቱ ጌታ ሆይ ፍላጎቴ ገደብ የለውም እና አንተ ከእኔ በላይ ፍላጎቴን ታወቃለህና አቤቱ ጌታ ሆይ የአንተ ፍቃድ ይሁን ።

አቤቱ ጌታ ሆይ በመንገድህ ምራኝ የእወቀትን ጥበብ ገለፅልኝ ።

አምላኬ ሆይ ለእኔ ያደረከው ነገር ድንቅ ነውና ተመስገን ።

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍3
ከወደድኩት ጥቅስ እነሆ ....

ሰው ስለገባው ነገር ብቻ ቢያወራ ኖሮ ምድር በጣም ፀጥተኛ ስፈራ ትሆን ነበር ።

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍4
ፍቃዱ ግርማ
( Zበኩር )

ታገስኩሽ እንደ ጉድ
ሺ! ነው የኔ መውደድ
አዘልኩሽ ስንት አመት
ወይ ከነጌ ዛሬ ይሻላል በማለት
እኔ የዋህ ሞኙ ቃል ሳልናገርሽ
እሹሩሩ አልኩሽ
ግን እንደዛ ሆኖም
ምንም አልተሳካም ።

እናም እሄውልሽ .. ........
ብችለው ብችለው ከቶ ሰላልሆነ
ጭራሽ ይባስ ብሎ ......
እየዋለ እያደረ ጥፋትሽ ገነነ
እኔም ተበሳጨሁ ውስጤ ተረበሸ
ላንቺ ያለኝ ፍቅር ጭራሽ ኮመሸሸ
ከእንግዲህ አበቃ የኔና ያንቺ ነገር
ጠጥቶ አይደለም .........
ወንድ ሲከፈው ነው የውሱጡን 'ሚናገር ።


t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍4
ፍቃዱ ግርማ
( Zበኩር )

እኔስ በ'ንቺ ቂም አልይዝም
ሄድሽ ብዬ አላማሽም
ላደረግሺው ክፉ ነገር
ይፍረድብሽ ንፁህ ፍቅር ።

ለገፋሺኝ አንቺ እኔን
ለሰበርሺው አንድ ልቤን
ባልመልስም አጠፌታ
ይሰጥሻል ፍርዱን ጌታ ።

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21'
👍3
ፍቃዱ ግርማ
( Zበኩር )

ማጣቴ እውነት ነው ፣
የለኝም አውቃለሁ
ማግኝት ተተክቶም......
እንሚቀያየር ተስፋ አለኝ አምናለሁ
እስከዛው ድረስ ግን ....
መሰናክል በዝቶ ብወድቅ ብነሳም
መልኬ ቢጠቆቁር ገርጥቼ ብከሳም
ከማመስገን ወጪ አላጉረመረምም
ገንዘብ ላያድነኝ .....
እኔ ነጋ ጠባ ሁሌ አልቆዝምም ።


t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍6
ፍቃዱ ግርማ
( Zበኩር )

መቼም ዬትም እንዴትም ቢሆን
የእራሳችሁ የሆነን ነገር አትልቀቁ
የስውንም ደግሞ አትናቁ ።

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
2👍2
ፍቃዱ ግርማ
( Zበኩር )

ከቆረጥሽ ከተነሳሽ
ሰላም ግቢ ላንቺ ይድላሽ
ደና ሁኚ እድሜ ይስጥሽ
ለደቂቃም ከቶ አይክፋሽ ።

አንቺው ኑሪ ተደላድለሽ
የኔን ተዪው ......
ደስታ ይሙላው ሳሎን ጎዳሽ
የኔ አለም ......
ትዝታ ግን ይብላኝለት
አንቺን ዛሬ .....
አስታወሰኝ በዚህ ሰዓት
ትዝታ ግን ይብላኝለት ።


t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍41👎1
ፍቃዱ ግርማ
( Zበኩር )

አንቺዬ ታድለሽ
አይጎልም ማጀትሽ
ታድለሻል ውዴ ....
አይጎልም ያንቺ ቤት
ይቀዳል ሁል ግዜ...
ከአመት እሰከ አመት ።

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍4
ፍቃዱ ግርማ
(Zበኩር )

ደስተኛ ነኝ ? አዎ ነገር ግን እኔ ደስተኛ የሆንኩት በዙሪያዬ ባሉ ሰዎች ወይንም በከበቡኝ ነገሮች ሳይሆን እኔ እራሴ ለእራሴ ባለኝ ቦታ ነው ።

በገዛ እጄ የእራሴው አእምሮ ለይ ነጭ ወረቀት ንፁህ ማንነቴ ለይ ከእራሴ ውጪ ከምፈልገው ነገር ወጪ ከሚያስፈልገኝ ነገር በቀር ማንም አይፅፍበትም ።

ልቤ ውስጥ ያለው ስፋት ጥልቅ ነው እሩቅ ነው ። ብዙ ሰዎች ሊለኩት ሞከሩ ግን አላወቁትም ምክኒያቱም ስፋቱን ማካለል ሰለከበዳቸው ደክሟቸው ቆመዋል ።
የኔ ልብ ሀገር ናት ።

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍3