ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል
1.78K subscribers
55 photos
2 videos
1 file
331 links
........ኑ
ስሜትን በግጥም እንግለፅ
ትውልድን በጥበብ እናንፅ ።

የፍቅር ቤት እዚህ ነው !
አሰተያየት ካላችሁ
👇
@fikee12 ላይ ማድረስ ይቻላል
Download Telegram
ፍቃዱ ግርማ

አያድርስ ከቶ

እማታገኝውን ሺህ ግዜ መናፈቅ
ለማይሆነው ነገር ሺህ ግዜ መጨነቅ
እራስክን ከማጣት ምንም አታተርፍም
ዝብርቅርቅ ባለበት በዚህ ከንቱ አለም
አይጣልብህ እንጂ አያድርስ ከቶ
በዚች አለም ኑሮ ማንስ ያቃል ረክቶ ። ?

ማንም
.......
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍4
ፍቃዱ ግርማ

ጥላቻ

በፍቅር እንዳልደመቅን ፈክተን እንደ አበባ
ደግነትም ጠፍታ ጥላቻ እኛን ቀርባ
ተለያዩ ብትል መሪር በሆነ ቃል
ቃልህ ቃልኪዳኔ እንዴት ብሎ ያልቃል
ጥላቻ የሚሏት እኛ ሀገር ገብታ
ታየቺኝ ስትመጣ ክፋትን ጎትታ
እናማ ወንድሜ ክንድህን አበርታ
ጥላቻ ለሚሏት መቼም አትረታ ።

አይዞህ እንበርታ !

........
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍2
አባቴ ማረኝ

ምፅዋቴ ሁሉ ሆነ በብርሃን
ከጠፉት በጎችህ እኔ አንዱ አሆን ??

አላውቅም ።

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
ፍቃዱ ግርማ

እስትንፋስን እፍ ብለህ ሰው አረከኝ
ከትቢያ ለይ
ተመስገን ነው የኔ ምላሽ ከምድር
እስኪ ሰማይ
ብወድቅ እንኳን ሆነህ ምርኩዝ
አነሳሃኝ እኔ ልጅህ እንድጎብዝ
ሰርክ ሁሌ እረኛዬ
አየሆንከኝ ሀይል ብርታት መፅናኛዬ
ለችግሬ መሻገሪያ
አንተ እኮ ነህ መነፅሬ ሁሉን ማያ
ምንም እንኳን እኔ ከንቱ እየሆንኩኝ
ባሰቸግርም
እኔን ምንም ርካሽ ምንም ለመፈወስ
አትሰለችም ።

......
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
3
እናት
ፍቅር
ሐገር


አሌክስ አብረሃም

/ ከንፈር ግን ሲገርም / !

እኔ የምልሽ ወዴ ፣
የጀነት በር ማለት ከንፈርሽ ነው እንዴ ?

ምን አባቴ ልበል.......!
ስትሰሚኝ ግዜ
ፊቴ የነበረው ፎከታም ግርግዳ ዬት አባቱ
ሄደ ?
ወስጤ የተገነባው የጭንቀት ባቢሎን
ከመኔው ተናደ !
ስትስሚኝ ግዜ
በህሊናዬ ወስጥ ያንን ሁሉ አበባ
ማን ተክሎት በቀለ !
ይሄስ ሁሉ ደስታ
ከዬት ተጠራርቶ ወስጤ ተቆለለ ?

ተፈጥሮን ገልብጦ እናቴን በጥብጦ ፣
ፀሐይን በምዕራብ አወጣት ከንፈርሽ ፣

መገን አሳሳምሽ !!

ብትስሚኝ ግዜ
ዝሆኖች በረሩ
እባቦች ጋለቡ ፣
በባዶ ልቤ ወስጥ
እልፍ ሰርጎች ገቡ ........

እናት ፡ ፍቅር ፡ ሐገር
አሌክስ አብራሃም

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍2
ፍቃዱ ግርማ

ጮህን .... ጮህን
ኡ......ኡ .....
አጣን እንጂ አንድም ሰሚ
መንገዱ እየጠፋን እያጣን ጠቋሚ
አለቀስን .......... ስቅስቅ አለን
ለፋን ዳከረን..... ተንከራተትን
ሄድን ሄድን ወጣን ወረድን
አኪያሀዱ ጉዞው ጠፍቶን
ምንም አጣን
ምንም ምንም
ነገሩ ሁሉ አለብን ጥምም ።
.
.
.
.
.
.
እኛም አለን ዝም !

.......
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍1
ፍቃዱ ግርማ

አገኝሁ የልቤን መሻት
እንደ ነብሴ የምወዳት
እንደ ብሌን ምሳሳላት
እስትንፋስ ናት የምወዳት ።
ማመስገኛ ዜማ ቃሌ
አገኘሁ ተዋህዳ ከአካሌ
ሰመረልኝ ደሟ ደሜ
ፈውስ ሆነች ለህመሜ
በህይወቴ ሆናኝ ብርታት
ወጣሁባት ስንት አቀበት ።

........
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍1
ፍቃዱ ግርማ

ምን አለ ባልመሸ ፣
ጀንበር ባልጠለቀ
ውሎ ቢያድር ምነው ፣
ሰማይ እነደሳቀ ።

እኔማ ጨረቃን ፣
ድሮም አልወዳትም
አጃቢዋ ብዙ ፣
እሷ ስርጎ የትም
ድግስ አይሰለቻት መብላት መጠጣቱ
ፀሃይ ስትዘቀዝቅ ይይዛታል ግቱ
ደግሞ አኳ ተንኮሏ
ላየው ሰው አመሏ
ይገርማል !

የሚዜዋ ብዛት የሷ ሳቅ ፈገግታ
ለሰርጎ ተብሎ ፣
ለሚጎተተው በግ ሆኖበታል ዋይታ
ጭንቅ ..........ሲቃ
ነብሱ ከስጋው ተናንቃ
አሁን....... አሁን
ጣሉኝ ጣሉኝ ከመሬት እንደ እቃ
እንዲህ ነው የበግ ጉዞ በጨረቃ
ለዚህ ነው ማልታደም ድግስ ሰርጎን
አመሎ ነው በግን ማረድ በሰቀቀን ።
አዎ ! ማረድ
እኔማ ጨረቃን ፣
ድሮም አልወዳትም
አጃቢዋ ብዙ ፣
አሷ ሰርጎ የትም ።


.........
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍21
ፍቃዱ ግርማ

ምን ያልሆነው አለ

እንደ አሮጌ እቃ ወዲህ ወዳ ሲሉን
አንደኛው ሲገፋን ሌላኛው ሲጥለን
ሲረማመድብን እንዳሻው አድርጎ
ለተበዳይ ወገን ከልካይ የለም ሸንጎ ።

የለም ፍርድ ለተከፋ
እንባ ብቻ በአካፋ
አይደለም ጭንቅ የእናት ምጥ
ብቻ...ብቻ ዝም ብሎት ከንፈር መምጠጥ
ማጨብጨብ ነው ለይስሙላ
መሻገሪያ ያልነው ፣
በቅፅበት ሲጠፋ ሳይሆነን ከለላ
ምን ይሉታል እሄን ሁላ
ኑሮ ነው ግን ወንድም ወንድሙን አየጠላ
ብቻ አላውቅም
እየተሸከምን ግፍን በትክሻ
አሁንስ አቃተን !
አጥንታችን ደቆ አሰኝን ወጌሻ ።

ኧረ በቃን !
አቃተን !
ተዉን !

........
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍2
ማርያም እናቴ

ምን ጎደለኝ አንቺን እዤ
በስምሽ ለይ ተመርኩዤ
ምን ጎደለኝ እኮ ምንድን
በአንቺ ልጅ ነው ፍጥረት 'ሚድን
አንቺን ይዤ ሁሉም አለኝ
ምንም የለም አንዳች ነገር የጎደለኝ ።

ክበሪልኝ 🙏🙏🙏

........
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍4
ፍቃዱ ግርማ

ሳጉረመርም ሳመነታ
ይጠራኛል የቤቴን በር እየመታ
ስወድቅበት እያነሳኝ
ሲከፋኝም እያፅናናኝ
ስጠፋበት ሲመልሰኝ
ረከስኩ ስል አከበረኝ ።

ማን አለ በዚ ምድር
ሲያሰቀይሙት የሚል ይቅር ?
አፅናኝ ማነው ? አስታማሚ
ችግር ስቃይ ሁሉን ሰሚ ?
እሱ ነው እሱ ብቻ
የኔን ቅኔ ወርቁን መፍቻ ።

እሱማ ........
ስለምነው አንገቴን አያስደፋኝ
ጨምሮ ነው የሚያነግሰኝ
ስለሚያውቀው የኔን ማጀት
በረከት ነው ሚሞላበት ።
.
.
.
እኔም አልኩኝ
ተመስገን / *3 / 🙏🙏🙏


........
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍9
ፍቃዱ ግርማ


ስወዳት
ሳፈቅራት
እሷን እሷን እያልኩ ዝንት አለም ከርሜ
ማግባቷን ሳልሰማ .....
ወለደች ይበሉኝ ዛሬ በቅዳሜ
ቱ ! ይገርማል !
ግን እንዴት አስቻለሽ እንደምን ተብሎ
ያፈቀረን ገላ መሄድ ዝም ብሎ
እንዴት ........እንዴት
ወዴት .........ወዴት
እንትን ......... 👧
ምን ? እኮ ምንድን ?
ተዪው ተዪው ምንም አይደል
ምንም ምንም .......
አንቺን ከተመቸሽ ጎዳሽ ሁሉ ሞልቶ
ለእኔም አታስቢ እግዜር አለ ከቶ
ብቻ ላንቺው ይድላሽ እሰከ መጨረሻ
አንድ ቀን ይመጣል ለኔም አንቺን መርሻ ።

ይ.....መ....ች.....ሽ...

.........
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍5
ፍቃዱ ግርማ

እሷና እሱ

እሱ....

ያወልሽ ጎዳናው ያውልሽ መንገዱ
አይገደኝም እኔ ሌላ ሰው መልመዱ ።

እሷ...

ድሮም አውቅሃለሁ ገራገር ነው ልብህ
ሁሉን መልመድ እንጂ ማፍቀር
ዬት ታውቃለህ

እሱ.....

መውደዴን ስሰጠው ፊቱን ላዞረብኝ
እሄው ነው ምላሼ ሆዴም ስሲቆርጥልኝ

እሷ.....

ከሄድክበትማ ጎዳና ይወስዳል
ግን ኃላ .....
ፍቅር ገፍቶ ሄዶ መመለስ ይከብዳል

እሱ ......

አልሺውና ፍቅር 😃
ዘውትር ነጋ ጠባ ካንቺ ጋር ጭቅጭቅ
ሰልችቶኛል እኔ ፣
ባክሽ ልሂድበት እስኪ አርጊኝ ለቀቅ

እሷ......

በል እንግዲህ ይቅናህ ጨርቅ ይሁን
መንገዱ
መለየትም አለ ሰው እየወደዱ ?
ይገርማል !

እሱ......

ምን ታደርጊዋለሽ ...
እንዲህ ነው አንዳንዴ አመል ካላመረ
ስው ይቆመጥጣል ....
እንደ ጥንስስ ጌሾ ለአፍ እየመረረ ።

እሷ.......

እ.......... እ...........
እሺ ....ባል ደና ሁን

እሱ.....

አሜን 🙏🙏🙏

..........
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
1👍1
ፍቃዱ ግርማ

እሷና እሱ

እሷ.............👩

ባክህ እንታረቅ አርግልኝ ይቅርታ
ካንተ ተለይቼ አላገኘም ፋታ

እሱ..................👨

በእናትሽ ኧረ ተይ አትቁሚ ከመንገዴ
የፈሰሰ ውሃ ይታፈሳል እንዴ

እሷ ..................👩

አውቃለሁ ጥፋቱ ከኔ እንደሆነ
ምን ግን አንተ እንዲህ ልብህ ደነደነ ?

እሱ.....................👨

አየሺው እንግዲህ ሲረሳ ትዝታ
መከራም ገንቢ ነው ሰው የጠፋ ለታ

እሷ.....................👩

ተው እንዲህ አትበለኝ ተው አታስለቅሰኝ
ወድጄም አይደለም እግሬ ነው የመራኝ

እሱ......................👨

ልክ ነሽ ትክክል ያልሺው ነገር ሁሉ
ጎዳናም ያስኬዳል ወሳጅ ነው ላመሉ

እሷ....................👩

እሺ ተወኩህ በቃ በኔ ካጣህ ፋታ
መቼም ለኔ ፍቅር ካጣህለት ቦታ

እሱ.......................👨

እሺ ...........
ይቅር ብዬሻለሁ ላደረግሺው ነገር
ህይወትሽን ምሪ .......
ከዚ ቡኃላ እንኳን አንጀምርም ፍቅር ።


...........
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍2
ፍቃዱ ግርማ

ይጨንቃል አንዳንድ ቀን
ያስተክዛል በሰቀቀን
ይጠፋል መንገድ ጎዙ
ይደርቃል የሰው ወዙ
አንዳንድ ቀን.........
አይገቱትም ሀሳብን
ጭልጥ ነው በሰመመን
ህልም ነው ሳይታወቅ
መገስገስ ነው ቅርብ ከሩቅ
.
.
.
.
አንዳንድ ቀን...........


.........
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
ፍቃዱ ግርማ

እሷና እሱ

እሱ ...............👨

ህሊናሽ ታወሮ መንገዱን ከሳተ
ክደቱን ከለመድሽ ውሎ ሰነበተ

እሷ..................🧑

ብሄድ ይሻለኛል ብጎዘው በግዜ
ውሸት ካስባለብኝ የፍቅሬ ኑዛዜ

እሱ...................👨

ካዩት ገላ ጋራ መሆን የትም የትም
ሺ ሰው መወደድ እኮ አፍቃሪ አያሰኝም

እሷ..................🧑

እንደዚህም አልከኝ ይሁን ችግር የለም
ሰው ስሙ ነው እንጂ ልቡ አይታወቅም

እሱ...................👨

አየሁት ውስጥሽን ተረዳሁት ወሉን
አፍቃሪን ሸንግሎ መኮብለል መሆኑን

እሷ...................🧑

አታምነኝም በቃ ብምል ብገዘትም
ሌላውን ልፈልግ አንተ አታዋጣኝም

አሱ....................👨

እሄው ዞሮ ዞሮ አፍሽ ተናገረ
ፍቅርሽ ከሺዎቹ ሄዶ እንዳደረ ።

እሷ.................🧑

እትኮንነኝ ልሂድ .......

እሱ ..............👨

ቻው ባይ ባይ ..........


.............
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
1👍1
ዶ/ር ዳዊት ወንድማገኝ

ፍቅር የልጅነት ስሜት ነው ። ልጅነት እውነት ነው ። ስሜት ደግሞ የማይዙትና የማይቆጣጠሩት ።
ፍቅር የማይዙት የማይቆጣጠሩት እውነት ነው ። ከተሰማ ሊክዱት የማይችል ፤ ከሌለም የማይፈጥሩትና ሊያሰመሰሉት የማይችል እውነት ።

ፍቅር ለምን ተፈጠረ ?
ሁሉም የተፈጠረው ለመኖር ስለሚያስፈልግ ነው ። ያለ ፍቅር መኖር ደመናን እንደመጨበጥ ነው ። አለማፍቀር አለመኖር ነው ። አለመኖር ደግሞ ያስፈራል ።
ፍቅር የተፈጠረው መኖር እውነት እንዲመስለን ይሆናል ።

ከጥቂት አመታት ቡኃላ እንደማንኖር ፤ ከጥቂት ዓመታት በፊትም እንዳልነበርን እያወቅን አሁን መኖራችንን እውነት ብሎ ለመቀበል ማፍቀር አንዱ አሰፈላጊ ነገር ነው ። ፍቅር አለመኖርን ያስረሳል ፤ መርሳትን የመሰለ ደግሞ ምን አለ ?

__ // ___


'' አለመኖር '' ከሚለው መፅሐፍ
የተወሰደ

...........
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
ፍቃዱ ግርማ

ናፍቆት

እሷና እሱ

እሱ.......................👨

የኔ ቆንጆ የኔ አባባ
ናፍቀሺኛል ሆዴ ባባ

እሷ.....................🧑

አይዞህ አይዞህ ........
እስከመጣ አንተን እስካይ
የኔም ናፍቆት ሆኖብኛል በላይ በላይ

እሱ....................👨

ወፍ አይደለሁ በሰማይ ለይ እኔም አልበር
ተራርቀን አደቀቀኝ ያንቺ ፍቅር

እሷ......................👨

ባላየህ ነው የኔን አንጀት ሲንሰፈሰፍ
ባየሁ ቁጥር ሰው ከሚስቱ ሲተቃቀፍ

እሱ ........................👨

እውነት ወዴ ማህተቤ ነሽ የፍቅሬ ቃል
ሌላው ቀርቶ ትንፋሽሽም ይናፍቃል

እሷ ......................👨

ያንተስ ቢሆን መች ይረሳል ሁሉም ነገር
የልቤ ስው ውብ ገራገር

እሱ.......................🧑

ግን ወዴ
ምን አረግሺኝ ላንቺ ዜማ ሰርክ ምቀኝ
እዚህ ሲሉኝ ካንቺ ዘንዳ እኔ ምገኝ

እሷ .........................👨

አየህ.......
እንደዚህ ነው በሙሉ ልብ ሰው ሲወዱ
ይነዳሃል ፍቅር ራሱ በመንገዱ

እሱ ...............👨

አሺ የኔ ትንቢተኛ......

እሷ................🧑

ሃ ! ሃ ! ሃ !........
መሽቷል አሁን ቶሎ ተኛ

እሱ ....................👨

እ...እ...እሺ ።


t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.ne/fikee21
👍2
ፍቃዱ ግርማ

ናፍቆት

እሷና እሱ

እሷ.........................🧑

ኡፍ.............
ምን ሆነህብኛል ልቤ ተሸበረ
ሌሊቱን በሙሉ ሲያቃዠኝ ያደረ

እሱ................👨

ምነው ውዴ...........
ኧረ ምንም አልሆንኩ አለሁኝ በጤና
አንቺ ሰላለሺኝ እመላለሳለሁ በአምላክ
ጎዳና 🙏

እሷ..................🧑

እሰይ .......
አሁን ቅልል አለኝ ድምፅህን ስሰማ
ነብሴ ትራባለች አንተኑ ደጋግማ

እሱ..............👨

አልሺወና......
አንቺ ስላለሽ ነው የምሄደው ቆሜ
ፍቅርሽን ሳስብ ነው የሚቀለኝ ሸክሜ

እሷ..................🧑

አለሁልህ የኔ አባት
ጎዳኝ ብቻ ያንተ ናፍቆት

እሱ..................👨

የኔንስ ማን አየው ትዝታ ሲገርፈኝ
ላያደርስ ነገር ሀሳብ መዓበሉ .....
ወደ አንቺ እየናጠኝ

እሷ...............🧑

ቻል አርገው እንግዲ አታማርር ፍቅሬ
አልፎ ታየዋለህ የትዕግስትን ፍሬ

እሱ..................👨

እሺ የኔ መካሪ ።🙏🙏🙏

.............
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍3
አባቴ ብስራተ ገብርኤል

ከእሳት ብወረወር መች እሸበራለሁ
ገብርኤል ይመጣል እጠብቀዋለሁ
አዳኝ ነው በ'ውነቱ ለታመኑት ሁሉ
ነዲዱ ነበልባል ይጠፋል በክንዱ ።

አሜን 🙏🙏🙏 19

.........
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.mr/fikee21
👍7