ከህይወት ገፅ የግጥም መድብል
1.79K subscribers
55 photos
2 videos
1 file
331 links
........ኑ
ስሜትን በግጥም እንግለፅ
ትውልድን በጥበብ እናንፅ ።

የፍቅር ቤት እዚህ ነው !
አሰተያየት ካላችሁ
👇
@fikee12 ላይ ማድረስ ይቻላል
Download Telegram
ፍቃዱ ግርማ

ጨፈርን እንደ ጉድ ደነስን እስኪበቃን
ደቂቃ ከሰዓት ሳንዘል አንዲት ቀን
በለፀግን አልን ልብሳችንን ጥለን
መዝናናቱን አልነው መንገዱ መች በቃን
ደግሞ ምላሳችን የልምዳችን ሱሱ
ዘምነናል ሆኗል ለጥያቄው መልሱ ።
ግን .....
እወነት ዘምነናል ?

.......
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍3
ፍቃዱ ግርማ

ጥላቻ አውሮሽ መንገድሽ ሲጠፋ
የጥፋትሽ ወሰን እያደር ሲሰፋ
ሀይ የሚልሽ ሸንጎ ዳኛ ስለጠፋ
ተኩሶ ጥሎ ቁም ሆነ ያንቺ ተስፋ ።

ይገርማል 😌


t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍1
ገብረ ክርስቶስ ደስታ

መነሻ ስእል

አያልቅም ይህ ጉዞ ........
ማስመሰል - መተርጎም
በቀለም መዋኘት
በመስመር መዋኝት
ከብርሃን መጋጨት
ለማወቅ ለመፍጠር ባዶ ቦታ መግባት ።
መፈለግ ... ... .. መፈለግ . . .
አዲስ ነገር መፍጠር
ከማይታየው ጋር ሄዶ መነጋገር ።
ህይወትን መጠየቅ
ሃሳብን መጠየቅ
አለምን መጠየቅ
መሄድ መሄድ መሄድ . . . .
ከጨረቃ በላይ
ከኮኮቦች በላይ
ከሰማዩ በላይ ።
መጎዝ ወደ ሌላ ባዶ ቦታ መግባት
በሃሳብ መደበቅ ፡
መፈለግ ማስገኘት ።
አያልቅም ይህ ጉዞ ......

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
ፍቃዱ ግርማ

'' አንቺዬ ''

ፍቅር እያጠፋሽ ጥላቻሽ በርክቶ
መቆም የቃተሽ ለት ከአንድ ስፍራ ረግቶ
ዘመቻሽ ከበዛ ጊዜ ገደብ አጥቶ
ጦር አዝምት መሆንሽ የሚያውቅልሽ ሁሉ
አንቺን በመረዳት የገባቸው ውሉ
እብድ ናት ከማላት ሌላ ምን ይበሉ ። ?

ምንም ...

......
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
እሳት ወይ አበባ

ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን

ወንድ ብቻውን ነው እሚያለቅስ

ከወዳጅ ዘመድ ርቆ
አንጀቱን በአንጀቱ ታጥቆ
ተሸሸጎ ተገልሎ ፥ ተሸማቆ ተሸምቆ
ከቤተ - ሰው ተደብቆ
መሽቶ የማታ ማታ ነው ፥ ሌት ነው የወንድ
ልጅ እንባው
ብቻውን ነው የሚፈታው .......
ብቻውን ነው የሚረታው .......
ችሎ ፥ ወጦ ፥ ተጨብጦ ፥ ተማምጦ
ተጣጥሮ
በሲቃ ግት ተወጥሮ
እንደ ደመና ተቋጥሮ
እውስጥ አንጀቱ ተቀብሮ ....
መሽቶ ፥ ረፍዶ ፥ ጀምበር ጠልቆ
የጨለማ ድባብ ወድቆ
በእንቅልፍ ጥላ ሲከበብ ፥ በዝምታ
ሲዋጥ አገር
ፍጡር ሁሉ ተሰለምልሞ ፥ ብቸኝነት
ብቻ ሲቀር ......
የኃላ የኃላ ማታ
ምድር አገሩ በእፎይታ
አይኑን በእንቅልፍ ሲያስፈታ
ሁሉ በእረፍት ዓለም ርቆ ፥ ብቸኝነት
ብቻ ሲቀርብ
ያኔ ነው ወንድ አይኑ የሚረጥብ
የብቻ ፥ እንባ አይኑ የሚረጥብ ።
.......................

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍4
ፍቃዱ ግርማ

አያድርስ ከቶ

እማታገኝውን ሺህ ግዜ መናፈቅ
ለማይሆነው ነገር ሺህ ግዜ መጨነቅ
እራስክን ከማጣት ምንም አታተርፍም
ዝብርቅርቅ ባለበት በዚህ ከንቱ አለም
አይጣልብህ እንጂ አያድርስ ከቶ
በዚች አለም ኑሮ ማንስ ያቃል ረክቶ ። ?

ማንም
.......
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍4
ፍቃዱ ግርማ

ጥላቻ

በፍቅር እንዳልደመቅን ፈክተን እንደ አበባ
ደግነትም ጠፍታ ጥላቻ እኛን ቀርባ
ተለያዩ ብትል መሪር በሆነ ቃል
ቃልህ ቃልኪዳኔ እንዴት ብሎ ያልቃል
ጥላቻ የሚሏት እኛ ሀገር ገብታ
ታየቺኝ ስትመጣ ክፋትን ጎትታ
እናማ ወንድሜ ክንድህን አበርታ
ጥላቻ ለሚሏት መቼም አትረታ ።

አይዞህ እንበርታ !

........
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍2
አባቴ ማረኝ

ምፅዋቴ ሁሉ ሆነ በብርሃን
ከጠፉት በጎችህ እኔ አንዱ አሆን ??

አላውቅም ።

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
ፍቃዱ ግርማ

እስትንፋስን እፍ ብለህ ሰው አረከኝ
ከትቢያ ለይ
ተመስገን ነው የኔ ምላሽ ከምድር
እስኪ ሰማይ
ብወድቅ እንኳን ሆነህ ምርኩዝ
አነሳሃኝ እኔ ልጅህ እንድጎብዝ
ሰርክ ሁሌ እረኛዬ
አየሆንከኝ ሀይል ብርታት መፅናኛዬ
ለችግሬ መሻገሪያ
አንተ እኮ ነህ መነፅሬ ሁሉን ማያ
ምንም እንኳን እኔ ከንቱ እየሆንኩኝ
ባሰቸግርም
እኔን ምንም ርካሽ ምንም ለመፈወስ
አትሰለችም ።

......
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
3
እናት
ፍቅር
ሐገር


አሌክስ አብረሃም

/ ከንፈር ግን ሲገርም / !

እኔ የምልሽ ወዴ ፣
የጀነት በር ማለት ከንፈርሽ ነው እንዴ ?

ምን አባቴ ልበል.......!
ስትሰሚኝ ግዜ
ፊቴ የነበረው ፎከታም ግርግዳ ዬት አባቱ
ሄደ ?
ወስጤ የተገነባው የጭንቀት ባቢሎን
ከመኔው ተናደ !
ስትስሚኝ ግዜ
በህሊናዬ ወስጥ ያንን ሁሉ አበባ
ማን ተክሎት በቀለ !
ይሄስ ሁሉ ደስታ
ከዬት ተጠራርቶ ወስጤ ተቆለለ ?

ተፈጥሮን ገልብጦ እናቴን በጥብጦ ፣
ፀሐይን በምዕራብ አወጣት ከንፈርሽ ፣

መገን አሳሳምሽ !!

ብትስሚኝ ግዜ
ዝሆኖች በረሩ
እባቦች ጋለቡ ፣
በባዶ ልቤ ወስጥ
እልፍ ሰርጎች ገቡ ........

እናት ፡ ፍቅር ፡ ሐገር
አሌክስ አብራሃም

t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍2
ፍቃዱ ግርማ

ጮህን .... ጮህን
ኡ......ኡ .....
አጣን እንጂ አንድም ሰሚ
መንገዱ እየጠፋን እያጣን ጠቋሚ
አለቀስን .......... ስቅስቅ አለን
ለፋን ዳከረን..... ተንከራተትን
ሄድን ሄድን ወጣን ወረድን
አኪያሀዱ ጉዞው ጠፍቶን
ምንም አጣን
ምንም ምንም
ነገሩ ሁሉ አለብን ጥምም ።
.
.
.
.
.
.
እኛም አለን ዝም !

.......
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍1
ፍቃዱ ግርማ

አገኝሁ የልቤን መሻት
እንደ ነብሴ የምወዳት
እንደ ብሌን ምሳሳላት
እስትንፋስ ናት የምወዳት ።
ማመስገኛ ዜማ ቃሌ
አገኘሁ ተዋህዳ ከአካሌ
ሰመረልኝ ደሟ ደሜ
ፈውስ ሆነች ለህመሜ
በህይወቴ ሆናኝ ብርታት
ወጣሁባት ስንት አቀበት ።

........
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍1
ፍቃዱ ግርማ

ምን አለ ባልመሸ ፣
ጀንበር ባልጠለቀ
ውሎ ቢያድር ምነው ፣
ሰማይ እነደሳቀ ።

እኔማ ጨረቃን ፣
ድሮም አልወዳትም
አጃቢዋ ብዙ ፣
እሷ ስርጎ የትም
ድግስ አይሰለቻት መብላት መጠጣቱ
ፀሃይ ስትዘቀዝቅ ይይዛታል ግቱ
ደግሞ አኳ ተንኮሏ
ላየው ሰው አመሏ
ይገርማል !

የሚዜዋ ብዛት የሷ ሳቅ ፈገግታ
ለሰርጎ ተብሎ ፣
ለሚጎተተው በግ ሆኖበታል ዋይታ
ጭንቅ ..........ሲቃ
ነብሱ ከስጋው ተናንቃ
አሁን....... አሁን
ጣሉኝ ጣሉኝ ከመሬት እንደ እቃ
እንዲህ ነው የበግ ጉዞ በጨረቃ
ለዚህ ነው ማልታደም ድግስ ሰርጎን
አመሎ ነው በግን ማረድ በሰቀቀን ።
አዎ ! ማረድ
እኔማ ጨረቃን ፣
ድሮም አልወዳትም
አጃቢዋ ብዙ ፣
አሷ ሰርጎ የትም ።


.........
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍21
ፍቃዱ ግርማ

ምን ያልሆነው አለ

እንደ አሮጌ እቃ ወዲህ ወዳ ሲሉን
አንደኛው ሲገፋን ሌላኛው ሲጥለን
ሲረማመድብን እንዳሻው አድርጎ
ለተበዳይ ወገን ከልካይ የለም ሸንጎ ።

የለም ፍርድ ለተከፋ
እንባ ብቻ በአካፋ
አይደለም ጭንቅ የእናት ምጥ
ብቻ...ብቻ ዝም ብሎት ከንፈር መምጠጥ
ማጨብጨብ ነው ለይስሙላ
መሻገሪያ ያልነው ፣
በቅፅበት ሲጠፋ ሳይሆነን ከለላ
ምን ይሉታል እሄን ሁላ
ኑሮ ነው ግን ወንድም ወንድሙን አየጠላ
ብቻ አላውቅም
እየተሸከምን ግፍን በትክሻ
አሁንስ አቃተን !
አጥንታችን ደቆ አሰኝን ወጌሻ ።

ኧረ በቃን !
አቃተን !
ተዉን !

........
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍2
ማርያም እናቴ

ምን ጎደለኝ አንቺን እዤ
በስምሽ ለይ ተመርኩዤ
ምን ጎደለኝ እኮ ምንድን
በአንቺ ልጅ ነው ፍጥረት 'ሚድን
አንቺን ይዤ ሁሉም አለኝ
ምንም የለም አንዳች ነገር የጎደለኝ ።

ክበሪልኝ 🙏🙏🙏

........
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍4
ፍቃዱ ግርማ

ሳጉረመርም ሳመነታ
ይጠራኛል የቤቴን በር እየመታ
ስወድቅበት እያነሳኝ
ሲከፋኝም እያፅናናኝ
ስጠፋበት ሲመልሰኝ
ረከስኩ ስል አከበረኝ ።

ማን አለ በዚ ምድር
ሲያሰቀይሙት የሚል ይቅር ?
አፅናኝ ማነው ? አስታማሚ
ችግር ስቃይ ሁሉን ሰሚ ?
እሱ ነው እሱ ብቻ
የኔን ቅኔ ወርቁን መፍቻ ።

እሱማ ........
ስለምነው አንገቴን አያስደፋኝ
ጨምሮ ነው የሚያነግሰኝ
ስለሚያውቀው የኔን ማጀት
በረከት ነው ሚሞላበት ።
.
.
.
እኔም አልኩኝ
ተመስገን / *3 / 🙏🙏🙏


........
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍9
ፍቃዱ ግርማ


ስወዳት
ሳፈቅራት
እሷን እሷን እያልኩ ዝንት አለም ከርሜ
ማግባቷን ሳልሰማ .....
ወለደች ይበሉኝ ዛሬ በቅዳሜ
ቱ ! ይገርማል !
ግን እንዴት አስቻለሽ እንደምን ተብሎ
ያፈቀረን ገላ መሄድ ዝም ብሎ
እንዴት ........እንዴት
ወዴት .........ወዴት
እንትን ......... 👧
ምን ? እኮ ምንድን ?
ተዪው ተዪው ምንም አይደል
ምንም ምንም .......
አንቺን ከተመቸሽ ጎዳሽ ሁሉ ሞልቶ
ለእኔም አታስቢ እግዜር አለ ከቶ
ብቻ ላንቺው ይድላሽ እሰከ መጨረሻ
አንድ ቀን ይመጣል ለኔም አንቺን መርሻ ።

ይ.....መ....ች.....ሽ...

.........
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍5
ፍቃዱ ግርማ

እሷና እሱ

እሱ....

ያወልሽ ጎዳናው ያውልሽ መንገዱ
አይገደኝም እኔ ሌላ ሰው መልመዱ ።

እሷ...

ድሮም አውቅሃለሁ ገራገር ነው ልብህ
ሁሉን መልመድ እንጂ ማፍቀር
ዬት ታውቃለህ

እሱ.....

መውደዴን ስሰጠው ፊቱን ላዞረብኝ
እሄው ነው ምላሼ ሆዴም ስሲቆርጥልኝ

እሷ.....

ከሄድክበትማ ጎዳና ይወስዳል
ግን ኃላ .....
ፍቅር ገፍቶ ሄዶ መመለስ ይከብዳል

እሱ ......

አልሺውና ፍቅር 😃
ዘውትር ነጋ ጠባ ካንቺ ጋር ጭቅጭቅ
ሰልችቶኛል እኔ ፣
ባክሽ ልሂድበት እስኪ አርጊኝ ለቀቅ

እሷ......

በል እንግዲህ ይቅናህ ጨርቅ ይሁን
መንገዱ
መለየትም አለ ሰው እየወደዱ ?
ይገርማል !

እሱ......

ምን ታደርጊዋለሽ ...
እንዲህ ነው አንዳንዴ አመል ካላመረ
ስው ይቆመጥጣል ....
እንደ ጥንስስ ጌሾ ለአፍ እየመረረ ።

እሷ.......

እ.......... እ...........
እሺ ....ባል ደና ሁን

እሱ.....

አሜን 🙏🙏🙏

..........
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
1👍1
ፍቃዱ ግርማ

እሷና እሱ

እሷ.............👩

ባክህ እንታረቅ አርግልኝ ይቅርታ
ካንተ ተለይቼ አላገኘም ፋታ

እሱ..................👨

በእናትሽ ኧረ ተይ አትቁሚ ከመንገዴ
የፈሰሰ ውሃ ይታፈሳል እንዴ

እሷ ..................👩

አውቃለሁ ጥፋቱ ከኔ እንደሆነ
ምን ግን አንተ እንዲህ ልብህ ደነደነ ?

እሱ.....................👨

አየሺው እንግዲህ ሲረሳ ትዝታ
መከራም ገንቢ ነው ሰው የጠፋ ለታ

እሷ.....................👩

ተው እንዲህ አትበለኝ ተው አታስለቅሰኝ
ወድጄም አይደለም እግሬ ነው የመራኝ

እሱ......................👨

ልክ ነሽ ትክክል ያልሺው ነገር ሁሉ
ጎዳናም ያስኬዳል ወሳጅ ነው ላመሉ

እሷ....................👩

እሺ ተወኩህ በቃ በኔ ካጣህ ፋታ
መቼም ለኔ ፍቅር ካጣህለት ቦታ

እሱ.......................👨

እሺ ...........
ይቅር ብዬሻለሁ ላደረግሺው ነገር
ህይወትሽን ምሪ .......
ከዚ ቡኃላ እንኳን አንጀምርም ፍቅር ።


...........
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21
👍2
ፍቃዱ ግርማ

ይጨንቃል አንዳንድ ቀን
ያስተክዛል በሰቀቀን
ይጠፋል መንገድ ጎዙ
ይደርቃል የሰው ወዙ
አንዳንድ ቀን.........
አይገቱትም ሀሳብን
ጭልጥ ነው በሰመመን
ህልም ነው ሳይታወቅ
መገስገስ ነው ቅርብ ከሩቅ
.
.
.
.
አንዳንድ ቀን...........


.........
t.me/fikee21
t.me/fikee21
t.me/fikee21