ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች
4.59K subscribers
21 photos
2 links
የፍልስፍና እይታዎች
Download Telegram
አራት መቶ ዓመታት የቀደመን ታላቁ ፈላስፋ ዘርያቆብ
የሀሳብ ባይተዋሮች ነን እኛ፡፡ ከክፍለ ዘመናት በፊት ቀድሞን የኖረው ኢትዮጵያዊ ፈላስፋ ይበልጠናል፡፡ ይህ ታላቅ አሳቢ አይዛክ ኒውተን ወይም ኢማኑኤል ካንትና ሄግል ሳይወለዱ በፊት የተወለደ ተራማጅ ፈላስፋ ነው፡፡ ሀሳቦቹ ዛሬ በታላላቅ የአዉሮፓና አሜሪካ የፍልስፍና ትምህርት ቤቶች ይጠናሉ፡፡በአፍሪካ ጭምር የመጀመሪያው ዘመናዊ ፍልስፍናን ያስተማረ ኢትዮጵያዊ ነው፡፡ ከ400 ዓመታት በፊት የኖረ ሲሆን አስደናቂ ፍልስፍናዎችም ነበሩት፡፡ በኃይማኖት ትምህርት ብዙ የገፋ ነበር፡፡ሆኖም አካባቢው ላይ ያስተዋላቸው ችግሮች መለስ ብሎ እውቀቱን እንዲያሰላስል መነሻ ሆነው፡፡ የተለያዩ ኃይማኖቶች የተለያዩ አምላኮችና፣ ምግባሮች ያስተምራሉ፡፡ ሁሉም የኔ ልክ ነው ብለውም ይነሳሉ፡፡ ያ እንዴት ይሆናል? እውነት አንድ ሆና ሳለ የተለያዩ አማኞች የተለያዩ መንገዶችን እየተከተሉ እውነቱ የኔ ነው ብለው ማሰባቸው ልክ ሊሆን አይችልም፡፡ ይህን መሰረት ይዞ ተነሳ ዘርያቆብ እናም እምነቶችን ለመዳኘት ምክኒያት ትልቅ ሚና እንደሚጫወት አስረገጠ፡፡ በዚያ እምነትን መንካት እሳትን ከመንካት በላይ አስፈሪ በነበረበት ዘመን ደፍሮ ፍልስፍናዊ አተያይ ያስተዋወቀ ጀግና ኢትዮጵያዊ ነበር፡፡ምክኒያትን ማዕከል አድርጎ ራሱን ብሎም ዓለምን ለማየት የሞከረ ‹ዘመናዊ› ፈላስፋ ነው፡፡ ስለሱ ማወቅ የቻልነው በቅርቡ ነው፡፡እንደኢትዮጵያዊ አሳቢ ግን ከሱ በኋላ የተነሳ እሱን የሚፎካከር ፈላስፋ አልተነሳም፡፡ከአራት መቶ ዓመታት በፊት የኖረ ኢትዮጵያዊ ነው፤ ረኔ ዴካርት፣
ፍራንሲስ ቤከን፣ ዊሊያም ሸክስፒር፣ ቶማስ ሆብስ፣ ጆን ሎክና ሌሎች ታዋቂ የአዉሮፓ ፈላስፎችና ጠበብት በተነሱበት ዘመን የኖረ ወርቅማ ልቅና የነበረው አፍሪካዊ ሊቅ ነው፡፡በተለይ ኃይማኖትን ደፍሮ በምክኒያት ለመረዳት ያደረገው ጥረት ብዙ ፈተና አስከትሎበታል፡፡
ያም ሆኖ ከኢትዮጵያ ሰማይ በታች
አስደናቂ የፍልስፍና ሀሳቦችን የወለደ ቀዳማይ ፈላስፋችን ነው፡፡
#የዘር ካርድ...
#በሙሀመድ አሊ ቡርሃን
"ትልቅ ሰው ትልቅ ሆኖ አይወለድም ፤ ትልቅ ለመሆን ራሱን ያሳድጋል እንጂ''/ሊዮ ቶልስቶይ /
አሁን ያለህበትን ሁኔታ እያየህ ለምን ትንሽ ሆንኩኝ ? ብለህ የምትቆጭ ከሆነ መቼም ቢሆን ትልቅ ሰው ልትሆን አትችልም።
:
ሁሉም በዓለም ላይ ያሉ ትልቅ ሰዎች መጀመሪያ ትንሽ ነበሩ። ማንም የማያውቃቸው ተራ ሰው ነበሩ ።
:
በጊዜ ሂደት ግን እውቀታቸውን እያዳበሩ አስተሳሰባቸውን እያሰፉ እምነታቸውን እያጠነከሩ ፍልስፍናቸውን እያጎለበቱ አመለካከታቸውን እያቀኑ ራእያቸውን እያገዘፉ ውሳኔያቸውን እያጠነከሩ አሁን ያላቸውን ትልቅ ማንነት ፈጠሩ ። አሁን
ያላቸውንም የማይደረስበት የመሰለ እጅግ ትልቅ ማንነትንም ፈጠሩ
:
ሊዮ ቶልስቶይ እንዳለው "ትልቅ ሰው ትልቅ ሆኖ
አይወለድም ፤ ትልቅ ለመሆን ራሱን ያሳድጋል እንጂ ።" አዎ ማንም ትልቅ ሆኖ አልተወለደም ።
:
ባራክ ኦባማ ፕሬዘዳንት ሆኖ አልተወለደም ። ራሱን ግን
የአሜሪካ መሪነት አዘጋጀ ። የመጀመሪ የአሜሪካ ጥቁር
ፕሬዘዳንትም ሆነ ።
:
ሀይሌ ገ/ስላሴ ሯጭ ሆኖ አልተወለደም ። ግን ራሱን
ለረጅም ርቀት ሯጭ ንጉስነት አዘጋጀው ። የ27 የዓለም
ሪከርዶችንም ሰባበረ ።

ሁለቱን ለምሳሌ አየን እንጂ ሁሉም ጀግኖች በአንድ ወቅት ራሳቸውን እንኳን መቆጣጠር የማይችሉ ህጻን ነበሩ ።
የሽንታቸውን ጨርቅ እንኳን እናታቸው ወይ አባታቸው
የሚቀይርላቸው የወላጆቻቸው ጥገኛ ነበሩ ።
ግን እነዚ ሰዎች ራሳቸውን ከጥገኝነት ህይወት አውጥተው አሁን ያሉበት ትልቅ ቦታ ደርሰዋል ።

አያችሁ ህይወት ሁላችንንም በልጅነታችን እንዴት ከጥገኝነት እንደምንላቀቅ አስተምራናለች ። አሁን ያለን ሂወት ላይ ያንን በልጅነታችን እንዴት ራሳችንን ከጥገኝነት እንዳወጣን በማስተማር ለድል እራሳችንን እናዘጋጅ ።
**
በልጅነታችን እየዳህን መሄድ ስንጀምር ምንም ያህል ጊዜ ብንወድቅ ተስፋ አንቆርጥም ፤ እንደገና እንሞክራለን እና ምን ልልህ ፈልጌ መሠለህ መውደቅን አትፍራ!!
#ከተነበበው
#ማረጋገጫ አለህ ??
አማኙ ማረጋገጫ አለህ ስልህ የለም እያልኩህ አይደለም
ኤቲስቱ ማረጋገጫ አለህ ብዬ ስጠይቅህ አለ እያልኩህ
አይደለም።
ያመናችሁበትም ያላመናችሁበትም ምክንያት በጣም አስቂኝ
ነው።
ያመኑበት ስትጠይቃቸው ሊያስረዱት የሚፈልጉት በተፅፏል
ነው ኤቲስቶቹ ደግሞ ስላላየሁት የለም ይልሀል።
አማኞቹ ያለሱ እውነት የለም ብለው አዕምሮአቸውን ሳጥን
ውስጥ ከተውታል ኤቲስቶቹ ደግሞ ፈጣሪ የሚለውን ቃል
ሲሰሙ በቀጥታ ከሀይማኖቱ ከተሰጠው ትርጉም ጋር
ያገናኙታል የሀይማኖቱ ደግሞ አያሳምናቸውም ከሀይማኖት
ውጪ ፈጣሪን ማሰብ ለነሱ ዳገት ነውና የለም ይሉሀል።
ቢግባንግን የሚያመልክም አልጠፋም።ቢግባንግ event
እንጂ ፈጣሪ አይደለም።የዚህ ሁላ ነገር መሰረቱ አንድ
ሲንግል በአይን ልትታይ የማትችል አተም ነች ሊተመን
በማይችል ኢነርጂ ታምቃለች በመጨረሻም
ፈነዳች። የመጀመሪያው አተም ከየት መጣ???
በአለም ላይ ብዙ አምላኮች አሉ ሁሉም ደግሞ በጣም
አስገራሚው ነገር የሚወደቱን ፍጥረት የሰው ልጅን
የሚያቃጥሉበት የእሳት ባህር ባለቤት ናቸው which means hell. ይህንንም ፍርሀት የሰው ልጅ ያመልክ ይሰግድ ጀመር ገሀነም የሚለው ቃል ባይኖር አንድ አማኝ እዚህ ምድር ላይ አይኖርም ነበር። ታላቁ እስክንድርም እኔን አትፈራኝም ብሎ ጠየቀው ዲዮጋንም"ክፋ ነህ እንዴ??"ብሎ ጠየቀው
እስክንድርም"አይደለውም"ብሎ መለሰለት "ክፋ ካልሆንክ
ለምን እፈራሀለው???"የዲዮጋን ጥያቄ ነበር።
አምላካችን ደግ ቸር ነው ይሉሀል መልሰው ደግሞ ገሀነም
ይጥልሀል ይሉሀል።
ቸር ከሆነ ለምን ስትላቸው ቤተሰቦችህ እያጠፋህ ዝም
ይሉህ ነበር መልሳቸው ነው።ይቅርታ ሳጠፋ ዝም ባይሉኝም
የጋለ ብረት ምጣድ ላይ ግን ጥደውኝ አያውቁም።
ሳይንስ ብዙ ያልሆነ ጥቂትም የማይባል ግኝቶችን እያገኘ
ይገኛል።በአማኙና በኤቲስቱ መካከል ያለው ዱላ ቀረሽ
ንትርክ ሳይንስ ላይም ተፅዕኖ እያሳደረ ይገኛልን።በቅርብ ጊዜ
እንኳን በ big bang theory በራሱ አምላክ ያስፈልገዋል
አያስፈልገውም እየተነታረኩ ነው።
ማመን ትክክል ሊሆን አይችልም ኤቲስት መሆን ደግሞ
ጠቢብነት አይደለም።አንዱ ተነስቶ There is no GOD ቢል
ለኤቲስቱ የህይወት ቃል፣ለአማኙ ደግሞ የሞት ነው።
መልስ የሌለው ጥያቄ ሊኖር እንደሚችል መጠርጠር
አስፈላጊ ነው።
አማኙ ቅዠት ውስጥ ነው ኤቲስቱ ደግሞ በሎጂክ ስም
ይማግጣል።ከአማኙም ከኤቲስቱም አለመሆን !!
ኦሾ/osho
ምንጭ ብርሃነ ሂሊና
💞 💕 💘
#ለማወቅ የምንፈልገውን ነገር ሁሉ መጀመርያ እናፈቅረው ዘንድ የተገባ ነው። ለማንኛውም የህይወት ዘርፍ የስኬት ቁልፍ ፍቅር ነው። ዳቪንቺ ስዕልን ከምንም በላይ አፈቀራት ታወቀባትም። ሞዛርት ሙዚቃን አፈቀራት ፥ ከፍ ከፍም አረገችው። ሼክስፒር ስነፅሁፍ ፍቅረኛው ሆነች፥በስሟም አነገሰችው። የፍቅር ንጉስ እየሱስ ክርስቶስ በፍቅሩ አለምን ማረከ ፥ አለም ተንበረከከችለትም።
እውነተኛ ታላቅነት እንግዲ ሚመጣው ከማፍቀር ነው። እየሱስን መምሰል ሚቻለው በፍቅር ብቻ ነው። ቡድሃን ለመሆን ማፍቀር ግዴታ ነው። ቡድሃ ማፍቀር ስትችል እግዚሃብሔርን መምሰል ትጀምራለህ ይላል።

ፍቅር ነፍስን በሚወዱት ሰው ውስጥ መግደል ነው ይለናል ኦሾ። ፍቅር ከስግብግብነት የፀዳ ማንነት ነው። እውነተኛ አፍቃሪ የሚያፈቅረውን ሰው ደስታ ለማየት ለ መሰዋት የተዘጋጀ ነው።
ሀዲስ አለማየው ስለ ፍቅር እንዲ ይላሉ፥ አይንን ክፉ ከማየት ምላስን ክፉ ከማውራት ጆሮንም ከመስማት ፥ምናብንም ከፉ ከማለም የማይከለክል ፍቅር ፥ ፍቅር አይደለም። ፍቅር ለ አሉታዊ ውጤት ምንም ግምት አይሰጥም። ለፍቅር አለም ሁሌም ብሩህ ናት።
ፍቅር ሙሉነትን የመፈለግ መንገድ ነው። ግን ይለናል ኦሾ ቀጥሎ ፦ እንደመሰለው እንደመሰላት እንደመሰለን እንፋቀራለን። በማይረባ መንገድ። እራስ ወዳድነትን በተላበሰ መንገድ እናፈቅራለን። ማፍቀር ግዴት ይመስል እናፈቅራለን። ጥላቻ አርግዘን እናፈቅራለን። እራስ ወዳድነትን አርግዘን እናፈቅራለን። ፈርተን እናፈቅራለን። ከዛም ሲሰለችን ስለ እውነተኛ ፍቅር መሞት ማላዘን እንጅምራለን። ባዶነት ይሰማናል። ትላንት ያፈቀርነው ዛሬ ጠላት ይሆንብናል። የማናውቀው ሰው ጠላት ሊሆነን አይችልም ። ጠላት እንኳን ጠላት ለመሆን የግድ በጓደኝነት ውስጥ ማለፍ አለበት። ልክ ያልሆነ ፍቅር ወዳጅ ሳይሆን ጠላት ያተርፋል። የማፍቀር ብቸኛው ምክንያት ፍቅር ካልሆነ ሌላው አላፊ ነውና ጭንቀትን ይወልዳል።

#ጥበብ ከጲላጦስ ቅፅ አንድ የተቀነጫጨበ
.. የተፈጠረው ሰውም የፈጠረው አምላክም አያልቅባቸውም። ምናልባት ሰውን ከሁሉ ሌላ ፍጡር የተለየ ብቸኛ የሚያደርገው፣ ከመልአክ እኩል ደግና በጎ አድራጊ ለመሆን መቻሉ፣ እና በዚያም መጠን ከሰይጣን እኩል ከይሲ እርኩስ ስራዎችን እንደ ቅዱስ ተግባር እያመለካቸውና እየታዘዛቸው መፈፀሙ ነው። ሂትለር ብዙ ሚሊዮን የሚኖሩባትን ሀገር አፀዳታለሁ፣ አይሁድ የሚባለውን ቆሻሻ ከኛ ከንፁሀን ነጮች አገር እየጠረግኩም፣ እያቃጠልኩም አስወጣዋለሁ ብሎ ተነስቶ ዛቻውን ፈፀመ።
.. ሂትለር ሰው አይደለም አንልም መቸስ። ግን ሂትለር ሰው ከሆነ "ሰው ሰይጣን ነው፣ ሰይጣን ሰው ነው" አንዳንዴ።
.. የሰው ልጅ ምድርን እስኪያጣብባት መብዛቱ እነ ሂትለርን በይህ በኩል፣ እነ ማህታማ ጋንድሂን በያ በኩል ማስገኘት ምን ያቅተዋል ?"
*
👉 ስብሀት ገብረ እግዚአብሄር
("ሰውና ማስመሰል".. ከተሰኘው መጣጥፉ የተቀነጨ
ሌላ ሰው
"......ሰው መሆን የጊዜ እስረኛ መሆን ነው።
'ጊዜ የዘላለም አሽከር ሲሆን ሰው ደግሞ የጊዜ ባሪያ ነው ። ሰው ጊዜን በደቂቃና በሰዓት : በወራትና በዓመታት ሸንሽኖ : ከግድግዳው ላይ ሰቅሎ በዕጁ ላይ ጠፍሮ ሊገዛው ሊቆጣጠረው ይሞክራል ። ጊዜ ደግሞ ሰውን ከልጅነት ወደ ወጣትነት : ከጉልምስና ወደ እርጅና እያክለፈለፈ ከሞት ደጃፍ ያደርስና መቃብር ይጨምረዋል ። በክረምትና በበጋ : በፀደይና በመጸው እየተመሠለ መልኩን እየቀያየረ ሲመጣና ሲሄድ : ሲዞርና ሲፈራረቅ ... የጊዜ ጉዞ ያዙሪት'ንጅ የወደፊት አይመስልም ። በድል ፈረስ ላይ ተቆናጦ በስኬትና በውድቀት : በቀጠሮና በድንገት : በጥበቃና በጥድፊያ ተጠቅሞ የሠውን ዕጣፈንታ የሚወስን ጊዜ መሆኑን በቀላሉ እንዘነጋለን ። ጊዜን መግዛት ሲባል ራስን እንጅ ጊዜን ማስገዛት አይደለም ።

በጊዜ ውስጥ "ትናንት" የትዝታ : "ነገ" ደግሞ የተስፋ ጎተራ ናቸው ።ካመለጠ ትናንት .... ያልመጣ ነገ ይሻላል ። በእጅ ያለ ዛሬ ግን ከሁሉም ይበልጣል ።

ዛሬ ሁሌም ያለ እየመሠለ የማይደገም... ተመልሶም የማይመጣ...ላንድ አፍታ ለቅፅበት ታይቶ ዳርቻ ከሌለው የዘላለም ጠፈር ገብቶ የሚሠወር ... በትናንትና በነገ መሀል የተሸነቆረ ነው ። የዛሬ ሚስጢሩና ጉልበቱ ያለው ደግሞ 'አሁን' ላይ ነው ። 'ቅድም' እና 'በሗላ' ግን ያለቦታቸው ዛሬ ውስጥ የተደነቀሩ የትናንትናና የነገ ሽርፍራፊዎች ናቸው።

የእድሜ ባለፀጋ የሆኑ ጨቅላ ህፃናት ካልተነካ ቱባ ዕድሜያቸው ላይ ብዙ ዛሬዎች መና ከዋሉ በስተመጨረሻ በፀፀት የተሞላ እርጅና ኩሊ መሆናቸው አይቀርም ። የልጅነት ጨዋታ : የወጣትነት ፍቅር :የጉልምስና ስኬትና የእርጅና ሞገስ በዋናነት የዛሬ ዕድል ፍሬዎች እንጅ የነገ ተስፋ ወይም የትናንት ትዝታ ውጤቶች አይደሉም ። ........."
#ሌላ ሰው
በምህረት
የሰው ልጅን በኦሾ እይታ
ስለ ሰው ልጅ ብዙ ብዙ
ያለው ኦሾ በዚች ምድር አምሳያውን የሚገድል ፍጡር ቢኖር
የሰው ልጅ ብቻ ነው በማለት ያስቀምጥና የትኛውም እንሰሳ
መርዝ አወጋጅቶ ስለት ስሎ ሰዋራ ቦታ ጠብቆ ወይ በገመድ
አንቆ አልያም ጥይት ተኩሶ አምሳያውን የገደለበት አጋጣሚ
በአለም አልታየም ይለናል
ሌላው በትምህርታዊ ነገር ስለ ሰው ልጅ የገለፀልን ነገር
እንዲህ ይላል በአንድ ሆስፒታል ውስጥ የመጀመሪያው ታማሚ
ክፍል የተዘጋ በር ላይ ' በእባብ የተነደፈ ሰው በህክምና ላይ
የሚገኝ ሲሆን ከ30 ደቂቃ ቦኃላ ድኖ ይወጣል ' ይላል
ሁለተኛው በር ላይ " በአንበሳ የተነከሰ ሰው በህክምና ላይ
ይገኛል ከአንድ ሰአት ቦኃላ ድኖ ይወጣል " ይላል ሶስተኛው በር
ላይ ደግሞ በሰው የተነከሰ ሰው በህክምና ላይ ይገኛል ህይወቱ
ስለ መትረፉ እንኳን እርግጠኞች አይደለንም " በማለት የሰው
ልጅን እርኩሳዊ ባህሪ ሊያስረዳን ሞክሯል ቅዱስ ሆናችሁ
ተወልዳችሁ ሰይጣን ሆናችሁ ትሞታላችሁ የሚለን እሾ
እርኩስም ቅዱስም የመሆን ምርጫው እኛው ጋር እንዳለ
አስረግጦ ያሳስበናል
የትኛውም እንሰሳ የተራክቦ ስሜቱን የሚወጣው የሴቷን ሽንት
አሽትቶና እርጉዝ አለመሆኗን አረጋግጦ ሲሆን ይህንንም
ለማድረግ ወቅትና የሴቷን ፈቃደኝነት ተከትሎ ነው የሰው ልጅ
ግን ስግብግብ በመሆኑ ያለ ሴቷ ፍቃድና አስገድዶ ደፋሪ ሆኖ
ከእንሰሳ በታች የዘቀጠ የስብዕና ኖሮት አለማፈሩ አስገራሚ
ፍጡር ያደርገዋል ።
ኦሾ/Osho
ግትርነት ምህረትና ርህራሄ አልባና ያደርጋል!!
ግትር መሆን ጅልነት ነው ። በብዙ አቅጣጫ መንቀሳቀስ ደግሞ #ብልህነት ነው ። ብልህነት ሁል ጊዜም እንደ ጅረት መፍሰስ ሲሆን ብልህ አለመሆን እንደ በረዶ ተጋግሮ መቅረት ነው ። ነገ የገዛ ራሱን አጋጣሚዎች ይዞ ይመጣልና የትላንቱን ሃሳቦቻችሁን የሙጥኝ ይዛችሁ ለመዝለቅ መሞከር እንደ በረዶ ረግታችሁ መቅረትን ያስከትላል ።በብልህነት ተንቀሳቀሱ ።/ኦሾ/
እስቲ በታሪክ አስደግፈን እንየው።
ንጉስ_ግኔስ_ፒሶ ቁጡ ፣ ግትር እና ማስተዋል የጎደለው ንጉስ ነበር ። #ፒሶ ። አንድ ቀን አንድ ወታደር ለአሰሳ ከወጣበት ሲመለስ አብሮት የወጣውን የመቶ አለቃ ትቶት ብቻውን ይመለሳል ። ይህን የሰማው #ንጉስ_ፒሶ ወታደሩ እንዲገደል ትእዛዝ ሰጠ ። ለሞት ፍርዱም ምክንያት ፦ " ወታደሩ መቶ አለቃውን ገድሎት ሊሆን ይችላል ፤ ባይገድለውም ደግሞ አለቃው ትቶ መምጣቱ በራሱ ብቻ ያስገድለዋል " የሚል ነበር ። ሞት የተፈረደበትን ወታደር የሚገድል ሌላ ወታደር ታዘዘና ወደ አንድ ከፍታ ይዞት ይወጣና ሰይፉን መምዘዝ ሲጀምር #የመቶ_አለቃው ድንገት ከተፍ ይላል ። ገዳዩ እና ተገዳዩ በዚህ ደስ ተሰኝተው ከመቶ አለቃው ጋር ሦስቱም ወደ ቤተ መንግስቱ ይመጣሉ ።
ይህን ጊዜ በቤተ መንግስቱ ደስታ ይሆናል ። ነገር ግን #ፒሶ ሶስቱን ወታደሮች በአንድ ላይ ሲመለከት በቁጣ ነደደ ። ወዲያው ሦስቱም እንዲገደሉ ትእዛዝ ሰጠ ።#የፒሶ ምክንያት ደግሞ ፦
"የመጀመሪያው እንዲሞት እስቀድሜ ስለፈረድኩበት ይሞታል ፣ ሁለተኛው ወታደሩን እንዲገድል ትእዛዝ ከሰጠሁት በኃላ ትእዛዜን ባለመፈፀሙ ይሞታል ፣ ሦስተኛው የመቶ አለቃ ደግሞ ለወታደሩ መሞት ምክንያት ስለሆነ እሱም ይሞታል"በማለት ፈረደ።
#አየህ ግትርነት ምህረትና ርህራሄ አልባና ያደርጋልና አስወግደው!!
ፍቅር ማለት በዚህ በምትመለከተው ጨለማ ውስጥ ከሚብለጨለጩት ቁጥር ስፍር የሌላቸው አምፑሎች መሀል፣ ነፍስ አንዷን መርጣ በብርሃኗ ስትደምቅ ነው።
ብርሃን ሁሉ የነፍስን ጨለማ አይገፍም ... ቢበዛ የራስህን ብርሃን ትፈልግ ዘንድ ያግዝህ ይሆናል። ራሳችንን፣ አካባቢያችንን፣ ዓለምን፣ መላውን የሰው ልጅ ሁሉ እንድናይ የሚረዳን ብርሃን ተመርጦ በልባችን ጓዳ ይበራል ... ሰው የቱንም ያህል በደማቅ ብርሃን ቢከበብ እውነተኛውን የራሱን ብርሃን እስካላገኘ ድረስ ነፍሱ ጨለማ ውስጥ ናት"
:
#ከዕለታት ..... ግማሽ ቀን
# አሌክስ አብረሃም
ገፅ 92
"ውጫዊው አለም የማህበረሰብ ተፅዕኖ ፍርሃትና በራስ ያለመተማመንን የፈጠረበት ክብር አልባ ትርምስ ሲሆን
የሰው ልጅ አካላዊና መንፈሳዊ እምቅ ጉልበቱን ያገኝ ዘንድ ፣ መለኮታዊ ግርማ ሞገሱን ይጎናፀፍ ዘንድ የታላቅነቱ ማእከል ወደ ሆነው ወደ ውስጣዊ ማንነቱ መመለስ አለበት። እውነተኛ የንፅህና ሃይል ከውስጥ ወደ ውጭ የሚንተገተግ ሁለንተናዊ ግርማሞገስ ነውና!!"
ኦሾ/osho
የዜን ገዳም ውስጥ ነው። ዋናው የዜን ማስተር በጣም የተንደላቀቀ ህይወት ነው የሚኖረው። የሚኖርበት ቤት የሚበላው ምግብ የሚለብሰው ልብስ የቅንጦት ነው። የበታቾቹ ግን ቁሳዊ ምቾት የላቸውም። የሚጠቀሙት ነገር ሁሉ መደዴ ነው።

አንዱ መነኩሴ ይሄ ሁሌ ይነደዋል ለካ። ከዛ ወደ ማስተሩ ሄዶ እንዲህ አለው፦

"እንዴት እንዲህ አይነት ከፍተኛ የመንፈስ ብቃት ላይ ደርሰህ ሳለ ለቁስ ትገዛለህ? ለኛ ለበታቾችህም ጥሩ አርአያ አይደለም። በመንፈስ የበለፀገ ሰው ለምቾት ደንታ ሊኖረው አይገባም። ቁሳቁስን መናቅ አለብህ።"

ማስተሩም መለሰ፦

"አየህ እኔ መንፈሴ ስለበለፀገ ቁስ ምንም መስሎ አይታየኝም። ለኔ መገልገያ ነው ከዛ ያለፈ ትርጉም የለውም። በመንፈስ ያልነቃ ሰው ምቾት ቢለምድ ይሰናከላል ይሸወዳል። እኔ ያለሁበት የመንፈስ ብቃት ግን ቁሳዊ ምቾትን ያለ መሰናክል መጠቀም ያስችለኛል። እና መንፈሳዊ ብቃት ማለት ስጋን መበደል አይደለም"
ኦሾ/Osho
🌿ስጋችሁ የነፍሳችሁ ማደርያ ነውና እንዳታቆሽሹት ፤
#ነፍሳችሁም የስጋችሁ ማእከል ናትና አታቆሽሿት !!ይህንን ምሳሌ ልብ በሉ ፦ስጋችሁን ልክ እንደ ብርጭቆ ቁጠሩ ፤ ነፍሳችሁን ደግሞ አንደ ውሃ በቆሻሻ ብርጭቆ ንፁህ ውሃ ብትጨምሩ ዞሮ ዞሮ ውሃው መበከሉ (መቆሸሹ) አይቀርም ፣ በንፁህ ብርጭቆ የቆሸሸ (የተበከለ) ውሃን ብትጨምሩ ዞሮ ዞሮ የተሟላ ንፁህነት አይገኝም። ስለዚህ በነፍሳችሁም_በስጋችሁም_ንፁህ_ሁኑ🌿
🌿ኦሾ/Osho
ሃይማኖት የፍልስፍና አስተሳሰብ ነው
🌿
ሃይማኖት በሕይወት ውስጥ አንድን አስተሳሰብ ብቻ መፍትሔ አድርጎ በእምነት መቀበል ነው። ሳይንስ ችግርን ለመፍታት ሃይማኖትን ሊጠቀም ይችላል። ሃይማኖት ችግሩን ከፈታ ይሄም ሳይንስ ነው። ካልፈታው ሌላ አስተሳሰብ መጠቀምም ሳይንስ ነው። ሃይማኖት ግን ችግርን ለመፍታት ሳይንስን አይጠቀምም። ምክንያቱም ለሃይማኖት ብዙ ችግሮችን ለመፍታት ከአንድ አስተሳሰብ ውጪ መጠቀም ሀጥያት በመሆኑ ነው ።

ሃይማኖት የፍልስፍና አስተሳሰብ ነው። ነገር ግን ፍልስፍና ውስጥ ካሉ ሌሎች አስተሳሰቦች የሚለይበት ምክንያት አስተሳሰቡ ትክክል በመሆኑ ሳይሆን ብዙ የተሳሳቱ ሰዎች ትክክል አድርገው ስለተቀበሉት ነው። ለዚህ ደግሞ ዋናው መነሻ ሌሎች ትክክል ሊሆኑ የሚችሉ የአስተሳሰብ አማራጮች ከተሳሳቱ ሰዎች ጋር በመነጣጠል ነው። ብዙ የአስተሳሰብ አማራጮችን በመዝጋት አንድ አስተሳሰብ ብቻ በእምነት መቀበል ካለማሰብ የሚመጣ ችግር ነው። ማሰብ ቢኖር ለሌሎች አስተሳሰቦች እኩል እድል ይሰጥ ነበር። አንድ አስተሳሰብ ሃይማኖት የሚሆነው ስለሌሎች አስተሳሰቦች ማሰብ አቁመህ አንዱን አስተሳሰብ ብቻ በእምነት ስትቀበለው ነው።

ምንጭ ፦ "ሰው መሆን"
እምነት ልክ እንደ ጭንብል ነው የራስህን ኦርጅናል ፊት እየደበቅክ ነው ማመን ሽግግር ነው ጥርጣሬ ምርምር ነው እና ማመን ደግሞ የምርምሩ እርካታ ነው ጥርጣሬ ጥያቄ ሲሆን ማመን መልስ ነው።
አማኝ በፍፁም አይንቀሳቀስም አንድ ጊዜ አምኗል ለዚያ ነው በቢሊዩን የሚቆጠሩ ሰዎች በቤተ ክርስትያኖች ፤ ቤተ መቅደሶች ፤ መስኪዶች ፤ ሙክራቦች ውስጥ የሚያመልኩት ዳሩ ግን አምልኳቸው ከእምነት የመነጨ ነው። አምልኳቸው ከእምነት የመነጨ በመሆኑ እኝህ በቢሊዩን የሚቆጠሩ ሰዎች ሀይማኖተኞች ሳይሆኑ ቀርተዋል። እግዚሀብሄርን አይሹም አግዚሀብሄርን አይፈልጉም እነሱ እግዚሀብሄርን ተቀብለዋል።
እየሱስን ተቀብለናል ይላሉ አቀባበላቸው ግን ደካማ ነው እየሱስን ለማግኘት አልደከሙም የሱን ኑሮ የሱን ስቃይ እሱ ባለፈበት መንገድ ሊጓዙ አይፈልጉም በህይወት ውስጥ ዋጋ የማይጠይቅ ምንም ነነር የለም ልትዋጋ ልትታገል ይገባል እናም ታገኘወለህ ።
ኦሾ/osho
ምንጭ:- ከፍስሀ ጋር መወለድ
"ለሰው ልጅ ከተነገሩት ውሸቶች መሀል እጅግ አደገኞቹ "ስልጡን ነህ" እና እንዲሁም "ሁሉም ሰብአዊ ፍጡር እኩል ነው" የሚባሉት አስተሳሰቦች ናቸው። ምክንያቱም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ስልጣኔ አለ ብለው ኖረው ቢሞቱም ፣ የሰው ልጅ ግን ገና አልሰለጠነም።
በተጨማሪም ይህ እኩልነት የሚባለው ነገር መሰረተ
ቢስ- ተረት ነው። ሌላው ቀርቶ በማንኛውም መንገድ ፣ በማንኛውም መለኪያ ሁለት ሰዎች እንኳን እኩል ሊሆን አይችሉም።"
#ኦሾ/Osho
ራስን መሆን
ትርጉም:- ደመላሽ ጥላሁን
#ሱፊዎች #ሲመክሩ………

አንድ ቀን ነስሩዲን በመንገድ ላይ ሲሄዱ ፊቱ በሀዘን የተኮማተረ አንድ ሰው ትንሽ ከረጢት አንጠልጥሎ ይመለከታል።

በዚህ ጊዜ ነስሩዲን ወደ ሰውየው ተጠግቶ "ምን ሆነሃል"ሲል ይጠይቀዋል።
ሰውየውም"በዚህ ዓለም ላይ የደከምኩበት ነገር በሙሉ በዚች ከረጢት ብቻ ሆነና አዝኛለሁ።
ነስሩዲንም "እንዴት ያሳዝናል"በማለት የሚያፅናናው መስሎ ከረጢቱን ነጥቆት ሮጠ።

በምድር ላይ አለኝ የሚለውን ነገር በሙሉ
የተነጠቀውም ሰውዬ እሪታውን እያቀለጠ
ነስሩዲንን ተከተለው።
ጥቂት ርቀት እንደተጓዙም ነስሩዲን እየሳቀ ቆሞ ጠበቀው።
ሰውየው ከናስሩዲን አጠገብ እንደደረሰም ከረጢቱን ነጥቆ በእቅፎ ይዞ እየተደሰተ"ከረጢቴ! ከረጢቴ! የጠፋችብኝ መስሎኝ ደንግጨ ነበር" አለ።
ናስሩዲንም መሳቁን ሳያቋርጥ:-

"አየህ!የሀዘንህ ምንጭ በእጅህ የያዝከው
ነገር ትንሽ በመሆኑ አልነበረም።
ነገር ግን የሌላውን ሰው ብዙ ነገር በመመልከት ነበር በማለት ጥሎት ሄደ"።
ለዚህ ነው ሱፊዎች ሲመክሩ:-

👉"በህይወት ስጦታ በቃኝ ማለት የደስታ ሁሉ ምንጭ ነው"የሚሉን
#በአዳዲስ ህንፃዎች ውስጥ አሮጌ ችግሮቻችንን
ተሸክመን ከትላንት የተሻልን ይመስለናል...!!"ሰው መሆንን ለማወቅ የሚኬድበት ትግል፣ሁሌም ከብርድ ለመሸሽ ከለላና ጥላ፣ እንዲሁም ሽፋን እንደመፈለግ ነው ። ለዚህም ማሳያው
የአብዛኛው ሰው ቋሚ ፍላጎት ህይወትን"መለወጥ" ነው ። ሁሉም ሰው "ራሴን ለውጬ" ፣"ቤተሰቤን ለውጬ" ፣ መለወጥ አለብኝ....። " ፣"ቤተሰቤን ልለውጥ" ፣ "ሃይማኖቴን ልለውጥ" እያለ ይኖራል ። በዚህ ሁሉ ለውጥ ውስጥ
እያንዳንዱ አዲስ ለውጥ አሮጌ ህይወት እየሆነ እንደ ልብስ ከመደረብ ውጪ እውነተኛ ለውጥ ሳይሆን ይቀራል ። እውነተኛ ለውጥ የማይኖረው ሰው ስላልጣረና ስላልሞከረ ሳይሆን ለውጥ ሂደት እንጂ መድረሻ ባለመሆኑ ነው ። በአንድ ለውጥ መርጋት በሰው ተፈጥሮ ውስጥ ከማይቻሉት ሀቆች አንዱ ነው ።በመሆኑም ሰው ቢለውጥ፣ ቢለውጥ ከደረባቸው የማንነት አልባሳት አንዱን ወይም ሌላውን እንጂ " ሰው...ነቱን " ሊሆን አይችልም ። በኑሮው ግን"ሰው...ነቱን" ሳይሆን ፣ ከድርብ አልባሳት አንዱን እና ለጊዜው የተመቸውን ሲሆን ሃብቱን፣ ጉልበቱንና ወገኑን፣ ሳይሆን ሃይማኖቱንና ብሄሩን፣ አልፎ አልፎም ሃገሩን እና የመሳሰለውን እየመዘዘ፤ የተወደደም፣ የተጠላም፣ የተከበረም፣ የተደፈረም፣የተፈራም፣ የተናቀም እየመሰለው ይኖራል ።
❖አለመኖር..
❖ደራሲ ፦ ዶ/ር ዳዊት ወንድማገኝ
#እውነት እርቃኑን ነው። እናንተን ለማሳመን እውነት መኖሩ በራሱ በቂ ነው። እውነት በራሱ ተቀባይነት ከሌለው እና በክርክር ላይ የሚመሰረት ከሆነ እውነት አይደለም። በክሮክሮች ሊለወጡ ይችላል። ከእናነተ የበለጠ ማሳመኛ ሃሳብ ያለው ሰው ያጋጠማችሁ ጊዜ ሊለወጡ ይችላሉ። ትልቅ ዋጋ ያለው ነገር ክርክር ሳይሆን /ልምድ/ተሞክሮ ነው።
ተሞክሮ ክርክር አያስፈልገውም። ተሞክሮ የራሱ መሠረት ነው። ወደ ውስጥ የሚጠልቅ ነው። ውስጣችሁን ስታገኙ በውስጣችሁ በሺ የሚቆጠሩ መልካም መዓዛ ያላቸው ፅጌረዳ አበቦች የፈነዱ ይመስላል የብርሀን፣ የውበትና የደስታ እርካታን ታገኛላችሁ።
ኦሾ/Osho
#አንዳንድ_ሀሳቦች

◉ዘር ( ተዘርቶ ሚበቅለው እንደሆነ ይታወቅልኝ )
ዘር ሲበቅል ድምፅ የለውም ግን ዛፍ ሆኖ ሲወድቅ ትልቅ ድምፅ ያሰማል ብዙ ግዜ ውድቀትም ይህው ነው ጩህት አይጠፋውም ፍጥረት ግን ምን ግዜም በዝምታ ውስጥ ነው።
ይህ የዝምታ ሀይልና በዝምታ ማደግ ይባላል።
-ኮንፊሺየስ


◉ልብህ ከፈጣሪ ካልተገናኘ የቱንም ያህል ቃላት በፊቱ ብትደረድር ከንቱ ድካም ነው ። እንዲህ አይነቱ ሰውም ከቤቱ ውስጥ ቆሞ በሩን የሚያንኳኳ ሰውን ይመስላል!!
ሱፊዝም


◉በሕይወት መንገድ ላይ ስትጓዝ አዳልጦህ ብትወድቅና #ተስፋ_ብትቆርጥ ፤ የተስፋ መቁረጥህ ምክንያት የስጋህ ሳይሆን #የእምነትህ_መውደቅ መሆኑን አስተውል!
ከሱፊዝም
አንድ ቀን ሙላ ነስሩዲን አዘውትረው ቡና በሚጠጡበት ስፍራ ከአንድ ሐኪምና መምህር ጓደኞቹ ጋር ወግ ይጀምራሉ ። የወጋቸው ርእስ ደግሞ "ሞት"ነበር ።
ሀኪሙ " እኔ ከሞትኩ በኀላ በሳጥኔ ውስጥ ሆኜ ሰዎች ከደጅ የሚነጋገሩትን አንድ ጊዜ የመስማት እድል ባገኝ "ታላቅ ሐኪም ፣ቤተሰቡን አፍቃሪ ነበር" እያሉ ሲመሰክሩልኝ መስማት እሻለሁ ።" አለ ።
መምህሩም " እኔ ደግሞ ታላቅ መምህር እንደነበርኩና በትውልድ ውስጥ ታላላቅ ሰዎችን እንዳፈራሁ ፣ እንዲሁም
ትዳሬን አፍቃሪ እንደነበርኩ ሲናገሩ ብሰማ ደስ ይለኛል " አለ ።
ሙላ ነስሩዲን የሁለቱንም አድምጦ " እኔ ግን " ተመልከቱ ! ይንቀሳቀሳል እኮ ..!" በማለት ሰዎች ወደ ሳጥኑ እየጠቆሙ ሲያወሩ መስማት ምኞቴ ነው " አለ

#ተዓምራትና ጣዖታት
ከጲላጦስ
(ኀይለጊዮርጊ ማሞ)
🌘የህይወት ለውጦችን ከመቃወም ይልቅ ራስን አስተጋብሮ መራመድ ጥበብ ነው ። ሕይወት ካንተ ውጪ ሳትሆን ከእናንተ ጋር ትሁን፡፡

💫 ራስህን ስጋት አታድርግ፡፡ መልካም ሰው ማንንም አያማርርም ። ያለፍቅር ሕይወት ዋጋ የለውም ፡፡ ፍቅር የሕይወት ውሃ ነው ፣ ፍቅርን የሚያቅ ሰው የነፍስ መብራት ነው። ሁሉም ነገር እና ሁሉም ሰው ከማይታዩ ብዙ ህብረቶች ጋር የተሳሰረ ነው።

☀️ምን ዓይነት ፍቅርን መፈለግ እንዳለብህ አትጠይቅ…የምስራቃዊ ወይም ምዕራባዊ እያልክ ክፍፍል አትፍጠር፣ ያንተ ክፍፍሎች ወደ ብዙ መከፋፈል ከማምራት በቀር አንተን አይቀይሩህም፡፡ ፍቅር ስያሜ የለውም ፣ ትርጓሜ የለውም፡፡ንፁህ እና ቀላል ነው።

💫የሰዎችን ልብ አትስበር ፡፡ከአንተ ይልቅ ደካማ እንደሆኑ አርገህ ቁልቁል አትመልከት፡፡በአንደኛው የዓለም ክፍል ውስጥ ያለ ሀዘን መላውን ዓለም ሊያሰቃይ ይችላል ፣በዛው ልክ ደግሞ የአንድ ሰው ደስታ እና ፈገግታ መላውን ዓለም ፈገግ ሊያደርገው ይችላል።

☀️ አብዛኛዎቹ ግጭቶች እና ውጥረቶች በቋንቋ ምክንያት የሚከሰቱ ናቸው።ለቃላቶች በጣም ትኩረት አትስጥ ፣ በፍቅር ሀገር ውስጥ ቋንቋ የራሱ የሆነ ቦታ የለውም።
ፍቅር ውብ ዝምታ ነው ፡፡


የሱፊው ሊቅ ሸምስ ታብሪዝ (Sufi Master Shams Tabrizi )