ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች
4.59K subscribers
21 photos
2 links
የፍልስፍና እይታዎች
Download Telegram
በእውነት ጎዳና ለመሄድ መወሰን በእሳት ላይ የመራመድ ያህል ነው ። እሳቱ ይፈጃችኋል።
ከእሳቱ የሚተርፈው ትንሽ አካላችሁ የእናንተ እውነተኛ ማንነት ነው።
እሳቱ የሚበላው በሙሉ ግን ዋጋ ቢስ እና በሌሎች የተጫነባችሁ ማንነታችሁ ነው ። ማንም እውነትን ሊያቃጥልም ሆነ ሊያጠፉ አይቻለውም ።
እውነትን ለማግኘት የግድ ሸክማችሁን ማራገፍ ይኖርባችኃል።

#Osho/ኦሾ

#እውነት፥እምነትና ሕይወት
#የኦሾ እይታዎች
።።።።።።።።።
#ሀይማኖትና #ፖለቲካ ተመሳሳይ እብዶች ናቸዉ:: ሁለቱም አንተ ባልፈፀምካቸዉ ስህተቶች ተጠያቂ ያደርጉሃል።
ገና አንተ ይችን አለም ከመቀላቀልህ በፊት የአንተ የዘር ሀረግ የሚመዘዝበት ትዉልድ ስህተት ስለ ሰራ አንተም የእሱ ዘር ነህና ወንጀለኛ ነህ ይሉሃል::
*
#ቻንድራ ሞሃንጄ/Osho
ከባህልና ከህግ የታሰረው ማህበረሰብ በፍቅር ተይዞ የምኳትቱን የልጆቻቸውን ጭወት አይሰሙም፡፡ ምክንያቱም ፍቅር ከባህልና ከህግ በላይ ነው፡፡
ማህበረሰቡ ከባህልና ከህግ በታች ናቸው፡፡ ሰው ከሁሉም በላይ በፍቅር ከፍ ብሎ መኖር ስችል እራሱ ባወጣው ህግና ደንብ እራሱን አስሮ በውስጡ የበታችነትን ስሜት ተከናንቦ ያልፋል፡፡
በፍቅር ውስጥ የምትኖር ነፍስ ብቻ ባሀልና ድክምታቼውን ለመሸፈን የምጠቀሙትን ህግ በላይ ሆና ለፍቅር አምላክ ትቀርባለች፡፡
ቅናት ፍቅርን የምንንድበት መሳርያ ነው፡፡ ፍቅር መልካም ስሜት ስሆን ቅናት ክፉ ስሜት ነው፡፡
:
መልካም የፍቅር ስሜት እንደ ውሃና ግባቶች ተጠቅመ ፍቅርን
በውስጥ ስታንከባክበውና ስታለመልመው ቅናት ደግሞ ክፉ የስሜት መሳርያ ነው ያለመለምከውን የምቆራርጡበት፡፡

የአንድ ጠቢብ ነፍስ
በዮሐንስ አሰማሃኝ/ቁቤ
#ሕዝባችን የተማረውም ያልተማረው ፣ ትንሹም ትልቁም ፣ ወንዱም ሴቷም ፣ የዚያ ሀይማኖት ሰዎች ሳይቀሩ በፍረጃ ጠፍተዋል። ፖለቲካ ማዕድ ቢሆን "በየአይነቱ" ያሉትን መተው አልተለመደም። እውቀታችን ማገናዘብን አልሰጠንም። ወይም እውቀታችን ማወቅ አልሆነም። መማራችን ምሁር (አዋቂ) አላደረገንም።

(ፍልስምና ፭)
" ስግብግብ ሀሳብ በአእምሮአችሁ ውስጥ እያለፈ ከሆነ፣ እንዲያልፍ ፍቀዱለት፤ ብስጭት እያለፈ ከሆነም ይለፍ፣ ምን የሚያገባችሁ ነገር አለ? ደግሞስ ማን ሆናችሁ ነው ጣልቃ የምትገቡት? ለምንስ ነው ከአእምሯችሁ ጋር በሀይል የምትጎዳኙት? ለምን ' እኔ ስግብግብ ነኝ፣ እኔ ተበሳጭቻለሁ.....' ብላችሁ ማሰብ ትጀምራላችሁ? በአእምሯችሁ ውስጥ እያለፈ ያለው አንድ የብስጭት ሀሳብ ብቻ ነው። ሀሳቡ ይለፍ፣ እናንተ ደግሞ አስተውላችሁ ተመልከቱት! "

ምንጭ ፦ " ብርሃነ ኅሊና..
ትርጉም ፦ አና ፍራንክ
#አንድ ሰው ስታፈቅር ፥ ሰውዬውን ሙሉ በሙሉ ትቀበላለህ። ከነሙሉ እንከኑ ። ምክንያቱም ይህ እንከን የሰውዬው አካል ነውና። የምታፈቅረው ሰው ለመለወጥ አትሞክር ። እንዲህ ከሆንክ እወድሃለው አትበል ። ምክንያቱም ለመቀየር የምታደርገው ጥረት ''እኔ ማፈቅረው ግማሽ አንተን ነው'' የሚል አስተሳሰብ አለበትና። ሰው ባያፈቅርህም እራስህን መሆን አትተው። አበባ ሰው የለም ብሎ ጫካ ውስጥ ማበቡን አይተውምና። ስታፈቅርም በቃ በቀላሉ አፍቅር!!!!
*
Osho/ኦሾ
ርካሹ መንገድ!!!

ሰው ላይ እንድትፈርድ የሚያስቸኩልህ ባህሪ የሚያሳየው ሁሉንም ሰው ከአንተ በታች ለማድረግ የምታደርገውን ጥረት ነው።

አንድ ሰው ልእለ ሰብነት (ታላቅነት) ላይ ለመድረስ ታላቅ ንቃት ይጠይቃል። ከውስጣችሁ ካለው ተራራ ጫፍ ላይ መውጣትይጠበቅ ባችኋል። ይህ ደግሞ አስቸጋሪ ይመስላል።

ስለዚህ ቀላሉና ርካሹ መንገዱ ራሳችሁን የበላይ ለማድረግ ከመጣር ይልቅ ....ምንም ድካም እማያስፈልገው ሌሎችን የበታች አርጎ መቁጠር ነው።

ለዛ ነው ሰው ላይ ለመፍረድ የምትቸኩለው። ሌላው ላይ ለመፍረድ የምታደርገው ጥረት አንተ የተሻልክ እንደሆንክ ለማሳየት ያለህን ፍላጎት ያረጋግጣል። "ይህ ሰውየ እኮ ሌባ ነው፤ ይህ ሰውየ እኮ ሴት ተደፍሯል፤ ይህኮ የለየለት እብድ ነው.............."

ለሁሉም ሰው ልክ ታወጣና መጨረሻ አንተ ብቻ ንፁህ ሆነህ ትቀራለህ። ግን ሰው ላይ መፍረድ የዝቅተኛ ሰው መለያ ነው።

ኦሾ/osho
#ከእለታት አንድ ቀን አንድ የፐርሺያ ንጉሥ ሁለት ሰዎች ላይ የሞት ፍርድ ፈረደባቸው፡፡
በመጨረሻም፤ “የሞት ፍርዱ ከመፈፀሙ በፊት የፈለጋችሁትን ተናገሩ” ሲል እድል ይሰጣቸዋል፡፡
አንደኛው፤ “ምንም የምናገረው የለኝም” አለ ሁለተኛው፤
ንጉሡ ምን ያህል ፈረሳቸውን እንደሚወዱት ስለሚያውቅ፤“ንጉሥ ሆይ፤ የአንድ ዓመት ጊዜ ከሰጡኝ ፈረስዎ ወደ ሰማይ እየከነፈ እንዲሄድ ላስተምረው እችላለሁ” አላቸው፡፡ንጉሡ በሰማይ ላይ የሚከንፍ ፈረስ እየጋለቡ ሲሄዱ ታያቸው፡፡ ካሁኑ ነሸጣቸውና ይቁነጠነጡ ጀመር፡፡“ይሁን አንድ ዓመት ሰጥተንሃል፡፡ ፈረሱን አምጥተው እንዲያስረክቡህ አደርጋለሁ” አሉ፡፡
የመጀመሪያው እሥረኛ በምንም አይነት ፈረስ እንደማይበር ስለሚያውቅ ፈረስ አስተማሪውን እሥረኛ ጓደኛውን እንዲህ ሲል ጠየቀው፤“ወዳጄ፤ ፈረስ በሰማይ እንደማይበር አሳምረህ ታውቃለህ፡፡ እንዲህ ያለ የዕብድ ሀሳብ ከየት አምጥተህ ነው ቃል የገባኸው፡፡ የመሞቻችንን ጊዜ ከማራዘም በስተቀር ምን ይፈይድልሃል?”
ፈረስ አስተማሪውም፤“አይምሰልህ ወዳጄ፤ ነፃነቴን የማገኝባቸውን አራት ዕድሎች ራሴ መስጠቴ ነው”አለ
አንደኛው እሥረኛም፤
“አራቱ ዕድሎች ምን ምን ናቸው?” ሲል በመጓጓት ጠየቀው፡፡
ፈረስ አስተማሪው፤ እንዲህ ሲል ዘረዘረለት፡-
1ኛ ወይ በዚህ ዓመት ውስጥ ንጉሡ ሊሞቱ ይችላሉ
2ኛ እኔም ልሞት እችላለሁ
3ኛ ወይ ደሞ ፈረሱም ሊሞት ይችላል
4ኛ ደሞስ ማን ያውቃል እኔ ፈረሱ በሰማይ እንዲበር ላስተምረው እችል ይሆናል አለው ይባላል።
* * *
እና ምን ልልህ ፈልጌ መሰለህ በችግሮች ተሸንፈህ ቀድመህ እጅ አትስጥ ጣር ሞክር ልፋ ታገል በነገሮች ተስፋ አድርግ እንጂ ተስፋ አትጣ።ህይወት አንድ ሺህ ጊዜ ተስፋ ቆርጠህ አንድ ሺህ ጊዜ ተስፋ የምታደርግባት የግብግብ መድረክ ናት።
"ተስፋ በሌለበት እንኳ ተስፍ አድርግ ያለው ጸሐፊው በምክንያት ነው።አይህ ወዳጄ ከመሰንበት መላ አይጠፋምና።
አንድን ሰው የግል ንብረት አድርጎ እንደማሰብ መርዘኛ ነገር የለም ሰውን የግል የማድረግ መሻት የውሸት ፍቅር ነው ከእንዲህ አይነቱ ስሜት ቢያንስ ጥላቻ ይሻላል በጥላቻ ውስጥ ውሸት የለም ከዚያ በላይም ጥላቻ አንድ ቀን ፍቅር ሆኖ ሊቀየር ይችላል
የሰውን ልጅ ግን የግል የማድረግ ፍላጎት ፈጽሞ ወደ ፍቅር ሊቀየር አይችልም ፍቅር ማለት በምትወደው ሰው ነፍስ ውስጥ ራስህን መግደል ነው ፍቅር ማለት ሞት ነው
ኦሾ/Osho
"...የሰው ልጅ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ መጠኑና ስፋቱ ቢለያይም ፣ ራሱ በሠራው አሊያም ሌሎች ባጠሩለት እስር ቤት ይኖራል፡፡ እንደ ራሱ አሳብና አመለካከት ግን ትልቅ እስር ቤት የሚኾንበት አንዳች ነገር የለም፡፡
ለካስ እስር ቤት ቦታ ሳይኾን አስተሳሰብ ነው፡፡ በዚህች ምድር እጅግ ብዙ ሰው በአእምሮው እስር ቤት ውስጥ በአሉታዊ አስተሳሰብ ታስሮ፣ በከንቱና እንቶ ፈንቶ ፍርሀት ተይዞ ማንም እንዳይረዳው ኾኖ የእስር ቤት ቊልፉን ራሱ ደብቆ ይኖራል፡፡"
በዚህ አጋጣሚ
"ሜሎሪና" መጽሐፍን ተጋበዙልኝ
#ለዕለተ ቅዳሜያችን
ብዙ ጊዜ ትወድቃላችሁ። ይህ ለክፉ አይሰጥም። እንደገና ተነስታችሁ ቁሙና ዳግም ያለመውደቅን ተማሩ። የበለጠ ንቁ። ስህተት መስራታችሁ አይቀርም ፣ ግን አንድ ስሄተት ደግማችሁ አትስሩ። ይህን የምላችሁ ሰው ጥበብን የሚያገኘው በዚህ መልኩ ነው።
አጭር ሆናችሁ አትቅሩ። የምትችሉት ርቀት ላይ ለመድረስ ሞክሩ። ሊያኮራ የሚችለውን ብቃት ይዞ ያልተፈጠረ ማንም ሰው የለም። አንድን አዲስና ውብ ነገር የመውለድ፣ህላዊን የበለጠ የማበልፀግ ብቃትን ሳይዝ የተፈጠረ ሰው የለም።
#ኦሾ/Osho
#ራስን የመኾን ድፍረት
#ትርጉም፦ዘላለም ንጉሴ
ሀገር ከራስ ለራስ የሚገነባ እምነት ነው።
*
"የስኬታማ ሰውነት ትልቅ መለኪያ የሚያካብተው ሀብት ወይም የሚኖረው ዝናና እውቀት አይደለም ትልቅ ሚዛን በሌሎች ላይ ልዩነት መፍጠር መቻል ነው።"
ኢትዮጵያዊ ዘር....
ከሀሳብ የሚወለድ የዘር ብይን ያስፈልጋል። ልማድና ጥንተ-ተረት አያሳድግም። የዛሬን ፈተና አይመልስም። በየአጥቢያ የምናየውን ጎሰኝነት አያቆምም። ኢትዮጵያዊ ዘር የተሰኝ የባህል ዝርያ ማዳበር አለብን። ቨከምርጥ ሀሳብ የሚፈልቅ የባህል ዝርያ የመስራት ራዕይ ያስፈልገናል።
****//*********
የዘር ካርድ

ቡርሐን አዲስ/መሀመድ አሊ/
የኒቼ እና የኦሾ ቅራኔ ምን ነበር...?

፨፨፨

በፍልስፍናው ዓለም በሃይማኖት እይታ ላይ ጥሩ ነገር ያላበረከቱ ወይም ክፉኛ ሃይማኖትን እና አምላክን ተዳፍረው አልፈዋል ከሚባሉት ፈላስፋዎች መሃል

#ፍሬድሪክ ኒቼ እና #ራጅናሽ ኦሾ ግንባር ቀደሞቹ ናቸው ።

ፍሬድሪክ ኒቼ ምን ነበር ያለው...?

" አምላክ ሞቷል(God is dead) ዛሬ እናንተ አምላክ የምትሉት በሰዎች አስተሳሰብ ውስጥ ተፈጥሮ አድጎና ጎልምሶ እንዲሁም አርጅቶ ያለፈ አስተሳሰብ ነው። "

በነገራችን ላይ ፍሬድሪክ ኒቼ የሱ ቀዳሚ የነበረው ፈላስፋ #አርተር ሾፐንሀወር አድናቂ ነበር እንዲሁም በፍልስፍና እይታዎቹ ላይም የሱ ተጽእኖ አለበት ይባላል...አርተር ሾፐን ሀወርም በፈጣሪ ህልውና የማያምን እንዲሁም ለስነ መለኮት መምህራን ከፍተኛ ጥላቻና ንቀት የነበረው ፈላስፋ ነበር ።

ኒቼ ይህንን ሃሳብ ማለትም "God is Dead" የሚለውን እይታውን "Joyful wisdom" በሚለው መጽሐፉ ላይ ለሕትመት ባበቃ ሰአት ከብዙ የሃይማኖት ተከታዮች ተቃውሞ ደርሶበት ነበር...ይህንን ንግግሩንም አንስቶ ራጅናሽ ኦሾ እኔም በጊዜው ብኖር እቃወመው ነበር ይለናል።

ይህንን እይታም ያስቀምጣል...
<< ፍሬድሪክ ኒቼ አምላክ ሞቷል ሲል ብዙ እምነቶች ተቃውሞ አንስተውበት ነበር። እኔም እቃወመዋለሁ ምክንያቱም እኔ ደግሞ የምለው እንኳን ሊሞት መጀመርያም #አልነበረም ነውና >> ይለናል ይህንን ንግግሩን ብርሃነ ኅሊና የሚለው መጽሐፍ ላይ እናገኘዋለን ።

ባብዛኛው ሰዎች ራጅናሽ ኦሾን የሳይኮሎጂስቱን ሲግመን ፍሩድ እና ፍሬድሪክ ኒቼን ፍልስፍናዎች ያስተጋባ ብለው የሃሰት ካባ ሊያለብሱት ቢሞክሩም እሱ ግን ከነሱም የተለየ አስተሳሰብ እንደነበረ ካሳየባቸው ንግግሮቹ አንዱ ይህ ነበር ።

#አሁን ታድያ ማን ይፍረድ እንደ ኒቼ የፈጣሪን ህልውና የተገዳደረ ፈላስፋ የለም የሚባለው ሚዛን ይደፋ ይሆን የኦሾን አይን ያወጣ #ክህደት በሉት #እውነት አፍጥጠን ስናይ...?

መልሱን ለህሊናችሁ...!!

፨ የዚህ ጽሑፍ አላማ የፈጣሪን መኖር መካድ ሳይሆን በሁለቱ ፈላስፎች መሃከል በሀለዎተ ፈጣሪ ዙርያ ያለውን እይታ ማሳወቅ ነው። በሌላ እንዳይተረጎም...

ግብዓት ምንጮች ፦ "ጥበብ ከጲላጦስ" እንዲሁም "ብርኀነ ኅሊና" መጽሐፍት
Via:- ራስን ፍለጋ
"እንደ #ንስር

የሆነ ቀን በናሽናል ጂኦግራፊ ንስር መርዛማውን ኮብራ እባብ ሲያድን ተመልክቼ ግራ ተጋባሁ፡፡ እባቡ ግዙፍ እና አደገኛ ሆኖ ሳለ እንዴት በንስሩ ሊሸነፍ ቻለ? አልኩኝ፡፡

መልሱ ግልጽ ነው፡፡ ንስሩ መጫወቻ ሜዳውን ያውቃል!!

ምናልባት ንስሩ እና እባቡ መሬት ላይ ቢገናኙ ኖሮ እባቡ አሸናፊ ንስሩ ደግሞ ተሸናፊ ይሆኑ ነበር፡፡
ንስሩ እባቡን ከላይ ወደታች ተመለከተ፡፡ እባቡን ሲገጥመውም ከመሬት ወደላይ ወሰደው፡፡ የንስሩ መርህ መጫወቻ ሜዳን መለየት ነው!!

እባብ መሬት መጫወቻ ሜዳው(አለሙ) ነው፡፡ መሬት ላይ እባብ ሃይለኛና አሸናፊ ነው፡፡ የንስሩ መጫወቻ ሜዳ (አለም) ደግሞ ከፍታ ነው፡፡ የከፍታን አለም ከማንም በላይ ያውቀዋል፡፡ በሜዳው ድል ማድረግንም ይችልበታል!!

ንስር ይህን ጠንቅቆ ያውቃልና እባቡን ከራሱ አለም አንፃር ተመለከተው፡፡ ቀጥሎም ተጋጣሚውን ከአለሙ (መሬት) ነጥሎ ወደራሱ አለም ወሰደው፡፡ በገዛ ሜዳውም ድልን ተቀናጀ!!

ወዳጄ ሆይ በየትኛውም መስክ ድልን ከፈለክ እንደ ንስር ሁን!!

መጫወቻ ሜዳህን ለይ፡፡ አለምህን በትክክል እውቅ፡፡ ካንተ አለም አንፃር መመልከትን ተለማመድ!!

ከምንም በላይ በምንም ምክንያት በተጋጣሚክ መጫወቻ ሜዳ ላይ አትፋለም፡፡ ያለህን አቅም ሁሉ ተጠቅመህ ተጋጣሚህን ወደ ራስህ መጫወቻ ሜዳ ውስደው!!!!!!!!!
በመጀመሪያ እራስ ወዳድነት ተፈጥሮችሁ መሆኑን ተቀበሉ። ተፈጥሮችሁ መሆኑን ከተቀበላችሁ ደግሞ ይህ እራስ ወዳድነታችሁ ውስጣችሁ የሆነ እያገለገለ ያለው ነገር አለ ማለት ነው። ያለዚያማ በዚያ አይኖርም ነበር ።
እራስ ወዳድ ስለሆናችሁ ነው መኖር ያበዛችሁት እንዲሁም የገዛ እራሳችሁን እምትከባከቡት። ያ ባይሆን ኖሮ ፣ እራስ ወዳድነት ተፈጥሮ ተፈጥሮዓዊ ባይሆንማ ኖሮ የሰው ልጅ ከዘመናት በፊት ነበር ይጠፋ የነበረው።
በሚኒሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ተርበው እኛ እንበላለን ፣ በአለማችን ላይ ብዙዎች ተጠምተው እኛ እንጠጣለን፣ እራስ ወዳድነት ይሄ ነው። ታዲያ ሌሎች እራስ ወዳድ አትሁኑ እያሉ በመጀመሪያ እራስ ወዳድነት ተፈጥሮችሁ መሆኑን ተቀበሉ። ተፈጥሮችሁ መሆኑን ከተቀበላችሁ ደግሞ ይህ እራስ ወዳድነታችሁ ውስጣችሁ የሆነ እያገለገለ ያለው ነገር አለ ማለት ነው። ያለዚያማ በዚያ አይኖርም ነበር ።
እራስ ወዳድ ስለሆናችሁ ነው መኖር ያበዛችሁት እንዲሁም የገዛ እራሳችሁን እምትከባከቡት። ያ ባይሆን ኖሮ ፣ እራስ ወዳድነት ተፈጥሮ ተፈጥሮዓዊ ባይሆንማ ኖሮ የሰው ልጅ ከዘመናት በፊት ነበር ይጠፋ የነበረው።
በሚኒሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ተርበው እኛ እንበላለን ፣ በአለማችን ላይ ብዙዎች ተጠምተው እኛ እንጠጣለን፣ እራስ ወዳድነት ይሄ ነው። ታዲያ ሌሎች እራስ ወዳድ አትሁኑ እያሉ ሲያስተምሯችሁ ከተፈጥሮአችሁ ውጭ ሁኑ እያሏችሁ መሆኑን አትዘንጉ።

እኔ ግን ተፈጥሮአችሁን እንድትሆኑ አስተምሯችኋለሁ። ማንም ተፈጥሮ አችሁን እንድትሆኑ አይነግራችሁም። ምክንያቱም ደግሞ እነሱም እራስ ወዳዶች ስለሆኑ ነው።
ከሞት በኋላ የዘላለም ህይወት ፣ የተትረፈረፈ ህይወት ስለሚበዛላችሁ ይህች 70 እና 80 አመት የምትሆን ምድራዊ ህይወችታሁን ለውጡ እያሉ ይሰብኳች ኋል። ይሄ ግን ያወድማችኋል እንጅ አያበለጽጋችሁም ።
ኦሾ/Osho
"ህይወት፣ በምድር ላይ ከተቀደደ መንገድ ይልቅ ወዳሰኘህ አቅጣጫ የምትበርበትን ሰማይ ትመስላለች። የምድር ላይ ሀያላን በቀደዱልህ መንገድ ላይ በካርታቸው እየተመራህ መሄድ መንገድ ተጓዥ አያሰኝም፤ ኑሮህም ኑሮ አይሆንም። ገና ወዳልተዳሰሰው ድንግል ሰማይ ለመንጎድ የምታስችልህን ክንፍ አነቃቃ። የራስህ የሆነም ካርታ ከአሻራዎችህ ላይ ቅዳ።"
ኦሾ /Osho
"ራስን መሆን..
አለም ከገደል ማሚቶ የተሻለ አይደለም!!

ፍቅር በራችሁን አንኳኩቶ ያውቃል? በጭራሽ! ምክንያቱም ገና ፍቅር መስጠት አልቻላችሁም። ማስታወስ ያለባችሁ የሰጠነው ሁሉ ወደ እኛው ተመልሶ እንደሚመጣ ነው። ይህም ከህይወት ህጎች አንዱ ነው።

መላው ዓለም ከገደል ማሚቶ የተሻለ አይደለም። ጥላቻ እንሰጣለን፣ ጥላቻም ወደኛው ተመልሶ ይመጣል። ሌሎችን እንሳደባለን ከዛም ስድብ ወደኛ ተመልሶ ይመጣል። እሾህ ስንሰጥ እሾህ ወደኛው ተመልሶ ይመጣል፡፡ የምንሰጠው ሁሉ በተለያዩ መንገዶች ወደኛ ተመልሶ ይመጣል። ፍቅርን ካካፈልንም እንደዚሁ በተለያዪ መንገዶች ተመልሶ ወደኛው ይመጣል። ስፍር ቁጥር በሌላቸው መንገዶች ፍቅር ወደ እኛ ተመልሶ ካልመጣ ፍቅር እንዳልሰጠን ማወቅ አለብን፡፡

ፍቅር እምትሰጠው እንጂ እምትቀበለው አይደለም።

ኦሾ/osho
በእዚህ ዓለም የህይወታችን መስመር የሚወሰነው ዘውትር ስለህይወት በምናንፀባርቀው አመለካከት ነው፤ ይህ አመለካከታችን ድርጊታችንን ይወልዳል ፤ ከአመለካከታችን የሚወለደው ድርጊት ደግሞ ወይ ያጠፋናል አላያም ያድነናል። በአጠቃላይ የወደፊት እጣፈንታችን ቅርጽ የሚበጀው ለህይወት በየቀኑ በምንሰጠው ትርጓሜ ነው። ስለዚህ የአንድ ሰው ወደ ነፍስ ወይም እውነተኛ ማንነቱ የሚያደርገውን የጉዞ አቅጣጫው የሚወስነው ለህይወት ባለው አመለካከት ይሆናል ማለት ነው። ነገር ግን የሰው ልጅ ይህ አመለካከቱ የእጣፈንታውን ተፈጥሮ እንደሚወሰን አውቆ ቢሆን ኖሮ እስከ ዛሬ ሲራመድ የነበረበትን የተበላሸ/ህይወትን በአስቀያሚነት እና በፋይዳቢስነት የሚስለውን/መንገድ እርግፍ አድርጎ በተወ ነበር።
ኦሾ/Osho
🎎
"ዓለም በሙሉ በብርሃን ልትጥለቀለቅ ትችላለች፣ ውስጥህ ግን አሁንም በጨለማ እየኖረ ነው። ከውልደትህ በኃላ የተጨመረልህ ነገር ሁሉ እውነተኛ ማንነትህ ያለመሆኑን ቀስ በቀስ የሚያሳይህ ጭላንጭል ብርሃን በውስጥህ ሳይኖር በብርሃን የተሞላ ዓለም ምን ይጠቅምሀል?"
' ' '
OSHO ኦሾ

#ነፃነት/
ራስን የመሆን ድፍረት
#ምን ይዞ እንደሚመጣ ለማይታወቀው መጪው ጊዜ መፈንጠዝና በምኞት ፈረስ መጋለብ ካላቆማችሁና፣ ትናንትናንና ነገን ትታችሁ ዛሬን መኖር ካልጀመራችሁ ነፃ አትወጡም። ነፃነት አሁን እዚህ ናት።
ያለህበት ጊዜ ብቻ ናት እውነት ህልውና ያላት። መጪው ጊዜ ምኞትህ፣ ያለፈውም ጊዜ ትዝታህ ነው። ህልውና የላቸውም።
የአሁኑን ጊዜ በንቃት ማሳለፍ ንቃተ ሂሊናህና ካለፈውና ከመጪው ጊዜ ሰብስበህ በአሁኑ ጊዜ ላይ ማትኮር ማለት የነፃነትን ጣዕም ማወቅ ነው።
ኦሾ/Osho