ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች
4.59K subscribers
21 photos
2 links
የፍልስፍና እይታዎች
Download Telegram
"የታላቅ ሰው ታላቅነት የሚገለፀው በተግባሩ እንጂ በንግግሩ አይደለም"
የተግባር መሠረቱ ደግሞ ጽኑ ፍላጎት ነው።"

*
#ኮንፊሺየስ
#እናትነት ፍቅር ነው -ንፁህ ፍቅር ፣ ያልተከለሰ ፍቅር።
እናት መሆን ማለት ንፁህ ፍቅር መስጠት መቻል ፣ ሰውን በፍቅር ማፍቀር ፣ ሰውን ሲያደግ ለማየት ባለ ጉጉት ሳቢያ መርዳት ማለት ነው።
# እውነተኛ ሃኪም እናት ናት!!!
ኦሾ/Osho
”ምክንያት ለሰው ልጅ ወሳኝ ባይሆን ኖሮ አእምሮ ባልተፈጠረ ነበር”

/ዘርያቆብ/
ያለ ቅድመ ሁኔታ የሚያፈቅሩ አፍቃሪ ይሁኑ ፍቅር ወሰን ወደሌለው መጨረሻ ወደሌለው ዓለም የሚያስገባ በር ነው ።
ፍቅር መጀመሪያ እንጂ መጨረሻ የለውም ይጀምራል እንጂ አያበቃም ።
ኦሾ/osho
"ህይወትን ወደ ቴክኖሎጂ አታሳንሷት ወደ ቴክኖሎጂ ያነሰች ህይወት ሁሉንም የደስታ ጣዕም ታጣለችና።"
ነፃ ስሜቶች
#ኦሾ/Osho
#ትርጉም በዮሐንስ አዳም
ፍቅር በኦሾ እይታ
<< ብዙ ሰዎች በፍቅርና በወዳጅነት መካከል ያለው ልዩነት ጠፍቶአቸው በጎዳናው ላይ ሲዳክሩ ይስተዋላል ። አንድ መስለው ይታዩዋቸዋል ፤ ነገር ግን አንድ አይደሉም ። ይመሳሰሉባቸዋል ነገር ግን በእውነታው አይመሳሰሉም ። እንዳውም ከወዳጅነት ይልቅ ከፍቅር ጋር የሚመሳሰለው ጥላቻ ነው ። ጥላቻ ተቃራኒውን ነው - ወዳጅነት የጥላቻን እውነታ ደብቆ የፍቅርን መልክ ይይዛል ። ነገር ግን ፍቅርን እየገደለ ነው ። አንድን ሰው የግል ንብረት አድርጎ እንደማሰብ (Possessiveness) መርዘኛ ነገር የለም ። ይኽን በሚገባ ከተረዳችሁ ወደ ቀጣዩ ጉዳይ እንዝለቅ... >> ይላል ።
💗
<< ለብዙዎች እንዲህ ሆኗልና ለእናንተም እንዳይሆንባችሁ ልንገራችሁ፤ ምክንያቱም በፍቅርና በግንኙነት መካከል ያለው ልዩነት ግራ አጋብቷችኋል ። በተለይም ከውጭ ሆነው ሲመለከቱ የኖሩ ሰዎች ሰለባው ሲሆኑ ኖረዋል ወዳጅነትንና የግል ማድረግን እንደ ፍቅር ወስደውት አይቻለሁ ። በዚህ መንገድም እውነተኛውን ነገር አጥተውታል ።
💗
ሰውን የግል ለማድረግ መሻት የውሸት ፍቅር ነው ። ከእንዲህ አይነቱ ስሜት ቢያንስ ጥላቻ ይሻላል ። በጥላቻ ውስጥ ውሸት የለም ። ከዚያ በላይ ደግሞ ጥላቻ አንድ ቀን ፍቅር ሆኖ ሊቀየር ይችላል የሰውን ልጅ የግል የማድረግ ፍላጎት ግን ፈጽሞ ወደ ፍቅር ሊቀየር አይችልም ።
💕
<< ፍቅር ማለት በምትወደው ሰው ነፍስ ውስጥ ራስህን መግደል ነው ። ፍቅር ማለት ሞት ነው ፤ የሚቻልህን ያህል ጥልቅ በሆነ ሞት ውስጥ ትገባለህ ፤ የምትሞተውም በምትወዳት ሴት ነፍስ ውስጥ ነው ። ዕለት ዕለት ወደ ጥልቅ የነፍሷም ቦታ ትወሰዳለህ ፤ ፍቅር ወደምታፈቅራት ሴት የነፍስ ቦታ የምታደርገው ዘላለማዊ ጉዞ ነው ። ጉዞውም ማቆሚያ የለውም ። አንዲትን ሴት ስታፈቅራት በአንተ ሕይወት ውስጥ ከአንተ በላይ ዋጋ አላት ። ፍቅር ማለት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መማረክ ማለት ነው ። ምክንያቱም አንዳች ቅድሙ ሁኔታ የምታስቀምጥለት ከሆነ ከምታፈቅረው ሰው በላይ ለራስህ ዋጋ ሰጥተሃል ማለት ነው ። ራስህን ዋነኛው ጉዳይ አድርገህ በፍቅር ውስጥ ስትመለከት ተፈቃሪዋ መጠቀሚያህ ሆነች ፤ የፍላጎትህ ማርኪያ አደረግሃት፤ በሌሎች ዘንድ መደነቂያህ ሆነች...መነሻውም መድረሻውም አንተ ሆነሃል ።
💕

ፍቅር ደግሞ መነሻው አንተ መድረሻው ግን ተፈቃሪው ይሁን ይልሃል ። በተፈቃሪው ውስጥ ትሟላለህ ፣ ትጠፋለህ ። የመሞት ሂደትና ክስተት ነው ። ለዚህም ነው ሰዎች ፍቅር የሚፈሩት ። ስለፍቅር ልታወራ ፣ ልትዘፍን ፣ ትችላለህ ነገር ግን የልብህ ጥልቅ ስሜት ቢመረመር ፍቅርን በመፍራት የተሞላ ነው ....
ኦሾ/Osho
ጥበብ 6
በተፈጥሮ የበላይ እና የበታች የሚባል ነገር የለም ። ትንሿ ሳር ሰማይ ካለው ትልቅ ኮከብ ጋር እኩል ዎጋ አላት ። በተፈጥሮ የስልጣን ተዋረድ የለም ፤ ማንም የበታች ማንም የበላይ አይደለም ፤ ሁሉም ራሱን ነው ። አንዳንድ ዛፎች ረጃጅም፣ሌሎች ደግሞ አጫጭሮች ናቸው ። ይህ ማለት ግን ረጅሙ ዛፍ ታላቅ፣የበላይ ነው ፣ እንደዚሁም ትንሹ ዛፍ የበታች ነው ማለት አይደለም።
በተፈጥሮ የሰዎች የስልጣን ተዋረድ የሚባል ነገር የለም።
➣Osho/ኦሾ
ኃይማኖትን መመርመር
#የሚያጠነክረን የምንበላው ምግብ ሁሉ አይደለም።
በልተነው የሚዋሃደን ምግብ እንጂ!
➦ሀብታም የሚያደርገን የምናገኘው ገንዘብ ሁሉ አይደለም፡፡የምንቆጥበውና የምንሰራበት ገንዘብ እንጂ!
➦አዋቂ የሚያደርገን የምናነበው ሁሉ አይደለም፡፡አንብበን የምንገነዘበውና የምናስታውሰው እንጂ!

#ክርስቲያኖች (ሙሲሊሞች)የሚያደርገን በንግግር የምንገልጸው አይደለም በሥራ የምናሳየው በጎ ምግባር እንጂ!!!!!!!!

/ፍራንሲስ ቤከን/
#መልአከ ሞት!
****
#የሞት መልአክ የአብረሃምን ቤት አንክዋክቶ ነፍሱን ሊወስዳት እንደመጣ ይነግረዋል።አብረሃምም በቅድምያ ከእግዚአብሄር ጋር እንዲነጋገር እድሉን ጠይቆ ወደ ቤቱ ውስጥ ይገባና እግዚአብሄርን በፀሎት ጠርቶ ይጠይቀዋል፣-"ለመሆኑ ጌታ ሆይ! የወዳጁን ነፍስ የሚወስድ ወዳጅ አይተህ ታውቃለህን?"

እግዚአብሄርም መለሰለት "አንተስ ከወዳጁ ለመገናኘት የማይናፍቅ ወዳጅ አይተህ ታውቃለህን?"

አብረሃም መልስ አጥሮት በሩን ከፍቶ ሲወጣ መልአከ ሞት ቆሞ ሲጠብቀው ተመለከተ።
* ** *
ጥበብ ከጲላጦስ
"ህይወታችሁን አክብሩ ። ህይወታችሁን በማክበርም የሌሎችን ህይወት ማክበር ትጀምራላችሁ።"
:
እንድታስታውሱ የምመክራቹሁ በህይወት እንድትኖሩ እና ህይወት ምን እንደሆነች ለማወቅ እንድትሞክሩ ነው። በሕይወት መኖራችሁ በጣም ውድ ነገር መሆኑ አስታውሱ። ህይወትን አክብሩ ። ከህይወት የበለጠ የተቀደሰ ፣ ከሕይወት የበለጠ መለኰታዊ የሆነ ነገር የለም።
#ህይወታችሁን አክብሩ። ህይወታችሁን በማክበርም የሌሎችን ህይወት ማክበር ትጀምራላችሁ። ዋናው ምክንያት ህይወትን ካከበራችሁ #አበባን እንኳን መቅጠፍ ይከብዳችኃል። አበባው ያስደስታችኃል ፣
ትወዱታላችሁ ፣ ትዳስሱታላችሁ ፣ ታሸቱታላችሁ ነገር ግን አበባውን መቅጠፍ ልክ እንደ እናንተ ህይወት ያለውን አካል ማጥፋት እና ማሰቃየት ነው።
#Osho/ኦሾ
#ኃይማኖትን መመርመር
በእውነት ጎዳና ለመሄድ መወሰን በእሳት ላይ የመራመድ ያህል ነው ። እሳቱ ይፈጃችኋል።
ከእሳቱ የሚተርፈው ትንሽ አካላችሁ የእናንተ እውነተኛ ማንነት ነው።
እሳቱ የሚበላው በሙሉ ግን ዋጋ ቢስ እና በሌሎች የተጫነባችሁ ማንነታችሁ ነው ። ማንም እውነትን ሊያቃጥልም ሆነ ሊያጠፉ አይቻለውም ።
እውነትን ለማግኘት የግድ ሸክማችሁን ማራገፍ ይኖርባችኃል።

#Osho/ኦሾ

#እውነት፥እምነትና ሕይወት
#የኦሾ እይታዎች
።።።።።።።።።
#ሀይማኖትና #ፖለቲካ ተመሳሳይ እብዶች ናቸዉ:: ሁለቱም አንተ ባልፈፀምካቸዉ ስህተቶች ተጠያቂ ያደርጉሃል።
ገና አንተ ይችን አለም ከመቀላቀልህ በፊት የአንተ የዘር ሀረግ የሚመዘዝበት ትዉልድ ስህተት ስለ ሰራ አንተም የእሱ ዘር ነህና ወንጀለኛ ነህ ይሉሃል::
*
#ቻንድራ ሞሃንጄ/Osho
ከባህልና ከህግ የታሰረው ማህበረሰብ በፍቅር ተይዞ የምኳትቱን የልጆቻቸውን ጭወት አይሰሙም፡፡ ምክንያቱም ፍቅር ከባህልና ከህግ በላይ ነው፡፡
ማህበረሰቡ ከባህልና ከህግ በታች ናቸው፡፡ ሰው ከሁሉም በላይ በፍቅር ከፍ ብሎ መኖር ስችል እራሱ ባወጣው ህግና ደንብ እራሱን አስሮ በውስጡ የበታችነትን ስሜት ተከናንቦ ያልፋል፡፡
በፍቅር ውስጥ የምትኖር ነፍስ ብቻ ባሀልና ድክምታቼውን ለመሸፈን የምጠቀሙትን ህግ በላይ ሆና ለፍቅር አምላክ ትቀርባለች፡፡
ቅናት ፍቅርን የምንንድበት መሳርያ ነው፡፡ ፍቅር መልካም ስሜት ስሆን ቅናት ክፉ ስሜት ነው፡፡
:
መልካም የፍቅር ስሜት እንደ ውሃና ግባቶች ተጠቅመ ፍቅርን
በውስጥ ስታንከባክበውና ስታለመልመው ቅናት ደግሞ ክፉ የስሜት መሳርያ ነው ያለመለምከውን የምቆራርጡበት፡፡

የአንድ ጠቢብ ነፍስ
በዮሐንስ አሰማሃኝ/ቁቤ
#ሕዝባችን የተማረውም ያልተማረው ፣ ትንሹም ትልቁም ፣ ወንዱም ሴቷም ፣ የዚያ ሀይማኖት ሰዎች ሳይቀሩ በፍረጃ ጠፍተዋል። ፖለቲካ ማዕድ ቢሆን "በየአይነቱ" ያሉትን መተው አልተለመደም። እውቀታችን ማገናዘብን አልሰጠንም። ወይም እውቀታችን ማወቅ አልሆነም። መማራችን ምሁር (አዋቂ) አላደረገንም።

(ፍልስምና ፭)
" ስግብግብ ሀሳብ በአእምሮአችሁ ውስጥ እያለፈ ከሆነ፣ እንዲያልፍ ፍቀዱለት፤ ብስጭት እያለፈ ከሆነም ይለፍ፣ ምን የሚያገባችሁ ነገር አለ? ደግሞስ ማን ሆናችሁ ነው ጣልቃ የምትገቡት? ለምንስ ነው ከአእምሯችሁ ጋር በሀይል የምትጎዳኙት? ለምን ' እኔ ስግብግብ ነኝ፣ እኔ ተበሳጭቻለሁ.....' ብላችሁ ማሰብ ትጀምራላችሁ? በአእምሯችሁ ውስጥ እያለፈ ያለው አንድ የብስጭት ሀሳብ ብቻ ነው። ሀሳቡ ይለፍ፣ እናንተ ደግሞ አስተውላችሁ ተመልከቱት! "

ምንጭ ፦ " ብርሃነ ኅሊና..
ትርጉም ፦ አና ፍራንክ
#አንድ ሰው ስታፈቅር ፥ ሰውዬውን ሙሉ በሙሉ ትቀበላለህ። ከነሙሉ እንከኑ ። ምክንያቱም ይህ እንከን የሰውዬው አካል ነውና። የምታፈቅረው ሰው ለመለወጥ አትሞክር ። እንዲህ ከሆንክ እወድሃለው አትበል ። ምክንያቱም ለመቀየር የምታደርገው ጥረት ''እኔ ማፈቅረው ግማሽ አንተን ነው'' የሚል አስተሳሰብ አለበትና። ሰው ባያፈቅርህም እራስህን መሆን አትተው። አበባ ሰው የለም ብሎ ጫካ ውስጥ ማበቡን አይተውምና። ስታፈቅርም በቃ በቀላሉ አፍቅር!!!!
*
Osho/ኦሾ
ርካሹ መንገድ!!!

ሰው ላይ እንድትፈርድ የሚያስቸኩልህ ባህሪ የሚያሳየው ሁሉንም ሰው ከአንተ በታች ለማድረግ የምታደርገውን ጥረት ነው።

አንድ ሰው ልእለ ሰብነት (ታላቅነት) ላይ ለመድረስ ታላቅ ንቃት ይጠይቃል። ከውስጣችሁ ካለው ተራራ ጫፍ ላይ መውጣትይጠበቅ ባችኋል። ይህ ደግሞ አስቸጋሪ ይመስላል።

ስለዚህ ቀላሉና ርካሹ መንገዱ ራሳችሁን የበላይ ለማድረግ ከመጣር ይልቅ ....ምንም ድካም እማያስፈልገው ሌሎችን የበታች አርጎ መቁጠር ነው።

ለዛ ነው ሰው ላይ ለመፍረድ የምትቸኩለው። ሌላው ላይ ለመፍረድ የምታደርገው ጥረት አንተ የተሻልክ እንደሆንክ ለማሳየት ያለህን ፍላጎት ያረጋግጣል። "ይህ ሰውየ እኮ ሌባ ነው፤ ይህ ሰውየ እኮ ሴት ተደፍሯል፤ ይህኮ የለየለት እብድ ነው.............."

ለሁሉም ሰው ልክ ታወጣና መጨረሻ አንተ ብቻ ንፁህ ሆነህ ትቀራለህ። ግን ሰው ላይ መፍረድ የዝቅተኛ ሰው መለያ ነው።

ኦሾ/osho
#ከእለታት አንድ ቀን አንድ የፐርሺያ ንጉሥ ሁለት ሰዎች ላይ የሞት ፍርድ ፈረደባቸው፡፡
በመጨረሻም፤ “የሞት ፍርዱ ከመፈፀሙ በፊት የፈለጋችሁትን ተናገሩ” ሲል እድል ይሰጣቸዋል፡፡
አንደኛው፤ “ምንም የምናገረው የለኝም” አለ ሁለተኛው፤
ንጉሡ ምን ያህል ፈረሳቸውን እንደሚወዱት ስለሚያውቅ፤“ንጉሥ ሆይ፤ የአንድ ዓመት ጊዜ ከሰጡኝ ፈረስዎ ወደ ሰማይ እየከነፈ እንዲሄድ ላስተምረው እችላለሁ” አላቸው፡፡ንጉሡ በሰማይ ላይ የሚከንፍ ፈረስ እየጋለቡ ሲሄዱ ታያቸው፡፡ ካሁኑ ነሸጣቸውና ይቁነጠነጡ ጀመር፡፡“ይሁን አንድ ዓመት ሰጥተንሃል፡፡ ፈረሱን አምጥተው እንዲያስረክቡህ አደርጋለሁ” አሉ፡፡
የመጀመሪያው እሥረኛ በምንም አይነት ፈረስ እንደማይበር ስለሚያውቅ ፈረስ አስተማሪውን እሥረኛ ጓደኛውን እንዲህ ሲል ጠየቀው፤“ወዳጄ፤ ፈረስ በሰማይ እንደማይበር አሳምረህ ታውቃለህ፡፡ እንዲህ ያለ የዕብድ ሀሳብ ከየት አምጥተህ ነው ቃል የገባኸው፡፡ የመሞቻችንን ጊዜ ከማራዘም በስተቀር ምን ይፈይድልሃል?”
ፈረስ አስተማሪውም፤“አይምሰልህ ወዳጄ፤ ነፃነቴን የማገኝባቸውን አራት ዕድሎች ራሴ መስጠቴ ነው”አለ
አንደኛው እሥረኛም፤
“አራቱ ዕድሎች ምን ምን ናቸው?” ሲል በመጓጓት ጠየቀው፡፡
ፈረስ አስተማሪው፤ እንዲህ ሲል ዘረዘረለት፡-
1ኛ ወይ በዚህ ዓመት ውስጥ ንጉሡ ሊሞቱ ይችላሉ
2ኛ እኔም ልሞት እችላለሁ
3ኛ ወይ ደሞ ፈረሱም ሊሞት ይችላል
4ኛ ደሞስ ማን ያውቃል እኔ ፈረሱ በሰማይ እንዲበር ላስተምረው እችል ይሆናል አለው ይባላል።
* * *
እና ምን ልልህ ፈልጌ መሰለህ በችግሮች ተሸንፈህ ቀድመህ እጅ አትስጥ ጣር ሞክር ልፋ ታገል በነገሮች ተስፋ አድርግ እንጂ ተስፋ አትጣ።ህይወት አንድ ሺህ ጊዜ ተስፋ ቆርጠህ አንድ ሺህ ጊዜ ተስፋ የምታደርግባት የግብግብ መድረክ ናት።
"ተስፋ በሌለበት እንኳ ተስፍ አድርግ ያለው ጸሐፊው በምክንያት ነው።አይህ ወዳጄ ከመሰንበት መላ አይጠፋምና።
አንድን ሰው የግል ንብረት አድርጎ እንደማሰብ መርዘኛ ነገር የለም ሰውን የግል የማድረግ መሻት የውሸት ፍቅር ነው ከእንዲህ አይነቱ ስሜት ቢያንስ ጥላቻ ይሻላል በጥላቻ ውስጥ ውሸት የለም ከዚያ በላይም ጥላቻ አንድ ቀን ፍቅር ሆኖ ሊቀየር ይችላል
የሰውን ልጅ ግን የግል የማድረግ ፍላጎት ፈጽሞ ወደ ፍቅር ሊቀየር አይችልም ፍቅር ማለት በምትወደው ሰው ነፍስ ውስጥ ራስህን መግደል ነው ፍቅር ማለት ሞት ነው
ኦሾ/Osho
"...የሰው ልጅ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ መጠኑና ስፋቱ ቢለያይም ፣ ራሱ በሠራው አሊያም ሌሎች ባጠሩለት እስር ቤት ይኖራል፡፡ እንደ ራሱ አሳብና አመለካከት ግን ትልቅ እስር ቤት የሚኾንበት አንዳች ነገር የለም፡፡
ለካስ እስር ቤት ቦታ ሳይኾን አስተሳሰብ ነው፡፡ በዚህች ምድር እጅግ ብዙ ሰው በአእምሮው እስር ቤት ውስጥ በአሉታዊ አስተሳሰብ ታስሮ፣ በከንቱና እንቶ ፈንቶ ፍርሀት ተይዞ ማንም እንዳይረዳው ኾኖ የእስር ቤት ቊልፉን ራሱ ደብቆ ይኖራል፡፡"
በዚህ አጋጣሚ
"ሜሎሪና" መጽሐፍን ተጋበዙልኝ
#ለዕለተ ቅዳሜያችን
ብዙ ጊዜ ትወድቃላችሁ። ይህ ለክፉ አይሰጥም። እንደገና ተነስታችሁ ቁሙና ዳግም ያለመውደቅን ተማሩ። የበለጠ ንቁ። ስህተት መስራታችሁ አይቀርም ፣ ግን አንድ ስሄተት ደግማችሁ አትስሩ። ይህን የምላችሁ ሰው ጥበብን የሚያገኘው በዚህ መልኩ ነው።
አጭር ሆናችሁ አትቅሩ። የምትችሉት ርቀት ላይ ለመድረስ ሞክሩ። ሊያኮራ የሚችለውን ብቃት ይዞ ያልተፈጠረ ማንም ሰው የለም። አንድን አዲስና ውብ ነገር የመውለድ፣ህላዊን የበለጠ የማበልፀግ ብቃትን ሳይዝ የተፈጠረ ሰው የለም።
#ኦሾ/Osho
#ራስን የመኾን ድፍረት
#ትርጉም፦ዘላለም ንጉሴ