ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች
4.59K subscribers
21 photos
2 links
የፍልስፍና እይታዎች
Download Telegram
#የኦሾ የፍልስፍና እይታዎች
#ለአዲሱ ትውልድ እውነትን የሚፈልግበትን ቦታ ስጠው፣ እውነትን መፈለግ ፈልጎ ከማግኘት ይልቅ ያስደስታል። ዋናው ቅዱስ ጉዞው ነው እንጂ መድረሻ መቅደሱ አይደለም። ልጆቻችሁ ኩራት እንዲሰማቸው እንጂ ታዛዥና ባሮች እንዲሆኑ አትፍቀዱ።
ነፃ እንዲሆኑ እርዷቸው። ከመኖርና ራስን ከመግለጽ ነፃነት ይልቅ ዋጋ ያለው ነገር ያለመኖሩን ንገሯቸው።
አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ከባርነት ይልቅ ሞትን እንዲመርጡ አስተምሯቸው።
#ነፃነት
ኦሾ/Osho
"ሰው በሁለት ነገሮች ተጠምዶ ህይወቱን ያባክናል። ወይ በበታችነት ስሜት ወይ ደግሞ በበላይነት ስሜት ይሰቃያል። አንድ ሰው በበታችነት ስሜት ከተያዘ ውስጡ በጥልቀት ይታመማል። ከንቱ እንደሆነ እያሰበ ከኖረ በህይወት የመቆየቱ ጉዳይ አስቸጋሪ ይሆናል። በህይወት እየኖረ ቢሆንም ሙት ነው።
እስከ እለተ ሞታቸው ድረስ በህይወት የሚቆዩ በጣም ጥቂት ሰዎች አሉ። አብዛኞቹ ግን ከመሞታቸው በፊት የሚሞቱ ናቸው። በሰባ አመታቸው ቢቀበሩም የሞቱት ግን ቀደም ብለው ነው። በሞታቸውና በቀብራቸው መሀል የሰላሳ ፣ የአርባ ወይም የሃምሳ ዓመታት ክፍተት ሊኖር ይችላል።
በዙርያችሁ የተንሰራፋውን ግዝፈተ ተፈጥሮ ስትመለከቱ የበታችነት ሊሰማችሁ ይችላል።
ከዚህ አንፃር ሲታይ ሰው ምንም ነው። በውቅያኖስ ሞገዶች ላይ እንደተንሳፈፈ ገለባ ነው። እንደዚህ አይነት የበታችነት ስሜት ስሜት አይምሮን ጨምድዶ ከያዘ የሰው ህይወት በመከፋት የተሞላ ይሆናል። በህይወት የሚኖር ሙት ይሆናል።
ህይወቱ አመድና ትቢያ ይሆናል። የህይወታችሁ ነበልባል ከውስጣችሁ ከጠፋ ፣ የፋኖሳችሁ ነበልባል ከጠፋ ፣ በፀሃይ ብርሃንም ምንም ማድረግ አትችሉም። ለናንተ ፀሃይ ምንም ጥቅም አይኖራትም።"
#ኦሾ/Osho
#የንቃት ፀሐይ
በተማሪ በተሞላው ክፍል ውስጥ የ ስነ ልቦና አስተማሪው እያስተማረ ነው። በመሀል ግን አንድ ትምህርት ያስተምራቸው ዘንድ ምሳሌም ይሰጣቸው ዘንድ ወደደና በ ብርጭቆ ውሃ ሞልቶ ወደ ተማሪዎቹ ዞረ። ሁሉም የጠበቁት ነገር ይሄ ብርጭቆ ግማሽ ሙሉ ነው ወይስ ግማሽ ጎዶል? የሚል የተለመደ ጥያቄ መስሏቸው ነበር።

ነገር ግን መምህሩ "ይሄ የያዝኩት ብርጭቆ ምን ያህል ይከብዳል? " የሚል ቀጥተኛ ጥያቄ ነበር። ሁሉም በየፊናው መልስ ይሆናል ያለውን ሁሉ ተናገረ። ከቁጥር መለያየት ውጪ ሁሉም ቀላል እንደሆነ ነው ያሰቡት።

ነገር ግን መምህሩ እንዲ ሲል መናገር ጀመረ " በርግጥ የያዝኩት ብርጭቆ ክብደቱ ትንሽ ነው። ብዙም አይከብድም። ነገር ግን የዚህ ብርጭቆ ክብደት በጊዜ የሚወሰን ይሆናል። ለምሳሌ ይሄን ብርጭቆ ለ 3 ወይም ለ አራት ደቂቃ ብይዘው ምንም ላይከብደኝ ይችላል። ነገር ግን ለ ሁለት ወይም ለ ሶስት ሰዓታት ይዜው ብቆይ የ እጄ መዛል የብርጭቆውን ክብደት ያገዝፈዋል። እንበል እና ሳልታክት ለ አንድ ቀን ብይዘው የብርጭቆው ክብደት ሳይሆን የእጄ መታመምና መብረክረክ አልፎም ፓራላዝ መሆን ብርጭቆውን አግዝፎ መሬት ላይ ያስወድቀዋል።" ሁሉም ተማሪዎች በአውንታ እራሳቸውን ነቀነቁ። መምህሩም ሁሉንም አይን አይናቸውን ካየ ቡዓላ መናገሩን ቀጠለ።

" በህይወትም ውስጥ አንድ አንድ ችግሮችና ጭንቀቶች መግዘፍ ሳይገባቸው በጭንቅላታችን ውስጥ ለረጅም ጊዜ ስለሚኒዛቸው ብቻ ይገዝፋሉ። ወድያው አሽቀንጥረን ባለመጣላችን ምክንያት እና ምክንያት እየፈጠርን ከመብሰልሰላችን ብዛት ቅንጣት ሆነው ሳለ ቋጥኝ ያክላሉ። በጊዜው መፍትሄ የሚሰጥበት ነገር ሆኖ እያለ ለሌላ ቀን ስላሳደርናቸው ብቻ ጭንቅላታችንን በውዘው ያሳምሙናል።

ጊዜ የማይፈታው ነገር ባይኖርም ጊዜ የሚያገዝፈውም ነገር አለ። በቅፅበት የሚፋታ ነገር በቅፅበት ካልተፈታ የጊዜ መርዘም ግዙፍ መስሎ እንዲታይ ሊያደርገው ይችላል።
የሌሊት ወፍ

“የሌሊት ወፍ በቀን የመኖር ስልጣን የላትም” ይላል ምንጩ ያልታወቀ የጥንት አፈ-ታሪክ፡፡ “ለዚህ ነው ሌሊቱን እየጠበቀች ከመሸ ተደብቃ ወጥታ ሳይነጋ ተደብቃ የምትገባው”፡፡

በጥንት ጊዜ በሰማይ አእዋፍና በምድር አራዊት መካከል ውጊያ ነበር ይባላል፡፡ የአሁኗ የሌሊት ወፍ ያን ጊዜ እንደማንኛውም የወፍ ዝርያ ነበረች፡፡ ይህቺ ወፍ (የአሁኗ የሌሊት ወፍ) በውጊያው ጊዜ የምድር አራዊት ሲያሸነፍ ለእነሱ ታግዝ ነበር፤ የሰማዩ ሲያሸነፍ ደግሞ ተገልብጣ ለእነሱ ታግዝ ነበር፡፡

አንድ ጊዜ ግን እነዚህ ሁለት ጸበኞች ታረቁና የጦርነቱ ሁኔታና ትውስታ ሲነሳ ምን ስታደርግ እንደነበረ ታወቀባት፡፡ ከዚያ ቀን ጀምሮ በሁሉም የተጠላችና የተገፋች ወደመሆን ስለመጣች በቀን የመኖር ስልጣኗን አጣችና ሌሊት መኖር ጀመረች ይባላል፡፡

አስመሳይነት፣ ሁለት መልክ ያለው ሕይወት፣ አቋም የለሽነት፣ ውሸተኛነት፣ አታላይነት፣ መስሎ አዳሪነት፣ ባለ ሁለት ምላስነት፣ ሸንጋይነት፣ ለሆድ አዳሪነት . . . የዘመኑ ችግር!

የብዙዎችን በነጻነትና ቀና ብሎ በድፍረት የመኖር አቅም ያሳጣ የዘመኑ ወረርሽኝ!
አስመሳይ ሆነህ ወዳጅህ ከሚበዛ፣ እውነተኛ ሆነህ ጠላትህ ቢበዛ ይሻላል፡፡ ሁለት መልክ ይዘህ ትርፋማ ከምትሆን፣ አንድ መልክ ይዘህ ባለህ ነገር መኖር ይሻልሃል፡፡

ከዶ/ር እዮብ ገፅ የተወሰደ
#የኦሾ እይታ
በአንዱ ላይ ቁመህ አንዱ ላይ ለመፍረድ አትሞክር»
።።።።። //።።።።።። //።።።።።።
<<ሕይወትህን የምታከብራት ከሆነ ልታድናት የምትችለዉ አንተ ብቻ እንጂ ሌላ አዳኝ የላትም።የሚለዉ ኦሾ ህይወት የተፈጠረችዉ በሙላት ለመኖር ነዉ ስለዚህ ይህ ትክክል ነው ይህ ደግሞ ስህተት ነዉ አትበል ።በማለት ምሳሌ አስቀምጦልናል፧ ለምሳሌ እግዚአብሔር አለምን ፈጠረ።ሰይጣንም አብሮ ባይፈጠር ኖሮ አለም ላይ ምንም ባልኖረ ነበር። ለሆነዉ ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ሀላፊነቱን ቢወስድም ሰይጣን በበኩሉ አዳምና ሄዋንን ከበለሱ እንዲበሉ ባያደርግ ኖሮ የዛሬዋ አለም እንዲህ ባልሆነ ነበር ።
#የመጀመሪያዉ አብዮተኛ ሰይጣን መሆኑን አታውቁም?መጀመሪያው አመፀኛ ምድራዊዉን ህይወት የገለፀው እኮ እሱ ነው።እንዲያ ባይሆን ዛሬም አዳም እና ሄዋን ሳር እየበሉ ይኖሩ
ነበር።በኤደን ገነት ታዲያ ምን ስራ ይኖራቸዉ ነበር? እግዚአብሔር እንደሆነ ከእውቀት ዛፍ አትብሉ ብሏቸዋል! ከዚህ ከዘላለም የህይወት ዛፍም አትብሉ በማለት አዟቸዋል። እና ምን ቀረ? ማወቅ በተከለከለበት መኖር በታገደበት አለም እንደ አጋዘን ጥንቸል ሳር ብሉ አላቸው,,,,, እናም በሰይጣን ምህረት ይችን አለም ለማየት በቃን። እግዚአብሄር የፈጠረው አዳም እና ሄዋን ያሉበት ምድር ብቻ ነው።ከዚያ ውጪ ነገር ግን የፈጠረው ሰይጣን ነው ።ልብ በሉ! ቡድሀ፣እየሱስ፣ሙሴ,,,,, የሀይማኖት መሪዎች ስም የሰማነው ሰይጣን በመኖሩ ብቻ ነው ።እናም ህይወት በተቃርኖዋ ውስጥ እንኖርባት ዘንድ የተገባ ነው ።"በአንዱ ላይ ቁመህ አንዱ ላይ ለመፍረድ አትሞክር!!"
#የኦሾ እይታ
ማንነት ምንድን ነው?
( ክፍል ፩ )

፨፨፨

ማንነት ስለሌላ ነገር የሚፈጠር ሀሳብ ሳይሆን ሰው መሆንን ማሰብ ነው ። ማንነት የውጫዊ ሀሳብ ሳይሆን የውስጥ ማሰብ ነው ። ሰው ማለት የሚያስብ እንስሳ ማለት ነው ። ማንነቱ ማሰቡ እንጂ አሳቡን መሆኑ አይደለም ። ሀሳብ ተለዋዋጭ ነው ። የማሰብ ማንነት ግን የማይለዋወጥ ቋሚ ሰው መሆን ነው ። ማንነት የሌላ መሆን ሀሳብ አይደለም ። ማንነት ሰው መሆንን ማሰብ ማለት ነው ። የምታስበው ሀሳብን ሆነህ መኖር አትችልም ።

ማንነት ውጫዊ ሀሳብን ሆኖ መኖር ሳይሆን ሰው መሆንን በማሰብ መኖር ነው ። እያወራን ያለንው ስለሰው ልጅ ማንነት ከሆነ የሰው ልጅ ማንነት ሰው የመሆንን እውነት በማሰብ መኖር ነው ። ካልሆነ የማንነት አማራጩ ሁለት ነው ። አንደኛውና ትክክለኛው ውሳኔ ሰው ሆኖ በማሰብ የመኖር ማንነት ነው ። ይህ ካልሆነ የሌላን ሀሳብ ለመኖር ሰው የመሆንን ሕይወት በቁም መሰናበት ።

ማንነት ራሽናል እውቀት ነው ። ማንነት ስሜት አይደለም ። ያለ-ራሽናል እውቀት ስሜት ግልብ ህልም ነው ። ለስሜት ለስሜት ከብትም ስሜት አለው ። የሰው ልጅ ማንነት ከከብት የሚለየው ግርድፉን ስሜቱን በራሽናል እውቀት መግራት ከቻለ ነው ። ስለራስህ የሚሰማህ ነገር ሁሉ የአንተ ማንነት አይደለም ። ማንነት የመሆን ስሜት ሳይሆን ራስን የማወቅ እውቀት ነው ። በራሽናል መንገድ ራስህን መዝነህ የምታውቀው እሱ የአንተ ማንነት ነው ። ማንነት ሀሳብ አይደለም ። ማንነት እውቀት ነው ። እውቀት ሀሳብ አይደለም ። እውቀት የማሰብ ብቃት ነው ። ስለዚህ እውቀት ማንነት የሚሆነው ያለማወቅን ማወቅ ካስቻለ ብቻ ነው ።

ማንነት ክህሎት ነው ። ማንነት በገና መደርደር አይደለም ። በገና መደርደር ክህሎት ካልታከለበት የጉልበት ስራ ነው ። ማሲንቆ መገዝገዝ ማንነት አይደለም ። ማሲንቆ መገዝገዝ ክህሎት ከሌለው ክር መገዝገዝ ነው ። ክህሎት ከበሮ መምታር አይደለም ። ከበሮ መምታት ብቻውን እንጨት ማጋጨት ነው ። ማንነት ድምፆችን መፍጠር ሳይሆን የሙዚቃን ጥበብ የመፍጠር ክህሎት ነው ።

ማንነት...

ይቀጥላል...

ምንጭ ፦ ሰው መሆን
ደራሲ ፦ ቢልልኝ ሐብታሙ

፨ ማንነት ላንተ/ላንቺስ ምንድን ነው?
#የኦሾ እይታዎች
✤✤✤✤✤✤
"መላው ዓለም ከእኔ በተቃራኒ ቢቆም እንኳን በውስጤ አንድም ጥርጣሬ አይፈጠርም፤ምክንያቱም የማውቀውን አውቃለው-የሆንኩትንም ሆኛለሁ።
#እናንተም ራሳችሁን ሁኑ!"
OSHO/ኦሾ
እውነትን መፈለግ
አና ፍራንክ
የሰው ልጅ የሚሰቃየው ራሱ ባጠረው አጥር ራሱ በገነባው ቅጥር ራሱ በሸበበው ውትርትር ነው። የዘር ፣ የሃይማኖት ፣ የርዕዮተ አለም ፣..... የፍልስፍና አጥር ። የብቸኝነት ፣ የአውሬነት ፣ የወፈፌነት ፣ ......አስማት የሚመስል አጥር።...

"ክቡር ድንጋይ"
የትኛውም መሻትና ፍላጎትህ ወይም ውድቀትህና ስኬትህ በአንተ ማንነት ላይ ብቻ ተመስርቶ የሚገለጥ እውነት ነው::
ስለዚህ አንተ ከምታውቀውና ከምታምነው በላይ ሌላ ማንነት አለህና እሱን ፈልገህ አግኝ::''
።።//።።
#ተዓምራት እና ጣዖታት
#ማንም ሰዉ ክፋ ሆኖ የተወለደ የለም ነገር ግን ሰዉን ክፋ የምያደርገዉ እራሱ የሰዉ ልጅ በሚያደርጋቸዉ ክፋ ተግባር ክፋትን ያስተምረዋል እሾህ የሌለዉ መሬት
እንቅፋት የሌለዉ ህይወት የለም እና ሁሉንም በትግስት እንለፍ !!
"በተመስጦ ማሰላሰል ለፅምናና ለብቻ ለመሆን መድፈር ነው። ቀስ በቀስ በራሳችሁ ላይ አዲስ ባህሪ አዲሲ የህያውነት መንፈስ፣ አዲስ ውብት እንዲሁም አዲስ አስተሳሰብ ሲለመልም ይሰማችኋል። ይህ ደግሞ ከማንም የተዋሳችሁት ሳይሆን በውስጣችሁ እያደገ ያለ ስሜት ነው።"
*
ኦሾ/osho

"የታላቅ ሰው ታላቅነት የሚገለፀው በተግባሩ እንጂ በንግግሩ አይደለም"
የተግባር መሠረቱ ደግሞ ጽኑ ፍላጎት ነው።"

*
#ኮንፊሺየስ
#እናትነት ፍቅር ነው -ንፁህ ፍቅር ፣ ያልተከለሰ ፍቅር።
እናት መሆን ማለት ንፁህ ፍቅር መስጠት መቻል ፣ ሰውን በፍቅር ማፍቀር ፣ ሰውን ሲያደግ ለማየት ባለ ጉጉት ሳቢያ መርዳት ማለት ነው።
# እውነተኛ ሃኪም እናት ናት!!!
ኦሾ/Osho