ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች
4.59K subscribers
21 photos
2 links
የፍልስፍና እይታዎች
Download Telegram
የመኖር አካል ሁን ለመኖር የወደፊቱን የገና ለገና ውጥን አትጠብቅ ወይም ወደ ኃላ በትዝታ ምናብ አትጓዝ ህይወት ወደ ፊትም ወደ ኃላም አትጓዝም አዕምሮ እንጂ ህይወት አሁን ናት!!
OSHO/ኦሾ
የመጀመርያው እና ከሁሉ የሚቀድመው የገዛ ራስን ማፍቀር ነው። ልባችሁ የሳሳ እንጂ ልበ- ደንዳኖች አትሁኑ። ለገዛ ራሳችሁ ግድ ይኑራችሁ።
እንዴት ለራሳችሁ ይቅርታ እንደምታደርጉለት እወቁ። ጨካኞች አትሁኑ ፤ ራሳችሁን አትቃረኑ። የዚያን ጊዜ እንደ አበባ ትፈካላችሁ።
ህያውነት 2
Osho/ኦሾ
"አንዳንድ ጊዜ ብዙም ማህበራዊ መስተጋብር የሌላቸው ከሰው መሀል ወጥተው ዳር የሚይዙ ሰዎች ማህበራዊ ኑሮ የሚጠሉ አይደለም ፤ ከዚህ ይልቅ የውሸት ድራማን ፣ ድድብናንና አስመሳይነትን መቋቋም ስለሚከብዳቸው ነው።"

#Osho /ኦሾ
የመጀመርያው እና ከሁሉ የሚቀድመው የገዛ ራስን ማፍቀር ነው። ልባችሁ የሳሳ እንጂ ልበ- ደንዳኖች አትሁኑ። ለገዛ ራሳችሁ ግድ ይኑራችሁ።
እንዴት ለራሳችሁ ይቅርታ እንደምታደርጉለት እወቁ። ጨካኞች አትሁኑ ፤ ራሳችሁን አትቃረኑ። የዚያን ጊዜ እንደ አበባ ትፈካላችሁ።
ህያውነት 2
Osho/ኦሾ
#በአበደ አለም ውስጥ ነው እየኖርን ያለነው።እናም በውስጣችሁ የሆነ ጤነኛነትን ልትፈልጉ ይገባል። ውስጣችሁ ብቻ ነው ። ልታገኙት የምትችሉት። እናም ያጤነኝነት ወደ ንቃት ፣ወደ ደስታ ወደ እርካታ የሚያደርሳችሁ መሰላል ይሆንላችኃል።
#የአምላክነት ቅምሻ
#ኦሾ/Osho
...... አንድ ሰው በራሱ መርምሮ ያላገኘውን ነገር እንዲያምን መጠየቅ የመረዳት ችሎታውን ማሰናከል ተራ አእምሮ እንዲኖረው ማድረግና ለዘላለም ደደብ ሆኖ እንዲኖር መፍረድ ነው
( ኦሾ )
#ኦሮማይን ባነበብኩ ቁጥር የሚገርመኝና የሚደንቀኝ አንድ
አባባል አለ። እንዲህ የሚል
"እግዚአብሔር ለፖለቲካ ጆሮ የለውም!"
/ኦሮማይ/ በአሉ ግርማ
"ትኩረትን መሰብሰብ ማለት በተመስጦ ማሰላሰል እንዳልሆነ አስታውሱ። ምክንያቱም ትኩረትን መሰብሰብ አእምሮን ስርዓት ማስያዝ ሲሆን በተመስጦ ማሰላሰል ደግሞ አእምሮን ወደጎን መተው/ስራ ማስፈታት/ ነው።"
/ ኦሾ...ብርሃነ ኅሊና
።።።።።።።።።።።።።።
"የኛ ሃገር ፖለቲከኞች የቋንቋና የስሜት ደጋፊ እንጂ የህሊና እና የእውቀት ደጋፊ የላቸውም"

"ለ21ኛው ክ/ዘመን የሚመጥን አኗኗር ይቅርና ለ21ኛው ክ/ዘመን የሚመጥን አሟሟት እያገኘን አይደለም"

"የመኪና አደጋ እየበዛ ያለው ራሱን ሳይገዛ መኪና የገዛ ሰው በመብዛቱ ነው"

"እብደት ማለት በአቅርቦትና ፍላጎት መካከል ላይ ያለው ልዩነት ነው። እብደት ማለት የሰው ልጅ እንስሳዊ ባህሪዩ እና መልአካዊ ባህሪዩ አለመጣጣም ነው"

"ሰው ማለት በእንስሳዊ ባህሪዩ የሚመገብ፤ በመልአካዊ ባህሪዩ ለተራበ የሚመግብ ነው"

"ፀጉር አስተካካዮች እንዳሉን ሁሉ ሀሳብን የሚያስተካክሉ ሰዎች ያስፈልጉናል። ህብረተሰብን የሚሰሩ ሰዎች ያስፈልጉናል፤ ያልተሰራ ማህበረሰብ ምን ዓይነት ችግር እንደሚፈጥር ከእኛ አፍሪካውያን በላይ ምስክርነት የለም።"

#መጋቢ_ሓዲስ_እሸቱ_አለማየሁ
የሌሎችን ድጋፍ የሚሹት የሌሎችን አመለካከት የያዙ ብቻ ናቸው"

በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ አንድ ሰው ከሌላ ሰው ጋር በፍፁም ተመሳሳይ የሆነ ተግባር እንዲፈፅም ይጠበቅበታል። ሰዎች ትንሽ ለየት ያለ ነገር ሲያደርጉ ከመቅፅበት ለማህበረሰቡ እንግዳ እንደሆኑ ተደርገው ይታያሉ። ሰዎች ደግሞ እንግዳ የሆነ ተግባር የሚፈፅሙ ሌሎች ሰዎችን በጣም ይፈራሉ።
ለዚህም ነው በዚህ ዓለም አንድ ግለሰብ መሆን ታላቅ ድፍረት እንደሆን የምናገረዉ አንድ ግለሰብ ለመሆን ከሁሉ የላቀ ድፍረት የተሞላበት መሰረት ያስፈልጋል።

"መላው አለም እኔን መቃወሙ አያስጨንቀኝም። ዋናው ነገር ተሞክሮዬ ተቀባይነትን ማግኘቱ ነው። ምን ያህል ሰዎች ከኔ ጋር እንደሆኑ ለማወቅ ቁጥራቸውን አልመለከትም። ትኩረት የማደርገው በተሞክሮዬ ተቀባይነት የሌላ ሰው ቃላትን እንደበቀቀን እየደገምኩ መሆን አለመሆኔን ወይም የምናገራቸው ነገሮች ከገዛ ራሴ የመነጩ መሆን አለመሆናቸው ላይ ነው።

ንግግሬ በገዜ ራሴ ተሞክሮ ውስጥ ከሆነ፤ የደሜ፣ የአጥንቴና የመቅኔዬ አካል ከሆነ፣ መላው አለም በአንድ ወገን ሊሆን ቢችል እንኳን፣እኔ ትክክል ነኝ። እነሱ ግን ተሳስተዋል። ምንም የሚያስጨንቅ ነገር የለም። እኔ ትክክል መሆኔ እችዲሰማኝ የእነሱ የድጋፍ ድምፅ አያስፈልገኝም። የሌሎችን ድጋፍ የሚሹት የሌሎችን አመለካከት የያዙት ብቻ ናቸው" ብሎ ማሰብ የግድ ይሆናል።
#Osho/ኦሾ
💞 ሰብአዊነት ሊወለድ የሚችለው ከፍቅር ልብ ነው!"

💕በፍቅር በተሞላ ልብ መኖር እጅግ አስፈላጊ ነው።የፍቅር አመለካከት ሁላችንም ውስጥ ሊኖር ይገባል።ሰብአዊነት ሊወለድ የሚችለው ከፍቅር ልብ ነው፤በፍቅር ልብ ውስጥ ጥልቅ የደስታ ስሜት ይኖራል።

💗ትንሽ ፍቅር ለሰው ከለገሷችሁ በኃላ የሚሰማችሁ የሀሴት ስሜት አስተውላችሁ ታውቁታላችሁ?
መስፈርት በሌለው ፍቅር(unconditional love) ወስጥ ሆናችሁ የሚኖረውን ሰላም አስተውላችሁ ታውቃላችሁ?

💕ንፁህ ፍቅር ሊኖር የሚችለው በምክንያቶችና በመሥፈርቶች ካልታጀበ ብቻ ነው፤በሁኔታ የሚወሰን ፍቅር (conditional love) ፍቅር አይደለም የማታውቁትን ሰው መንገድ ላይ ፊት ለፊት ፈገግታውን ተመልክታችሁ የሚሰማችሁን ደስታ አስተውላችሁታል?

💗የወደቀን ስታነሱ የደከመን ስትረዱ የታመመን አበባ ስታበረክቱና ስጠይቁ የሚሰማችሁ የደስታ ስሜት ወሰን የለውም፤ ይህን የምታደርጉት አባታችሁ ወይም እናታችሁ ስለሆኑ አይደለም በሰውነት የምታበረክቱት ስጦታ ለእናንተ በተራው ታላቅ ደስታና እርካታና ስለሚያበረክት እንጂ። ለዚህም ነው "ሰብአዊነት ሊወለድ የሚችለው ከፍቅር ልብ ነው የምላችሁ።"

💗ኦሾ/Osho
ራሳችንን ለማወቅ የሌሎችን ሰዎች አይኖች መመልከታችን በጣም አስገራሚ ነው።
ሰው ሌሎች ሰዎች ስለሱ መጥፎ ነገር ሊናገሩ ይችላሉ ብሎ በማሰብ ይፈራል። እሱን በተመለከተ ሰዎች ጥሩ ሲናገሩ ይደሰታል፤ ምክንያቱም ስለ ራሱ ያለው እውቀት ሌሎች ስለሱ በሚሰጡት አስተያየት ላይ የተመሰረተ ነው። ስለራሱ ቅጽበታዊ የሆነ እውቀት የለውም፤ ራሱን የሚያውቅበት ቀጥተኛ ተሞክሮ የለውም። ራስን በቀጥታ የማወቅ ተሞክሮ ሊከሰት የሚችል ቢሆንም ከራሳችን ለማምለጥ ስለምንሞክር ግን አይከሰትም።

አይምሮን ለመጋፈጥ የመጀመርያው ዘዴ ሌሎች ስለሚሉት ወይም ለሌሎች እንዴት ሆነን መታየት እንደሚኖርብን አለመጨነቅ ነው። አንድ ሰው መሰረታዊ እሱነቱን በቀጥታ መጋፈጥ አለበት። ለብቻው ሆኖ አይምሮውን በመክፈት ውስጡ ያለውን ነገር መመልከት አለበት። ይህ የድፍረት ተግባር ነው። ከውስጥ ወዳለው ሲዖል ለመግባት የሚያስችል የድፍረት ተግባር። እርቃን ማንነትን ለመመልከት የሚወሰድ የድፍረት እርምጃ ነው። ታላቅ ድፍረት ያስፈልጋል።
:

#ኦሾ/Osho
#ምንጭ ፦ የነፍስ መንገድ
1. ሩቅ ካለ የለየኸው ጠላትህ በላይ ከጎንህ ያለው ውዳጅህ ጉዳት ይሰርግሃል።

2. መገንጠል.... መለየት እንጂ መበታተን አይደለም። መነጠል ራስን መለካት በራስ ልክ መወሰን... ልክን መሆን እንጂ መጀነን አይደለም።

ተነጥሎ ማሰብ ከአጀብ ጎርፍ ያድናል። መነጠል ጎራ መጎበን አይደለም። ከራስ ህሊና መታረቅ ነው። የራስ ታማኝ ሰብዕ መሆንና ንጥረ ስፍርን ለክቶ በመጠን ልኬታ መርጋት ነው።
......

ህገ-ሰው

1. ሰው ካለ ጉድለት አለ.... ሰው ማለት ከቶም ላይሞላ የሚባዝን ባለ መንታ እልህ ፍጡር ነው። በመደገፍም ሆነ በመቃወም እኩል ጉልበት አለው። ልዩነቱ የአቅጣጫ ጀርባ ጀርብነታቸው ብቻ ነው።

እንዲህ በተቃሮኖ የተማገረ ሰው... ዳር ከያዘ ውሎው ሁሉ ዳሩን ስለማስጠበቅ እንጂ መሀል ካለው ማዕድ ገድ እንዲል አይታሰበውም።

...
2. የሰው ችግሩ በሰልፍ ካሰበ ነው። ሰልፍ ለጦርነት እንጂ ለሀሳብ ባዕድ ነው። ሰው ቡድን ከሆነ የሚሳካለት የጦር ጀብዱ ነው።

ሀገር ላቅና ካለ ወይም ከፍ ያለ ዓላማ ማዝለቅ ሲሻ ግን የሚያዋጣው የግሉ የሆነን የመረዳት ስፍር ነውና አጀቡ ይከሳል ወይም ይቀንሳል።

ምክኒያቱም ለእያንዳንዱ አዋቂ በላጭ አዋቂ አለው። እናም በልህቀት ያስተዋሉ ጥቂት ራሶች በላቀ ስፍራቸው ስለብዙሃን የሚሆን ህብረ ፀሀይ ሆነው ህዝባቸውን ይፈነጥቁታል....

በአጀብ ስንጋፋ ግን... በቡድን የሚያስብ የጭንቅላት ተፈጥሮ የለምና በቀጥታ ጉዳዩ ወደ ስሜታሙ የስጋ ጦርነት ይጎመጃል። እያንዳንዷ ደቂቃ ክብረ ስብዕናን ወይም አምለካከትን በመሸንቆር ላይ ትገደባለች።

....

'ቆይ ጉዱን ነው አደባባይ እማወጣለት' እያሉ ከፍ ያለ ዓላማ አለኝ ማለት... ለራስም ካለመታመን ነው።

3. ማናችንም ከግድፈት አንጠራም። ምክኒያቱም ሰው ማለት እየተሳሳተ የሚነቃና በስተቱ የሚማር እንጂ በቅቶ የተመረተ ምርት አይደለም።

እንደ ብሔር እንደኃይማኖት ወይም እንደ ሀገር የ'በቅተናል...' ወይም 'ልከኞች እኛ ነን' ወረት (fashine) ውስጥ ሳንገባ አልቀረንም ብል እችል ይሆን?
በፀሎቱ ቋንቋ ከሚማርከኝ ይልቅ በልቡ ንፅህና የሚገዛኝ እኔ ፊት የተወደደ ነው "
💗
ሀሰን አልባስሪ አንድ ቀን ሀቢብ አልጃሚ ቤት የምሽት የፀሎት ሰአት ይደርስና ለመስገድ አበረው ይቆማሉ። ነገር ግን ፀሎት እንደጀመሩ አል-አጃሚ አንድ የፀሎት ቃል አበላሽተው ሲናገሩ ያስተዋሉት አል ባስሪ በተበላሸ ቃል ከሚሰግድ ሰው ጋር አልፀልይም ብለው ፀሎታቸውን አቋርጠው ሌላ ቦታ በመፀለይ ገብተው ይተኛሉ ።
💗
በእንቅልፍ ሰአታቸው ፈጣሪ ይመጣና ይጠይቃቸዋል ሀሰን በተበላሸ ቃላት ከፀለየው አል አጃሚ ኋላ ቆመህ ወደ እኔ ብትፀልይ ኖሮ በዘመንህ ከፀለይከው ሁሉ ይህን እሰማልህ ነበር" ።አንተ የቃላት መበላሸትን እንጂ የልብ ጉድፍን አላስተዋልክም ።እኔ ግን በፀሎቱ ቋንቋ ከሚማርከኝ ይልቅ በልቡ ንፅህና የሚገዛኝ እኔ ፊት የተወደደ ነው " በማለት ፈጣሪ አል ሀሰንን ገሰፀው ።
💗
#ሱፊዝም
#ከጲላጦስ
ከ"ሕማማት" መጽሐፍ የተወሰደ
አዳም ረታ እንዳስነበበን
እግዚአብሔር ሁሉን ነገር ያውቃል ማለት አስቀድሞ ይወስናል ማለት አይደለም ። ነገሮችም የሚሆኑት እግዚአብሔር አስቀድሞ ስላወቃቸው ሳይሆን በተቃራኒው እርሱ ያወቃቸው ስለሚሆኑ ነው ። እግዚአብሔር ስለወደፊት ያለው እውቀት እኛ ስላለፈው ታሪክ የዓይን ምስክሮች ሆነን እንደምናውቀው ያለ ነው።.../ አስቀድሞ የተነገሩ ትንቢቶች እንዴት ይታያሉ መጀመሪያ ትንቢት እንደ መንስኤ ሳይሆን እንደ ውጤት ካልተረዳነው ነገሩን ለመረዳት እንቸገራለን ። ትንቢቶች የሚነገሩት ነገሮች ስለሚሆኑ ነው እንጂ ነገሮች የሚሆኑት ትንቢት ስለተነገረ አይደለም "ትንቢቱ ይፈጸም ዘንድይህ ሆነ ተብለው የተጻፉት ቃላት ሁሉም የተጻፉት ትንቢቱ እንደተፈጸመ ከተረጋገጠ በኋላ ነው እንጂ ትንቢቱ እስከሚፈጸምባት እስከመጨረሻዋ ቅጽበት ድረስ ትንቢቱ የተነገረበት ሰው ትንቢቱን የመለወጥ እድል አለው ። እግዚአብሔር የተናገርኩት ከሚጠፋ ብሎ የሰዎችን የመዳን በር የሚዘጋ ጨካኝ አይደለም ስለሰው ልጅ መጥፋትና መዳን የሚነገሩ ትንቢቶች እንደሁኔታው ሊፈጸሙ የሚችሉ ትንቢቶች (conditional prophecies ) ናቸው እንጂ እንደ ሰማይ ምድር ማለፍ የማይለወጡ ትንቢቶች (fixed prophecies )አይደሉም ።

"ሕማማት " መጽሐፍ
ከ ገፅ 72-ገፅ 82
"…ነገን ማሰብ ተገቢ ቢሆንም ፣ በዛሬ ጥረት ነገን የተሻለ ማድረግ አርቆ አሳቢነት ቢሆንም ዛሬን ገድሎ ነገን ለመውለድ ማሰብ፣ ዛሬን አበላሽቶ ነገን ማሳመር፣ ዛሬን አጨልሞ ነገን ማብራት ግን ሞኝነት ነው።
ዛሬን አቆሽሸን ነገን ማፅዳት አይቻልም። ..."
* * *
#ከሰበዝ የተቆነጠረ ሊነበብ የሚገባው ተከሽኖ የተሰናዳ መጽሐፍ ይነበብ!!
*
#ዶክተር ዓለማየሁ ዋሴ እሸቴ
በሁለንተናው ኃይል ቅጽበቷን ኑራት
:
ይህ ቀላሉ የደስተኝነት ሚስጢር ነው። ምንም ነገር ስታደርግ ያለፈው ሁኔታ በጭንቅላትህ እንዲሄድ አትፍቀድለት ፣ ለወደፊት ያለውም እንዲረብሽህ አትፍቀድለት። ምክንያቱም ያለፈው አብቅቷል ፣ የወደፊቱ ገናአልመጣም። በትዝታ መኖር ፣ የወደፊቱን በማለም መኖር፣በሌለ ነገር ላይ መኖር ነው። በሌለ ነገር ላይ ስትኖር አሁን ያለው ነገር እያመለጠህ ነው።
በዚህም ብላሽ ትሆናለህ ምክንያቱም መላው ህይወትህን ትስታለህ።
:
#ኦሾ/OSho/
#የነፃነት መንገድ
ፍቅር ማካፈል እንጂ ልመና አይደለም ፍቅር ንጉስ እንጂ ለማኝ አይደለም። ፍቅር የሚያውቀው መስጠትን ብቻ ነው። ስለልመና የሚያውቀው ነገር የለም።
ፍቅር ከውጪ የሚገኝ ነገር አይደለም። ፍቅር የውስጣዊ ህልውናችሁ ሙዚቃ ነው። ማንም ፍቅርን ሊሰጣችሁ አይችልም።
ፍቅር ከውስጣችሁ የሚፈልቅ እንጂ ከውጭ የሚገኝ አይደለም። ፍቅርን ልትገዙት የምትችሉበት ሱቅ ወይም ገበያ የለም። ፍቅር በየትኛውም ዋጋ ሊገዛ አይችልም። ፍቅር ውስጣዊ ማበብ ነው።

ኦሾ/osho
ማህበረሠቡ ያለማቋረጥ እንድታገል ፣ እንድትወዳደር ይጠብቅሀል። ሌላውን ጥለህ እንድታልፍ የሌላውን እግር ጎትተህ አንተ ከፍታውን እንድትይዝ ፣ ስልጣኑን ሀይሉን እንድትሸከም ይጠብቅሀል።
ይህ አለም እኮ ከጦር ሜዳ አይተናነስም። እናም ቀዝቃዛ ጦርነት ያለማቋረጥ እየተካሄደ ነው። እያንዳንዱ ሰው የእያንዳንዱ ሰው ጠላት ነው። ወዳጅነት በሌለበት አለም ውስጥ ነው ያለነው።ጠላትነት ብቻ ነው ያለው።
:
#የአምላክነት ቅምሻ
ኦሾ/Osho
ከሱፊዝም መንደር ጎራ ብለን ከሼኽ ሙዛፌር ወግ ቆነጠርን ።
:
በሱፊዝም ዕውቀት ታላቅ ክብር ከሚቸራቸው አንዱ ናቸው ሼኽ ሙዛፌር
:
ሼኽ ሙዛፌር ከተማሪዎቻቸወሰ አንዱ በውስጡ ለዓለም ሀብትና ምቾት የሚመኝ መሆኑን በተደጋጋሚ በማስተዋላቸው በጥበብ ምክራቸው ሊመልሱት ደጋግመው ደከሙ።
:
ነገር ግን የተማሪው ልብ ለመንፈሳዊው ዕውቀት በቀላሉ የሚከፈት አለመሆኑን ሼክ ሙዛፌር ስለተረዱ አንድ ቀን አስጠሩትና እንዲህ አለት:- እኔ በየትኛውም ጨለማ ውስጥ የማየት ብቃት እንዳለኝ ታውቃለህን? ተማሪውም ግራ በተጋባ መንፈሰሰ:- "ታዲያ ለምንድ ነው ማታ ማታ መብራት ይዘው ወደ ቤትዎ ሲያመሩ የማይዎት?" በማለት መልሶ ጠየቃቸው።
"መብራቱማ እንዳንተ በጨለማ የማያዩ ሰዎች እንዳይረግጡኝ ነው"በማለት የልቡን ስንፍና እግረ መንገዳቸውን ገለጡለት።
:
ለሱፊዎች ወደ ፈጣሪ መቅረቢያ ብቸኛው መንገድ ለእሱ የተከፈተ ልብና የተሰጠ አእምሮ ነው ልብን ለዓለማዊ ነገር እያስገዙ ፈጣሪን መለመን ትርፉ ከንቱ ድካም ነው። ለዚህም ነው ሼኽ ሙዛፌር ሲመክሩ "ከአንድ ዓመት ፀሎት የአንድ ሰዓት ማሰብ ይበልጣል" የሚሉን። ለአንድ ሰዓት በትክክል ያሰበ ሰው አንድ ዓመት ከፀለየ ይልቅ እውነትን የማግኘት ዕድሉ ሰፊ ነውና!
#እውነት እና እምነት
#ከጲላጦስ
#የኦሾ የፍልስፍና እይታዎች
#ለአዲሱ ትውልድ እውነትን የሚፈልግበትን ቦታ ስጠው፣ እውነትን መፈለግ ፈልጎ ከማግኘት ይልቅ ያስደስታል። ዋናው ቅዱስ ጉዞው ነው እንጂ መድረሻ መቅደሱ አይደለም። ልጆቻችሁ ኩራት እንዲሰማቸው እንጂ ታዛዥና ባሮች እንዲሆኑ አትፍቀዱ።
ነፃ እንዲሆኑ እርዷቸው። ከመኖርና ራስን ከመግለጽ ነፃነት ይልቅ ዋጋ ያለው ነገር ያለመኖሩን ንገሯቸው።
አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ከባርነት ይልቅ ሞትን እንዲመርጡ አስተምሯቸው።
#ነፃነት
ኦሾ/Osho