ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች
4.59K subscribers
21 photos
2 links
የፍልስፍና እይታዎች
Download Telegram
'ድሮ ፖለቲካ አስተሳሰብ ነበር። ሃሳብ ደግሞ ሰው ሰራሽ ነው። አርቲፊሻል ነው። ስለአንድ ነገር ሃሳብ ከሌለህ የለህም። አይገባህም፣ ወይ ግድ የለህም።
==/
በአሁን ዘመን አተረጓጎም ግን ከፖለቲካ ጋር ተፈጥረሀል። አንተ ጎሳህን እንደ ሃሳብ አትመርጥም። ስለዚህ ገና ስትወለድ በሆነ ስልት ወገን ይዘሃል ማለት ነው። ሽል ፖለቲከኛ ሆኗል። ጡት የሚጠባ ልጅ ፖለቲከኛ ሆኗል።
==/
ባትፈልግም ወግነሃል፣ ማለት መወገንህን ሳታውቀው። ባትፈልግም ግድ ባይሰጥህም ሥልጣን ሽሚያ ተሰልፈሃል አሉ። አሁን ባዮሎጂ ሆኗል። እንደ ደርግ ጊዜ በቃኝ ብለህ እንኩዋን መሸሽ አትችልም። ከጥላህ እንደማምለጥ ነው።
==/
በሃሳብ ሳይሆን አሁን የምትገናኘው እንደ እንስሳት በጠረን ነው። ጠጋ ብለሽ ብብት እያሸተትሽ የአወላለዱን ካርታ ትፈልጊያለሽ።'
==/

"የስንብት ቀለማት" አዳም ረታ
➟የአንድ ዘመን የምድራችን ታላቅ አሳቢና ደፋር::
➟ከክርስቶስ በኋላ የተፈጠረ በጣም አደገኛ ሰው::
➟ከ20ኛው ክፍለ ዘመን ከ1000ቹ ታላላቅ ሰዎች መሀል አንዱ::
➟ከመላው አስቀያሚ ሰብዓዊነት ጋር አንድ ብቻውን ሆኖ ትግል የገጠመና አለምን ያናወጠ::

እነዚህ በተለያዩ ግዜ ስለ'ሱ ከተነገሩ አባባሎች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ በመንፈሳዊ ክህሎት የላቀ የአዕምሮ ባለቤት ለመሆን የበቃው ገና በ21 አመቱ ነበር፡፡ በዚህ የወጣትነት ዕድሜ ላይ መንፈሳዊ ብቃትን የተጎናፀፈ ግለሰብ እስካሁን እንዳልታየም ይነገራል:: ፍልስፍና ፒኤች ዲግሪ አግኝቷል፡፡ በተለያዩ የህንድ ዩኒቨርስቲ በመምህርነት አገልግሏል፡፡ ድፍረቱ የትየለሌ ነው::

በለየለት ድፍረቱ ያየውን የሰማውን ያነበበውን እውነት ነው ብሎ ያመነበትን ነገር ሁሉ አውጥቶ ይዘከዝከዋል፡፡ በንግግሮቹ ያልዳሰሰው ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ህይወት፣ ያላፈረጠው ባህላዊ ቁስለት ከቶም የለም፡፡ እምነትን፣ ባህልን፣ ሀይማኖትን፣ ጋብቻን፣ ወሲብን፣ ማህበራዊ፣ ስርዐተ ትምህርትን በሚገርም አሳማኝ ንግግሮቹ ያብጠለጥላቸዋል፡፡

"መላው አለም ከኔ በተቃራኒው ቢቆም እንኳን በውስጤ አንድም ጥርጣሬ አይፈጠርም ምክንያቱም የማውቀውን አውቃለሁ የሆንኩትን ሆኛለሁ!!” ይል ነበር:: እጅግ መሳጭ በሆነ የንግግር ጥበቡና በማስረጃ በተደገፈ የክርክር ዘይቤ አለምን ውድቅ ያደርግና የራሱን ብሩህ አዲስ የህይወት አቅጣጫ የሚለውን ያስተዋውቃል፡፡

ለየትኛውም እምነት፣ አስተሳሰብ፣ ባህልና ወግ ሐይማኖት ግድየለሽ እንዲያውም ፈፅሞ አላስፈላጊ ነው ባይ ሲሆን ከዚህ በላይ ግን ውስጣዊ ማንነትን ፍለጋ ላይ መድከም ብቸኛው የሰው ልጅ ከተያዘበት የባርነት ሰንሰለት የሚወጣበት መንገድ መሆኑን ደጋግሞ ይናገራል፡፡ መሰረታዊ ችግሩም ይህም ከግዜው ቀድሞ መምጣቱ እንደሆነ የሚዘግብም አልታጡም፡፡

በልጅነቱ ግዜ ከሌሎች የዕድሜ እኩዮች የሚለይበት በአንባቢነቱ ነበር፡፡ በአለም ላይ ያሉ በርካታ መፅሐፍትን ያነበበ ሰው መሆኑ ብዙዎች የሚስማሙበትና የሚመሰክርለት ነው፡፡ በፑና ማዕከልም ባለው የግል ላይብረሪው ውስጥ 100,000 በላይ የግል የመፃሕፍት ስብስቦች ነበሩት፡፡

ከ 600 በላይ መፃሕፍት ታትመውለታል፡፡7,000 ሰዐታት የሚፈጁ የኦዲዮቴፖች ንግግሮች አሉት፡፡ እነዚህም ለደቀመዛሙርቱ (ሳንያሲንስ) በጥያቄና መልስ ፕሮግራም የሰጠው የረጅም አመታት ትምህርቶች እንዲሁም በታላላቅ መድረኮች ላይ ያደረጋቸው ንግግሮች ተውጣጥተው የተፃፉ ናቸው፡፡

ስራዎቹ በመላ አለም በተለያዩ ቋንቋዎች እየተተረጎሙ እስካሁን በመሰራጨት ላይ ናቸው፡፡ “እኔ አንድም ተከታይ እንዲኖረኝ አልሻም ሌሎችን የምትከተሉ ከሆናችሁ ትጠፋላችሁ!!” እያለ ዘውትር ለተከታዮቹና ለአድናቂዎቹ የሚናገር ቢሆንም በአለም ዙሪያ አያሌ ተከታዮችንም አፍርቷል ለዚህም ተቀዳሚው ማስረጃ በአሜሪካ በአውሮፓ በእሲያ በህንድ የተቋቋሙት (Osho Commune International) የተሰኙት ማዕከላት ናቸው፡፡

ከሞተ በኋላ ህንድ ፑና ውስጥ ወደ አቋቋመው ማዕከልም በበርካታ አድናቂቹና ተከታዩቹ ከተለያዪ ሀገራት ወደ ስፍራው አሁንም ድረስ ይጓዛሉ፡፡ በማዕከሉም እራሱ የፈጠራቸው የተለያዩ የተመስጦ ዘዴዎችንም እንደትምህርት የሚሰጡበት ማዕከልም ሆኖል፡፡

የአለማችን ታላቅ አወዛጋቢ ሰው!! ህንድ ውስጥ ኩችዋይ በምትባል መንደር ዲሴንበር 11፣ 1931 ነው የተወለደው:፡ በቤተሰብ የወጣለት መጠሪያ ስሙ ቻንድር ዋሀን ጄይን ሲሆን በሁላ ላይ ስሙን ባግዋን ሸሪ ራጅኒሽ በሚል ቀይሮታል፡፡ አለም የሚያውቀውም “ኦሾ”በሚለው ስሙ ነው፡፡

ህንድ ፑና ውስጥ ጀንዋሪ 19 1990 በ 58 ዓመቱ ሲሞት የሞቱ መነሻ አሜሪካ ሀገር በነበረበት ግዜ በአሜሪካ የስለላ ድርጅት (CIA) ታሊየም በተባለ መድሀኒት መርዘውት እንደነበረና በሱ ህምም መነሻነት እንደሞተ ተከታዩች ያምናሉ፡፡ ክሮኒክ ፋቲግ ሲንድረም የተባለ የጤና ችግርም እንደነበረበትና ይህም በሽታው ለሞት እንዳበቃው የሚናገሩ ወገኖችም አሉ፡፡

Osho! Never born Never died only visited this planet earth between December 11, 1931to January 19, 1990 ተከታዮቹ እንዲህ ነው የሚያስብት
👉 አሉታዊ እሳቤዎች ፀረ መርዝ 👈
* ፍቅር እይታ ሁሉኑም ነገር ነው
* አሉታዊ እይታ ህይወትን ይመርዛል
* አሉታዊዎች ለሞት ልከኛ ናቸው
* ለህይወት ግን ስህተት
* ህይወት አዎንታ እሳቤ ትሻለች ትፋፋለችም ምክንያቱም ቅን እይታ ሰውን ደስተኛ ከማድረግ አልፎ ፈጣሪም ( creative ) ያደርገዋልና
--- አንዲት በእድሜ የገፋች ሴት ነበረች
እድሜዋ በጨመረ ቁጥር ይበልጥ ወጣትነት የሚሰማት ምክንያቱም ወጣትነት ከአመለካከት ጋር እንጂ ከእድሜ ጋር አይገናኝምና በእድሜና እድሜ በሚሰጠው ፀጋ ከወጣት በላይ ወጣት መሆን ይቻላል
አዛውንቷ ሁሉም እስቲገረምባት ደስተኛና በፈጠራ የተሞላች ነበረች
--- ሆኖም በህይወትሽ ውስጥ ጥቂት ደመናዎች መኖራቸው አልቀረም አላት አንድ ጎብኚ
--- ደመናዎች ? መለሰች
እርግጥ ነው እኮ ደመናዎች ባይኖሩ ኖሮማ የተባረኩት ጠብታዎች ከየት ይመጡ ነበረ
--- ችግሮች በሚገኙበት ሁኔታ ውስጥ ( ህይወት ያለ ችግር አትሰራም )
* ቀና አእምሮ ክንፎችን ያበቅላል
* ሌሎች ግን ምርኩዝ ይገዛሉ
* ክንፍ አብቅይንጂ
* ምርኩዝ አትልቀሚ
( ኦሾ )
".......በአንድ ልብ ውስጥ ፍቅር እና ጥላቻ በጋራ ሊኖሩ አይችሉም። እነዚህ ሁለት ነገሮች እንደ ሞትና ህይወት ተቃራኒዎች ናቸው። በአንድ ልብ ውስጥ በጋራ ሊኖሩ አይቻላቸውም። ታዲያ "ፍቅር" ብለን የምንጠራው ነገር ምንድነው?"

"አነስተኛ ጥላቻ በውስጣችን ሲኖር "ፍቅር" እንለዋለን፤ መጠኑ ከፍ ያለ ጥላቻን ደግሞ "ጥላቻ" ብለን እንጠረዋለን። ሁለቱም አነስተኛና ከፍተኛ የጥላቻ መጠኖች ናቸው። በዚህ ሁነት ውስጥ ባለ ልብ ውስጥ ፍቅር ከነጭራሹ የለም። ስህተቱ የሚፈጠረው በጥላቻው መጠኖች ሳቢያ ነው። ከመጠን ጋር በተያያዘ ቅዝቃዜና ሙቀት ሁለት የተለያዩ ነገሮች እንደሆኑ ታስቡ ይሆናል። ሁለት የተለያዩ ነገሮች አይደሉም። ሙቀትና ቅዝቃዜ የአንድን ነገር ደረጃዎች የሚያሳዩ ናቸው። የሙቀት መጠን ሲያንስ ቅዝቃዜ መሰማት ይጀምራል። የሙቀት መጠን ሲበዛ ደግሞ ሙቀት መሰማት ይጀምራል......"

".....ከኢጎ በመነጨ ፍቅር ከተፈቀራችሁ ከትንሽ ጊዜያት በኋላ በአፍቃሪ እጆች እንደታቀፋችሁ ሳይሆን በብረት ሰንሰለት እንደተጠፈራችሁ ይሰማችኋል። ከትንሽ ጊዜያት በኋላ ውብ ንግግሮችን ሲናገር፣ ውብ ዘፈኖችን ሲዘፍንላችሁ የነበረው ፍቅር፣ በውብ ዘፈኖቹና ንግግሮቹ ውስጥ መርዝ ደብቆ እንደነበር ታውቃላችሁ። የአበቦችን መልክ ተላብሶ የሚመጣው ፍቅር ምንጩ ኢጎ ከሆነ አበቦችን በዳሰሳችሁ ጊዜ እጆቻችሁን የሚወጉ እሾሆችን ታገኛላችሁ......"
አንስታይን የአንፃራዊነትን ንድፈ ሃሳብ ካረቀቀ በኋላ መቶ ፊዚስቶች ተሰብስበው የአንስታይንን ሃሳብ የሚቃረን አንድ መጽሐፍ አሳተሙ። አንስታይን ሲሰማ እንዲህ አለ፦

"ለምን መቶ ሁሉ?! አንፃራዊነት ስህተት ከሆነ ለማረም አንድ ፊዚስት ብቻ ይበቃ ነበር!"

መንጋ ሲሰባሰብ ሃይል ያገኛል። ሁሌም ከመንጋው ጋር ሳይሆን ከእውነት ጋር ለመቆም የአላማ ፅናትን ይጠይቃል። እነዛ 100 ፊዚስቶች አሁን የሉም። የአንስታይን ንድፈሃሳብ ግን አሁንም አለ፤ ወደፊትም ይኖራል
ንስርን ለመጥለፍ የምትሯሯጥ የወፍ ዝርያ አሞራ ብቻ ናት ። አሞራዋ ጀርባው ላይ ተቀምጣ ንስሩን አንገቱን ትነክሰዋለች ። ነገር ግን ምላሽ አይሰጥም ወይም ከአሞራ ጋር አይጣላም ፤ጊዜ ወይም ጉልበት ከአሞራው ጋር አያባክንም። ግን ክንፎቹን ዘርግቶ ሰማይ ላይ ከፍ ብሎ መብረር ይጀምራል ። በረራዉ ከፍ ሲል ለመተንፈስ ይቸገራል እናም አሞራው በኦክስጅን እጥረት ምክንያት ይወድቃል።

መልስ መስጠት ያለባቹ ለሁሉም ውጊያዎች ፣ለሁሉም ክርክር ወይም ትችቶች አይደለም። ዝም ብላቹ ከፍታቹን ጨምሩ ፍጥነታቹን መቋቋም ሲያቅታቸው ይወድቃሉ። ከ አሞራዎች ጋር ጊዜ ማባከናችሁን አቁሙ። በቃ ወደ ከፍታቹ ውሰዱአቸው እና ይሸሻሉ። በአላስፈላጊና በትንንሽ ነገሮች ላይ ጊዜና ጉልበታችሁን ማባከናችሁን ካላቆማቹ በአስፈላጊ ነገሮች ላይ ሀይላቹን ታጣላቹ ፤ ጊዜያቹንም እንደዛው። ጠላት ጀርባህ ላይ ተቀምጦ አንገታቹ ሊደፋ ይችላል... ነገር ግንአስታውሱ ጊዜ የማይከፍተው ቁልፍ መንገድ የለም! የችግሮቻችሁን ምንጮቻቹን በስኬቶቻቹ አሽሿቸው። ሀይላቹን ለመልካም መሻታቹ አውሉት፤ እንዲሁም ስሜቶቻችሁን አጠንክሯቸው ሀይል ይሆኗችኋል። ጥልቅ ፍላጎት የሌለው ሰው ስኬት አልባ ህይወትን ይመራል።
ባንተ ውስጥ ያንተን እድገት የሚቃወም ጭራቅ አለ፡፡ከድህነት እንድታመልጥ አይፈልግም፡፡ከመጥፎ ጓደኞችህ ስትሸሽ ያመዋል፡፡ከሱስ ስትርቅ ይጨንቀዋል፡፡ፍላጎቱ ለጊዛዊ ደስታ ጊዜና ሐይልህን በከንቱ እንድታባክን ነው፡፡
+
በተለይ አዲስ ነገር ስትሞክር ይንጫጫል፡፡
"ይህን ማድረግ አደጋ አለው!! ጎመን በጤና! ዋ! ትከስራለህ !ይሳቅብሃል!!" በማለት አዛኝ መስሎ እንደ ሐውልት ያስቆምሃል፡፡በጊዜ ሂደትም ወደኃላ ጎትቶ ይጥልሃል፡፡በገዛ ራስህ ህይወት አቅም ታጣለህ፡፡እሱ ንጉስ አንተ ባርያ ትሆናለህ::
+
ባርነት አልሰለቸህም? የራስህ ህይወት ንጉስ መሆን አላመማረህም? ከጭራቁ እስር ቤት ነጻ መውጣትስ? በፈለከው ሰዓት የፈለከውን ነገር ማድረግስ? የራስህን ህይወት መኪና መሪ መጨበጥስ? ህልምህን አሳክተህ ከስኬት ተራራ ጫፍ መሆንስ? አያጓጓህም? መልስህ "አዎ!" ከሆነ በመጀመርያ በውስጥህ ያንቀላፋውን ጀግና ቀስቅሰው፡፡
+
ባንተ ውስጥ ያንቀላፋ ምንም ነገር ማድረግ የሚችል ጀግና ሰው አለ፡፡ይህ ጀግና ፈጣሪን የሚመስል ገራሚ ሐይል ነው፡፡ይህንን ሐይል ማድመጥ ጀምር፡፡የጭራቁን አቅምና ሐይል ከውስጥህ ነቅሎ ይጥለዋል፡፡
+
ጭራቁ ማንነትህ ፈሪ ነው፡፡ጀግናው ማንነት # አማኝ ነው፡፡ጭራቁ ማንነትህ ሰነፍ ነው፡፡ጀግናው ማንነትህ # ለፊ ነው፡፡ጭራቁ ማንነትህ "ሰው ምን ይለኛል?" ይላል፡፡ስህተት ይፈራል፡፡ፍጹም መስሎ ለመታየት ይሞክራል፡፡ጀግናው ማንንትት ግን "እኔ ራሴን ምን እላለው? ፈጣሪስ ምን ይለኛል?" ይላል፡፡ፍጹም መስሎ የመታየት ምኞት የለውም፡፡እሱ የህይወት ዘመን ተማሪ ነው፡፡ ጭራቁ ማንነትህ ጊዛዊ ደስታን ብቻ ይፈልጋል፡፡ጀግናው ማንነትህ ግን ረጅሙን የውስጥ ሰላም፣ ፍቅር፣ ወሳጣዊ ደስታና ስኬት ይሻል፡
የላቀ አስተሳሰብና ክህሎት በማስቀደም ስኬትን መጎናጸፍ ።
ምንጭ ስነ-ልቡና
➲ ቅቤና ማር ተከራከሩ

//ዳንኤል ክብረት//

ማርም ተናገረች፡- “የምጣፍጠው እኔ አናት ላይ የምትወጪው ግን አንቺ ነሽ ለምንድነው?” አለቻት። ቅቤም፡- “እኔም ወድጄ አይደለም ገፍተው፣ ገፍተው ነው አናት ላይ ያወጡኝ” አለች ይባላል። ቅቤ፣ ቅቤ የሚኮነው ተንጦ፣ ተንጦ ነው። እግዚአብሔር ሁሉም ሎሌው ነው። በክፉዎች ሳይቀር ይሠራል። ወዳሰበልን የሚያደርሰን እየገፋን ነው። ካልተገፋን ያለንበትን ትንሽ ቦታ ተላምደን እንኖራለን። እርሱ በደጎች አይገፋንም፣ ደጎች መግፋት ባሕርያቸው አይደለምና። ክፉዎች ግን ቅድስናም ይሉኝታም የላቸውምና በእነርሱ ይገፋናል። እነርሱ የሚያውቁት ወደ ገደል እንደሚገፉን ነው፣ ሳያውቁት ግን ወደ ተራራ ይገፉናል። ጠላቶች የነጻ ሠረገላ ናቸው። ለኛ ከ ማይገባን ቦታ እየገፉን ወደ ሚገባን ቦታ ... ከ ዝቅታ ወደ ከፍታ ቦታ ያደርሱናል። በእውነት ጌታ ሆይ ጠላቶቻችንን ባርክልን። እነርሱ ባይኖሩ ሥራው አይበዛልንም ነበር። ይህን ጥንቁቅ ሕይወት፣ ይህን ዝግጅት፣ ይህን ቶሎ ቶሎ መሥራት ያገኘነው ከጠላቶቻችን ነው። እያንዳንዱን ቀን በትክክል እንድንኖር ያተጉንን ጠላቶች እባክህ ባርክልን። የሰዓት ደወል ብንሞላ ጠዋት 12 ሰዓት ሞልተነው፣ ማታ 12 ሰዓት ሊጮህ ይችላል። ቀስቅሱን ብንላቸው ወዳጆቻችን ከሥራችን ለእንቅልፋችን አዝነው ይተውናል። ክፉዎች ግን በሰዓቱ ያነቁናል። እንደዚህ ያሉ ነጻ ደወሎችን ያስቀመጠልን አምላክ ስሙ ይባረክ። እነርሱ እንዳይነቅፉን ስንጠነቀቅ የቅድስናን ሕይወት ያለማምዱናልና እነዚህ ጠባቂዎቻችን ናቸው። የተገፉ ሁሉ ከፍ እንጂ ዝቅ ሲሉ አይተን አናውቅም። ገፊዎች ሲገፉን ከእኛ የክፋት ሰፈር ምን ትሠራላችሁ? እልፍ በሉ እያሉን ነው። ጠላቶች ሐሰተኛ ወዳጆችን ወስደው እውነተኛ ወዳጆችን ያስቀሩልናል። ክፉዎች ጥሩ ማጣሪያ ናቸው። ተረስተን የምንኖረውን እነርሱ ያሳውቁናል። በነጻ ማስታወቂያ ይሠሩልናል። ሰዎች ስማችንን የሚያነሡት በሁለት ነገር ነው። ስለሚወዱንና ስላስደሰትናቸው ሲሆን በተቃራኒው ደግሞ ስለሚጠሉንና ስላስጨነቅናቸው ነው። እንዲሁ ርእስ መሆን አይገኝም። የአትርሱኝ ሳንከፍል ላስታወሱን በረከት ይሁን። ዮሴፍ ባይገፋ ኖሮ ጎበዝ እረኛ ሆኖ ይቀር ነበር። በመገፋቱ የግብፅ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነ። ጠላት ያውቃል እንላለን፣ እንደ ጠላት ግን አላዋቂ የለም። ኢየሱስን ከኢየሩሳሌም ሊያጠፋ ገደለው፣ በሞቱ ግን በዓለም ሁሉ አበራ። ጠላት ሰፈር እየቀማ ዓለም ያወርሳል። ሰው ማፍረስ ይችል ይሆናል፣ እግዚአብሔር ደግሞ ማስነሣት ይችላል ።
.
"መገፋት ጥሩ ነው እጅግም ሳይወድቁ፣ የተገፉት ቆመው የገፉት ወደቁ"
ጠቃሚ ምክር !

★★★
በወጣትነት ሁሉም ነገር ትክክል ነው ከሚል መመሪያ ውጣ ፤ ሁሉንም ካላየሁ አላምንም አትበል ። ሰምቶ ማመን ፣ ከተጎዱት መማር አስተዋይነት መሆኑን አትርሳ ። የሰማንያ ዓመት ዕውቀትን ለመገብየት ግድ ሰማንያ ዓመት መኖር የለብህም ። ሰማንያ ዓመት ከኖሩት በትሕትና መጠየቅ ይገባሃል ።
:
ምክርን ብትሰማ በነጻ ትማራለህ ። ምክርን አልሰማ ብትል ግን በዋጋ እንደምትማር እወቀው ። በዋጋ መማር ግን አድካሚ ደግሞም የሚያስመርር ነው ። ብልህ ከሆንህ በሰው ከደረሰው ትማራለህ ፣ ሞኝ ከሆንህ ግን በራስህ ሲደርስ ትማራለህ ።
:
የታየህን አሳይ ፣ ያልታየህን አጥራው ። በደንብ ያልተረዳኸውን አታስተምረው። ያልቀመስከውን ለሰው አትጋብዝ ። የሰማኸውን ሁሉ አትመን ። ያየኸውን ሁሉ ስጡኝ ፣ የተናገርከውን ሁሉ ፈፅሙ አትበል ። የሰጠኽውን እርሳ እንጂ አታውራ። ፍፃሜውን ሳታይ ምስጋና አታብዛ ። ቀኑ ሳይመሽ ቀኑ ጥሩ ነው አትበል ።
:
ዓይንህ የፊቱን ቢያይ ልብህ የኋላውን ያስብ ። ነገ ላይ እንድትደርስ የትናንቱን አትርሳ ። የምትሄድበት እናዳይጠፋህ የመጣህበትን አትዘንጋ ።
:
የአባቶችህን መልካም ሥራ አብነት አድርግ ። ካሳለፉት ሕይወት ተማር እንጂ አወዳሽና ወቃሽ አትሁን ። ሌሎች መሆን ያለባቸውን ስታውቅ አንተ መሆን ያለብህ እንዳይጠፋህ ተጠንቀቅ ። ደግሞም አንተም በታሪክ ፊት መሆንህን እወቀው ።
:
ክፋት አይሙቅህ ፣ መልካም ነገርም ብርድ ብርድ አይበልህ ። ለክፋት አቅም ካለህ ለበጎ ነገርም አቅም አለህና ተግባርህ የምርጫ ውጤት ነውና አስብበት ።
:
ገንዘብ የሚመልሰው የገንዘብን ጥያቄ ብቻ ነውና ሁሉንም ነገር ገንዘብ ያስገኝልኛል ብለህ አታስብ ። ላለው አትሩጥ ፣ ምጽዋትህና ተግባርህ በአቅምህ መጠን ይሁን እንጂ ከአቅምህ አትነስ ። ድሃም ሆነህ ተበድረህ ስጦታ አትስጥ ። በጣም ካልቸገረህ ለቅንጦት አትበደር ። ያንተን ድርሻ ከጨረስህ ያልተጨረሰ የሌሎችን ድርሻ ፈፅምላቸው ።
:
ለሀብታም አትሳቅ ፣ የደሀ ጉልበት አይለፍብህ ፣ ያለ ሰው ሰው አልሆንክምና ሰው አትጥላ ፣ የወጣህበትን መሰላል አትገፍትር ፣ ለመውረድም ያስፈልግሃልና ፣ ያየኽውን ሴት ሁሉ የመውደድ ጠባይህ ካለቀቀህ ትዳር አትያዝ ፣ ካልጋበዙህ በቀር አማካሪ አትሁን ፣ ባልጠሩህ ሥፍራ አቤት አትበል ፣ ካልሾሙህ መሪ አትሁን ፣ ጉድለት በሌለበት ቦታ ጊዜህን አታባክን ፣ የሰው ፊት ጥገኛ ሁነህ ሲስቁልህ የምትስቅ ሲቆጡህ የምታለቅስ አትሁን ፣ ነገርህን በልክ ፣ ቃልህን በጣዕም ፣ ድምፅህን በዝግታ ፈፅመው ።
:
እውር እንዳይሉህ ያልታየኽን አያለሁ አትበል ። ጨካኝ እንዳይሉህ ያልተሰማህን ጩኸት እሰማለሁ አትበል ። ንፉግ እንዳይሉህ ያለ አቅምህ እረዳለሁ አትበል ። ነገር አይገባውም እንዳይሉህ ያልገባህን እንደገባህ አድርገህ አትለፍ ። አንድ በጎ ዕውቀት ሳትጨብጥ የዋልክበትን ቀን እንደ ኖርክበት አትቁጠረው ፣ ስለዚህ መፅሐፍትን አንብብ ፣ አዋቂዎችን ጠይቅ ፣ ሁሉን ሳትንቅ ስማ ።
:
ሥልጣን ሲሰጥህ መሪ እንጂ አለቃ አትሁን ፤ ከፊት እየቀደምህ አስከትል እንጂ ከኋላ ሆነህ አትቅደም ።
:
በዓላማ ኑር ፤ እንቅፋቶች የሚያጸኑህ እንጂ ተግባርህን የሚያስተውህ አይሁኑ ። ሕይወት ትምህርት ቤት መሆኑና ባለማወቅ ብዙ ትህምርቶች እንዳያመልጡህ ተጠንቀቅ ።
:
የመከራ ቀን ወዳጆችህን አትርሳ ፤ የዛሬ ሰው ብቻ አትሁን ፤ የትላንቱንም አስብ ፤ አንገት የተፈጠረው ዞሮ ለማየት ነውና ።
:
ዓለም ዋዣቂ ናት ። ከፍና ዝቅ ስትል አትደናገጥ ፤ ፀሐይ ዝናብን ተከትላ ትፈነጥቃለች ። ከመከፋትም በኋላ ትልቅ መፅናናት ይሆናል ። ከሌሊት በኋላም ሌሊት አይመጣም ። ከሀዘን በኋላ ደስታ ይሆናልና በርታ!
:
መነቀፍን አትፍራ ፤ ነቀፋህን ግን አጥራው ፤ ስለ ሀሰት ሳይሆን ስለ እውነት ተገፋ ፤ ሌሎችን ውደድ ፍቅር ስጦታ እንጂ ብድር አይደለምና አልወደዱኝም ብለህ በአበዳሪዎች አንቀጽ አትካሰስ ፤ የገባህን አድርግ የዚህ ዓለም ሰው ሲወድህም ሲጠላህም ባለማወቅ ነው ። ብዙዎች ስለወደዱህ ይወድሃል ፤ ብዙዎች ስለጠሉህ ይጠላሃል ።
:
ሁልጊዜ የበላዮችህን አትመልከት ፤ የበታቾችህንም ተመልከት ። ለድምፅ አልባዎች ጩህላቸው ፣ ለተጠቁት ተሟገትላቸው ። እውነት እውነት በማለትህ የምታጣው ሀሰተኛ ወዳጅህን ብቻ ነው ። እውነት እውነት በማለትህ የምታተርፈው ግን እውነተኛ ወዳጅን ነው ።
:
ደጋፊዎች ተከታዮች አይደሉም ። ሰዎች ስለደገፉህም የያዝኩት እውነት ነው ብለህ መንቻካ አትሁን ፤ ምናልባት ዛሬ የሚጮሁልህ ዛሬን ሊረሱብህ ሊሆን ይችላልና ። ሲያለቅሱልህም ቃልህ ማርኳቸው ሳይሆን የሞተ ዘመዳቸው ትዝ ብሏቸው ሊሆን ይችላልና አለቀሱ ብለህ ንግግርህን ድንበር አታሳጣው ። እውነትንም በደጋፊ ብዛት እንዳትመዝናት ተጠንቀቅ ።
:
ለእውነታ እንጂ ለይሉኝታ አትኑር ፤ ያን ስልህ የምትኖርበት ሕዝብና ባሕል ከእውነት ጋር እስካልተጋጨ መጋፋት የለብህም። ሠዎች የሚቀበሉህ ባሕላቸውን ስታውቅና ስታከብርላቸው ነው ።
:
ልጅነት የለሰለሰ መሬት ፣ ወጣትነት የአዝመራ ዘመን ፣ ሽምግልና ደግሞ የአጨዳ ዘመን መሆኑን አስተውል ። በሽምግልናህ የምታጭደው የወጣትነትህን አዝመራ ነውና ዛሬ ለምትዘራው ተጠንቀቅ ።
:
የሰዎችን ያለማወቅ አግዝ ፤ ዕውቀትህ ባላወቁት ላይ እንድትኮራና እንድትፈርድ አያድርግህ የአዋቂ ኩሩ ቁጥሩ ካላዋቂዎች ነውና ማወቅ ባለዕዳነት እንዳይሆን አላዋቂዎችን እርዳቸው !!

ሁሉን ወሬ ላውራ አትበል ፣ የደበቁህን ምስጢር አታውጣጣ ፣ የሰማኽውን ወሬና የተገለጠልህን ምስጢር ምን መፍትሔ ሰጠኸውና ? ያየህውን ሥራ ሁሉ እሰራለሁ የሰማኸውን ትምህርት ሁሉ እማራለሁ አትበል ። ይህ የተሰወረው የቅንዓት ጠባይ ነውና ሁሉን ልያዝ ማለትም ዝንጉ አድረጎ እንዳያስቀርህ ሁሉም ውስጥ ልኑር አትበል ።

ቆንጆዎች ቁንጅናቸው ሁሉን የሚተካ እየመሰላቸው ከዕውቀትና ከትሕትና ይርቃሉ ። ሁሉንም ሰው በመልካቸው የሚማርኩት ስለሚመስላቸው ኩሩና ተንኮለኞች ይሆናሉ ። አንተ ግን ቆንጆ ወዳጅን እንጂ ቆንጆ ቁመናን አትሻ ፤ ቆንጆ ትዳርን እንጂ ቆንጆ ሴትን አትመኝ ፤ የላይ ነገር ከንቱና ኀላፊ ነውና በሚፈርስ አካል ፣ ኑሮ በሚለውጠው መልክ አትደለል።

እወድሃለሁ ብለህ የምትናገረውን ቃል ውለታ አታድርገው ፣ መውደድህን የምትናገረው እንወድሃለን እንዲሉህ አይሁን ፣ ሠላም ያለው አፍቃሪ የራሱን ፍቅር ያለ ምክንያት መፈፀም የሚችል ብቻ እንደሆነ እወቅ ። መወደድህን ለመስማት አትጠብቅ ።

የሰዎችን ያለማወቅ አግዝ ፤ ዕውቀትህ ባላወቁት ላይ እንድትኮራና እንድትፈርድ አያድርግህ የአዋቂ ኩሩ ቁጥሩ ካላዋቂዎች ነውና ማወቅ ባለዕዳነት እንዳይሆን አላዋቂዎችን እርዳቸው ።

ዛሬ የመዝራት ዘመንህ ነገ መከርህ ነውና በእምነት እውነትን ዝራ ፤ በምታውቀው ቦታ ላይ አገልጋይ በማታውቀው መልካም ተግባር ላይ ደጀን ሁን ፤ በቦታህ መምህር ያለቦታህ ተማሪ ሁን ፤ ክብሩ እንዳይቀንስብህ ከዕቃ ትምክህት ፣ ከዕውቀት ሙግት ራቅ ።

ሁሉን ወሬ ላውራ አትበል ፣ የደበቁህን ምስጢር አታውጣጣ ፣ የሰማኽውን ወሬና የተገለጠልህን ምስጢር ምን መፍትሔ ሰጠኸውና ? ያየህውን ሥራ ሁሉ እሰራለሁ የሰማኸውን ትምህርት ሁሉ እማራለሁ አትበል ። ይህ የተሰወረው የቅንዓት ጠባይ ነውና ። ሁሉን ልያዝ ማለትም ዝንጉ አድረጎ እንዳያስቀርህ ሁሉም ውስጥ ልኑር አትበል ።

ቂም አፍን የሚያመር ፣ ልብን የሚያነቅዝ ፣ ተግባርን የሚያልፈሰፍስ ነውና ለበደለህ ሰው ቅያሜህን ግለጥለት ፤ ቂመኝነት በክፉ መሸነፍ እንጂ ጀግንነት አይምሰልህ ።

ከህሊናህና ከመንፈሳዊ አማካሪህ ሳትመክር ምንም ነገር አትወስን ፤ አጥርተህ ሳትሰማ ቃል አትግባ ። መከራ ካልደረሰ በቀር ባል በሌለበት ቤት ውስጥ ከሚስቲቱ ጋር ብቻህን አትቀመጥ ።
:
የሚበልጥህ ልኩራብህ እንዳይልህ ፣ ያነሰህ ልድረስብህ ብሎ እንዳያጠፋህ የሀብትህን ልክ እንዳታወራ ፤ በገዛ አፍህ ባንዱ ትከብራለህ ባንዱ ትቀላለህና።

በጣም በማክበርህ እንዳታመልከው ፤ በጣም በመናቅህ እንዳታዋርደው ሠው እንዳንተ መሆኑን እወቀው ።

የእኔ መናገር ምን ይለውጣል? ብለህም ስህተትን አትለፍ ፤ የእኔ አስተዋፅኦ ምን ይጠቅማል ? ብለህም ስጦታህን አትጠፍ ።

መልካም ቃል ከስጦታ ይበልጣልና መልካም ቃል ተናገር ፤ ማንኛውም ስጦታ ከልመና ወንበር አያስነሣም ። የተስፋ ቃል ግን እንደሚያስነሣ አውቀህ ለሰዎች የተስፋ ቃል ስጣቸው ።

ትምህርት ለዕውቀት ያዘጋጃል እንጂ ዕውቀትን አይጨርስም ። ዕውቀትህን የምትይዝበትን ሥነ-ሥርዓት ግን ያሳይሃል ። አእምሮህን ለማረቅ ትምህርት ፣ ሰውነትህን ለመግዛት ትዕግስት ፣ ከማንም ጋር ለመኖር ሥነ-ሥርዓት ያስፈልግሃል ። ለህሊናህ እረፍት ግን እምነት ያሻሃል ። ተከታይ ለማበጀት ደግሞ ግልጽ መሆንና ታማኝነት ግድ ይልሃል ።

አንተው እውነትን ጠልተሃት ዘመኑ እውነትን ጠልቷል አትበል ። ዘመን እኔና አንተ ነን ፤ በራሱ ክፉና ደግ የሆነ ዘመን የለም።

መልካም ምክር ብትሰማ ሕይወት ቀላል ይሆንልሃል ። ትክክለኛም ውሳኔ ከመልካም ምክር ነውና..!!
"መንጋው ስሜታዊ እንጂ ምክንያታዊ አይደለም "
:
ከ"አልገባኝም መጽሐፉ የተወሰደ በዚህ አጋጣሚ እንድታነቡት ጋበዝኳችሁ!!!
:
"ምን አይነት መጽሐፍ ቢያነቡ ይመከራል ?" የዳግም ጥያቄ ነበር በአንድ በኩል ብቻ የተሳለ ሰይፍ ባይሆን ይመረጣል ታሪክ ፣ ፍልስፍና ፣ ግለ ታሪክ ፣ ጥናታዊ ስራዎች ፣ ልብ ወለድ ፣ ግጥም . . . ሌላንም ቢያነብ ቢያጣጥም መታደል ነው ።
:
ከዚህ ጋር ተያይዞ ምን ትዝ አለኝ ? እዚህ አገር እስከ ቅርብ ጊዜያት ድረስ መጽሐፍ ይዞ መታየት በተለይ የፍልስፍና ይዘት ያላቸው መጽሐፍትን ማንበብ ከወፈፌነት ከኢ- አማኝነት ጋር የማያያዝ ልማድ ነበር። አሁን አሁን አንዳንድ ሰዎች ጋር ይህ አመለካከት አይጠፋም። ኢ- አማኝ መሆን ፍልስፍና መጽሀፍትን ማንበብ ፣ ሲልም ፍልስፍናን እንደ አንድ ዘርፍ ወስዶ ማጥናት ምን አይነት ምክንያታዊ ግንኙነት የለም። በዚህ ዙሪያ ሰዎች የሚጠቅሷቸው እንደ #ኦሾ#ራምፖ#ፍሮይድ#ኒቼ . . .ዓይነት መጽሐፍት አሉ።

በመጽሐፍ ደረጃ ፍሮይድ የጻፈው ' the future of an illusion' የሚለውን መጽሐፍ አንብቤ "ከሃይማኖት ጋር ፍቺ ፈጽሜያለሁ " ባለው ሰው ላይ ሰዎች ሲነጋገሩ ሰምቻለሁ። ነገሩ አዲስ አይደለም ። ኢ- አማኝ የሆንኩት 'እንዲህ አይነት ' መጽሐፍ አንብቤ ነው ማለት ተለምዷል። በእርግጥ እያንዳንዱ ሰው ያሻውን የማለት መብት አለው። አንድ መጽሐፍ አንብበን ኢ-አማኝ እንሆናለን ብለን እየተቀባበልን ያንኑ መጽሐፍ በተራ ብናነብ የሚፈጠር ነገር የለም ።
አፍላጦን "መንጋው ስሜታዊ እንጂ ምክንያታዊ አይደለም " ለምሳሌ እንደ አንድ አንባቢ መጽሐፉን አንብቤዋለሁ ። ነገር ግን እሱን መጽሐፍ አንብቤ ኢ-አማኝ አልሆንኩም።
*
#አልገባኝም
#ዮናስ ዘውዴ ከበደ
ለጋስነት እውነተኛ ሃብታምነት ነው። እናም ለጋስ ለመሆን እና ለማካፈል ብዙ ነገሮች ሊኖራችሁ አያስፈልግም። ለጋስ ለመሆን ያላችሁን የትኛውንም ነገር ማካፈል አለባችሁ። ምናልባትም ብዙ ላይኖራችሁ ይችላል። ነገር ግን ያላችሁን በማካፈል ለጋስ መሆን ትችላላችሁ።
#OSHO/ኦሾ
#ሱፊዝም
በመጀመርያ ወላጆችህ ፣አስተማሪዎችህ፣ ጎረቤቶችህ፣ ህብረተሰቡ፣ አንተን እንደ አንተነትህ ተቀብለውህ አያውቁም።
ሁሉም አንተን ሌላ ስብዕና ይዘህ እንድትኖር እንደ አዲስ ያርሙሃል።ያንተ ራስህን መሆን መቻል ግን አይመሰገንም። ገና ወደፊት የምትመስለው ስብዕና ነው የሚመሰገነው።
Osho/ኦሾ
የኦሾ ቁልፍ መልዕክት
#የተነገራችሁን ሁሉ ቀጥታ እንደወረደ አምናችሁ አትቀበሉ ከዚያ ይልቅ እውነትን በብልሃትና በንቃት ለማግኘት ሞክሩ።
/Osho/
"በማንም ተጽእኖ ሥር አትውደቁ። አትመሰጡባቸው።
ማንንም አትከተሉ። ከማንነታችሁ መንገድ ልታፈነግጡ ትችላላችሁና።"
*
#ኦሾ/Osho
አንተ ትክክል መሆን አለመሆንህን ለማወቅ
የህሊናህ እና የድርጊትህ እንጂ የሌሎች ሰዎች
ድጋፍና ምስክርነት አያሻህም ። ትክክለኛውን
እንጂ አብዛኛውን ለመሆን አልተፈጠርክም።
ትክክል ባትሆን እንኳን መቶ በመቶ የሌላ ሰው
ቅጂ አትሁን።"
#ኦሾ/Osho
#ውስጣዊ ማንነቱ የተከፋፈለ ግለሰብ በአብሮነት የማይስማማ ማህበረሰብን ይፈጥራል፤ንቃተ-ህሊና ያለው ግለሰብ ያልተከፋፈለ ውስጣዊ ማንነት ሲኖረው የተዋሃደ ማህበረሰብንም ይፈጥራል።ንቃት የሌለው ማንነት ለዘላለማዊ ሙት ነውና
ንቁ!!!!**
#Osho/ኦሾ .
የመኖር አካል ሁን ለመኖር የወደፊቱን የገና ለገና ውጥን አትጠብቅ ወይም ወደ ኃላ በትዝታ ምናብ አትጓዝ ህይወት ወደ ፊትም ወደ ኃላም አትጓዝም አዕምሮ እንጂ ህይወት አሁን ናት!!
OSHO/ኦሾ
"አንዳንድ ጊዜ ብዙም ማህበራዊ መስተጋብር የሌላቸው ከሰው መሀል ወጥተው ዳር የሚይዙ ሰዎች ማህበራዊ ኑሮ የሚጠሉ አይደለም ፤ ከዚህ ይልቅ የውሸት ድራማን ፣ ድድብናንና አስመሳይነትን መቋቋም ስለሚከብዳቸው ነው።"

#Osho /ኦሾ
የመጀመርያው እና ከሁሉ የሚቀድመው የገዛ ራስን ማፍቀር ነው። ልባችሁ የሳሳ እንጂ ልበ- ደንዳኖች አትሁኑ። ለገዛ ራሳችሁ ግድ ይኑራችሁ።
እንዴት ለራሳችሁ ይቅርታ እንደምታደርጉለት እወቁ። ጨካኞች አትሁኑ ፤ ራሳችሁን አትቃረኑ። የዚያን ጊዜ እንደ አበባ ትፈካላችሁ።
ህያውነት 2
Osho/ኦሾ
የኦሾ ቁልፍ መልዕክት
#የተነገራችሁን ሁሉ ቀጥታ እንደወረደ አምናችሁ አትቀበሉ ከዚያ ይልቅ እውነትን በብልሃትና በንቃት ለማግኘት ሞክሩ።
/Osho/