#ለፈገግታ
******
እድለኛ ከሆንክ ታገባለህ ...ማግባት እድል ይጠይቃል ….በጣም እድለኛ ከሆንክ ጥሩ ሴት ታገባለህ … ጥሩ ሴት ማግባት እንዴት ሰላም አለው መሰለህ …እጅግ በጣም እድለኛ ከሆንክ ያፈቀርካትን ሴት ታገባለህ … ፍቅር የትኛውንም ጉድለት ይሸፍናል የትም ብትሄድ ካፈቀርካት ሴት አታመልጥም ….እጅግ እጅግ በጣም እድለኛ ከሆንክ የምታውቃትን ሴት ታገባለህ … አውቀህ ገብተህበታል ምንም ቢፈጠር አይመለከተንም !! እዛው ተወጣው!
:
#/አሌክስ አብርሃም /

<<የሌሎችን ድጋፍ የሚሹት የሌሎችን አመለካከት የያዙ ብቻ ናቸው>>
👇
(ኦሾ)
በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ አንድ ሰው ከሌላ ሰው ጋር በፍፁም ተመሳሳይ የሆነ ተግባር እንዲፈፅም ይጠበቅበታል። ሰዎች ትንሽ ለየት ያለ ነገር ሲያደርጉ ከመቅፅበት ለማህበረሰቡ እንግዳ እንደሆኑ ተደርገው ይታያሉ። ሰዎች ደግሞ እንግዳ የሆነ ተግባር የሚፈፅሙ ሌሎች ሰዎችን በጣም ይፈራሉ።
ለዚህም ነው ሁለት ሰዎች አውቶብስ ወይም ባቡር ውስጥ አልያም ፌርማታ ላይ ሲገናኙ ዝም ብለው መቀመጥ የማይችሉት። ምክንያቱም ሁለቱም እንግዶች ናቸው። በመሆኑም ብዙም ሳይቆዩ ይተዋወቃሉ። ስምህን ማንልበል?
ወዴት ነው ምትሄደው?
ስራህስ ምንድነው? ይባባላሉ። በዙህ መልኩ ጥቂት መረጃዎችን ከተለዋወጡ በኋላ ይረጋጋሉ። አንዳቸው እንደሌላኛው ሁሉ የሰው ልጅ ናቸው ለካ!
ሰዎች ያለማቋረጥ በማይመጥኑት ህዝብ መሀል መሆንን ይፈልጋሉ።ለየት ያለ ተግባር ስትፈፅሙ ወዲያውኑ መላው ህዝብ ይጠራጠራችሁና ነገሮች ይበላሻሉ። ከዚያ ግን ያወቋችሁ ለውጡን ለማየት ይችላሉ። እራሳችሁን በፍፁም የማትቀበሉ ሰዎች ሆናችሁ መቆየታችሁን ያውቃሉ። እናም አሁን በድንገት እራሳችሁን ስትቀበሉት ያያሉ።
በማህበረሰባችን ውስጥ ማንም ቢሆን የገዛ ራሱን አይቀበልም። ሁሉም የገዛ ራሱን ይኮንናል።ራስን መኮነን የህዝብ የአኗኗር ዘዬ ነው። ራሳችሁን መቀበል ስትጀምሩ ደግሞ ከማህበረሰቡ ውስጥ ወጥታችኋል። ማህበረሰቡ ደግሞ ከማዕቀፉ የወጣን ማንንም ሰው ታግሶ የመጠበቅ ልማድ የለውም። ምክንያቱም ማህበረሰቡ የሚኖረው ቁጥሮችን ቁጥሮችን መሰረት አድርጎ ነው። ይሄ ደግሞ የቁጥሮች ፖለቲካዊ አስተሳሰብ ነው። ሰዎች ብዙ ቁጥሮች ሲኖሩ ጥሩ ስሜት ይሰማቸዋል። በርካታ ቁጥሮች ሰዎችን ትክክል እንደሆኑ አድርገው እንዲያስቡ ያደርጓቸዋል። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ደጋፊዎች ስላሏቸው ሊሳሳቱ አይችሉም። ብቻቸውን ሲተው ግን ትልቅ ጥርጣሬ መቀስቀስ ይጀምራል። ከእነሱ ጋር ማንም ሰው የለምና ትክክል ለመሆናቸው መተማመኛው ምንድነው?
ለዚህም ነው በዚህ ዓለም አንድ ግለሰብ መሆን ታላቅ ድፍረት እንደሆን የምናገረዉ
አንድ ግለሰብ ለመሆን ከሁሉ የላቀ ድፍረት የተሞላበት መሰረት ያስፈልጋል።
<<መላው አለም እኔን መቃወሙ አያስጨንቀኝም። ዋናው ነገር ተሞክሮዬ ተቀባይነትን ማግኘቱ ነው። ምን ያህል ሰዎች ከኔ ጋር እንደሆኑ ለማወቅ ቁጥራቸውን አልመለከትም። ትኩረት የማደርገው በተሞክሮዬ ተቀባይነት _ የሌላ ሰው ቃላትን እንደበቀቀን እየደገምኩ መሆን አለመሆኔን ወይም የምናገራቸው ነገሮች ከገዛ ራሴ የመነጩ መሆን አለመሆናቸው ላይ ነው። ንግግሬ በገዜ ራሴ ተሞክሮ ውስጥ ከሆነ፤ የደሜ፣ የአጥንቴና የመቅኔዬ አካል ከሆነ፣ መላው አለም በአንድ ወገን ሊሆን ቢችል እንኳን፣እኔ ትክክል ነኝ። እነሱ ግን ተሳስተዋል። ምንም የሚያስጨንቅ ነገር የለም። እኔ ትክክል መሆኔ እችዲሰማኝ የእነሱ የድጋፍ ድምፅ አያስፈልገኝም። የሌሎችን ድጋፍ የሚሹት የሌሎችን አመለካከት የያዙት ብቻ ናቸው>> ብሎ ማሰብ የግድ ይሆናል።

🎎
"ዓለም በሙሉ በብርሃን ልትጥለቀለቅ ትችላለች፣ ውስጥህ ግን አሁንም በጨለማ እየኖረ ነው። ከውልደትህ በኃላ የተጨመረልህ ነገር ሁሉ እውነተኛ ማንነትህ ያለመሆኑን ቀስ በቀስ የሚያሳይህ ጭላንጭል ብርሃን በውስጥህ ሳይኖር በብርሃን የተሞላ ዓለም ምን ይጠቅምሀል?"
' ' '
OSHO ኦሾ
#ነፃነት/
ራስን የመሆን ድፍረት

#በሁሉም ነገር አዲስ መንገድ ፈልጉ ።በየዕለቱ አዲስ ነገር መፈለጋችሁን ስትቀጥሉ ህይወታችሁ አንጠልጣይ፣አስደናቂ ይሆናል።አይሰለቻችሁም። የሚሰላች ሰው እምነት የሌለው ነው።አንድ ነገር ለማውቅ ሁልጊዜ ጉጉ ሁኑ።ሁልጊዜ ከማወቅ ከመመርመር ከማግኘት ፣ከመፈለግ ጫፍ ስትደርሱ ንቃታችሁ ይበሉጡን ይጨምራል ።
ኦሾ/Osho(አካለ አዕምሮ)
ኦሾ/Osho(አካለ አዕምሮ)
#ለዕለተ ቅዳሜያችን
ስንቃርም ያገኘነውን ከኦሾ እይታዎች ጥቂት ወደ እናንተ እንበትን ዘንድ የተጋባ ሆኖ አገኘነው!!
*
#ገንዘብተኝነትን አውግዙ ፤ ገንዘብን ግን አትጥሉ በሰለጠነው አለም ገንዘብና ሀብት የግድ የሚያስፈልግ የኑሮ #መስተጋብሮች ናቸውና። ያለ ሀብትና ገንዘብ ሳይንስና ቴክኖሎጂ አይሰምርም ፣ የሰው ልጅ የደረሰባቸው የእድገት ደረጃዎች ያለ ነዋይ አይሳካም ነበር ።
#በዘመነች አለም ህይወት ያለ ገንዘብ ዲዳ ትሆናለች ! ገንዘብን ተጠቀሙበት ፤ ነገር ግን ገንዘብ ላይ አትጣበቁ ። ገንዘብ ላይ ሙጭጭ ባላችሁ ቁጥር በእናንተ "ሙጭጭ" ማለት የተነሳ አለም የበለጠ #ትደኸያለች ። ገንዘብተኛ ማለት ከፈረሱ የቀደመ ጋሪ ማለት ሲሆን ትርፉ ከሰብአዊነት አፈንግጠው በሰዎች ዘንድ መጠላት ነው ።
ኦሾ/Osho

ቢጨልፉት ከማያልቀው ከኦሾ የፍልስፍና እይታዎች ቆንጥረን ወደ እናንተ እንካችሁ አለን !
በደስታችሁ በሀዘናችሁ በእንቅስቃሴያችሁ እውነተኛ ከሆናችሁ ዉሎ አድሮ ሀሳባችሁን የሚረዳላችሁ በእናንተ መንገድ የሚጓዙ ሰዎች ማግኘታችሁ የማይቀር ነው የሚለን ህንዳዊው የፍልስፍና ሰው ኦሾ እኔ ራሴ መንገዱን ስጀምረው ብቻዬን ነበርኩ ዛሬ ግን መንገዴን የሚከተሉ ሰዎች በዝተዋል ከዛም በዘለለ ጉዞዬ አለማቀፋዊ ሆኗል ይለናል። በርግጥ በብቸኝነት መንገዴ እኔ ማንንም ወደ መንገዱ አልጋበዝኩም ነገር ግን ልቤ የፈቀደውን ከማድረግ ወደ ኃላ አላልኩም፡፡
የእኔ ሀላፊነት የልቤን እንጅ በዓለም የሚኖርን የማንንም ትዕዛዝ ማድመጥ አይደለም፡፡
በርግጥም አበክሬ የምነግራችሁ ነገር " ራሳችሁን አትቃወሙ ራስን መቃወም ራስን እንደ ማጥፋት ነውና፡፡ራሣችሁንና ማንነታችሁን ስታከብሩና ስትቀበሉ ሰዎች በፍቅር ይቀበሏችሗል፡፡
የእናንተ ሀላፊነት ሊሆን የሚገባው ራሳችሁን ማድመጥና በራሳችሁ መተማመን ነው፡፡
የዚያኔ አለም ሁለት እጆቻን ዘርግታ በፍቅር ትቀበላችሃለች፡፡
#ኦሾ/Osho

#አንዲት ሴት ቆንጆ ስለሆነች ብቻ የምትወዷት ከሆነ ፍቅራችሁ እውነተኛ ፍቅር አይደለም። ነገ ያቺ ያፈቀራችሃት ሴት ታረጅና ፣ ድንገት ትታመምና አስቀያሚ ልትሆን ትችላለች። ምናልባትም አፍንጫዋ ላይ ቀዶ ጥገና ይደረግላት ይሆናል።
ያን ጊዜ ፍቅራችሁን ምን ይውጠዋል? ፍቅር ውስጥ ያስገባችሁ ውቧ አፍንጫዋ ነበር። አሁን ያ አፍንጫዋ የለምና ፍቅራችሁም ይጠፋል። ሴትዬዋ ሸክም ትሆንባችኋለች።
በምክንያት ባልተሞላ ልብ የሚመጣው ፍቅር ግን በነገሮች ላይ ጥገኛ አይደለም። ይህን ፍቅር ከሰውዬው ውበት ወይም እውቀት ወይም ተሰጥኦ ጋር የሚያገናኘው ምንም ነገር አይኖረውም።
በፍቅር ትምሉና ያን ፍቅር ማካፈል ትፈልጋላችሁ። እናም ለመቀበል ዝግጁ ለሆነው ሁሉ አመስግናችሁ ትሰጡታላችሁ። ስጦታ ነው የምትሰጡት ስለ ሞላችሁ ስለተረፋችሁ ነው።
#ኦሾ /Osho

30 seconds read: A story by Khalil Gibran
(በግሩም ተበጀ)
——
በአእምሮ ሕሙማን ሆስፒታሉ የአትክልት ሥፍራ ስዘዋወር የፍልስፍና መፅሐፍ የሚያነብ አንድ ወጣት አገኘሁ…
ባህሪውና ጤነኛ ገፅታው ከሌሎቹ ሕሙማን ለየት ማለቱን ያሳብቃል፡፡
አጠገቡ ሄጄ ተቀመጥኩና፣ “እዚህ ምን ትሰራለህ ?” ስል ጠየቅኩት፡፡
በጣም ተገርሞ ትክ ብሎ ካየኝ በኋላ ከዶክተሮቹ አንዱ አለመሆኔን ሲረዳ እንዲህ ሲል መለሰልኝ፣
“ይኸውልህ ነገሩ እንዲህ ነው … የታወቀ ጠበቃ የሆነው አባቴ እንደ እሱ እንድሆን ይፈልጋል፡፡ ግዙፍ የገበያ አዳራሽ ያለው ሐብታሙ አጎቴ በፋንታው የእሱን ፈለግ እንድከተል ይሻል፡፡ እናቴ ደግሞ እንደምትወደው አባቷን እንድሆን ትፈልጋለች፡፡ እህቴ በበኩሏ የስኬት ሚዛን ማለት ባሌ ነው ከማለት አትቦዝንም፡፡ ወንድሜ ደግሞ እንደ እርሱ ምርጥ አትሌት እንድሆን ይጥራል…
በትምህርት ቤትም ይኼው ነው፡፡ የሙዚቃ እና የእንግሊዝኛ መምህሮቼ በየፊናቸው እኔን ምሰል፣ እኔም ተከተል ይሉኛል፡፡ ሁሉም አንድ ሰው ሌላኛውን እንደሚያየው ሳይሆን ራሳቸውን መስታወት ውስጥ እያዩ እንዳሉ ያህል ነው የሚያዩኝ፡፡
ስለዚህም እዚህ የአእምሮ ሕሙማን ማዕከል ገባሁ፡፡ ቢያንስ ቢያንስ እዚህ ራሴን መሆን እችላለሁ”

ወንጀለኛው
(ካህሊል ጂብራን)
አንድ በርሀብ የተጎዳ፣ ፈርጣማ ሰውነት ያለው ወጣት በእግረኛ መንገድ ላይ ተቀምጦ እጆቹን በመዘርጋት ረሃብና ሃፍረት እየሸነቆጡት በሚያሳዝን ዜማ ይለምናል። ምሽት ላይ ከናፍሮቹ እና ጉሮሮው ደረቁበት። እጁ ግን እንደሆዱ ባዶ ነበር። ከተቀመጠበት ተነስቶ ከከተማ ወጣና በአንድ የዛፍ ጥላ ስር ተቀምጦ በምሬት ያነባ ጀመር። ከዚያም ረሃብ ውስጡን እየሞረሞረው ግራ የተጋቡ አይኖቹን ወደ ሰማይ ላካቸውና እንዲህ አለ፤ <<ጌታዬ ሆይ፣ ወደ አንድ ሃብታም ሄጄ ስራ እንዲሰጠኝ ጠየቅሁት። እሱ ግን ቡትቶዬን አይቶ ፊቱን አዞረብኝ። የአንድ ትምህርት ቤት በር አንኳኳሁ፣ ግን ባዶ እጄን ነበርና ችላ ተባልኩ። ቁራሽ ዳቦ የሚያስገኝልን የትኛውንም አይነት ስረ ሞከርኩ፣ ይሄ ሁሉ ግን ከንቱ ነበር። ተስፋ በመቁረጥ እንዲመፀውቱኝ ለመንኩ፣ መፅዋቾቹ ግን ተመለከቱኝና "ጠንካራና ሰነፍ ነው፤ መለመን አልነበረበትም" አሉኝ... "ጌታዬ ሆይ፣ እናቴ የወለደችኝ በአንተ ፍቃድ ነው። አሁን መጨረሻው ከመድረሱ በፊት ምድር ወደ አንተ እንድመለስ ፈቅዳልኛለች።"
፧
ይሄን ጊዜ ፊቱ ተለዋወጠ። ብድግ አለና አይኖቹን በቁርጠኝነት አጉረጠረጣቸው። ከአንዱ የዛፍ ቅርንጫፍ ወፍራም አርጩሜ ቆርጦ ወደ ከተማዋ በመቀሰር ጮኾ ተናገረ። <<ያለኝን ድምፅ ሁሉ አጠራቅሜ ዳቦ ስጡኝ ብያችሁ ነበር። እናንተ ግን ችላ አላችሁኝ። አሁን በጉልበቴ አገኘዋለሁ! በፍቅር እና በርህራሄ ስም ለምኜያችኋለሁ፤ ስብዕና ግን ዋጋ አልነበረውም። አሁን በርኩስ መንፈስ ስም አገኘዋለሁ!"
ዓመታት ሲያልፉ ወጣቱ ዘራፊ፣ ነፍሰ-ገዳይ እና የነፍስ አጥፊ ሆነ፣ የተቃወሙትን ሁሉ ያጠፋል፤ ጉልበቱን በመጠቀም ብዙ ሃብት ሰበሰበ። ከግብረ-አበሮቹ አድናቆትን አገኘ፣ በሌሎች ሌቦች ተከበረ፣ በህዝቡ ዘንድ ደግሞ ተፈሪ ሆነ።
ሃብቱና በጉልበቱ ያገኘው ተፈሪነቱ፣ አሚሩ የከተማዋ ባለስልጣን አድርጎ እንዲሾመው አበቃው- ብልህነት የጎደላቸው አገረ-ገዢዎች አሳዛኝ ሥራ። ከዚያ በኋላ ስርቆት ህጋዊ ስራ ሆነ፤ ጭቆና በስልጣን ይደገፍ ጀመር፤ ደካሞችን ማጥፋት የተለመደ ተግባር ሆነ እናም ዙፋኖች ይፈሩና ይከበሩ ጀመር።
#ስለዚህ ስግብግብነት ነካ ያደረገው ስብዕና አይናፋሮችን ወንጀለኛ፣ ሰላማዊ ሰዎችን ደግሞ ነፍሰ-ገዳይ ያደርጋል፤ ስግብግብነት የጎበኘው ስብዕና ያድግና መልሶ ስብዕናን አንድ ሺ እጥፍ ጊዜ ያጠፋዋል!
፨፨፨
ምንጭ ፦ እንባ እና ሳቅ(Tears and Laughter)
ደራሲ ፦ ካህሊል ጂብራን
ትርጉም ፦ ተስፋሁን ምትኩ

“የሚያፈቅር አዕምሮ እንጅ ልብ አይደለም ”
ቴዎድሮስ፡- ቀለል ያለ ጥያቄ ላንሳ፡፡ በልማድ “እገሊትን ከልቤ አፈቅራታለሁ” “እገሌን ከልቤ ጠላሁት” እንላለን፡፡ እንደ ልብ ስፔሻሊስትነትዎ ይህን አባባል እንዴት ያዩታል? ልብ ከመውደድና መጥላት ጋር የሚገናኝ ተግባር አለው?
...
ዶ/ር በላይ፡- (ፈገግ ብለው) እሱማ “ከልብህ ካሰብክ …” ይባላል፡፡ የሚታሰበው ግን በልብ ሳይሆን በአንጎል ነው፡፡ ቀይ ልብ ስታይ የፍቅር ልብ ስታይ “የፍቅር ልብ” (Valantine heart) ትለዋለህ፡፡ ይህ አባባል በመላው ዓለም በዘልማድ የሚባል ነው፡፡ ልብ “ፓምፕ” ነው፡፡ ማሰብ አይችልም፡፡ ገና በእናታችን ማህፀን ሆነን እናቶች የወር ተኩል ነፍሰ ጡር ሆነው ጀምሮ ሌላ የሰውነት ቅርፅ በወጉ ሳይኖረን ልባችን መምታት ይጀራምል፡፡ ስትሞት ልብህ መስራቱን ካላቆመ (ሁሉም አካልህ ሞቶ) “ሞተ” አትባልም፡፡ ይህ ጉዳይ በመላው ዓለም ክርክር የሚያስነሳ ነው፡፡ እስከ ፍርድ ቤት የደረሱ ጉዳዮችም አሉ፡፡ በትክክለኛው አገላለጽ ልቡ ሳይሞት አዕምሮው ከሞተ ሰውየው ሞቷል፡፡፡ ነገር ግን የሀኪሙን ማረጋገጫ ለማግኘት ልብ ሥራውን ማቆም አለበት፡፡ ጥያቄውን ለማጠቃለል ልብ ከማፍቀር፣ ከመጥላት፣ ከማሰብ ጋር የሚገናኝ ነገር የለውም፡፡
ቴዎድሮስ፡- ዘፈኖቻችን ሁሉ “ልቤ፣ ልቤ” ነው የሚሉት፡፡ እርስዎ ሲሰሟቸው ምን ይላሉ?
ዶ/ር በላይ፡- ይህ ከሰው ልጅ መፈጠር ጀምሮ በዘልማድ የሚነገር፤ ነገር ግን ምንም ሳይንሳዊ መሰረት የሌለው አባባል ነው፡፡ ለልብ የተሰጠው ገለጻ በሙሉ ለአንጎል መሰጠት ያለበት ነው፡፡ ምክንያቱም አንጎል ነው የሚወደው፤ የሚጠላው፤ የሚያስበው፤ የሚራራው፤ የሚጨክነው፡፡ ልብ አይደለም፡፡
ቴዎድሮስ፡- በእግዚአብሔር መኖር ያምናሉ?
ዶ/ር በላይ፡- አዎን፡፡ ማን አለኝ?
ቴዎድሮስ፡- ማንም ስለሌለዎት ነው ወይስ የእርሱ በእርግጥም መኖር ነው እንዲያምኑ ያደረግዎት?
ዶ/ር በላይ፡- እግዚአብሔር አለ፡፡ በእግዚአብሔር አምናለሁ፡፡ ለዚህ ደግሞ ምንም ተጨማሪ መረጃ አያስፈልገኝም፡፡
ቴዎድሮስ፡- የአንድ ኃይማኖት ተከታይ መሆን በእግዚአብሔር ለማመን ይረዳዎታል?
ዶ/ር በላይ፡- በእግዚአብሔር ለማመን ምንም አያስፈልገኝም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስም፤ ቁርዓንም አያስፈልጉኝም፡፡ እነዚህ መጻሕፍት ምን ያስተምሩኛል? ከግራ ወደ ቀኝ፤ ከታች ወደ ላይ፤ ከቀኝ ወደ ግራ ብታነባቸው … አንዳንድ ጊዜ እንደውም ጥሩ የፍልስፍና መጻሕፍት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ከእናቴ የሰማሁትን አንድ አባባል አለ፡፡
“ጽድቅና ኩነኔ ቢኖርም ባይኖርም
ከክፋት ደግነት ሳይሻል አይቀርም”
ይህ አባባል ለእኔ ያለው ትርጉም ኃይማኖት ቢኖርም ባይኖርም፤ እግዚአብሔር ቢኖርም ባይኖርም፤ ጽድቅና ኩነኔ ቢኖርም ባይኖርም ከክፋት ደግነት መሻሉን የሚገልጽ ነው፡፡ እኔ ለእናቴ “እንኳንስ መጽሐፍ ቅዱስ ላነብ ይህም በዛብኝ” አልኳት፡፡ “ከክፋት ደግነት ይሻላል” ኡፍ! ይህ ቀለል አለኝ፡፡ ግን ደግሞ ሳስበው ይህም በዛብኝ፡፡ ቁርዓኑን ብታመጣው፤ መጽሐፍ ቅዱስን ብታገላብጠው የሚያስተምርህ ነገር ቢኖር ደግነትን ነው፡፡ ኃይማኖት ቢኖርህም ባይኖርህም ደግሞ ጥሩ ስሜት ይሰጥሀል፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር በሀዋርያት አርፎ በእነሱ የተጻፈ ነው፡፡ እግዚአብሔር እነሱን ለማስተማር ይሆናል የተናገረው፡፡ እርሱ ኃያል ነው፤ በሁሉም ስፍራ ይገኛል፡፡ ሁሉንም በአንድ ጊዜ ማድረግ የሚችል ከሆነ ለእኔ የሚበቃኝን አዕምሮዬ ውስጥ ያስገባልኛል፡፡
ስለዚህ በእግዚአብሔር አምናለሁ፡፡ ብዙም ጣጣ አታብዛብኝ፡፡
(ከቴዎድሮስ ተ/አረጋይ “ፍልስምና” መፅሃፍ ላይ ከዶ/ር በላይ አበጋዝ ጋር ከተደረገው ቃለምልልስ የተቀነጨበ)

ህይወት በትክክለኛው መንገድ ከተኖረ ሞት አይፈራም። የሚለን ኦሾ ህይወትን ከኖራችሁ ሞትን በፀጋ ትቀበላላችሁ ምክንያቱም እንደ እረፍት፣ እንደ እንቅልፍ ትመለከቱታላችሁና። ከህይወት ጫፍ መድረስ ከቻላችሁ ሞት ውብ እረፍት ፣ ብራኬ ይሆናል። በተቃራኒው ካልኖራችሁ ግን በርግጠኝነት ሞት ጊዜያችሁን ፣ የህይወት እድሎቻችሁን ይነጥቃችኋል። ካልኖራችሁ ነገ የሚባል ነገር የለም ፍርሃት ይነግሳል። ፍርሃቱ የሚመጣው በሞት ሳቢያ ሳይሆን በደንብ ህይወትን ባለመኖር ነው።"
#Osho/ኦሾ
#Osho/ኦሾ
የኛ እኮ የትም የሌለ እኮ ነው። መንገድ ዘግቶ ሆስፒታል አቃጥሎ አምፑላንሱ ትቶታል "አምፑላንሱን ለምን ተውከው" ይባላል "እናቶች ሲታመሙ ሊወልዱ ሲሉ በምን ይሄዳሉ"
ጥፋቶቻችን ጥፍሮቻችን ውስጥ የሚያስደብቁ ናቸው። ለነገሩ ጥፍሮቻችንም የዋላ ቂም በቀልዎቻችንን በማከክ ተጠምደው ለመደበቂያነትም አይሆኑም።
ለነገሩ ለመቃወም እራሱ እኮ በትክክል መቆም ያስፈልጋል ጎበዝ
ተስፋሁን ከበደ(ፍራሽ አዳሽ)

ምክረ ኮንፊሺየስ ፡-
:
"አለምን ሥርዓት ለማስያዝ በመጀመሪያ ሀገርን ሥርዓት ማስያዝ ያስፈልጋል ፤ ሀገርን ሥርዓት ለማስያዝ ደግሞ ቤተሰብን ሥርዓት ከማስያዝ ይጀምራል ፤ ቤተሰብን ሥርዓት ለማስያዝ የራስን ህይወት ሥርዓት ማስያዝ ይጠይቃል ፤ የራስን ህይወት ሥርዓት ለማስያዝ ደግሞ ልብን መግራት ያስፈልጋል፡፡ "ስለዚህም በኮንፊሺየስ አባባል የዓለም ነገር መነሻውና መጨረሻው ዞሮ ዞሮ ልባችን ነው፡፡ ልባችን ሥርዓት ሲያጣ ዓለም ላይ ይገለጣል እንደማለት ይሆናል፡፡ ለዚህም ነው "የሀገር ጥንካሬ ከቤተሰብ ብርታት ይጀምራል የሚለው"

"በሚያምሩና ጥሩ ሽታ ባላቸው ፅጌረዳዎች መሃል ቆመህ የአበቦቹ ጥሩ መአዛ ካልሸተተህ ችግሩ ከአፍንጫህ እንጂ ከአበቦቹ እንዳልሆነው ሁሉ አንዳንዴ ሰውን ስታስቀይምም ወደ ውስጥህ ተመልከት ፍልስፍናም አላማው ራስን ማየት ራስን መጠየቅ እራስን መመርመር ነውና ! ብዙ ራስህን ስትጠይቅ ብዙ አለማወቅህን ወደ ማወቅ ትመጣለህ ።"
ሱፊዝም
ሱፊዝም
'ድሮ ፖለቲካ አስተሳሰብ ነበር። ሃሳብ ደግሞ ሰው ሰራሽ ነው። አርቲፊሻል ነው። ስለአንድ ነገር ሃሳብ ከሌለህ የለህም። አይገባህም፣ ወይ ግድ የለህም።
==/
በአሁን ዘመን አተረጓጎም ግን ከፖለቲካ ጋር ተፈጥረሀል። አንተ ጎሳህን እንደ ሃሳብ አትመርጥም። ስለዚህ ገና ስትወለድ በሆነ ስልት ወገን ይዘሃል ማለት ነው። ሽል ፖለቲከኛ ሆኗል። ጡት የሚጠባ ልጅ ፖለቲከኛ ሆኗል።
==/
ባትፈልግም ወግነሃል፣ ማለት መወገንህን ሳታውቀው። ባትፈልግም ግድ ባይሰጥህም ሥልጣን ሽሚያ ተሰልፈሃል አሉ። አሁን ባዮሎጂ ሆኗል። እንደ ደርግ ጊዜ በቃኝ ብለህ እንኩዋን መሸሽ አትችልም። ከጥላህ እንደማምለጥ ነው።
==/
በሃሳብ ሳይሆን አሁን የምትገናኘው እንደ እንስሳት በጠረን ነው። ጠጋ ብለሽ ብብት እያሸተትሽ የአወላለዱን ካርታ ትፈልጊያለሽ።'
==/
"የስንብት ቀለማት" አዳም ረታ

➟የአንድ ዘመን የምድራችን ታላቅ አሳቢና ደፋር::
➟ከክርስቶስ በኋላ የተፈጠረ በጣም አደገኛ ሰው::
➟ከ20ኛው ክፍለ ዘመን ከ1000ቹ ታላላቅ ሰዎች መሀል አንዱ::
➟ከመላው አስቀያሚ ሰብዓዊነት ጋር አንድ ብቻውን ሆኖ ትግል የገጠመና አለምን ያናወጠ::
እነዚህ በተለያዩ ግዜ ስለ'ሱ ከተነገሩ አባባሎች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ በመንፈሳዊ ክህሎት የላቀ የአዕምሮ ባለቤት ለመሆን የበቃው ገና በ21 አመቱ ነበር፡፡ በዚህ የወጣትነት ዕድሜ ላይ መንፈሳዊ ብቃትን የተጎናፀፈ ግለሰብ እስካሁን እንዳልታየም ይነገራል:: ፍልስፍና ፒኤች ዲግሪ አግኝቷል፡፡ በተለያዩ የህንድ ዩኒቨርስቲ በመምህርነት አገልግሏል፡፡ ድፍረቱ የትየለሌ ነው::
በለየለት ድፍረቱ ያየውን የሰማውን ያነበበውን እውነት ነው ብሎ ያመነበትን ነገር ሁሉ አውጥቶ ይዘከዝከዋል፡፡ በንግግሮቹ ያልዳሰሰው ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ህይወት፣ ያላፈረጠው ባህላዊ ቁስለት ከቶም የለም፡፡ እምነትን፣ ባህልን፣ ሀይማኖትን፣ ጋብቻን፣ ወሲብን፣ ማህበራዊ፣ ስርዐተ ትምህርትን በሚገርም አሳማኝ ንግግሮቹ ያብጠለጥላቸዋል፡፡
"መላው አለም ከኔ በተቃራኒው ቢቆም እንኳን በውስጤ አንድም ጥርጣሬ አይፈጠርም ምክንያቱም የማውቀውን አውቃለሁ የሆንኩትን ሆኛለሁ!!” ይል ነበር:: እጅግ መሳጭ በሆነ የንግግር ጥበቡና በማስረጃ በተደገፈ የክርክር ዘይቤ አለምን ውድቅ ያደርግና የራሱን ብሩህ አዲስ የህይወት አቅጣጫ የሚለውን ያስተዋውቃል፡፡
ለየትኛውም እምነት፣ አስተሳሰብ፣ ባህልና ወግ ሐይማኖት ግድየለሽ እንዲያውም ፈፅሞ አላስፈላጊ ነው ባይ ሲሆን ከዚህ በላይ ግን ውስጣዊ ማንነትን ፍለጋ ላይ መድከም ብቸኛው የሰው ልጅ ከተያዘበት የባርነት ሰንሰለት የሚወጣበት መንገድ መሆኑን ደጋግሞ ይናገራል፡፡ መሰረታዊ ችግሩም ይህም ከግዜው ቀድሞ መምጣቱ እንደሆነ የሚዘግብም አልታጡም፡፡
በልጅነቱ ግዜ ከሌሎች የዕድሜ እኩዮች የሚለይበት በአንባቢነቱ ነበር፡፡ በአለም ላይ ያሉ በርካታ መፅሐፍትን ያነበበ ሰው መሆኑ ብዙዎች የሚስማሙበትና የሚመሰክርለት ነው፡፡ በፑና ማዕከልም ባለው የግል ላይብረሪው ውስጥ 100,000 በላይ የግል የመፃሕፍት ስብስቦች ነበሩት፡፡
ከ 600 በላይ መፃሕፍት ታትመውለታል፡፡7,000 ሰዐታት የሚፈጁ የኦዲዮቴፖች ንግግሮች አሉት፡፡ እነዚህም ለደቀመዛሙርቱ (ሳንያሲንስ) በጥያቄና መልስ ፕሮግራም የሰጠው የረጅም አመታት ትምህርቶች እንዲሁም በታላላቅ መድረኮች ላይ ያደረጋቸው ንግግሮች ተውጣጥተው የተፃፉ ናቸው፡፡
ስራዎቹ በመላ አለም በተለያዩ ቋንቋዎች እየተተረጎሙ እስካሁን በመሰራጨት ላይ ናቸው፡፡ “እኔ አንድም ተከታይ እንዲኖረኝ አልሻም ሌሎችን የምትከተሉ ከሆናችሁ ትጠፋላችሁ!!” እያለ ዘውትር ለተከታዮቹና ለአድናቂዎቹ የሚናገር ቢሆንም በአለም ዙሪያ አያሌ ተከታዮችንም አፍርቷል ለዚህም ተቀዳሚው ማስረጃ በአሜሪካ በአውሮፓ በእሲያ በህንድ የተቋቋሙት (Osho Commune International) የተሰኙት ማዕከላት ናቸው፡፡
ከሞተ በኋላ ህንድ ፑና ውስጥ ወደ አቋቋመው ማዕከልም በበርካታ አድናቂቹና ተከታዩቹ ከተለያዪ ሀገራት ወደ ስፍራው አሁንም ድረስ ይጓዛሉ፡፡ በማዕከሉም እራሱ የፈጠራቸው የተለያዩ የተመስጦ ዘዴዎችንም እንደትምህርት የሚሰጡበት ማዕከልም ሆኖል፡፡
የአለማችን ታላቅ አወዛጋቢ ሰው!! ህንድ ውስጥ ኩችዋይ በምትባል መንደር ዲሴንበር 11፣ 1931 ነው የተወለደው:፡ በቤተሰብ የወጣለት መጠሪያ ስሙ ቻንድር ዋሀን ጄይን ሲሆን በሁላ ላይ ስሙን ባግዋን ሸሪ ራጅኒሽ በሚል ቀይሮታል፡፡ አለም የሚያውቀውም “ኦሾ”በሚለው ስሙ ነው፡፡
ህንድ ፑና ውስጥ ጀንዋሪ 19 1990 በ 58 ዓመቱ ሲሞት የሞቱ መነሻ አሜሪካ ሀገር በነበረበት ግዜ በአሜሪካ የስለላ ድርጅት (CIA) ታሊየም በተባለ መድሀኒት መርዘውት እንደነበረና በሱ ህምም መነሻነት እንደሞተ ተከታዩች ያምናሉ፡፡ ክሮኒክ ፋቲግ ሲንድረም የተባለ የጤና ችግርም እንደነበረበትና ይህም በሽታው ለሞት እንዳበቃው የሚናገሩ ወገኖችም አሉ፡፡
Osho! Never born Never died only visited this planet earth between December 11, 1931to January 19, 1990 ተከታዮቹ እንዲህ ነው የሚያስብት

👉 አሉታዊ እሳቤዎች ፀረ መርዝ 👈
* ፍቅር እይታ ሁሉኑም ነገር ነው
* አሉታዊ እይታ ህይወትን ይመርዛል
* አሉታዊዎች ለሞት ልከኛ ናቸው
* ለህይወት ግን ስህተት
* ህይወት አዎንታ እሳቤ ትሻለች ትፋፋለችም ምክንያቱም ቅን እይታ ሰውን ደስተኛ ከማድረግ አልፎ ፈጣሪም ( creative ) ያደርገዋልና
--- አንዲት በእድሜ የገፋች ሴት ነበረች
እድሜዋ በጨመረ ቁጥር ይበልጥ ወጣትነት የሚሰማት ምክንያቱም ወጣትነት ከአመለካከት ጋር እንጂ ከእድሜ ጋር አይገናኝምና በእድሜና እድሜ በሚሰጠው ፀጋ ከወጣት በላይ ወጣት መሆን ይቻላል
አዛውንቷ ሁሉም እስቲገረምባት ደስተኛና በፈጠራ የተሞላች ነበረች
--- ሆኖም በህይወትሽ ውስጥ ጥቂት ደመናዎች መኖራቸው አልቀረም አላት አንድ ጎብኚ
--- ደመናዎች ? መለሰች
እርግጥ ነው እኮ ደመናዎች ባይኖሩ ኖሮማ የተባረኩት ጠብታዎች ከየት ይመጡ ነበረ
--- ችግሮች በሚገኙበት ሁኔታ ውስጥ ( ህይወት ያለ ችግር አትሰራም )
* ቀና አእምሮ ክንፎችን ያበቅላል
* ሌሎች ግን ምርኩዝ ይገዛሉ
* ክንፍ አብቅይንጂ
* ምርኩዝ አትልቀሚ
( ኦሾ )

".......በአንድ ልብ ውስጥ ፍቅር እና ጥላቻ በጋራ ሊኖሩ አይችሉም። እነዚህ ሁለት ነገሮች እንደ ሞትና ህይወት ተቃራኒዎች ናቸው። በአንድ ልብ ውስጥ በጋራ ሊኖሩ አይቻላቸውም። ታዲያ "ፍቅር" ብለን የምንጠራው ነገር ምንድነው?"
"አነስተኛ ጥላቻ በውስጣችን ሲኖር "ፍቅር" እንለዋለን፤ መጠኑ ከፍ ያለ ጥላቻን ደግሞ "ጥላቻ" ብለን እንጠረዋለን። ሁለቱም አነስተኛና ከፍተኛ የጥላቻ መጠኖች ናቸው። በዚህ ሁነት ውስጥ ባለ ልብ ውስጥ ፍቅር ከነጭራሹ የለም። ስህተቱ የሚፈጠረው በጥላቻው መጠኖች ሳቢያ ነው። ከመጠን ጋር በተያያዘ ቅዝቃዜና ሙቀት ሁለት የተለያዩ ነገሮች እንደሆኑ ታስቡ ይሆናል። ሁለት የተለያዩ ነገሮች አይደሉም። ሙቀትና ቅዝቃዜ የአንድን ነገር ደረጃዎች የሚያሳዩ ናቸው። የሙቀት መጠን ሲያንስ ቅዝቃዜ መሰማት ይጀምራል። የሙቀት መጠን ሲበዛ ደግሞ ሙቀት መሰማት ይጀምራል......"
".....ከኢጎ በመነጨ ፍቅር ከተፈቀራችሁ ከትንሽ ጊዜያት በኋላ በአፍቃሪ እጆች እንደታቀፋችሁ ሳይሆን በብረት ሰንሰለት እንደተጠፈራችሁ ይሰማችኋል። ከትንሽ ጊዜያት በኋላ ውብ ንግግሮችን ሲናገር፣ ውብ ዘፈኖችን ሲዘፍንላችሁ የነበረው ፍቅር፣ በውብ ዘፈኖቹና ንግግሮቹ ውስጥ መርዝ ደብቆ እንደነበር ታውቃላችሁ። የአበቦችን መልክ ተላብሶ የሚመጣው ፍቅር ምንጩ ኢጎ ከሆነ አበቦችን በዳሰሳችሁ ጊዜ እጆቻችሁን የሚወጉ እሾሆችን ታገኛላችሁ......"

አንስታይን የአንፃራዊነትን ንድፈ ሃሳብ ካረቀቀ በኋላ መቶ ፊዚስቶች ተሰብስበው የአንስታይንን ሃሳብ የሚቃረን አንድ መጽሐፍ አሳተሙ። አንስታይን ሲሰማ እንዲህ አለ፦
"ለምን መቶ ሁሉ?! አንፃራዊነት ስህተት ከሆነ ለማረም አንድ ፊዚስት ብቻ ይበቃ ነበር!"
መንጋ ሲሰባሰብ ሃይል ያገኛል። ሁሌም ከመንጋው ጋር ሳይሆን ከእውነት ጋር ለመቆም የአላማ ፅናትን ይጠይቃል። እነዛ 100 ፊዚስቶች አሁን የሉም። የአንስታይን ንድፈሃሳብ ግን አሁንም አለ፤ ወደፊትም ይኖራል‼

ንስርን ለመጥለፍ የምትሯሯጥ የወፍ ዝርያ አሞራ ብቻ ናት ። አሞራዋ ጀርባው ላይ ተቀምጣ ንስሩን አንገቱን ትነክሰዋለች ። ነገር ግን ምላሽ አይሰጥም ወይም ከአሞራ ጋር አይጣላም ፤ጊዜ ወይም ጉልበት ከአሞራው ጋር አያባክንም። ግን ክንፎቹን ዘርግቶ ሰማይ ላይ ከፍ ብሎ መብረር ይጀምራል ። በረራዉ ከፍ ሲል ለመተንፈስ ይቸገራል እናም አሞራው በኦክስጅን እጥረት ምክንያት ይወድቃል።
መልስ መስጠት ያለባቹ ለሁሉም ውጊያዎች ፣ለሁሉም ክርክር ወይም ትችቶች አይደለም። ዝም ብላቹ ከፍታቹን ጨምሩ ፍጥነታቹን መቋቋም ሲያቅታቸው ይወድቃሉ። ከ አሞራዎች ጋር ጊዜ ማባከናችሁን አቁሙ። በቃ ወደ ከፍታቹ ውሰዱአቸው እና ይሸሻሉ። በአላስፈላጊና በትንንሽ ነገሮች ላይ ጊዜና ጉልበታችሁን ማባከናችሁን ካላቆማቹ በአስፈላጊ ነገሮች ላይ ሀይላቹን ታጣላቹ ፤ ጊዜያቹንም እንደዛው። ጠላት ጀርባህ ላይ ተቀምጦ አንገታቹ ሊደፋ ይችላል... ነገር ግንአስታውሱ ጊዜ የማይከፍተው ቁልፍ መንገድ የለም! የችግሮቻችሁን ምንጮቻቹን በስኬቶቻቹ አሽሿቸው። ሀይላቹን ለመልካም መሻታቹ አውሉት፤ እንዲሁም ስሜቶቻችሁን አጠንክሯቸው ሀይል ይሆኗችኋል። ጥልቅ ፍላጎት የሌለው ሰው ስኬት አልባ ህይወትን ይመራል።

ባንተ ውስጥ ያንተን እድገት የሚቃወም ጭራቅ አለ፡፡ከድህነት እንድታመልጥ አይፈልግም፡፡ከመጥፎ ጓደኞችህ ስትሸሽ ያመዋል፡፡ከሱስ ስትርቅ ይጨንቀዋል፡፡ፍላጎቱ ለጊዛዊ ደስታ ጊዜና ሐይልህን በከንቱ እንድታባክን ነው፡፡
+
በተለይ አዲስ ነገር ስትሞክር ይንጫጫል፡፡
"ይህን ማድረግ አደጋ አለው!! ጎመን በጤና! ዋ! ትከስራለህ !ይሳቅብሃል!!" በማለት አዛኝ መስሎ እንደ ሐውልት ያስቆምሃል፡፡በጊዜ ሂደትም ወደኃላ ጎትቶ ይጥልሃል፡፡በገዛ ራስህ ህይወት አቅም ታጣለህ፡፡እሱ ንጉስ አንተ ባርያ ትሆናለህ::
+
ባርነት አልሰለቸህም? የራስህ ህይወት ንጉስ መሆን አላመማረህም? ከጭራቁ እስር ቤት ነጻ መውጣትስ? በፈለከው ሰዓት የፈለከውን ነገር ማድረግስ? የራስህን ህይወት መኪና መሪ መጨበጥስ? ህልምህን አሳክተህ ከስኬት ተራራ ጫፍ መሆንስ? አያጓጓህም? መልስህ "አዎ!" ከሆነ በመጀመርያ በውስጥህ ያንቀላፋውን ጀግና ቀስቅሰው፡፡
+
ባንተ ውስጥ ያንቀላፋ ምንም ነገር ማድረግ የሚችል ጀግና ሰው አለ፡፡ይህ ጀግና ፈጣሪን የሚመስል ገራሚ ሐይል ነው፡፡ይህንን ሐይል ማድመጥ ጀምር፡፡የጭራቁን አቅምና ሐይል ከውስጥህ ነቅሎ ይጥለዋል፡፡
+
ጭራቁ ማንነትህ ፈሪ ነው፡፡ጀግናው ማንነት # አማኝ ነው፡፡ጭራቁ ማንነትህ ሰነፍ ነው፡፡ጀግናው ማንነትህ # ለፊ ነው፡፡ጭራቁ ማንነትህ "ሰው ምን ይለኛል?" ይላል፡፡ስህተት ይፈራል፡፡ፍጹም መስሎ ለመታየት ይሞክራል፡፡ጀግናው ማንንትት ግን "እኔ ራሴን ምን እላለው? ፈጣሪስ ምን ይለኛል?" ይላል፡፡ፍጹም መስሎ የመታየት ምኞት የለውም፡፡እሱ የህይወት ዘመን ተማሪ ነው፡፡ ጭራቁ ማንነትህ ጊዛዊ ደስታን ብቻ ይፈልጋል፡፡ጀግናው ማንነትህ ግን ረጅሙን የውስጥ ሰላም፣ ፍቅር፣ ወሳጣዊ ደስታና ስኬት ይሻል፡
የላቀ አስተሳሰብና ክህሎት በማስቀደም ስኬትን መጎናጸፍ ።
ምንጭ ስነ-ልቡና