ፍልስፍና እና የፍልስፍና አባባሎች
4.59K subscribers
21 photos
2 links
የፍልስፍና እይታዎች
Download Telegram
ታላቁ ታላቅነት ከፍ ብሎ ማሰብ ነው!

ንስር የአእዋፋት ሁሉ ንጉስ ነው ቢባል አያንስበትም ህይወቱን ሙሉ እያደነ ነው ሚኖረው ያለፍርሃት ነገር ግን በስተመጨረሻ በእርጅናው ዘመን ህይውቱን የሚነጠቀው በትንሿ አእዋፍ ነው ክንፉ ውስጥ ትገባና እየበላች በቁሙ ታመነምነዋለች በስተመጨረሻም ለሷም ቢሆን ግን አንድ መላ አያጣም ከፍ ብሎ ከዳመና በላይ በመብረር ወፏ ልትቋቋመው የማትችለው የአየር ንብረት ውስጥ በመግባት ያሸንፋታል እንዲህ ነው ሰዎች ታላቅ ነኝ የሚል ጀግና በትንሽ ይሸነፉል።
ለዚህ ደግሞ ታላቁ ታላቅነት ከችግርና ችጋር በላይ ከፍ ብሎ ማሰብ ነው።
ጋዜጠኛው፦ፍልስፍና ያሳብዳል ??
.
ስብሐት፦ፍልስፍና አያሳብድም።አንድ ሰው ፍልስፍና አንብቦ ካበደ መጀመሪያውኑ ለማበድ የሚያበቃ እርሾ በውስጡ ነበር ማለት ነው።
.
ጋዜጠኛው ፦ፍልስፍና ለምን በጥርጣሬ ይታያል??
.
ስብሐት፦ ብዙ ሰዎች ፍልስፍናን በሩቁ ይላሉ ይፈራሉ።መጀመሪያዉኑ የነበራቸው እምነት ጠንካራ ስላልነበር ትንሽ ፍልስፍና እንዳነበቡ ከስር መሰረታቸው ይናጋሉ!ልባቸው በጥርጣሬ ይሞላል።ልብ አድርግ ያናጋቸው ፍልስፍናው አይደለም!ቀድሞ የነበራቸው ደካማ እምነት ነው !
.
ከ ቃለመጠይቅ የተቀነጨበ
“ ካህሊል ጂብራን አንድ ውብ ታሪክ ፅፏል፡፡ ይህ ሰው ብቻውን ብዙ ውብ ታሪኮችን ስለፃፈ በመላው አለም ታሪክ ውስጥ የሚፎካከረው ያለ አይመስልም፡፡
ይህ የምነግራችሁ ታሪክ በጣም አጭር ነው፡፡ የካህሊል ጂብራን ውበት ያለውም እዚህ ላይ ነው፡፡ ወደ ፊልምነት የሚቀየሩ ታላላቅ ታሪኮችን አይፅፍም፤የሚፅፋቸው ታሪኮች በጣም ጥቂት መስመሮችን የሚፈጁ ብቻ ናቸው፡፡ይሁንና የሰው ልጅን ውስጡን ሰርስረው ይገባሉ፡፡”
እንግዲህ ይህን የተናገረው በሚያነሳቸው ሀሳቦቹ ከብዙሀኑ የማይገጥመው እና ብዙ ታላላቅ ስራዎችን ያበረከቱ ሰዎችን በሚነቅፈው ኦሾ ነው፡፡ ካህሊል ጂብራን The Wanderer የሚለው የአጫጭር ታሪኮች ስብስብ ውስጥ ያለውን Garments የሚለውን ስራውን ነው የሚጠቅሰው፡፡
#moral #lesson
አንዴ አንድ ሰው ሰዎች በተሰበሰቡት መድረክ ላይ ይወጣና አንድ ቀልድ ይነግራቸዋል፡፡ሁሉም ይስቃሉ፡፡ሳቁ እንዳባራ እንደገና ለሁለተኛ ግዜ ያንኑ ቀልድ ይደግምላቸዋል፡፡አሁን የተወሰኑት ብቻ ይስቃሉ፡፡መሳቅ እንዳቆሙ ደግሞ ለሶስተኛ ግዜ ያንኑ ቀልድ ደገመው፡፡አሁን ማንም አልሳቀም፡፡ከዛ ይህን ጥያቴ ጠየቀ.........
<<<ለተመሳሳይ ቀልድ ለብዙ ግዜ አትስቁም ታዲያ ለተመሳሳይ ችግር ሁሌ ለምን ታለቅሳላችሁ???>>>
<< !!!መልስ የለም!!!>>
ዘመን እኮ ንፋስ ወይንም በፊኛ የተሞላ አየር አይደለም፡፡ እያንዳንዱን ዘመን የምንፈጥረው እኛው ነን፡፡ ጀግና ከሆንን የታታሪነት ዘመን እንፈጥራለን፡፡ ነቀዞች ከሆንን የንቅዘት ዘመን እንፈጥራለን፡፡ የውሻ ዘመን ጩኸትና ጭራ መቁላት ይበዛበታል፡፡ የጅብ ዘመን ሆዳም ይበዛበታል፡፡ የአህያ ዘመን ሸክም ይበዛበታል፡፡ የድመት ዘመን ቡጭሪያ ይበዛበታል፡፡ የጥንቸል ዘመን ፍርጠጣ ይበዛበታል፡፡ የጦጣ ዘመን ብልጠት ይበዛበታል፡፡ ዘመኑ ምን አደረገን?! እያንዳንዱን ዘመን የምንፈጥረው እኛው ራሳችን ነን፡፡ ውስጣችንን መፈተሽ ሲያቅተን፣ ራሳችንን መግዛት ሲሳነን፣ ፀባያችንን ማረቅ ሲያስቸግረን በዘመን እናላክካለን፡፡ ዘመንን እናማርራለን፡፡››

➦ሲሳይንጉሱ
➦ረቂቅ አሻራ
" የገንዘብ ትልቁ ኀይሉ የኪስን ድህነት ማጥፋቱ ሳይሆን የአእምሮን ራቁትነት ማጋለጡ ላይ ነው ። "
ገንዘብ ኖሮክ አሰተዳደሩን ወይም አጠቃቀሙን ካላወቅክ የገንዘብ ሀያልነት አንተ ላይ ሲሰራ ይታያል እንድትገዛበት (እንድትገበያይበት) የተፈጠረው ነገር አንተን ሲገዛ ይገኛል ያኔ ገንዘብክ የአምሮክን እርቃንነት ልትሸፍነው በማትችለው መልኩ ይገለጣል ይህ ደግሞ አጠቃቀምን አለማወቅ ነው ክፋቱ ያንተ ታውሮ የሌሎችንም ማሳወሩ ።
ገንዘብ ኖሮክ ደግሞ አጠቃቀሙን ስታውቀው ግን ገንዘብ መጠቀሚያ እንጂ የአምሮ ወይም የአሰተሳሰብ ልዕልናክን አሊያም ዝቅጠትን የሚያጋልጥ ሳይሆን አንተን የሚያገለግል ስለሚሆን አንተን ጠቅሞ ሌላውን ይጠቅማል።
ስለዚህ ገንዘብ በራሡ ነፃ (neutral) ነገር ነው። የማንም የአእምሮ ራቆትነት ብሎም የአስተሳሰብ ልዕልናን አያሣይም ሠውየው ስለ ገንዘብ እና አጠቃቀሙ ያለው እስተሳሰብ እንጂ ገንዘብ ከመጠቀሚያነት ያለፈ ሀይል ያለው ነገር ሆኖ አይደለም።
ዶ/ር ምህረት ደበበ
" የተቆለፈበት ቁልፍ "
የሮበርት ሙጋቤ ንግግሮች ፥-
"ሴት ሆይ፥- በፌስቡክ 'የኔ መልአክ' ብሎ የሚያቆላምጥሽኝ ወንድ ብሎክ አርጊው፡፡አይደለም በፌስቡክ በመጽሀፍ ቅዱስ እንኳን የሴት መልአክ የለም፡፡
ወንድ ሆይ ፥- ሰይጣን የለም ብለህ አትከራከር፡፡በዚህ ቅጽበት ላንተ 'ደህና እደር' ብላ ሜሴጅ ጽፋልህ ለአንዱ ደግሞ 'በር ላይ ነኝ' እያለች ነው፡፡"
ዘረኝነት በጨለማ ውስጥ እንደመፋለም ነው።የጨለማ ፍልሚያ ማለት ደግሞ የራስን ወንድም ጭምር ቢሆን እንደመፋለም ነው። ከማን ጋ እየተዋጋን እንደሆነ አንረዳም። ሀገር ሲባል ቋንቋ:ልማድ ወይም እምነት የሚመስለን ሰዎች ፍጹም ስህተት ውስጥ ነን። ዘር ወይም ጎሳ ጭምር ሀገር ማለት አይደሉም ። ባህሎች ናቸው።ሲወርድ ሲዋረድ ከትውልድ ትውልድ በትውፊት የሚሻገሩ እምነቶች ናቸው።
ሀገር ግን ሀሳብ ነው።በውስጡ አላማ አለው።ፍልስፍና አለው።ራዕይ አለው።ዜግነት የሚሰኝ ከጎጥ ውጪ የሆነ ግለሠብነት አለ። የሀገር ምንነት ፍልስፍናዊ ነው። ፍጹም ልማዳዊ መሆን የለበትም።መሆንም አይችልም።ከልማድ የሚነሳ መንግስት የለም።የጎሳ ቲኦክራሲ ልንፈጥር እንችላለን ። ዘመናዊ አለም የሚገዳደር ጠንካራ የመንግስት ይዘት ግን አናገኝም።
ኢትዮጵያን ማሠብ ያለብን ልንፈጥር ከምንችለው አብዮትና አንድ መሠረት ያለው የዜግነት ቅርጽ አንጻር እንጂ በቀበሌ ቋንቋና ትውፊት ላይ የምንተራስ ከሆነ ሀገር የሚለው ቃል አልገባንም ማለት ነው።የተለያዩ ጎሳዎች በሚናገሩት ቋንቋ:እምነት ወይም ልማድ ሀገር የሚለውን ጥልቅ ሀሳብ ሊዳኙ ሲሞክሩ ማየት ተለምዷል።
ነውር ነው።ሀገርና ልማድ የማይለይ ትውልድ ተፈጥሯል ማለት ነው።ልማድ ምክንያት የሌለው የማይለወጥ ግን እንዲሁ በህዝቦች ሽግግር የሚያልፍ ስርዐት ነው።ሀገር ግን ከዚህ ይለያል።በየዘመኑ እያደገ በሚመጣ ፍልስፍና : ርዕዮት አለም ወይም ዕሳቤ የሚጎለብት ትርጉምና ምንነት የሚኖር የብዙ ህዝቦች አንዴነት መጠሪያ ነው።
➦መሀመድ አሊ ቡርሀን ➦"የዘር ካርድ"
የሰው ልጅ በህይወት ዘመኑ ሁሉ መጠኑና ስፋቱ ቢለያይም ራሱ በሰራው አሊያም ሌሎች ባጠሩለት እስር ቤት ውስጥ ይኖራል። እንደ ራሱ አሳብና አመለካከት ግን ትልቅ እስር ቤት የሚሆንበት ነገር የለም። ለካስ እስር ቤት ቦታ ሳይሆን አስተሳሰብ ነው። በዚህች ምድር እጅግ ብዙ ሰው በአእምሮው እስር ቤት ውስጥ በአሉታዊ አስተሳሰብ ታስሮ በከንቱና እንቶ ፈንቶ ፍርሀት ተይዞ ማንም እንዳይረዳው ኾኖ የእስር ቤት ቁልፉን ራሱ ደብቆ ይኖራል።
ከ"ሜሎሪና" መጽሐፍ
©~የተራራውን ካርታ በማንበብ ብቻ ተራራውን ማግኘት አትችሉም ! ተራራው አንድ ሆኖ ሳለ ካርታው ብዙ ሊሆን ይችላል ። ቁምነገሩ ተራራውን አግኝታችሁ ከጫፉ ላይ መውጣት እንጂ የተራራውን ካርታ መሸምደድ አይደለም ! የእግዚሃብሔር (የፈጣሪ) ሰው መሆን ማለት ወደ ተራራው ሄዶ ተራራውን አግኝቶ እሱን መረዳት ነው ። የምትጓዙት ወደ ካርታው ከሆነ ተራራውን አታገኙም !ምክንያቱም ካርታው (ማነዋሉ) ተራራው አይደለምና

#ኦሾ
ዓለም በ"አሜን" ባዮች ስለተከበበች በየጊዜው መንታ መንገዶች ላይ ቆማ ወደፊት ለመራመድ ታመነታለች። በድንቁርና ውስጥ መጠፋፋትን ማለም ዕጣ ፈንታዋ ይሆናል። አዲስ አሻራና ታሪክን የሚያሳርፍ አይገኝም። አይደለም ሰዎች ከተማዎች በዚያ ዓይነት ድብታ ውስጥ ያንቀላፋሉ።

ትውልድ እየመጣ ትውልድ ይሄዳል። ነገር ግን የተለየ አብዮት አይከሰትም። ሁሉም "አሜን" እያለ ያደገድጋል። የቀረበለትን ያነግሣል። "ጠላትህ ነው" ተብሎ የተነገረውን ይጠላል። "ወዳጅህ ነው" ተብሎ የተነገረውን ይወድዳል። ምክንያትን አይጠይቅም። ሲደሰትም፣ ሲቆጣም፣ ሲለግምም፣ ሲያብርም ... በስሜት ላይ እንጂ በተረጋገጠ ገዢ እውነታ ላይ ተመሥርቶ አይደለም።

ከዚህ ውስጥ 'ለምን?' ብሎ የሚጠይቅ ሰው፤ ይዘን የመጣናቸውን ፍሬዎች በነሲብ ከመብላታችን በፊት በጥንቃቄ እንድንመዝናቸው ያነቃናል፣ ምክንያቱም ሁሉም የሐሳብ ፍሬ አይበላም። የተበላሹ ፍሬዎች ሊያጋጥሙን ይችላሉ። በመዳፋችን የያዝናቸውን መልካም በረከቶችና ክፉ መርገሞችን እናነጻጽራለን። እጃችን ላይ ያለው ምንድን ነው? ምንስ እናድርግበት?

ለምሳሌ ዓለም በእጃችን ነው። እናፍርሰው ወይስ እንስራው? አገር በእጃችን ነው እናልማው ወይስ እናጥፋው? ቤተሰብ፣ ልጆች በእጃችን ናቸው በመልካምነት ወይስ በክፋት እንቅረፃቸው? ትናንት በእጃችን ነበር በታሪክነቱ ተቀብለነው ወይስ ክደነው እንለፍ? ዛሬ በእጃችን ነው በአግባቡ እንጠቀምበት ወይስ በከንቱ እናባክነው? ነገ በእጃችን ነው መጪውን እንለውጥበት ወይስ ትናንትን እንድገምበት?

ታሪክ በእጃችን ነው እናድምቀው ወይስ እንሰርዘው? አንድነት በእጃችን ነው ለሥራ እንነሳበት ወይስ ለጥፋት እናብርበት? ፍቅር በእጃችን ነው እንዋደድበት ወይስ እንዋቀስበት? ሰላም በእጃችን ነው በደኅና እንደር ወይስ እንታወክበት?
በእጃችን ላይ ባሉት በረከቶች መልካምና ክፉ ነገሮችን ማጨድ እንችላለን።
ያለፉ ክፉ ነገሮችን ማስታወስና ቀጣዩ የህይወት ጉዞህን መፍራት አቁም!

ያለፉ ክፉ ትውስታዎችን በአንዳች ነገር (ለምሳሌ፦ በንስሃ፣ በይቅርታ፣ በካሳ፣ በእርቅ) ዝጋቸው። ካልቻልክ ደግሞ በሚጎዱህ ልክ አታስታውሳቸው። መርሳት የሚባለው ፀጋ የተሰጠን አንድም ክፉ ነገሮችን መርሳት እንድንችል ነው። ቆሻሻውን አጽዳ።

ሰዎች በአንድ ወቅት ክፉ አድርገውብህ ይሆናል፤ እነዚህ ሰዎች በአንተ ላይ ቆሻሻውን አከማቹት ማለት ነው። አንተም ለዘመናት የቆሻሻቸው ማራገፊያ ሆነህ ይዘኸው እየተጓዝክ ነው። አራግፈው።

ቆሻሻ ምንም ቢራገፍ ከመኪና ቆሻሻው ላይ የሚተርፍ ቅሬት መኖሩ አያጠራጥርም። አንተም ቆሻሻውን ስታራግፍ አንተ ላይ የሚቀሩ ትርፍራፊዎች አይጠፉም። ተሸክመኻቸው አትዙር፤ አራግፋቸው።

ያለፉ ቆሻሻዎችን አለማጽዳት ነገን እንድንፈራው ያደርገናል። ያለፉ ቆሻሻዎችን በሚገባ ካጸዳናቸው ግን ነፃነት፣ ንጽህናና ብሩህ ተስፋን እናገኛለን።

ብዙ ሰዎች የትናንት እስረኞች ናቸው። እርሾው መልካም ካልሆነ ሊጡ ብሎም እንጀራው እንደሚበላሽ ሁሉ ትናንትህ ካልጸዳ ነገህ ይበላሻል።
#ለፈገግታ
******
እድለኛ ከሆንክ ታገባለህ ...ማግባት እድል ይጠይቃል ….በጣም እድለኛ ከሆንክ ጥሩ ሴት ታገባለህ … ጥሩ ሴት ማግባት እንዴት ሰላም አለው መሰለህ …እጅግ በጣም እድለኛ ከሆንክ ያፈቀርካትን ሴት ታገባለህ … ፍቅር የትኛውንም ጉድለት ይሸፍናል የትም ብትሄድ ካፈቀርካት ሴት አታመልጥም ….እጅግ እጅግ በጣም እድለኛ ከሆንክ የምታውቃትን ሴት ታገባለህ … አውቀህ ገብተህበታል ምንም ቢፈጠር አይመለከተንም !! እዛው ተወጣው!
:
#/አሌክስ አብርሃም /
<<የሌሎችን ድጋፍ የሚሹት የሌሎችን አመለካከት የያዙ ብቻ ናቸው>>
👇
(ኦሾ)

በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ አንድ ሰው ከሌላ ሰው ጋር በፍፁም ተመሳሳይ የሆነ ተግባር እንዲፈፅም ይጠበቅበታል። ሰዎች ትንሽ ለየት ያለ ነገር ሲያደርጉ ከመቅፅበት ለማህበረሰቡ እንግዳ እንደሆኑ ተደርገው ይታያሉ። ሰዎች ደግሞ እንግዳ የሆነ ተግባር የሚፈፅሙ ሌሎች ሰዎችን በጣም ይፈራሉ።

ለዚህም ነው ሁለት ሰዎች አውቶብስ ወይም ባቡር ውስጥ አልያም ፌርማታ ላይ ሲገናኙ ዝም ብለው መቀመጥ የማይችሉት። ምክንያቱም ሁለቱም እንግዶች ናቸው። በመሆኑም ብዙም ሳይቆዩ ይተዋወቃሉ። ስምህን ማንልበል?
ወዴት ነው ምትሄደው?
ስራህስ ምንድነው? ይባባላሉ። በዙህ መልኩ ጥቂት መረጃዎችን ከተለዋወጡ በኋላ ይረጋጋሉ። አንዳቸው እንደሌላኛው ሁሉ የሰው ልጅ ናቸው ለካ!

ሰዎች ያለማቋረጥ በማይመጥኑት ህዝብ መሀል መሆንን ይፈልጋሉ።ለየት ያለ ተግባር ስትፈፅሙ ወዲያውኑ መላው ህዝብ ይጠራጠራችሁና ነገሮች ይበላሻሉ። ከዚያ ግን ያወቋችሁ ለውጡን ለማየት ይችላሉ። እራሳችሁን በፍፁም የማትቀበሉ ሰዎች ሆናችሁ መቆየታችሁን ያውቃሉ። እናም አሁን በድንገት እራሳችሁን ስትቀበሉት ያያሉ።

በማህበረሰባችን ውስጥ ማንም ቢሆን የገዛ ራሱን አይቀበልም። ሁሉም የገዛ ራሱን ይኮንናል።ራስን መኮነን የህዝብ የአኗኗር ዘዬ ነው። ራሳችሁን መቀበል ስትጀምሩ ደግሞ ከማህበረሰቡ ውስጥ ወጥታችኋል። ማህበረሰቡ ደግሞ ከማዕቀፉ የወጣን ማንንም ሰው ታግሶ የመጠበቅ ልማድ የለውም። ምክንያቱም ማህበረሰቡ የሚኖረው ቁጥሮችን ቁጥሮችን መሰረት አድርጎ ነው። ይሄ ደግሞ የቁጥሮች ፖለቲካዊ አስተሳሰብ ነው። ሰዎች ብዙ ቁጥሮች ሲኖሩ ጥሩ ስሜት ይሰማቸዋል። በርካታ ቁጥሮች ሰዎችን ትክክል እንደሆኑ አድርገው እንዲያስቡ ያደርጓቸዋል። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ደጋፊዎች ስላሏቸው ሊሳሳቱ አይችሉም። ብቻቸውን ሲተው ግን ትልቅ ጥርጣሬ መቀስቀስ ይጀምራል። ከእነሱ ጋር ማንም ሰው የለምና ትክክል ለመሆናቸው መተማመኛው ምንድነው?

ለዚህም ነው በዚህ ዓለም አንድ ግለሰብ መሆን ታላቅ ድፍረት እንደሆን የምናገረዉ
አንድ ግለሰብ ለመሆን ከሁሉ የላቀ ድፍረት የተሞላበት መሰረት ያስፈልጋል።
<<መላው አለም እኔን መቃወሙ አያስጨንቀኝም። ዋናው ነገር ተሞክሮዬ ተቀባይነትን ማግኘቱ ነው። ምን ያህል ሰዎች ከኔ ጋር እንደሆኑ ለማወቅ ቁጥራቸውን አልመለከትም። ትኩረት የማደርገው በተሞክሮዬ ተቀባይነት _ የሌላ ሰው ቃላትን እንደበቀቀን እየደገምኩ መሆን አለመሆኔን ወይም የምናገራቸው ነገሮች ከገዛ ራሴ የመነጩ መሆን አለመሆናቸው ላይ ነው። ንግግሬ በገዜ ራሴ ተሞክሮ ውስጥ ከሆነ፤ የደሜ፣ የአጥንቴና የመቅኔዬ አካል ከሆነ፣ መላው አለም በአንድ ወገን ሊሆን ቢችል እንኳን፣እኔ ትክክል ነኝ። እነሱ ግን ተሳስተዋል። ምንም የሚያስጨንቅ ነገር የለም። እኔ ትክክል መሆኔ እችዲሰማኝ የእነሱ የድጋፍ ድምፅ አያስፈልገኝም። የሌሎችን ድጋፍ የሚሹት የሌሎችን አመለካከት የያዙት ብቻ ናቸው>> ብሎ ማሰብ የግድ ይሆናል።
🎎
"ዓለም በሙሉ በብርሃን ልትጥለቀለቅ ትችላለች፣ ውስጥህ ግን አሁንም በጨለማ እየኖረ ነው። ከውልደትህ በኃላ የተጨመረልህ ነገር ሁሉ እውነተኛ ማንነትህ ያለመሆኑን ቀስ በቀስ የሚያሳይህ ጭላንጭል ብርሃን በውስጥህ ሳይኖር በብርሃን የተሞላ ዓለም ምን ይጠቅምሀል?"
' ' '
OSHO ኦሾ

#ነፃነት/
ራስን የመሆን ድፍረት
#በሁሉም ነገር አዲስ መንገድ ፈልጉ ።በየዕለቱ አዲስ ነገር መፈለጋችሁን ስትቀጥሉ ህይወታችሁ አንጠልጣይ፣አስደናቂ ይሆናል።አይሰለቻችሁም። የሚሰላች ሰው እምነት የሌለው ነው።አንድ ነገር ለማውቅ ሁልጊዜ ጉጉ ሁኑ።ሁልጊዜ ከማወቅ ከመመርመር ከማግኘት ፣ከመፈለግ ጫፍ ስትደርሱ ንቃታችሁ ይበሉጡን ይጨምራል ።
ኦሾ/Osho(አካለ አዕምሮ)
#ለዕለተ ቅዳሜያችን
ስንቃርም ያገኘነውን ከኦሾ እይታዎች ጥቂት ወደ እናንተ እንበትን ዘንድ የተጋባ ሆኖ አገኘነው!!
*
#ገንዘብተኝነትን አውግዙ ፤ ገንዘብን ግን አትጥሉ በሰለጠነው አለም ገንዘብና ሀብት የግድ የሚያስፈልግ የኑሮ #መስተጋብሮች ናቸውና። ያለ ሀብትና ገንዘብ ሳይንስና ቴክኖሎጂ አይሰምርም ፣ የሰው ልጅ የደረሰባቸው የእድገት ደረጃዎች ያለ ነዋይ አይሳካም ነበር ።
#በዘመነች አለም ህይወት ያለ ገንዘብ ዲዳ ትሆናለች ! ገንዘብን ተጠቀሙበት ፤ ነገር ግን ገንዘብ ላይ አትጣበቁ ። ገንዘብ ላይ ሙጭጭ ባላችሁ ቁጥር በእናንተ "ሙጭጭ" ማለት የተነሳ አለም የበለጠ #ትደኸያለች ። ገንዘብተኛ ማለት ከፈረሱ የቀደመ ጋሪ ማለት ሲሆን ትርፉ ከሰብአዊነት አፈንግጠው በሰዎች ዘንድ መጠላት ነው ።
ኦሾ/Osho
ቢጨልፉት ከማያልቀው ከኦሾ የፍልስፍና እይታዎች ቆንጥረን ወደ እናንተ እንካችሁ አለን !

በደስታችሁ በሀዘናችሁ በእንቅስቃሴያችሁ እውነተኛ ከሆናችሁ ዉሎ አድሮ ሀሳባችሁን የሚረዳላችሁ በእናንተ መንገድ የሚጓዙ ሰዎች ማግኘታችሁ የማይቀር ነው የሚለን ህንዳዊው የፍልስፍና ሰው ኦሾ እኔ ራሴ መንገዱን ስጀምረው ብቻዬን ነበርኩ ዛሬ ግን መንገዴን የሚከተሉ ሰዎች በዝተዋል ከዛም በዘለለ ጉዞዬ አለማቀፋዊ ሆኗል ይለናል። በርግጥ በብቸኝነት መንገዴ እኔ ማንንም ወደ መንገዱ አልጋበዝኩም ነገር ግን ልቤ የፈቀደውን ከማድረግ ወደ ኃላ አላልኩም፡፡
የእኔ ሀላፊነት የልቤን እንጅ በዓለም የሚኖርን የማንንም ትዕዛዝ ማድመጥ አይደለም፡፡
በርግጥም አበክሬ የምነግራችሁ ነገር " ራሳችሁን አትቃወሙ ራስን መቃወም ራስን እንደ ማጥፋት ነውና፡፡ራሣችሁንና ማንነታችሁን ስታከብሩና ስትቀበሉ ሰዎች በፍቅር ይቀበሏችሗል፡፡
የእናንተ ሀላፊነት ሊሆን የሚገባው ራሳችሁን ማድመጥና በራሳችሁ መተማመን ነው፡፡
የዚያኔ አለም ሁለት እጆቻን ዘርግታ በፍቅር ትቀበላችሃለች፡፡
#ኦሾ/Osho
#አንዲት ሴት ቆንጆ ስለሆነች ብቻ የምትወዷት ከሆነ ፍቅራችሁ እውነተኛ ፍቅር አይደለም። ነገ ያቺ ያፈቀራችሃት ሴት ታረጅና ፣ ድንገት ትታመምና አስቀያሚ ልትሆን ትችላለች። ምናልባትም አፍንጫዋ ላይ ቀዶ ጥገና ይደረግላት ይሆናል።
ያን ጊዜ ፍቅራችሁን ምን ይውጠዋል? ፍቅር ውስጥ ያስገባችሁ ውቧ አፍንጫዋ ነበር። አሁን ያ አፍንጫዋ የለምና ፍቅራችሁም ይጠፋል። ሴትዬዋ ሸክም ትሆንባችኋለች።

በምክንያት ባልተሞላ ልብ የሚመጣው ፍቅር ግን በነገሮች ላይ ጥገኛ አይደለም። ይህን ፍቅር ከሰውዬው ውበት ወይም እውቀት ወይም ተሰጥኦ ጋር የሚያገናኘው ምንም ነገር አይኖረውም።
በፍቅር ትምሉና ያን ፍቅር ማካፈል ትፈልጋላችሁ። እናም ለመቀበል ዝግጁ ለሆነው ሁሉ አመስግናችሁ ትሰጡታላችሁ። ስጦታ ነው የምትሰጡት ስለ ሞላችሁ ስለተረፋችሁ ነው።
#ኦሾ /Osho
30 seconds read: A story by Khalil Gibran
(በግሩም ተበጀ)
——
በአእምሮ ሕሙማን ሆስፒታሉ የአትክልት ሥፍራ ስዘዋወር የፍልስፍና መፅሐፍ የሚያነብ አንድ ወጣት አገኘሁ…
ባህሪውና ጤነኛ ገፅታው ከሌሎቹ ሕሙማን ለየት ማለቱን ያሳብቃል፡፡
አጠገቡ ሄጄ ተቀመጥኩና፣ “እዚህ ምን ትሰራለህ ?” ስል ጠየቅኩት፡፡
በጣም ተገርሞ ትክ ብሎ ካየኝ በኋላ ከዶክተሮቹ አንዱ አለመሆኔን ሲረዳ እንዲህ ሲል መለሰልኝ፣
“ይኸውልህ ነገሩ እንዲህ ነው … የታወቀ ጠበቃ የሆነው አባቴ እንደ እሱ እንድሆን ይፈልጋል፡፡ ግዙፍ የገበያ አዳራሽ ያለው ሐብታሙ አጎቴ በፋንታው የእሱን ፈለግ እንድከተል ይሻል፡፡ እናቴ ደግሞ እንደምትወደው አባቷን እንድሆን ትፈልጋለች፡፡ እህቴ በበኩሏ የስኬት ሚዛን ማለት ባሌ ነው ከማለት አትቦዝንም፡፡ ወንድሜ ደግሞ እንደ እርሱ ምርጥ አትሌት እንድሆን ይጥራል…
በትምህርት ቤትም ይኼው ነው፡፡ የሙዚቃ እና የእንግሊዝኛ መምህሮቼ በየፊናቸው እኔን ምሰል፣ እኔም ተከተል ይሉኛል፡፡ ሁሉም አንድ ሰው ሌላኛውን እንደሚያየው ሳይሆን ራሳቸውን መስታወት ውስጥ እያዩ እንዳሉ ያህል ነው የሚያዩኝ፡፡
ስለዚህም እዚህ የአእምሮ ሕሙማን ማዕከል ገባሁ፡፡ ቢያንስ ቢያንስ እዚህ ራሴን መሆን እችላለሁ”
ወንጀለኛው
(ካህሊል ጂብራን)
አንድ በርሀብ የተጎዳ፣ ፈርጣማ ሰውነት ያለው ወጣት በእግረኛ መንገድ ላይ ተቀምጦ እጆቹን በመዘርጋት ረሃብና ሃፍረት እየሸነቆጡት በሚያሳዝን ዜማ ይለምናል። ምሽት ላይ ከናፍሮቹ እና ጉሮሮው ደረቁበት። እጁ ግን እንደሆዱ ባዶ ነበር። ከተቀመጠበት ተነስቶ ከከተማ ወጣና በአንድ የዛፍ ጥላ ስር ተቀምጦ በምሬት ያነባ ጀመር። ከዚያም ረሃብ ውስጡን እየሞረሞረው ግራ የተጋቡ አይኖቹን ወደ ሰማይ ላካቸውና እንዲህ አለ፤ <<ጌታዬ ሆይ፣ ወደ አንድ ሃብታም ሄጄ ስራ እንዲሰጠኝ ጠየቅሁት። እሱ ግን ቡትቶዬን አይቶ ፊቱን አዞረብኝ። የአንድ ትምህርት ቤት በር አንኳኳሁ፣ ግን ባዶ እጄን ነበርና ችላ ተባልኩ። ቁራሽ ዳቦ የሚያስገኝልን የትኛውንም አይነት ስረ ሞከርኩ፣ ይሄ ሁሉ ግን ከንቱ ነበር። ተስፋ በመቁረጥ እንዲመፀውቱኝ ለመንኩ፣ መፅዋቾቹ ግን ተመለከቱኝና "ጠንካራና ሰነፍ ነው፤ መለመን አልነበረበትም" አሉኝ... "ጌታዬ ሆይ፣ እናቴ የወለደችኝ በአንተ ፍቃድ ነው። አሁን መጨረሻው ከመድረሱ በፊት ምድር ወደ አንተ እንድመለስ ፈቅዳልኛለች።"


ይሄን ጊዜ ፊቱ ተለዋወጠ። ብድግ አለና አይኖቹን በቁርጠኝነት አጉረጠረጣቸው። ከአንዱ የዛፍ ቅርንጫፍ ወፍራም አርጩሜ ቆርጦ ወደ ከተማዋ በመቀሰር ጮኾ ተናገረ። <<ያለኝን ድምፅ ሁሉ አጠራቅሜ ዳቦ ስጡኝ ብያችሁ ነበር። እናንተ ግን ችላ አላችሁኝ። አሁን በጉልበቴ አገኘዋለሁ! በፍቅር እና በርህራሄ ስም ለምኜያችኋለሁ፤ ስብዕና ግን ዋጋ አልነበረውም። አሁን በርኩስ መንፈስ ስም አገኘዋለሁ!"
ዓመታት ሲያልፉ ወጣቱ ዘራፊ፣ ነፍሰ-ገዳይ እና የነፍስ አጥፊ ሆነ፣ የተቃወሙትን ሁሉ ያጠፋል፤ ጉልበቱን በመጠቀም ብዙ ሃብት ሰበሰበ። ከግብረ-አበሮቹ አድናቆትን አገኘ፣ በሌሎች ሌቦች ተከበረ፣ በህዝቡ ዘንድ ደግሞ ተፈሪ ሆነ።

ሃብቱና በጉልበቱ ያገኘው ተፈሪነቱ፣ አሚሩ የከተማዋ ባለስልጣን አድርጎ እንዲሾመው አበቃው- ብልህነት የጎደላቸው አገረ-ገዢዎች አሳዛኝ ሥራ። ከዚያ በኋላ ስርቆት ህጋዊ ስራ ሆነ፤ ጭቆና በስልጣን ይደገፍ ጀመር፤ ደካሞችን ማጥፋት የተለመደ ተግባር ሆነ እናም ዙፋኖች ይፈሩና ይከበሩ ጀመር።
#ስለዚህ ስግብግብነት ነካ ያደረገው ስብዕና አይናፋሮችን ወንጀለኛ፣ ሰላማዊ ሰዎችን ደግሞ ነፍሰ-ገዳይ ያደርጋል፤ ስግብግብነት የጎበኘው ስብዕና ያድግና መልሶ ስብዕናን አንድ ሺ እጥፍ ጊዜ ያጠፋዋል!

፨፨፨

ምንጭ ፦ እንባ እና ሳቅ(Tears and Laughter)
ደራሲ ፦ ካህሊል ጂብራን
ትርጉም ፦ ተስፋሁን ምትኩ